የኮደርስ ስልጠና የነገዋን የበለጸገች ዲጂታል ኢትዮጵያ ለመገንባት ጠንካራ መሠረት እየጣለ ነው፦የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ
*****
ሀገራዊው "5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ ወጣቶችን ከቀላል የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ቴክኖሎጂ ፈጠራ እና አምራችነት በማሸጋገር የነገዋን የበለጸገች ዲጂታል ኢትዮጵያ ለመገንባት ጠንካራ መሠረት እየጣለ መሆኑን የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ጀማል አብራሂም እንደገለጹት በክልሉ እስካሁን በተከናወነው ሥራ 50 ሺ 581 ወጣቶችን ማሠልጠን ተችሏል።
ከሰልጣኞቹ መካከልም ከ37 ሺ በላይ የሚሆኑት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ማግኘት ችለዋል ብለዋል።
ስልጠናው ወጣቶች በቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን ክህሎት በማሳደግ የነገዋን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች በዲጂታል እውቀት የመምራት አቅም እንደሚፈጥርላቸው ኃላፊው ጠቁመዋል።
የዲጂታል ክህሎት ስልጠናውን በማስፋፋት ወጣቶች የቴክኖሎጂ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የስልጠናው ዋና ትኩረት መሆኑን አቶ ጀማል ገልፀዋል።
በመሆኑም ወጣቶች በኮዲንግ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ በሶፍትዌር ልማት እና በዲጂታል ፈጠራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ይህንን ታሪካዊ ዕድል በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
መሰል ዲጂታል ኢኒሼቲቮች ወጣቶች የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ራሳቸውን እና ሀገራቸውን በብቃት እንዲጠቅሙ ሰፊ ዕድሎችን የሚከፍቱ መሆናቸውም ተመላክቷል።
በሄኖክ ግርማ
14/01/19

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለሚገቡ ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ።
***
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ለሚቀላቀሉ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የማበረታቻ ድጋፍ አድርገዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለመግቢያ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ ውጤት የሚመጣው በጥረት መሆኑን ገልጸው፣ ከሠራንና ከተጋን ራስን መቀየር ይቻላል ብለዋል።
በዓለም ላይ ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች በፈተና ውስጥ ያለፉ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ኦርዲን፤ በፈተና ማለፍ እንደሚያጠነክራቸው እና ሁልጊዜ ማደግና መለወጥ የሚቻለው በምቾት ሳይሆን በፈተና ውስጥ በማለፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በቀጣይም ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ተቋም ሲገቡ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም፣ ትጋትና ጥረትን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሙሉ ትኩረታቸውን በትምህርታቸው ላይ ብቻ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የክልሉ መንግሥት ለትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተማሪዎች ያለምንም ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ጨምረው ገልጸዋል።
የክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብይ አበበ በበኩላቸው፣ የተደረገው ድጋፍ ተማሪዎች በትምህርታቸው ጠንክረው የተሻለ ውጤት በማምጣት ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲጠቅሙ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ አብይ አክለውም፣ ድጋፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚያጋጥሟቸውን ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች በማቃለል በትምህርታቸው ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚዎች የሆኑት ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ የተደረገላቸው ድጋፍ ለቀጣይ ስኬታቸው ከፍተኛ ተነሳሽነት የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
ከድጋፉ ባሻገርም ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሰጧቸው ምክርና ተሞክሮ በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በሄኖክ ግርማ እና ገዛኸኝ አራጌ
15/01/19

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የክልሉ መንግሥት ያደረገላቸው ድጋፍ ለቀጣይ ስኬታቸው ከፍተኛ ተነሳሽነት የሚፈጥር መሆኑን ወደ ከፍተኛ ተቋም የሚገቡ ተማሪዎች ገለጹ።
ተማሪዎቹ ድጋፉ የቤተሰብን ጫና ያቃለለና እፎይታን የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
የሐረሪ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብይ አበበ በበኩላቸው፣ ድጋፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚያጋጥሟቸውን ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች በማቃለል በትምህርታቸው ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ተማሪዎቹ ድጋፉ የቤተሰብን ጫና ያቃለለና እፎይታን የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
የሐረሪ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብይ አበበ በበኩላቸው፣ ድጋፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የሚያጋጥሟቸውን ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች በማቃለል በትምህርታቸው ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዘመናዊቷ ሐረር፦ የኮሪደር ልማት ያመጣቸው አዳዲስ መልኮች
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለሚገቡ ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ለተማሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት፦