Hanif Tube
243 subscribers
11 photos
10 videos
1 file
30 links
Download Telegram
Forwarded from đŸ•‹ISLAMIC ZONE🕋 ™ (Ã/Ĺ )
በጁምዓ ቀን ወደ መስጂድ ስትገባ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ሁለት ረከዓ መስገድ ይኖርብሃል!

ከጃቢር ቢን አብደላህ (ረ.ዐ ) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦

﴿جَاءَ رَجُلٌ وَالنَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَخْطُبُ النَّاسَ يَوْمَ الْجُمُعَةِ، فَقَالَ : " أَصَلَّيْتَ يَا فُلَانُ ؟ " قَالَ : لَا، قَالَ :  قُمْ فَارْكَعْ رَكْعَتَيْنِ﴾

“አንድ ሰው ነቢዩ (ﷺ) ለሰዎች ኹጥባ እያደረጉ ሳለ ወደ መስጂድ ገብቶ ተቀመጠ። እከሌ ሆይ ሰግደሃልን? አሉት። አልሰገድኩም አለ። ተነስ ሁለት ረከዓ ስገድ አሉት።”

ቡኻሪ ዘግበውታል: 930



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ኢብኑ አብባስ رضي الله عنهما እንዳስተላለፉት
የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል:- በልቦናው ወስጥ ከቁርዓን ምንም ነገር የሌለበት ሰው ልክ እንደ ባዶ ቤት ነው። ከቁርአን ጋር ያለንን አላቃ እንፈትሽ ባረከላሁፊኩም



@Hanif_tube
☞::::::::::::::አስታዉስ::::::::::::::::☜

☞ዛሬ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ/ጀናዛ ትባላለህ ፣
☞ዛሬ የቱንም ሀብት ቢኖርህ ነገ ግን 1 ሜትር ከፈን ብቻ ነው የሚኖርህ ፣
☞ዛሬ የተነደላቀቀ አልጋ ላይ በትተኛ ነገ አፈር ውሰጥ ትተኛለህ ፣
☞ዛሬ ምንም ቤተሰብህ ብትከበብ ነገ ቀብር ውስጥ ብቻህን ትቀራለህ፣
☞ዛሬ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህ ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነህ፣
☞ዛሬ ምንም በዘርህና በጎሳህ በትመካ
ነገ ብቸኛ ነህ ፣
☞ዛሬ ማንም ሁን ምን ነገ አንተ ሬሳ ነህ ሬሳ !!!
☞ዛሬ የምትናፈቅ ቢትሆን ነገ ሬሳ ሆነህ እንዳትሸት ሰዎች ቶሎ ያሸሹሀል ፣
ስለዚህ ዛሬ ላይ ለነገ የሚጠቅምህን ስራ ብትሰራ መልካም ነው ! !!
ወደ አላህ ተመለስ ! !!
እምቢ ብለህ ካመጽክ ግን መሬት እንኳ ሳትገባ ፈተናህ ይጀምራል
Hanif Tube pinned «☞::::::::::::::አስታዉስ::::::::::::::::☜ ☞ዛሬ ስምህ ማንም ቢሆን ነገ ግን ሬሳ/ጀናዛ ትባላለህ ፣ ☞ዛሬ የቱንም ሀብት ቢኖርህ ነገ ግን 1 ሜትር ከፈን ብቻ ነው የሚኖርህ ፣ ☞ዛሬ የተነደላቀቀ አልጋ ላይ በትተኛ ነገ አፈር ውሰጥ ትተኛለህ ፣ ☞ዛሬ ምንም ቤተሰብህ ብትከበብ ነገ ቀብር ውስጥ ብቻህን ትቀራለህ፣ ☞ዛሬ የቱንም ያህል ስልጣን ቢኖርህ ነገ ከሁሉም ጋር እኩል ነህ፣ ☞ዛሬ…»
«ልጄ ሆይ! በሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ ዓይንህን ጠብቅ።በስብስብ መሐል ከሆንክ ምላስህን ጠብቅ።በሰላት ውስጥ ስትሆን ደግሞ ልብህን ጠብቅ፡፡


@Hanif_tube
አንች ሰነፍ ተነሽ ሱብሒ ሶላት ስገጅ.. ብለህ áˆ´á‰ľ ልጅህ ወይም ታናሽ እህትህ ላይ ከመጮህህ በፊት ሶላት ያላት ስለመሆኑ አረጋግጥ💀


@Hanif_tube
ከሳሪ (የከሰረ ሰው) ማለት አላህ ወንጀሉን አይምርልኝም ብሎ የጠረጠረ ነው።

ከልብህ መሃርታውን ጠይቀው እንጂ ይምርሃል።


@Hanif_tube
"ሁሌም ደስታ"

🗣እስልምናን መሳይ ፀጋ አላህﷻ ሰጥቶሃልና ሁሌም ፈገግ በልና ሰውን ሁሉ ይግረመው። ባንተ ጉዳይ ፍጥረት ሁሉ ይወዛገብ። "ምን አግኝት ነው እንዲህ ሳቅ በሳቅ የሆነው?" ይበል



@Hanif_tube
የወደድከዉን ነገር በአንተ እና አላህ መካከል አቁየዉ ሰዎች የሚያምሩ ነገሮችን ያበላሻሉ!!


@Hanif_tube
አንተ በመሞትህ የሌሎች ህይወት አይቋረጥም ፤ ሁሉም እንደ ወትሮው ህይወቱን መግፋቱን ይቀጥላል ፤ አንተ ግን የማይረሳ ሰው የለምና ትረሳለህ ፣ እናም ለአኺራህ ጥረህ ስራ በመጪው አለም ዘላቂ ህይወትህ የሚጠቅምህ መልካም ስራህ ብቻ ነውና።
ብዙ የሚያስተምር አሳማሚ ምስል ከታች አለልህ ተመልከትና አስተንትን !


@Hanif_tube
በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል። ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ አስተሳሰብ እንድንይዝ ያረገናል። ሰው የአስተሳሰብ እና የድርጊት ውጤት ነው።
ውሏችን ከመልካም ሰዉ ጋር ይሁን።


@Hanif_tube
ሶላት መስገድ የከበደው ችግሩ ከሸይጣን የባሰ ነው ፣
ሸይጣን ለአደም ነው ሱጁድ አላደርግም ያለው ፣
ሶላትን የተወ ግን ለአደም ጌታ ነው አልሰግድም ያለው! ! !


@Hanif_tube
ሙእሚን ከጌታው እዝነት
የተሰተረውን ቢያውቅ ኖሮ
ጤንነትን እንደሚያጣጥመው
ሙሲባንም ያጣጥም ነበረ ።


@Hanif_tube
❤‍🩹  وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

በአላህም ላይ ተመካ፡፡
መመኪያም በአላህ በቃ፡፡



@Hanif_tube
የአላህ መልዕክተኛ() እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል:- "ለአደን ወይም ለከብት ጥበቃ ሳይሆን እንዲሁ ውሻን በባለቤትነት የያዘ በየቀኑ ከምንዳው ሁለት ቂራጥይጎድልበታል።"                

(ቡኻሪና ሙስሊም)



@Hanif_tube
💜 “የሴት ልጅ ውበቷ ሐያዕዋ ሲሆን
የጥበበኛ ሰው ውበቱ ደግሞ ዝምታ  ነው።”
ሐሰን አል በስሪ…

የአደም ልጅ ሆይ! ጥቂት ቀናት ብቻ ነው የቀረህ። አንድ ቀን ሲያልፍህ ከአንተ ህይወት የተወሰነው ወስዶ ላይመለስ እንደሚነጉድ እወቅ… ብለዋል

እንዲሁም…

ከገንዘብና ከሃብት ይልቅ ለጊዜ እጅግ የሚሳሱ ሙእሚኖችን አውቃለሁ ብለዋል።

በኩጥባ ላይም ህዝቡን ሲመክሩም…

ይህቺ አላፊ ኑሮአችሁና ምድራዊ ፀጋዎች አያታልሏችሁ። ነገ አደርገዋለሀየ… ነገ አለ…  አትበሉ። ከምድር ተሰናብታችሁ ወደ አላህ መች እንደምታመሩ አታውቁምና…
አንድ ሰው ካማኸው ምንድን ነው መፍትሄው?

እንዳማኸው ካወቀ በግልፅ ወዳማኸው ሰው ሂድና ይቅርታ (ዐውፍታ) ጠይቀው።

ካላወቀ፦ አላህ ወንጀሉን እንዲምርለት ዱዓእ አድርግለት፣ በዛ ባማኸው ቦታ ስለርሱ ጥሩ ጎን አውራና አወድሰው። መልካም ሥራ መጥፎን ያብሳልና!

ኢብኑ ዑሠይሚን