Forwarded from Online
ሕማማትን በሕማማት ++ ራስህን ፈልገው ++
ወዳጄ ሆይ እባክህን ጌታችን ከተያዘበት ሐሙስ ማታ እስከ ተቀበረበት ዓርብ ያለው ክስተት ውስጥ ራስህን ፈልገው፡፡ በዚያ ከነበሩት ሰዎች አንተ ማንን ትመስላለ? ወዳጅ አየመሰለ የሚሸጠው ይሁዳ አንተ ነህ? ወይንስ ፈርቶ የሚክደውን ጴጥሮስን? የአንተ ጠባይ በእነዚያ ሃያ ሰዓታት ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ማንን ይመስላል? ጌታን አስረው እያዳፉ የወሰዱትን ትመስላለህ? በሐሰት የሚመሰክሩበት ውስጥ ነህ? ወይንስ ያለ ጥፋቱ አስረው ከሚያንገላቱት ውስጥ ነህ? ያለ ህግ አግባብ በግፍ ከፈረዱበት ውስጥ ነህ? ወይስ ገዢዎችን ለማስደሰት ብለው በጥፊ ከሚመቱት ውስጥ ነህ? እንደ ጲላጦስ አይነት ዳኛ ትሆን? ንጹሕ መሆኑን እያወቅህ ገርፈኸው ይሆን? ይሰቀል ሲባል አብረው ከሚጮኹት ትሆን? ከሄሮድስ ጭፍሮች ጋር ስቀህበታል ወይንስ ከገሊላ ሴቶች ጋር አልቀስህለታል? ወዳጄ ሆይ በዕለተ ዓርብ ከነበሩት አንተ ማንን ትመስላለህ? የቀኙ ወንበዴ ነህ ወይንስ የግራው ፣ የቆምከው ከሰደቡት ጋር ነው ወይንስ ከእናቱ ጋር?

Forwarded from አክሊል (ĥ€ñï)
1. አልችልም ብለህ በምታስብበት ጊዜ ... ይህንን አስታውስ
☞ " ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13)
2. አንድ ነገር እንደሚጎድልህ በምታስብበት ጊዜ
..... ይህንን አስታውስ
☞ " አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን
ሁሉ ይሞላባችኋል።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:19)
3. በምትፈራበት ጊዜ
...... ይህንን አስታውስ
☞ " እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ
አልሰጠንምና።"
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:7)
4. እግዚአብሔር የሚፈልገውን ለማድረግ በቂ እምነት የለኝም ብለህ በምታስብበት ጊዜ
. .... ይህንን አስታውስ
☞ " እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈኝ "
(ወደ ሮሜ ሰዎች 12:3)
5. ደካማ ነኝ ብለህ በምታስብበት ጊዜ
...... ይህንን አስታውስ
☞ " እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር
የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው፡፡ እና፤ አምላካቸውን የሚያውቁ
ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም። "
(መዝ . 27:1 ፤ ዳን 11:32)
6. ሰይጣን ሕይወትህን እስኪቆጣጠር ድረስ የፈተነህ በሚመስልህ ጊዜ
..... ይህንን አስታውስ
☞ " በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:4)
7. ተሸንፌለሁ ብለህ በምታስብበት ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ
የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:14)
8. ጥበብ ጎድሎኛል ብለህ በምታስብበት ጊዜ
..... ይህንን አስታውስ
☞ " ክርስቶስ ለአንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብ እንደ ሆነልህና ሳይነቅፍ በልግስና
እግዚአብሔር እንደሚሰጥ የሚያረጋግጠውን ቃል ፡፡ 1ኛ ቆሮ. 1:30 ፤ ያዕ. 1:5 )
9. መንፈስህ ሲጫጫንህና ሲከብድህ በምታስብበት ጊዜ
..... ይህንን አስታውስ
☞ 22፤ ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።
23፤ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። (ሰቆ ኤር . 3፡21-23)
10. ጭንቀትና ውጥረት በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:7)
11. የታሰርክ መስሎ በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:17)
12. እንደ ተኮነንክ መስሎ በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህንን አስታውስ
☞ " እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1)
13. ብቸኝነት በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህንን አስታውስ
☞ " ኢየሱስ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። "
(የማቴዎስ ወንጌል 28:19-20)
14. የተረገምክና መጥፎ ዕድል የተፀናወተህ መስሎ በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 3:13)
15. አለመርካት በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:11)
16. ዋጋ ቢስ እንደ ሆነክ በሚሰማህ ጊዜ
...... ይህንን አስታውስ
☞ " እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን
ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21)
17. እየተሰደድክ መሆንህ በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን
ይቃወመናል?"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31)
18. ግራ የገባህ መስሎ በሚሰማህ ጊዜ
..... ይህን አስታውስ
☞ " እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ "(1ኛ ቆሮ
14:33)
፤ እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን
መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።"
(1ኛ ቆሮ 2:12)
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን፫

Forwarded from ገድለ ቅዱሳን
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። +++
+ ዛሬ ሚያዝያ17 ቀን።
+ እንኳን ለሰሞነ ሕማማት አራተኛ ቀን ለጸሎተ ሐሙስና ለሕጽበተ እግር በሰላም አደረሰን።
+ ዕለተ ሐሙስ
የዕለቱ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሐፀበ እግረ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ አነኒ ሐፀብኩ እግሪክሙ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ"። ቅዱስ ያሬድ።
+ ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተ ክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
1.ሕጽበተ እግር ይባላል፡፡
+ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት ጳሳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ /ዮሐ. 13፤4-15
2.የጸሎት ሐሙስ ይባላል፡፡
+ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ /ማቴ. 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1/
3.የምስጢር ቀንም ይባላል፡፡
+ ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፡፡በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፡፡ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም፡፡ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡
4.የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡
+ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳ ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ /ሉቃ. 22፤18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡
5.የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡
+ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱም ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ.15፤15/ ከባርነት ነጻ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ /ማቴ 26፤17-19/
6.አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል፡፡
+ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ፡፡
+ በዚች ቀን የዘብዴዎስ ልጅ የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ወንድም ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት ዐረፈ። ይህም በእስያ ውስጥ ከአስተማረ በኋላ ዕርቅ በተገኘባት በእውነተኛ አምላክ በጌታችን ወንጌል ሊያስተምራቸው ወደ ተበተኑ ወደ ዐሥራ ሁለቱ ነገድ ወጣ። እነርሱም አንድ አምላክን የሚአመልኩ አልነበሩም እየራሳቸው የመረጡትን የሚአስቷቸው ጣዖታትን ያመልኩ ነበረ እንጂ። ከቄሣር ሥልጣን በታች የተሾመ ኄሮድስም ሹመቱ በሚዳብር መንግሥቱ በሚያጽና ገንዘብ ብዙ ግብር እንዲገብሩ እጅ መንሻም እንዲአስገቡ አዘዘ።
ቅዱስ ያዕቆብ ግን ወደእርሳቸው በደረሰ ጊዜ በአገራቸው ቋንቋ ሰበከላቸው የፍጥረትን ሁሉ ቋንቋ ማወቅን እግዚአብሔር ሰጥቶት ነበርና የሚያውቀው የሰው ቋንቋ ብቻ አልነበረም የእንስሳና የአራዊት የሰማይ ወፎችንም ቋንቋ ነበረ እንጂ። በውስጣቸው በሰበከም ጊዜ የከፋሥራቸውን ትተው በሕያው እግዚአብሔር በአንድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት በሆነ መንፈስ ቅዱስ ነፍሶቻቸው በእጁ ውስጥ በተያዙ በአንድ አምላክ እንዲያምኑ አዘዛቸው ። እርሱም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ የሚመጣ ነው። ዳግመኛም በማይጠፋና በማይበላሽ በሰማያት ድልብ ይሆናቸው ዘንድ ከገንዘባቸው ለችግረኞችና ለድኆች እንዲመጸውቱ አዘዛቸው።
ትምህርቱንም በሰሙ ጊዜ ከክፋ ሥራቸው ተመልሰው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብም ትምህርቱን ፈጥነው ስለተቀበሉት እጅግ ወደዳቸው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው በየአገራቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። ዳግመኛም ከእንስሶቻቸው ከሚዘሩአቸው እህሎችና ወይን አትክልቶች ፍሬዎች ለካህናትና ለድኆች ምግብ ሊሆን ለቤተ ክርሰቲያን የመጀመርያውን መባ እንዲሰጡ አዘዛቸው። ሕዝቡም በአንድ ቃል ያዘዝከንን ሁሉ እኛ እናደርጋለን አሉት። ከዚህ በኋላ ከእንስሳት መጀመሪያ የተወለደውን ከእህሉም ቀዳምያቱንና ዓሥራትን ለቤተ ክርስቲያን አመጡ።
ኄሮድስም ቅዱስ ያዕቆብ ለቤተ ክርስቲያን መባ ይሰጡ ዘንድ እንዲሚያዝ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጣውና ሕዝቡ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድኆች ምጽዋትና ለቤተ ክርስቲያን መባ እንዲሰጡ የምታዝ አንተ ነህን" አለው። "አዎን እኔ ነኝ" አለው ያን ጊዜ ኄሮድስ ተቆጥቶ ራሱ በሰይፍፍ አንገቱን መትቶ ቆረጠው። በኢየሩሳሌምም ሁከትና ሽብር ሆነ ደግሞ ከፋሲካ በዓል በኋላ ሊገድለው አስቦ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ወስዶ አሠረው የእግዚአብሔር መልአክም ኄሮድስን ቀሠፈው ተልቶ ተበላሽቶ ሞተ ልዑል አምላክን አላከበረውምና።
የቅዱስ ያዕቆብን ሥጋ ግን ምዕመናን ወሰዱት ገንዘው በቤተ መቅደስ ውስጥ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ በረከት ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
+ + +
+ የዕለቱ ሕጽበተ እግር ምስባክ፦ "ተሐፅበኒ ወእምበረድ እጸዓዱ(ወእጻዓዱ)። ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወኃሤተ። ወይትፌሥሑ አዕፅምተ ጻድቃን"። መዝ50፥7-8። የሚነበበው ወንጌል13፥4-13።
+ + +
+የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወሠራዕከ ማእደ በቅድሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ። ወአጽሐድከ በቅብዕ ርእስየ"። መዝ22፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ26፥26-። የሚቀደሰው ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ነው።
+ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበ ሰላም።

Forwarded from ✞ገድለ ቅዱሳን✞
††† እንኩዋን ለታላቁ "ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
+*" ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ "*+
=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን
በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም::
"ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ
መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል"
ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::
+ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም
ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ:
ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ
መዛሙርቱን መጥራት ነበር::
+ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ
ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ
12ቱን ሐዋርያት መረጠ::
+እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)
+እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3
ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ
ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::
+ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ
ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም
ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው
ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ
ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)
+ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር
ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት
በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር
ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው
ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)
+የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19):
እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ
ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም
ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ::
(ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር
አከበራቸው::
+ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጌዜ ገና
ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን
በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ
ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::
+ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም
በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው:
ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::
+ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና
በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው::
በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን:
ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት
ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)
+ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል
በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ
እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ
ግን እንደ ትውፊቱ በዚህች ቀን ዓለምን በእጣ ለ12
ተካፈሏት::
+ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና
ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች
ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው
ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::
+በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር
ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት
መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ
ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ::
አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ::
እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::
+ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው
ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ
ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም
ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው
አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና
እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና
ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::
✞ ቅዱስ ያዕቆብ ✞
=>በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱሱ ሐዋርያ አባቱ ዘብዴዎስ: እናቱ
ማርያም ባውፍልያ: ትንሽ ወንድሙ ደግሞ ዮሐንስ
ወንጌላዊ ይባላል::
+ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን አሳ አጥማጅነቱን ትቶ:
ከጌታችን እግር ተምሮ በዓለም ወንጌልን አስፋፍቷል::
(ማር. 1:19) ከሌሎቹ ሐዋርያት በተለየም የእንስሳትን
ቁዋንቁዋ ያውቅ ነበር::
+በመጽሐፍ ቅዱስ በሔሮድስ መገደሉ (ሰማዕትነቱ)
የተነገረለት ከ12ቱ ብቸኛው ነው:: ሰማዕት የሆነውም
በ44 ዓ/ም : ማለትም ከጌታ ዕርገት 10 ዓመታት በሁዋላ
: ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሳይበተኑ ነው::
(ሐዋ. 12:1)
=>እግዚአብሔር ከቅዱስ ያዕቆብና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን::
=>ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ (ከ12ቱ
ሐዋርያት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
=>+"+ በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው
ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን
ጫነባቸው:: የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ
ገደለው:: አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ
ዼጥሮስን ደግሞ ያዘው:: የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ::
+"+ (ሐዋ. 12:1)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

ሰሙነ ህማማት ዘሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ)
በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ ማቴ. 26፣ 36-46 ዮሐ.17
#ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡
#የምስጢር_ቀን_ይባላል
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡
#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል
ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል /ሉቃ. 22፣20/ ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡
#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት /ዮሐ. 15፣15/፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡

⛪. #የሰሙነ_ህማማት_ዕለተ_ሐሙስ
#ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተ ክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
➡️1.#ሕጽበተ_እግር_ይባላል፡፡
➡️2. #የጸሎት_ሐሙስ ይባላል፡፡
➡️3. #የምስጢር_ቀንም ይባላል፡፡
➡️ 4.#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ ይባላል፡፡
➡️ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ /ዮሐ. 13፤4-15/
➡️2. #የጸሎት ሐሙስ ይባላል፡፡
➡️የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ /ማቴ. 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1/
➡️3. #የምስጢር ቀንም ይባላል፡፡
➡️#ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፡፡በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
➡️#በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፡፡ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም፡፡ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡
➡️ 4.#የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡
➡️ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳ ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ /ሉቃ. 22፤18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡
➡️5. #የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡
➡️ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱም ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ.15፤15/ ከባርነት ነጻ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ /ማቴ 26፤17-19/
➡️6. #አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል፡፡
➡️ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ
ቅዱስ ስም አሜን!
በዚኽች ዕለት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት
ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡
የክብር ባለቤት ጌታችን በአልአዛር ቤት ከደቀ
መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ
ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም
አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ
ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ
ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ
እለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን
ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ
ነው ብሎለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን
በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል
ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት
መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡
ሌላው በዚህ ዕለት የተፈጸመው ተገባር ሕጽበተ
እግር ነው፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል “እራትም ሲበሉ
ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ
አሳልፎ እንዲሰጠው ሐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ
ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ
ወስዶ ታጠቀ፤በኋላም በመታጠቢያው ውኃ
ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” /
ዮሐ.13፥1-10/ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል
ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን
አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ
አለው” /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር
ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ
ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም”
በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
አንድ ደቀ መዛሙርቱን ሥርዓተ ጥምቀት ፈጸመ
ሁለተኛ በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር
ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ
የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ.
11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው
ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አላየውም፡፡
√ ሌላው በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ
እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር
ለይቶ ነገራቸው፡፡ እንዲህም ብሎ “እጁን
በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው”
በዚህ ዕለትም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ
ክርስቶስ መከራ የተቀበለልን የእኛን ሥጋ
የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን
ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው
እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /
ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/
❖ የዚህ ቀን ስያሜዎች፦ ❖
☞ ጸሎተ ሐሙስ
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን
የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም
ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ
መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ
ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17/
በዚህም ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ
ይጠራል፡፡
☞ ሕጽበተ እግር
ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት
የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡
ወንጌሉ እንደሚል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ
በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ
እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ
ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ
ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም
በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን
እግር አጠበ፡፡”/ማቴ.26፥27/
☞ የምሥጢር ቀን
በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር
በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ
ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ
ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው
አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው
እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ ዕለት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን
ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ
ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ
ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር
ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን
ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት
ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ የምሥጢር ቀን
ይባላል፡፡
☞ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ አዲስ የሆነውን የሐዲስ ኪዳን
መስዋዕት የመሠረተበት ነው፡፡ ቀድሞ የነበረውን
መስዋዕተ ኦሪት ሽሮ የሐዲስ ኪዳን ደምና
ሥጋውን ፈትቶ ስላቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን
ሐሙስ ይባላል፡፡ /ሉቃ.22፥20/
☞ የነጻነት ሐሙስ
በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የመለሰበት
ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር
በማብቃቱ የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡
❖ሥርዓተ ጸሎተ ሐሙስ ❖
☞ በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ
እንደተለመደው ይከናወናሉ ለየት ያለው ሥርዓት
መንበሩ /ታቦት/ ጥቁር ልብስ ይለብሳል ጸሎተ
ዕጣን ይጸለያል ቤተ ክርስቲያኑ በማዕጠንት
ይታጠናል፡፡
በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኰስኰስቶችን ውኃ
ሞልቶ ያቀርባል አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ
መታጠቢያ፡፡ ጸሎተ አኮቴት የተባለ የጸሎት ዐይነት
ተጸልዮ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ /በሊቀ
ጳጳሱ/ እጅ ተባርኮ የሕጽበተ እግር ሥርዓት
ከካህናት እስከ ምእመናን ከወንዶች እስከ ሴቶች
በካህኑ አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡ ሥርዓተ
ኅጽበቱ የሚከናወነውም በውኃ ብቻ ሳይሆን
የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓቱ
ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡
ምስጢሩም ወይራ ጸኑዕ ነው ክርስቶስ ጽኑ መከራ
መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም /
የሚያጥበውና የሚታጠበው ክርስቲያን/ መከራ
ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ነው፡፡ የወይኑ ቅጠል
በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን
የሕይወት መጠጥ ይሆናቸው ዘንድ መስጠቱን
ለማዘከር ነው፡፡ ማቴ 26.26 ይህም ሥርዓት
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ
ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለምእመናን
ለማሳየት ነው ዮሐ. 13፤14፡፡ በቀኝና በግራ
የቆሙ ሊቃውንትም ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ
አርዳኢሁ ሐፀበ እያሉ ይዘምራሉ፡፡
ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው
ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን
ይቀበላሉ፡፡
የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴው የሚከናወነው በተመጠነ
ድምፅ ነው፡፡ ደወሉ የጸናጽል ድምጽ ሲሆን በቀስታ
ስለሚጮህ ነው፡፡ የድምጽ ማጉያ አይጠቀሙም፡፡
ምክንያቱም ዲያቆኑና ካህኑ ዜማውን በቀስታ
የሚሉት ይሁዳ በምስጢር ጌታችንን ማስያዙን
ለመጠቆም ሲሆን በሌላ በኩል የዘመነ ብሉይ
ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማስታወስ
ነው፡፡ በመቀጠል ክቡር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር
ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው
አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና
ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡
❖ ጉልባን ❖
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ
ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ
ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ
በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን
ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ
ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን
የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ
ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ
አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን
መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም
በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ
አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን
ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ
ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ
የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ
ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ
ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ
የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ
ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ
እንደሚያስጠ
ቅዱስ ስም አሜን!
በዚኽች ዕለት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት
ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡
የክብር ባለቤት ጌታችን በአልአዛር ቤት ከደቀ
መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ
ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም
አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ
ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ
ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ
እለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን
ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ
ነው ብሎለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን
በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል
ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት
መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡
ሌላው በዚህ ዕለት የተፈጸመው ተገባር ሕጽበተ
እግር ነው፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል “እራትም ሲበሉ
ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ
አሳልፎ እንዲሰጠው ሐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ
ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ
ወስዶ ታጠቀ፤በኋላም በመታጠቢያው ውኃ
ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” /
ዮሐ.13፥1-10/ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል
ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን
አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ
አለው” /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር
ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ
ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም”
በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
አንድ ደቀ መዛሙርቱን ሥርዓተ ጥምቀት ፈጸመ
ሁለተኛ በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር
ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ
የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ.
11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው
ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አላየውም፡፡
√ ሌላው በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ
እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር
ለይቶ ነገራቸው፡፡ እንዲህም ብሎ “እጁን
በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው”
በዚህ ዕለትም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ
ክርስቶስ መከራ የተቀበለልን የእኛን ሥጋ
የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን
ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው
እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /
ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/
❖ የዚህ ቀን ስያሜዎች፦ ❖
☞ ጸሎተ ሐሙስ
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን
የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም
ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ
መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ
ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17/
በዚህም ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ
ይጠራል፡፡
☞ ሕጽበተ እግር
ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት
የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡
ወንጌሉ እንደሚል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ
በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ
እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ
ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ
ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም
በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን
እግር አጠበ፡፡”/ማቴ.26፥27/
☞ የምሥጢር ቀን
በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር
በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ
ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ
ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው
አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው
እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ ዕለት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን
ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ
ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ
ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር
ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን
ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት
ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ የምሥጢር ቀን
ይባላል፡፡
☞ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ አዲስ የሆነውን የሐዲስ ኪዳን
መስዋዕት የመሠረተበት ነው፡፡ ቀድሞ የነበረውን
መስዋዕተ ኦሪት ሽሮ የሐዲስ ኪዳን ደምና
ሥጋውን ፈትቶ ስላቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን
ሐሙስ ይባላል፡፡ /ሉቃ.22፥20/
☞ የነጻነት ሐሙስ
በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የመለሰበት
ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር
በማብቃቱ የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡
❖ሥርዓተ ጸሎተ ሐሙስ ❖
☞ በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ
እንደተለመደው ይከናወናሉ ለየት ያለው ሥርዓት
መንበሩ /ታቦት/ ጥቁር ልብስ ይለብሳል ጸሎተ
ዕጣን ይጸለያል ቤተ ክርስቲያኑ በማዕጠንት
ይታጠናል፡፡
በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኰስኰስቶችን ውኃ
ሞልቶ ያቀርባል አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ
መታጠቢያ፡፡ ጸሎተ አኮቴት የተባለ የጸሎት ዐይነት
ተጸልዮ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ /በሊቀ
ጳጳሱ/ እጅ ተባርኮ የሕጽበተ እግር ሥርዓት
ከካህናት እስከ ምእመናን ከወንዶች እስከ ሴቶች
በካህኑ አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡ ሥርዓተ
ኅጽበቱ የሚከናወነውም በውኃ ብቻ ሳይሆን
የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓቱ
ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡
ምስጢሩም ወይራ ጸኑዕ ነው ክርስቶስ ጽኑ መከራ
መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም /
የሚያጥበውና የሚታጠበው ክርስቲያን/ መከራ
ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ነው፡፡ የወይኑ ቅጠል
በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን
የሕይወት መጠጥ ይሆናቸው ዘንድ መስጠቱን
ለማዘከር ነው፡፡ ማቴ 26.26 ይህም ሥርዓት
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ
ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለምእመናን
ለማሳየት ነው ዮሐ. 13፤14፡፡ በቀኝና በግራ
የቆሙ ሊቃውንትም ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ
አርዳኢሁ ሐፀበ እያሉ ይዘምራሉ፡፡
ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው
ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን
ይቀበላሉ፡፡
የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴው የሚከናወነው በተመጠነ
ድምፅ ነው፡፡ ደወሉ የጸናጽል ድምጽ ሲሆን በቀስታ
ስለሚጮህ ነው፡፡ የድምጽ ማጉያ አይጠቀሙም፡፡
ምክንያቱም ዲያቆኑና ካህኑ ዜማውን በቀስታ
የሚሉት ይሁዳ በምስጢር ጌታችንን ማስያዙን
ለመጠቆም ሲሆን በሌላ በኩል የዘመነ ብሉይ
ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማስታወስ
ነው፡፡ በመቀጠል ክቡር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር
ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው
አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና
ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡
❖ ጉልባን ❖
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ
ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ
ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ
በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን
ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ
ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን
የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ
ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ
አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን
መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም
በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ
አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን
ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ
ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ
የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ
ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ
ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ
የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ
ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ
እንደሚያስጠ
Forwarded from Online
ማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው
ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
+ + +
ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን
ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት
ነው፡፡ በወንጌልም እንደተጻፈው ፋሲካውን
የሚያከብሩበት ቀን ሲደርስ ጌታ ኢየሱስም
ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሒዳችሁ ፋሲካን እንበላ
ዘንድ አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም በየት
እንድናዘጋጅልህ ትወዳለህ አሉት? ወደ ከተማ
ገብታችሁ የውኃ ማድጋ የሚሸከም ስምዖን
የተባለ ሰው ታገኛላችሁ፤ ወደ ገባበት ቤት እርሱን
ተከተሉት፤ መምህር ከደቀ መዛሙርቶቼ ጋር ፋሲካ
የሚያደርግበት አዳራሽ ወዴት ነው ይልሃል? በሉት
እርሱ የተነጠፈውንና ታላቁን አዳራሽ ያሳያችኋል፤
በዚያም ፋሲካን አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም
ወደ ተላኩበት ከተማ ገብተው አልዓዛርን የውኃ
ማድጋ ተሸክሞ አገኙት፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም
ለስምዖን ጌታ በቤቱ ፋሲካን ሊያዘጋጅ መሻቱ
እንደሆነ ነገሩት፤ እርሱም የፍጥረታት ጌታ በቤቱ
ሊመጣ እንዳለ አስቦ ተደሰተ፤ ወደ ሚስቱ
አክሮሲናም ሔዶ ይህ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳ
እኔንም በኃጢአቴ ይቅር ይለኛል፤ ያነጻኝ ዘንድ
ከሐዋርያት ጋር በቤታችን ይመጣል አላት፤
አክሮሲናም እጅግ ተደሰተች፡፡
ጌታችንም ጊዜው ሲደርስ ከሐዋርያት ጋር
በአንድነት መጣ፤ ስምዖንም ከቤቱ ወጥቶ ሮጦ
ከጌታ እግር ሥር ሰገደ፤ ወደ ቤቱም ከሐዋርያት
ጋር አስገባቸው፡፡ ይሁዳ ግን ይህን ሰዓት
አልነበረም፤ ውጪ ከሻጭና ለዋጭ ጋር ገንዘብ
ሲደራደር ነበር፤ ስምዖንም ለሚስቱ አክሮሲና
ጌታና ሐዋርያት የሚገቡበት በእግራቸው
የሚረግጡት ምንጣፍ እንድታነጥፍ አዘዛት፡፡
አክሮሲና ግን የጌታን መልክ አታውቀውም ነበር፤
ያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጸሎት ሲጸልዩ አይታ
‹‹ከእናንተ ውስጥ መምህሩ ማነው››
አለቻቸው፤እነርሱም ዝም አሉ፤ መልከ መልካም
ወደ ሆነውና የጌታ ወዳጅ ወደሆነው ዮሐንስ
ተመልክታ እርሱ ይሆን አለች፤ ጴጥሮስ ግን ቀበል
አድርጎ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ከውስጠኛው ክፍል ቆሞ
ይጸልያል፤ ጌታ እርሱ ነው›› አላት፡፡ እርሷም ገብታ
ሰገደችለት፤ ይሁዳም በመጨረሻ ሳጥን ተሸክሞ
መጣ፤ ጠባቂውንም እኔ የጌታ ደቀ መዝሙር ነኝ
አለው፡፡ በር ጠባቂውም እለእስክንድሮስም
የተነጠፈውን እስካጥፍ ጠብቅ ብሎ ዘለፈው፤
ልብሱንም አንስቶ አስገባው፤ /ግብረ ሕማማት
፭፻፹፫-፫፻፹፭/፡፡
በአንደኛው ሰዓት ሌሊት (ሐሙስ ለአርብ ምሽት)፤
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልብሱን አኖረ፤ማበሻ
ጨርቅም አንስቶ ወገቡን ታጠቀ፤ ይህችውም ሥራ
የምታሠራና የምታስጌጥ ናት፤ ለዛሬው የመነኮሳት
መታጠቂያ አብነት ናት፡፡ ለምሳሌ፡- ኢዮአብ ወደ
ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረችው ያለ
ዓይነት ነው፤ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር
ያጥብ ዘንድ በጴጥሮስ ጀመረ፤ ጴጥሮስ ግን እኔ
ባንተ ልታጠብ አይገባኝም አለ፤ ጌታችንም መልሶ
‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን
ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ
የለህም›› (ዮሐ.፲፫፥፰)፡፡ ሌሎቹንም ሐዋርያት
አጠባቸው፤ አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳንም እግሩን
አጠበው፡፡ ጌታ አሳልፎ እንደሚሰጠው ሳያውቅ
ቀርቶ አልነበረም፤ ፍቅርን ሲያስተምረውና ለንስሐ
ጊዜ ሲሰጠው ነው እንጂ፤ እኛንም ለሚወደን ብቻ
ሳይሆን ለሚጠላን እንኳን በጎ ማድረግ እንደሚገባ
ሲያስተምረን ነው፡፡
ጌታችን ጾመና ጹሙ አለን፤ተጠመቀና ተጠመቁ
አለን፤ ጸለየና ጸልዩ፤ ሰገደናም ስገዱ አለን፤
የሐዋርያትንም እግር አጥቦ እናንተም እንዲህ
አድርጉ ብሎ መምህረ ትሕትናነቱን ገለጠልን፡፡
ዛሬም ከፓትርያርኩ ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፤ካህናት
በየመአርጋቸው የምእመናኑን እግር በማጠብ
የጌታን የትሕትና ሥራ ያስቡታል፡፡
ለሐዋርያት ትሕትናን ሲያስተምራቸው ጌታችን
እግራቸውን እንደ አጠባቸው ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡
ከዚያም ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ ብሎ
ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው፤ ዛሬም የልጅነት
ጥምቀት የሚቀበሉ ምእመናን በዚያኑ ዕለት
ከክርስትና ቤት ወደ ቤተ መቅደስ ሔደው የጌታን
ክቡር ሥጋና ደም ይቀበላሉ፤ መሠረቱም ጌታችን
ለሐዋርያት ያደረገውን ተመርኩዞ ነው፡፡ ከፍ ከፍ
ሊል የሚወድ ራሱን ዝቅ ያድርግ ብሎም
አስተምሯቸዋል፤ አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ
ምሥጢር ጌታ ለጴጥሮስ ‹‹እኔ እግርህን
ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም››
ያለውን ሲተረጉሙ ‹‹እኔ በአገልጋይ አምሳል
እግርህ ካላጠብኩህ አንተም ከበታችህ ላሉት
ራስህን ዝቅ ለማድረግ አትችልም፤ ራስህን ዝቅ
ዝቅ ካላደረግህ አለቃ ልትሆን አትችልም››
ለማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ ጌታችን
ደግሞ አምላክ ፈጣሪ መምህር ሳለ ዝቅ ብሎ
እንዳጠባቸው እነርሱም ክህነታቸውንና
መምህርነታቸውን በትሕትና እንዲጀምሩ
ሲያስተምራቸው ነው፡፡
በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ምሽት፤ ጌታችን
ሕብስቱን ባርኮ ለዐሥራ ሦስት ፈትቶ ሰጣቸው፤
ዐሥራ ሦስተኛውን እርሱ የሚቀበለው ነውና ነገር
ግን የሚረባውና የሚጠቅመው አይደለም፤ ‹‹ዝ
ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ›› ብሎ ሕብስቱን
ባርኮ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ ››
ወይኑንም ባርኮ ‹‹ይህ ደሜ ነው እንካችሁ
ጠጡ›› ብሎ ሰጣቸው፡፡አስራ ሦስት አድርጎ
መፈተቱ ሐዋርያትን እንዳይገርማቸው
(እንዳያስፈራቸው) ነው፤ እራሱም ጥዒሞ
አጥዐሞሙ/ቀምሶ አቀመሳቸው/ እንዲል አብነት
ለመሆን፤ አንድም ነገ በመልዕተ መስቀል አስራ
ሦስቱ ሕማማተ መስቀል እቀበላለሁ ሲል ነው፤
ጌታ ይህን ባያደርግ ኖሮ ዛሬ ካህኑ የጌታን ሥጋና
ደም ሳይቀበል አቀብሎ ብቻ በሄደ ነበርና ለእነርሱ
ለማስተማር ነው፡፡
ማዕዱንም እየበሉ ጌታችንም ‹‹እውነት እውነት
እላችኋለሁ! ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ
ይሰጠኛል›› አላቸው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፩)፡፡ ሐዋርያት
ሁሉ ደነገጡ! እርስ በርሳቸው ተያዩ፤‹‹እኔ እሆን?
እኔ እሆን?›› ተባባሉ፤ ጴጥሮስም ዮሐንስን ጠጋ
ብሎ ‹‹ማነው አሳልፎ የሚሰጠህ ብለህ ጌታን
ጠይቀው›› አለው፤ወንጌላዊው ዮሐንስም ጌታን
ጠጋ ብሎ ጠየቀው ጌታችንም ‹‹ከእኔ ጋር እጁን
ከወጪቱ የሚያገባ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል››
አለ፤ (ማቴ.፳፮፥፳፫/ሉቃ.፳፪፥፳፩)፡፡ ሐዋርያትም
‹‹ሁላችን ከወጪቱ የምንጠቅስ አይደለምን?››
ሲሉ ጌታችን ‹‹እኔ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው
ነው›› አላቸው፤ ያንጊዜ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ
ሰጠው፤ ስለዚህ ወንጌላውያኑ ይህን ታሪክ ይዘው
አንድ ሳለ በተለያየ አገላለጥ ገለጡልን፡፡
ይሁዳም እንደቸኮለ ሰው ይቅበዘበዝ
ነበር፤እርሱም ጌታን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጠው
በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ጌታም ወደ ይሁዳ ጠጋ
ብሎ ‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ! ልትሠራው የምትሻው
ሥራ ካለ ሒድ›› አለው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፯)፤
ይሁዳም ፈጥኖ ወጥቶ ወደ አይሁዳውያን ጌታን
አሳልፎ ሊሰጥ ዋጋ ሊነጋገር ሔደ፡፡
ከሦስተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ አምስተኛይቱ
ሰዓተ ሌሊት ድረስ
ለደቀ መዛሙርቱ ሲመክራቸው የመንፈስ
ቅዱስንም መምጣት አብዝቶ ሲነግራቸው፤
ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቀና፤ እርሱ ከአባቱ ጋር
አንድ እንደሆነም ነገራቸው፤ ለብቻው ፈቀቅ ብሎ
ወዙ እንደ ደም እስኪፈስ እየሰገደ ጸለየ፤ወደ ደቀ
መዛሙርቱ ተመለሰ፤ ተኝተው አገኛቸው፤
ቀሰቀሳቸው፤ ጴጥሮስንም አንድ ሰዓት ያህል እንኳን
ከእኔ ጋር መትጋት አቃታችሁን? ወደ ፈተና
እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ አለው! (ሉቃ.፳፪፥፲፬-
፵፮)፡፡
የጌታችን በአይሁድ መያዝ (ስድስተኛው ሰዓተ
ሌሊት)
ጌታችንም ከአብ ጋር ስላለው አንድነትና ክብር
ለሐዋርያት ካስተማራቸው በኋላ ‹‹ኢየሱስም
ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ
ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤
በዚያም ገባ›› (ዮሐ.፲፰፥፩)፡፡ወንዙን ተሻግሮ
ያለውን ዛፍ አልፎ ወዳለው ዱር ገባ፡፡ ይሁዳም
ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
+ + +
ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን
ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት
ነው፡፡ በወንጌልም እንደተጻፈው ፋሲካውን
የሚያከብሩበት ቀን ሲደርስ ጌታ ኢየሱስም
ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሒዳችሁ ፋሲካን እንበላ
ዘንድ አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም በየት
እንድናዘጋጅልህ ትወዳለህ አሉት? ወደ ከተማ
ገብታችሁ የውኃ ማድጋ የሚሸከም ስምዖን
የተባለ ሰው ታገኛላችሁ፤ ወደ ገባበት ቤት እርሱን
ተከተሉት፤ መምህር ከደቀ መዛሙርቶቼ ጋር ፋሲካ
የሚያደርግበት አዳራሽ ወዴት ነው ይልሃል? በሉት
እርሱ የተነጠፈውንና ታላቁን አዳራሽ ያሳያችኋል፤
በዚያም ፋሲካን አዘጋጁልን አላቸው፤ እነርሱም
ወደ ተላኩበት ከተማ ገብተው አልዓዛርን የውኃ
ማድጋ ተሸክሞ አገኙት፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም
ለስምዖን ጌታ በቤቱ ፋሲካን ሊያዘጋጅ መሻቱ
እንደሆነ ነገሩት፤ እርሱም የፍጥረታት ጌታ በቤቱ
ሊመጣ እንዳለ አስቦ ተደሰተ፤ ወደ ሚስቱ
አክሮሲናም ሔዶ ይህ አልዓዛርን ከሞት ያስነሳ
እኔንም በኃጢአቴ ይቅር ይለኛል፤ ያነጻኝ ዘንድ
ከሐዋርያት ጋር በቤታችን ይመጣል አላት፤
አክሮሲናም እጅግ ተደሰተች፡፡
ጌታችንም ጊዜው ሲደርስ ከሐዋርያት ጋር
በአንድነት መጣ፤ ስምዖንም ከቤቱ ወጥቶ ሮጦ
ከጌታ እግር ሥር ሰገደ፤ ወደ ቤቱም ከሐዋርያት
ጋር አስገባቸው፡፡ ይሁዳ ግን ይህን ሰዓት
አልነበረም፤ ውጪ ከሻጭና ለዋጭ ጋር ገንዘብ
ሲደራደር ነበር፤ ስምዖንም ለሚስቱ አክሮሲና
ጌታና ሐዋርያት የሚገቡበት በእግራቸው
የሚረግጡት ምንጣፍ እንድታነጥፍ አዘዛት፡፡
አክሮሲና ግን የጌታን መልክ አታውቀውም ነበር፤
ያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጸሎት ሲጸልዩ አይታ
‹‹ከእናንተ ውስጥ መምህሩ ማነው››
አለቻቸው፤እነርሱም ዝም አሉ፤ መልከ መልካም
ወደ ሆነውና የጌታ ወዳጅ ወደሆነው ዮሐንስ
ተመልክታ እርሱ ይሆን አለች፤ ጴጥሮስ ግን ቀበል
አድርጎ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ከውስጠኛው ክፍል ቆሞ
ይጸልያል፤ ጌታ እርሱ ነው›› አላት፡፡ እርሷም ገብታ
ሰገደችለት፤ ይሁዳም በመጨረሻ ሳጥን ተሸክሞ
መጣ፤ ጠባቂውንም እኔ የጌታ ደቀ መዝሙር ነኝ
አለው፡፡ በር ጠባቂውም እለእስክንድሮስም
የተነጠፈውን እስካጥፍ ጠብቅ ብሎ ዘለፈው፤
ልብሱንም አንስቶ አስገባው፤ /ግብረ ሕማማት
፭፻፹፫-፫፻፹፭/፡፡
በአንደኛው ሰዓት ሌሊት (ሐሙስ ለአርብ ምሽት)፤
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ልብሱን አኖረ፤ማበሻ
ጨርቅም አንስቶ ወገቡን ታጠቀ፤ ይህችውም ሥራ
የምታሠራና የምታስጌጥ ናት፤ ለዛሬው የመነኮሳት
መታጠቂያ አብነት ናት፡፡ ለምሳሌ፡- ኢዮአብ ወደ
ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረችው ያለ
ዓይነት ነው፤ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር
ያጥብ ዘንድ በጴጥሮስ ጀመረ፤ ጴጥሮስ ግን እኔ
ባንተ ልታጠብ አይገባኝም አለ፤ ጌታችንም መልሶ
‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን
ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ
የለህም›› (ዮሐ.፲፫፥፰)፡፡ ሌሎቹንም ሐዋርያት
አጠባቸው፤ አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳንም እግሩን
አጠበው፡፡ ጌታ አሳልፎ እንደሚሰጠው ሳያውቅ
ቀርቶ አልነበረም፤ ፍቅርን ሲያስተምረውና ለንስሐ
ጊዜ ሲሰጠው ነው እንጂ፤ እኛንም ለሚወደን ብቻ
ሳይሆን ለሚጠላን እንኳን በጎ ማድረግ እንደሚገባ
ሲያስተምረን ነው፡፡
ጌታችን ጾመና ጹሙ አለን፤ተጠመቀና ተጠመቁ
አለን፤ ጸለየና ጸልዩ፤ ሰገደናም ስገዱ አለን፤
የሐዋርያትንም እግር አጥቦ እናንተም እንዲህ
አድርጉ ብሎ መምህረ ትሕትናነቱን ገለጠልን፡፡
ዛሬም ከፓትርያርኩ ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፤ካህናት
በየመአርጋቸው የምእመናኑን እግር በማጠብ
የጌታን የትሕትና ሥራ ያስቡታል፡፡
ለሐዋርያት ትሕትናን ሲያስተምራቸው ጌታችን
እግራቸውን እንደ አጠባቸው ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡
ከዚያም ዝ ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ ብሎ
ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው፤ ዛሬም የልጅነት
ጥምቀት የሚቀበሉ ምእመናን በዚያኑ ዕለት
ከክርስትና ቤት ወደ ቤተ መቅደስ ሔደው የጌታን
ክቡር ሥጋና ደም ይቀበላሉ፤ መሠረቱም ጌታችን
ለሐዋርያት ያደረገውን ተመርኩዞ ነው፡፡ ከፍ ከፍ
ሊል የሚወድ ራሱን ዝቅ ያድርግ ብሎም
አስተምሯቸዋል፤ አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ
ምሥጢር ጌታ ለጴጥሮስ ‹‹እኔ እግርህን
ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም››
ያለውን ሲተረጉሙ ‹‹እኔ በአገልጋይ አምሳል
እግርህ ካላጠብኩህ አንተም ከበታችህ ላሉት
ራስህን ዝቅ ለማድረግ አትችልም፤ ራስህን ዝቅ
ዝቅ ካላደረግህ አለቃ ልትሆን አትችልም››
ለማለት ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡ ጌታችን
ደግሞ አምላክ ፈጣሪ መምህር ሳለ ዝቅ ብሎ
እንዳጠባቸው እነርሱም ክህነታቸውንና
መምህርነታቸውን በትሕትና እንዲጀምሩ
ሲያስተምራቸው ነው፡፡
በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ምሽት፤ ጌታችን
ሕብስቱን ባርኮ ለዐሥራ ሦስት ፈትቶ ሰጣቸው፤
ዐሥራ ሦስተኛውን እርሱ የሚቀበለው ነውና ነገር
ግን የሚረባውና የሚጠቅመው አይደለም፤ ‹‹ዝ
ውእቱ ሥጋየ ዝ ውእቱ ደምየ›› ብሎ ሕብስቱን
ባርኮ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ ››
ወይኑንም ባርኮ ‹‹ይህ ደሜ ነው እንካችሁ
ጠጡ›› ብሎ ሰጣቸው፡፡አስራ ሦስት አድርጎ
መፈተቱ ሐዋርያትን እንዳይገርማቸው
(እንዳያስፈራቸው) ነው፤ እራሱም ጥዒሞ
አጥዐሞሙ/ቀምሶ አቀመሳቸው/ እንዲል አብነት
ለመሆን፤ አንድም ነገ በመልዕተ መስቀል አስራ
ሦስቱ ሕማማተ መስቀል እቀበላለሁ ሲል ነው፤
ጌታ ይህን ባያደርግ ኖሮ ዛሬ ካህኑ የጌታን ሥጋና
ደም ሳይቀበል አቀብሎ ብቻ በሄደ ነበርና ለእነርሱ
ለማስተማር ነው፡፡
ማዕዱንም እየበሉ ጌታችንም ‹‹እውነት እውነት
እላችኋለሁ! ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ
ይሰጠኛል›› አላቸው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፩)፡፡ ሐዋርያት
ሁሉ ደነገጡ! እርስ በርሳቸው ተያዩ፤‹‹እኔ እሆን?
እኔ እሆን?›› ተባባሉ፤ ጴጥሮስም ዮሐንስን ጠጋ
ብሎ ‹‹ማነው አሳልፎ የሚሰጠህ ብለህ ጌታን
ጠይቀው›› አለው፤ወንጌላዊው ዮሐንስም ጌታን
ጠጋ ብሎ ጠየቀው ጌታችንም ‹‹ከእኔ ጋር እጁን
ከወጪቱ የሚያገባ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል››
አለ፤ (ማቴ.፳፮፥፳፫/ሉቃ.፳፪፥፳፩)፡፡ ሐዋርያትም
‹‹ሁላችን ከወጪቱ የምንጠቅስ አይደለምን?››
ሲሉ ጌታችን ‹‹እኔ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው
ነው›› አላቸው፤ ያንጊዜ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ
ሰጠው፤ ስለዚህ ወንጌላውያኑ ይህን ታሪክ ይዘው
አንድ ሳለ በተለያየ አገላለጥ ገለጡልን፡፡
ይሁዳም እንደቸኮለ ሰው ይቅበዘበዝ
ነበር፤እርሱም ጌታን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጠው
በልቡ እያሰበ ነበር፡፡ ጌታም ወደ ይሁዳ ጠጋ
ብሎ ‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ! ልትሠራው የምትሻው
ሥራ ካለ ሒድ›› አለው፤ (ዮሐ.፲፫፥፳፯)፤
ይሁዳም ፈጥኖ ወጥቶ ወደ አይሁዳውያን ጌታን
አሳልፎ ሊሰጥ ዋጋ ሊነጋገር ሔደ፡፡
ከሦስተኛው ሰዓተ ሌሊት እስከ አምስተኛይቱ
ሰዓተ ሌሊት ድረስ
ለደቀ መዛሙርቱ ሲመክራቸው የመንፈስ
ቅዱስንም መምጣት አብዝቶ ሲነግራቸው፤
ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቀና፤ እርሱ ከአባቱ ጋር
አንድ እንደሆነም ነገራቸው፤ ለብቻው ፈቀቅ ብሎ
ወዙ እንደ ደም እስኪፈስ እየሰገደ ጸለየ፤ወደ ደቀ
መዛሙርቱ ተመለሰ፤ ተኝተው አገኛቸው፤
ቀሰቀሳቸው፤ ጴጥሮስንም አንድ ሰዓት ያህል እንኳን
ከእኔ ጋር መትጋት አቃታችሁን? ወደ ፈተና
እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ አለው! (ሉቃ.፳፪፥፲፬-
፵፮)፡፡
የጌታችን በአይሁድ መያዝ (ስድስተኛው ሰዓተ
ሌሊት)
ጌታችንም ከአብ ጋር ስላለው አንድነትና ክብር
ለሐዋርያት ካስተማራቸው በኋላ ‹‹ኢየሱስም
ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ
ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤
በዚያም ገባ›› (ዮሐ.፲፰፥፩)፡፡ወንዙን ተሻግሮ
ያለውን ዛፍ አልፎ ወዳለው ዱር ገባ፡፡ ይሁዳም
Forwarded from Online
ይህችን ስፍራ ቀድሞ ጌታ ይመጣባት ስለነበር
ያውቃት ነበርና ጭፍሮችንና የካህናት አለቆችን
ፈሪሳውያን ሌሎች ፋና ጋሻ ጦርም የያዙትን
አስከትሎ መጣ፡፡ ጌታችንም ‹‹ተነሡ እንሂድ! እነሆ
አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል›› አላቸው ወደ እነርሱ
መጥቶ ቀረበ፤ ይሁዳም ወደርሱ ቀርቦ፤
‹‹መምህር ሆይ ቸር ውለሃል፤ ሰላም ላንተ
ይሁን›› ብሎ ሳመው፤ ይህ መሳም ለአይሁድ
ጥቆማ ወይም ምልክት ነበር፡፡ ምክንያቱም የጌታ
መልክና የወንጌላዊው የዮሐንስ መልክ
ይመሳሰልባቸው ነበርና ሲለይላቸው ነው፤
ጌታችንም ‹‹በስኢምኑ ታገብኦ ለወልደ ዕጓለ
እመሕያው፤ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ
ትሰጠዋለህን?›› አለው (ሉቃ.፳፪፥፵፰)፡፡
ይሁዳም ከጭፍሮቹ ጋር መጣ፤ ጌታ ኢየሱስንም
ከበውት ወደ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቃ ቀያፋ
ወዳለበት ወሰዱት፤ ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ
ይከተለው ነበር፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ
ከአንደኛው ቅጥር ግቢ ገብቶ ተቀመጠ፡፡
አይሁድም በክርስቶስ ላይ ሁለት የሐሰት
ምስክሮችን አመጡ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ
አፍርሱት፤ በሦስተኛው ቀን እሰራዋለሁ›› ብሏል
ብለው ከሰሱት፤ ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ ‹‹እንዲህ
ሲያጣሉህ አትሰማምን›› አለው፡፡ ጌታችን ግን
ምንም አልመለሰለትም፤ሊቀ ካህናቱም ‹‹ክርስቶስ
ተብሎ የተነገረልህ የእግዚብሔር ልጅ አንተ
እንደሆንክ ንገረኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ
አልክ›› አለው፤ ያን ጌዜ ሊቀ ካህናቱ ተናዶ
ልብሱን ቀደደው፤ራሱንም በብረት ዘንግ መቱት፤
የስቃዩ ጅማሬ ይህን ጊዜ ነበር፡፡
የክርስቶስን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር
ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ
ጋር ለመተባበር ያብቃን!!!
(ምንጭ፡- ማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር፣ መጋቤ
ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ)
ያውቃት ነበርና ጭፍሮችንና የካህናት አለቆችን
ፈሪሳውያን ሌሎች ፋና ጋሻ ጦርም የያዙትን
አስከትሎ መጣ፡፡ ጌታችንም ‹‹ተነሡ እንሂድ! እነሆ
አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል›› አላቸው ወደ እነርሱ
መጥቶ ቀረበ፤ ይሁዳም ወደርሱ ቀርቦ፤
‹‹መምህር ሆይ ቸር ውለሃል፤ ሰላም ላንተ
ይሁን›› ብሎ ሳመው፤ ይህ መሳም ለአይሁድ
ጥቆማ ወይም ምልክት ነበር፡፡ ምክንያቱም የጌታ
መልክና የወንጌላዊው የዮሐንስ መልክ
ይመሳሰልባቸው ነበርና ሲለይላቸው ነው፤
ጌታችንም ‹‹በስኢምኑ ታገብኦ ለወልደ ዕጓለ
እመሕያው፤ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ
ትሰጠዋለህን?›› አለው (ሉቃ.፳፪፥፵፰)፡፡
ይሁዳም ከጭፍሮቹ ጋር መጣ፤ ጌታ ኢየሱስንም
ከበውት ወደ ሽማግሌዎችና የካህናት አለቃ ቀያፋ
ወዳለበት ወሰዱት፤ ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ
ይከተለው ነበር፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ
ከአንደኛው ቅጥር ግቢ ገብቶ ተቀመጠ፡፡
አይሁድም በክርስቶስ ላይ ሁለት የሐሰት
ምስክሮችን አመጡ ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ
አፍርሱት፤ በሦስተኛው ቀን እሰራዋለሁ›› ብሏል
ብለው ከሰሱት፤ ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ ‹‹እንዲህ
ሲያጣሉህ አትሰማምን›› አለው፡፡ ጌታችን ግን
ምንም አልመለሰለትም፤ሊቀ ካህናቱም ‹‹ክርስቶስ
ተብሎ የተነገረልህ የእግዚብሔር ልጅ አንተ
እንደሆንክ ንገረኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ
አልክ›› አለው፤ ያን ጌዜ ሊቀ ካህናቱ ተናዶ
ልብሱን ቀደደው፤ራሱንም በብረት ዘንግ መቱት፤
የስቃዩ ጅማሬ ይህን ጊዜ ነበር፡፡
የክርስቶስን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር
ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ
ጋር ለመተባበር ያብቃን!!!
(ምንጭ፡- ማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር፣ መጋቤ
ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ)
Forwarded from ✞ገድለ ቅዱሳን✞
+++ የይሁዳ እግሮች +++
ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመሥጠት ከአይሁድ ጋር የተስማማው ረቡዕ ዕለት ነበር፡፡ ይህን ስምምነት አድርጎ እንደጨረሰ ወደ ጌታና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ማኅበር ተመለሰ፡፡ ከረቡዕ ጀምሮ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስም ከጌታ ፊት ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ አሳለፈ፡፡ ይህ በትክክል ይሁዳ ምን ዓይነት አስመሳይና ክፉ ሰው እንደነበረ ያሳያል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁኔታዎች አስፈርተውት ጌታውን ለሦስተኛ ጊዜ አላውቀውም ብሎ ከካደ በኋላ ጌታችን ለአንድ አፍታ ቀና ብሎ ስለተመለከተው ብቻ የጌታውን ፊት በድፍረት ለመመልከት አቅም አጥቶ መራራ ልቅሶን እያለቀሰ ከአጥር ውጪ ወጥቶ ነበር፡፡ ይሁዳ ግን አሳልፎ ሊሠጠው ከተስማማባት ሰዓት ጀምሮ ድምፁን አጥፍቶ ከጌታችን ጋር እንደ ወትሮው አብሮ ሲቀመጥ አንድ ጊዜ እንኳን አልተሸማቀቀም፡፡
ልብ አድርጉ! በራሱ ሃሳብ አመንጪነት ፣ ራሱ ወደ አይሁድ ሸንጎ ሔዶ ፣ ብር ለመቀበል ተስፋ ተቀብሎ ከመጣ በኋላም የጌታችንን ዓይኑን እያየ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› ብሎ ለመጠየቅም ድፍረት ነበረው! በዚያች ሰዓት እንደ ዳታንና አቤሮን መሬት ተሰንጥቃ ስላልዋጠችው ፣ ምላሱ ከጉሮሮው ጋር ስላልተጣበቀ ፣ በድፍረትና በመናቅ በእውነተኛው ጌታ ላይ የተናገሩት የሽንገላ ከንፈሮቹ ዲዳ ባለመሆናቸው የፈጣሪን ትዕግሥቱን እናደንቃለን፡፡ ሁሉን የሚያውቀው ጌታ ግን ይሁዳ ሊሸነግለው መሞከሩን ቢያውቅም ‹አንተ አስመሳይ!› ብሎ አላዋረደውም፡፡
የእግዚአብሔር ነቢይ ኤልሳዕ ሎሌው ግያዝ የማይገባውን ገንዘብ ከለምጹ ከነጻው ከሶርያዊው ንዕማን ተቀብሎ ቤቱ ወስዶ ከሸሸገ በኋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ከፊቱ መጥቶ ሲቆም ‹ግያዝ ሆይ ከወዴት መጣህ?› ብሎ ጠይቆት ነበረ፡፡ ግያዝም ‹‹እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሔድሁም›› አለ፡፡ ኤልሳዕም ፡- ‹‹ልቤ ከአንተ ጋር አልሔደምን?›› ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ይጣበቃል ብሎ ረግሞት እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ወጣ፡፡ (፪ነገሥ. ፭፥፳‐፳፯)
ሐዋርያው ጴጥሮስም ሐናንያና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስት ገንዘባቸውን ከቤታቸው ሸሽገው መንፈስ ቅዱስን ሊያታልሉና በማስመሰል በፊቱ ሊቆሙ ሲሞክሩ ‹እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሻችሁም› ብሎ በካህን ቃሉ ተናግሮ ተቀሥፈው እንዲሞቱ አድርጓቸዋል፡፡ (ሐዋ. ፭፥፩-፲)
የነቢያትና የሐዋርያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኤልሳዕና ከጴጥሮስ በላይ የልብን የሚያውቅና መቅጣት የሚቻለው ነው፡፡ ሆኖም ከአይሁድ ጋር ሊሸጠው ተዋውሎ የመጣው ይሁዳ ዓይኑን በጨው አጥቦ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› እያለ ሲዘብትበት በታላቅ ትዕግሥት ዝም አለው፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን ሊያታልሉ የሞከሩ ሰዎች እንዲህ ከተቀጡ የነቢያትን አምላክ ሊያታልል የሞከረ ‹‹…እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?›› (ዕብ. ፲፥፳፱)
ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬) በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ሥራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉሥ ግን በትሕትና እንደ ሎሌ ሆነ፡፡ (፩ሳሙ. ፳፭፥፵፩)
ጌታችን አጎንብሶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግሥት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው፡፡ ‹‹ወኀፀበ እግረ ይሁዳ አስቆሮታዊ ዘያገብኦ›› ‹‹የሚያስይዘውን የአስቆሮቱ የይሁዳንም እግር አጠበ›› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ)
ከአንድ ቀን በፊት ክፋትን ለማሴር ወደ አይሁድ ካህናት ግቢ የሮጡትን የይሁዳን እግሮች ጌታችን አጎንብሶ አጠባቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሊያስይዘው ወደ አይሁድ የሚሮጥባቸውን እግሮች ፣ የሚይዙትን ወታደሮች እየመራ ወደ እርሱ የሚመለስባቸውን እግሮች አጠበለት፡፡ ምንም እንኳን በነገው ዕለት እግሮቹን እንዲቸነከር አሳልፎ የሠጠው መሆኑን ቢያውቅም ሰውን ወዳጁ ክርስቶስ ግን የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመጨረሻ ጊዜ እግሩን አጥቦ ተሰናበተው፡፡
እንደ ነቢዩ ዳዊት ‹‹አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ!›› ከማለት በቀር በምን አንደበት ልንናገር እንችላለን? (መዝ. ፴፮፥፯) ‹‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ያለን ጌታ አሳልፎ የሚሠጠውን የይሁዳን እግር ሲያጥብ ከማየትስ በላይ በቂም በቀል ለሚቆስለው ልባችን ምን መድኃኒት ይኖር ይሆን?
ይሁዳ ሆይ እስቲ አንድ ጊዜ ንገረን ፤ ጌታ አጎንብሶ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት አስቻለህ? ‹እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ› የሚሰገድለት አምላክ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት ትንሽ እንኳን አልተሰማህም? አንተ እግሩን ልታጥበው እንኳን የማይገባህ ፈጣሪ እግርህን ሲያጥብህ እያየህ እንዴት ልብህ ደነደነ? መጥምቁ ዮሐንስ ‹የጫማውን ጠፍር ልፈታ አይገባኝም› ያለው ጌታ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት ልብህ በጸጸት አልተሰበረም? ረቡዕ አሳልፈህ ልትሠጠው ተስማምተህ መጥተህ ሐሙስ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት አልጨነቀህም? ከአይሁድ ጋር የተስማማኸው ነገር ‹ይቅርብኝ› ለማለት ጌታችን ከእግርህ በታች ዝቅ ብሎ ካጠበህ ሰዓት የተሻለ ማሰቢያ ጊዜ ከየት ይገኛል? በፍቅሩ ውስጥ ክፋትህ ፣ በትሕትናው ውስጥ ትዕቢትህ እንዴት አልታየህም? እንዴትስ እግሮችህን ሠጥተህ ያለ አሳብ ታጠብህ?
ቅዱስ ጴጥሮስ እንኳን ‹‹ጌታ ሆይ አንተ [እንዴት] የእኔን እግር ታጥባለህ?› ብሎ ተጨንቆ ጠይቆ ነበር፡፡ ‹የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም› ብሎ ተከላክሎም ነበር፡፡ ልበ ደንዳናው ይሁዳ ግን ዝም ብሎ እግሮቹን ሠጠ፡፡ የከዳውን ጌታ የቁልቁል እየተመለከተ ለአፍታ እንኳን ልቡ አልተመለሰም፡፡ ሐዋርያት ጌታ ባጠበው እግራቸው ለጊዜው ፈርተው ቢሮጡም በኋላ ግን በጸጸት ተመለሱበት፡፡ በአምላክ እጅ በታጠበ እግራቸው ያለመሰልቸት ዓለምን ዞረው ወንጌሉን አስተምረው እስከሞት ድረስ ታመኑ፡፡ በእግራቸውም እንደ ስማቸው ሐዋርያት (ተጓዦች) ሆኑበት፡፡ ይሁዳ ግን በአምላክ እጅ በታጠበው እግሩ ወደ አይሁድ ገስግሶ ጌታ ለሚያንገላታው ጦር መንገድ እየመራበት ተመለሰ፡፡
‹‹ኦ እግዚኦ ዘኢትደፈር ይሁዳ ደፈረከ››
‹‹አቤቱ የማትደፈር አንተን ደፋር ይሁዳ ደፈረህ!››
(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፩፥፳፩)
"ሕማማት" ከተሰኘው የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተወሰደ ምንባብ,
(ሕማማት ባለ ስድስት ምዕራፍ፣ ባለ 528 ገጽ መጽሐፍ ነው)

💛 🍒 💛
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
የያዕቆብና የድንግል ማርያም ኃዘን ሲነጻጸር
💛
የአበው አለቃ የያዕቆብ ለቅሶ ዛሬ ታደሰች አለ፡፡ ወዳጆቼ ሆይ ፦ ድንግል ማርያም በድንግልና ስለፀነሰችው ልጇ ለምን አታለቅስም? ድንግል ማርያም ስለሳመችው ልጇ ለምን አታለቅስም ፤ ድንግል ማርያም አምላካዊ በሆነ አፉ የድንግልና ጡቷን (ወተቷን) ስለሰጠችው ልጇ ለምን አታለቅስም?
ድንግል ማርያም በቤተልሔም በረት ስለተወለደው ልጇ ለምን አታለቅስም? ዘጠኝ ወር በማሕፀኗ ስለተሸከመችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም? ራሄል ስንኳ ፈጽማ ስላልሳመቻቸው ልጆቿ አለቀሰች፡፡ ድንግል ማርያም ከቦታ ወደ ቦታ ይዛው ስለተሰደደች ልጇ ለምን አታለቅስ?
እንደ ሰው ሁሉ በእቅፏ ስለታቀፈችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ? መቃብራቸውን ፈጽማ ስላላየችው ልጆቿ ራሄል ለምን አለቀሰች?፡፡ ድንግል ማርያም አንድ በሆነው ልጇ መቃብር በር ለምን አታለቅስ? ያማረ ጽሕም የነበረው ሽማግሌ ለቅሶ ዛሬ በድንግል ዘንድ ታደሰ፡፡
ያዕቆብ ወንድሞቹ ሲያስሩት ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም፡፡ ድንግል ግን ልጇን በመስቀል ተቸንክሮ ተመለከተችው፡፡ ያዕቆብ በእርሱ ላይ ያለቅስ ዘንድ በጥልቅ ጉድጓድ እያለ አላየውም፡፡ ድንግል ግን በአይሁድ ጉባኤ መካከል ተሰቅሎ ተመለከተችው፡፡
ያዕቆብ ዮሴፍን ወንድሞቹ ሲያራቁቱት አላየም ፤ ድንግል ግን የሚመክራቸው ባጡ በአይሁድ ጉባኤ መካከል ራቁት ሆኖ ልጇን ተመለከተችው፡፡ ያዕቆብ ልብሱን በሌላ ደም ነክረው ዮሴፍን ወንድሞቹ በሃያ ብር ሲሸጡት አላየም፡፡ በእርሱ ላይም አለቀሰ ፤ ልብሱንም ቀደደ፡፡ አምላካዊ ደም ግን ማርያም ስለ እርሱ በምታለቅስበት ዐለት ላይ ፈሰሰ፡፡ ድንግል ያየችውን ሌላውን ልብስም ለልጇ ዛሬ አለበሱት፡፡ ልብሶቹንም ለየራሳቸው ተካፈሉ፡፡
የዮሴፍ ወንድምቹስ በሸጡት ጊዜ ተጸጸቱ፡፡ ደቂቀ እስራኤል ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም፡፡ የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሠቱ ፤ አይሁድ ግን ጌታቸው ከመቃብር በተነሣ ጊዜ አልተደሰቱም፡፡ ድንግል ሆይ በልጅሽ መቃብር ላይ ያለቀስሽው ለቅሶ በእውነት ጥዑም ነው ፤ በመላእክት ዘንድም ድምፅሽ ያማረ ነው፡፡
💛
(ርቱዓ ሃይማኖት)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

+ ዛሬ ሚያዝያ18 ቀን።
+ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለዐበይት በዓል ለአንዱ ለሰሞነ ሕማማት አምስተኛ ቀን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
+ "ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ተጸፋእከ በውስተ ዐውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ ወተዐገሰ ምራቀ ርኩሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ። ትርጉም፦ ለቤተክርስቲያን ብለህ ልትቀድሳት በደምህ በአደባባይ በጥፊ ተመታህ ንጹሕ ክርስቶስ በአዳም ጥፋት ልትወቀስ በከንቱ ልትከሰስ አመላለሱህ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ ሁሉን ቻይ ሳለህ ምንም ማድረግ ሳይሳንህ በአይሁድ እጅ ተገረፍህ ወዮ ወሰን ለሌላት ትዕግስት ስለኛ ብለህ መከራ ተቀበልህ ምንም በደል ሳይኖርብህአምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉህ። ቅዱስ ያሬድ።
+ + +
+ "ሰላም ለቅንዋተ እደዊሁ ወእገሪሁ። ሰላም ለሕማሙ ወሰላም ለሞቱ። ሰላም ለገቦሁ ቅድስት ዘኅውኅዘ እምኔሃ ደም ወማይ ፅሙር። አንቅዕተ ብዕል ወክብር። ሰላም ለግንዘቱ በዘጠብለልዎ፤ሰላም ለመቃብሩ ኀበ ቀበርዎ"። ትርጉም፦ ለእጆቹና ለእግሮቹ ችንካሮች ሰላምታ ይገባል።ለሕማሙ ሰላምታ ይገባል፤ለሞቱም ሰላምታ ይገባል።የሀብት(የብልጥግና)የክብር ምንጭች የኾኑ ደምና ውሃ አንድነት(ተባብሮ)ከርሷ የፈሰሰ ለኾነች ለቅድስት ጐኑ ሰላምታ ይገባል።ለሚጠቀልሉት ገንዘብ ለኾነ ለግንዘቱ ሰላምታ ይገባል፤በቀበሩት ዘንድ ላለ መቃብሩ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ ዕለተ ዓርብ
+ የስቅለት ቀን ስቅለት ማለት መስቀል፣ መሰቀል፣ አሰቃቀል ማለት ነው፡፡ መስቀል በቁሙ መስቀያ፣ መመዘኛ፣ መሰቀያ፣ መንጠልጠያ፣ ለሞት የሚያበቃ መከራ በማር 8፥34 "ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስለ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽልአ ለነፍሱ ወያጥብዕ ወይፁር መስቀል ሞቱ ወይትልወኒ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ሕዝቡን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክኖም የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" ይላል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ. 1፤17 ላይ ወኢኮነ በጥበበ ነገር ከመ ኢንስዐር መስቀሎ ለክርስቶስ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም ይላል፡፡ ጌታችን በተሰቀለ ዕለት ከሰድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፡፡ ፀሐይ ጨለመ፣ እነሆም የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተውም ከነበሩት ቅዱሳን ብዙዎች ተነሱ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ለብዙዎች ታዩ፡፡ ማቴ. 27፤51 ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም በመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቀለቱ መታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ ከርቤ እየታጠነ ስቅለቱ የሚመለከቱ ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድ ይዋላል፡፡ የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ረግጦ ከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩን ለማስታወስም መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁር ልብስ ይሸፈናሉ፡፡ ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞር የሚያሰማው የቃጭል ድምፅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅሶ አንድም ዋይ ዋይ እያሉ የተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌ ነው፡፡ ሉቃ. 23፤31 በዕለተ ዓርብ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ አንቀጸ ገነት ተከፈተልን፣ ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰችልን።
+ የዕለቱ ስንክሳር።
+ በዚች ቀን የቅዱስ ሱስንዮስ አገልጋይ ቅዱስ አውሳቢዮስ በሰማዕትነት ዐረፈ። ከዲዮቅልጥያኖስ ቅዱስ ሱስንዮስን በሚያሠቃየው ጊዜ ንጉሥ ሆይ "ለሱስንዮስ አውሳብዮስ የሚባል አገልጋይ አለው እርሱም በፍጹም ልቡ እንደ ጌታው ክርስቶስን ያመልከዋል የአንተን አማልክት አያመልክም" አሉት "አምጡት" አለ። ወደርሱም በቀረበ ጊዜ ስለ ሃይማኖቱ ጠየቀው እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ንጉሡም ብዙ አባበለው አማልክቶቹን ማምለክ በመተዉም ገሠጸው ቅዱሱም የእውነተኛ አምላክ የእግዚአብሔር አምልኮ በመተዉ ንጉሡን መልሶ ገሠጸው። ስለዚህም ንጉሥ ቊጣን ጨምረ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ይህም ቅዱስ ከጌታው ከሱስንዮስ ቀድሞ የሰማዕትነትነት አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
+ በዚች ዕለት የአባ ብሶይ ወንድም አባ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ዐረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ሲድራቅ የእናቱ ስም ማርያም ነው። ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ ከርሳ የምትባል የእናቱ እኅት ወስዳ ከልጅዋ ጋራ አሳደገችው። ሰባት ዓመትም በሆናቸው ጊዜ ወደ መምህር ወሰደጀቻቸውና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሕጉንም ተማሩ በጾም በጸሎትም ሲጋደሉ ኖሩ። የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ተገለጠላቸው ስለ ክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምስክር እንዲሆኑ ነገራቸው።
+ ከጥቂት ወራትም በኋላ ሰይጣን ከዲዮቅልጥያኖስን አስቶት ለጣዖት በሰገደ ጊዜ እሊህን ቅዱሳን ክርስቲያኖች እንደሆኑ ነገር ሠሩባቸው። የእንዴናው ገዥ አርያኖስም ወደርሱ አስቀርቦ ለጣዖት እንዲሰግዱ ግድ አላቸው እምቢ በአሉትም ጊዜ ደማቸው እስኪፈስ ከባላ ላይ ሰቅለው እንዲገርፋቸው አዘዘ። ከጾምና ከስግደት የተነሣ ሥጋው ስለደከመ የሥቃዩ ሕማም ለአባ ጴጥሮስ ታወቀው ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከሕማሙ ፈወሰው። አርያኖስም አይቶ አባ ጴጥሮስ ወደ ምሥራቅ አገር ወስደው በዚያ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ።
+ አባ ብሶይም በእሥር ቤት እያለ መልአክ ነጥቆ ወደ ወንድሙ ወደ ጴጥሮስ አደረሰው። እርስበርሳቸውም ተቃቅፈው ተሳሳሙ በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም እንዲሰበስባቸው ወደ ጌታችን ጸለዩ እንሆ ወደ እርሳቸውም ከሰማይ ቃል መጣ። እንዲህ የሚል "ተጋዳዮች ሆይ በሰማያት በብዙ ጉባኤ መካከል ትኖራላችሁና ሰላም ይሁንላችሁ ሥጋችሁም በምድር አይለያይም"። ከዚህም በኋላ መልአክ አባ ብሶይን ወደ እሥር ቤት መለሰው። ጭፍሮችም ኃይል ድል አድራጊ አባ ጴጥሮስ ራሱን ቆረጡ ሥጋውንም በዕንጨት ላይ ሰቀሉ። አባ ብሶይም በጭልታ ይሰደው ዘንድ የእሥር ቤት ጠባቂውን ለመነው ሒዶም የአባ ጴጥሮስን ሥጋ ዋጀው በሽቱ አድርጎ ገንዞም በሥውር ቦታ ቀበረው። በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
+ በዚች ቀን በጠርሴስ አገር ውስጥ መከራ የተቀበሉ የከበሩ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ18 ስንክሳር።
+ መልካም የስቅለት በዓልና የስግደት ቀን ለሁላችንም ይሁንልን።