የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
1.35K subscribers
168 photos
2 files
39 links
የ ኢ/ኦ/ተዋህዶ/ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የጠበቁ የ አባቶች ምክር;ግጥም;ተከታታይ አምዶች;ልሳነ ግእዝ;ጥያቄናመልሶች የምናገኝበ ስለሆነ ቻናሉን ይቀላቀሉ። for any opinion @Abeln ይላኩ
"ይህች ቤተክርስቲያን
ክርስቶስን ከቶ አታውቀውም" በሉ
ግድ የለም ለቃሉ !
ግን ድምጽ ቀንሱ !
የጌታን መከራ ሕማሙን አስባ
ስግድት ላይ ናትና ልጆቿን ሰብስባ
ግድ የለም አንቋሿት
ግን አትረብሿት !!
Download Telegram
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን
🔔 🔔 🔔

የማንቂያ መልእክት ለምዕመናን !

🔔

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

" በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤"
(ፊልጵ.፩፥፳፰)

አፅራረ ቤተክርስቲያን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ምቹ በመሠላቸው ጊዜ ሁሉ የተለያዩ መከራዎችንና ግፎችን በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የተለያየ ዓላማና ግብ ያላቸው እኩያን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለውን አስተዳደራዊ ለውጥና በአንዳንድ አካባቢዎች ያለውን አለመረጋጋት እንደ ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር የዘመናት ምኞታቸው የሆነውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የማዳከምና ብሎም የማጥፋት ምኞታቸውን ለማሳካት የተለያዩ የጥፋት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት እንደመሆኑ በብዙ ወጀብና ማዕበል ውስጥ ሳትናወጽ ጸንታ ትኖራለች፡፡ በቅዱሳን በጻድቃንና በሰማዕታቱ ደምና አጥንት ታጥራ ፡ በቅዱሳኑ ጾምና ጸሎት ተከልላ ሁሉን ታልፋለች፡፡ በውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ጠላቶቿ መከራና ግፍ ቢያጸኑባትም የምትቀበለው መከራ የጽናቷ ምስጢር ሆኖላት ፣ የሰማዕታቱ ደም የክርስትናው ዘር ሆኖ ለበለጠው ሰማያዊ አክሊልና ለሰማዕትነት ክብር የተመረጡ ልጆቿ እየተጋደሉ ሁሉን እያሳለፈች የአምላኳን መምጣትና ለፍጻሜ መገለጥ እነሆ ትጠባበቃለች፡፡

በዚህም ወቅትም በስሙነ ህማማት ፣ በዕለተ ስቅለትና በበዓለ ትንሣኤው ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን የጥቃት ኢላማ ያደረጉ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ተልእኮ ተቀብለው ሰይጣናዊ ተግባር ለመፈጸም የተሰማሩ የሽብር ቡድኖች መኖራቸውን የደህንነት መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በቁጥጥር ሥርም የዋሉ የጥፋት ቡድኑ አባላት መኖራቸው ተገልጿል፡፡ ይህ ዓይነቱ የክፋት ተግባር ለቅድስት ቤተክርስቲያን አዲሷ ባይሆንም ከመቼውም ጊዜ በላይ ኦርቶዶክሳውያን በአንድነት የሚቆሙበት ፡ በጾም በጸሎት የሚተጉበት ጊዜ መሆኑን አባቶች እያሳወቁ ይገኛሉ፡፡ በቀጣይ የሚጠብቁን የቤት ሥራዎች ብዙ መሆናቸው እንዳለ ሆኖ አሁን ግን ፦

በእያንዳንዱ አጥቢያ የምንገኝ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ማህበራት ፣ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ፣ የአካባቢ ወጣቶች ፣ ምዕመናን ፣ እናቶችና አባቶች ፣ ወንዶችም ሴቶችም ሁሉም በንቃት በአንድ መንፈስና በአንድ ልብ ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ተግባራት እናከናውን

✞ በቅድስት ቤተክርስቲያንና በዙሪያ ገቧ ያሉትን እንቅስቃሴዎች በንቃት መከታተል ፣ የተለየ አጠራጣሪ ነገር ሲገጥም ለቤተክርስቲያን ፣ ለጸጥታና ለህግ አካላት ወዲያው ማሳወቅ

✞ ወደ ቅጽረ ቤተክርስቲያን ስንሄድ ለሥርዓተ አምልኮና ለሥግደት አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች (የጸሎት መጻሕፍት) ውጪ ሌላ ተጨማሪ እቃዎችን አለመያዝ

✞ የሰበካ ጉባኤ አባላትና የሰንበት ተማሪዎች ወደ ቅጽረ ቤተክርስቲያንም ሆነ ወደ ቤተመቅደስ ስንገባ (በሁሉም የቤተክርስቲያን መግቢያ በሮች) ለመፈተሽና ለማንኛው ጠቃሚ የሆነ ተግባር ሲጠይቁን መተባበርና በአንድነት መንፈስ መንቀሳቀስ

✞ ልብሰ ተክህኖን የለበሱ አባቶቻችንን ተመሳስለው ክፉዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሰበካ ጉባኤ አባላትና የሰንበት ተማሪዎች ከአባቶቻችን ካህናት ጋር በመናበብ መንቀሳቀስ

✞ ወደ ቅጽረ ቤተክርስቲያን ይልቁንም ወደ ቤተ መቅደስ የሚገቡ ንዋያተ ቅድሳትን ፡ መባዎችንና ማናቸውንም የታሸጉ ነገሮች በጥንቃቄ የሚያይና የሚፈትሽ አካል ማዘጋጀት ፣ ከዚህ አካል ጋር ተባብሮ መንቀሳቀስ

✞ በፍጹም መረጋጋትና ስክነት በሥርዓተ ጸሎቱና በሥርዓተ ሥግደቱ እንዲሁም በሁሉም ሥርዓቶች ላይ መሳተፍ፡፡ ግፊያና መገፋፋትን ማስወገድ፡፡

✞ በምሽትና በሌሊት መርሐግብሮች ላይ በንቃት ሆኖ በውስጥም በውጪም መከታተል፡፡

የቤተክርስቲያን አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ፡ ሀገራችን ኢትዮጵያን ፡ ህዝቧንም በምህረቱና በቸርነቱ ይጠብቅልን፡፡ ክፉውን ሁሉ ያርቅልን፡፡ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን፡፡
🔔
" እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።"
(መዝ.፳፥፯)

" የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ... የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና። "
(ት.ዘካር.፪፥፰)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
🔔
ይቆየን!

🔔 🔔 🔔
ቃም ጨለመ፤ ከዋክብትም በከበረ ስቅለቱ ጊዜ ለምእመናን እንዳያበሩ ብርሃናቸውን ነሡ፤ ጨረቃም በምልአቱ ሳለ አላበራም፤ ፀሓይ ብርሃኑን በነሣ ጊዜ ፍጡራን ኹሉ በጨለማ ተያዙ፤ የፈጠራቸው ፈጣሪያቸው እንደ ሌባ እንደ ወንበዴ በዕንጨት ላይ ተሰቅሎ እንዳያዩ ቀኑ ጨለመ፤ ባለሟሉ መልአክም ከሓድያንን ያጠፋቸው ዘንድ ሰይፉን በእጁ መዝዞ ይዞ ከመላእክት መኻከል ወጣ፤ የክርስቶስም ቸርነት በከለከለችው ጊዜ ያ መልአክ የቤተ መቅደሱን መጋረጃ በሰይፉ መታው ቀደደውም፤ ከላይ እስከ ታችም ወደ ኹለት አደረገው (ማቴ ፳፯፥፶፩፤ ማር ፲፭፥፴፰፤ ሉቃ ፳፫፥፵፭)።

መላእክትም ኹሉ በሰማይ ኹነው ርሱን አይተው በአንድነት ሲቈጡ የአብ ምሕረቱ፣ የወልድ ትዕግሥቱ፣ የመንፈስ ቅዱስ ቸርነቱ ከለከለቻቸው፤ ፀሓይ ብርሃኑን ነሣ፤ በጨለማ ተይዞ ሲድበሰበስ ዓለምንም ተወው፤ ይኽ ኹሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው ከመለየቱ አስቀድሞ ተደረገ) (ቅዱስ አትናቴዎስ)

☞ “እስመ ሶበ ተሰቅለ ክርስቶስ ጸልመ ሰማይ አሜሃ ወፀሓይኒ ሰወረ ብርሃኖ ወወርኅኒ ደመ ኮነ…” (ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ያን ጊዜ ሰማይ ጨለማ ኾነ፤ ፀሓይም ብርሃኑን ነሣ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ምድርም ተነዋወጠች ደንጊያውም ተከፈለ፤ መቃብራትም ተከፈቱ፤ ስለዚኽም ለፍጡራን ከፈጣሪያቸው ጋር ሊታመሙ ተገባቸው (ማቴ ፳፯፥፵፭-፶፩) (ቅዱስ ሱኑትዩ)

☞ “ፀሓይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወከዋክብት ወድቁ ፍጡነ ከመ ኢይርአዩ ዕርቃኖ ለዘአልበሶሙ ብርሃነ” (ፀሓይ ጨለመ፤ ጨረቃም ደም ኾነ፤ ከዋክብትም ፈጥነው ወደቁ፤ ብርሃንን ያጐናጸፋቸውን የጌታን ዕርቃን እንዳያሳዩ) (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)

ሊቁ አባ ጊዮርጊስም ምስጢሩን በመጠቅለል በሕማማት ሰላምታው ላይም፡-
“ፀሓይ ብሩህ አሜሃ ጊዜ ቀትር ጸልመ
ወወርኅኒ ጽዱል ተመሰለ ደመ
ትንቢት ከመ ቀደመ፤ ስብሐት ለከ”
(ብሩህ የኾነ ፀሓይ ያን ጊዜ በቀትር (በስድስት ሰዓት) ጨለመ፤ ጽዱል የኾነ ጨረቃም ደምን መሰለ፤ አስቀድሞ ትንቢት እንደተነገረ፤ ጌታ ሆይ ምስጋና ይገባኻል) በማለት ከትንቢተ ነቢያት በመነሣት በዚኽ በስድስት ሰዓት ምስጋናው ላይ በሰዓቱ ከተከናወነው ምስጢር በመነሣት አስተምሯል፡፡

በመስቀል የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና በሰማይ ከላይ የተጠቀሱት ተአምራት ሲደረጉ ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር ደግሞ አራት ተአምራት ማለት የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀደደ፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯፥፵፭፤ ፳፯፥፶፩፤ ፳፯፥፶፪-፶፫)፡፡

አንድያ ልጇን በመስቀል ተሰቅሎ አካሉ ደም ለብሶ ስታየው ኹሉ ሲሸሽ በታማኝነት ቀራንዮ ድረስ ከተገኘው ከሚወድደው ደቀ መዝሙር ከዮሐንስ ጋር መሪር ልቅሶን በምታለቅስበት ጊዜ ዮሐንስ ጌታን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ኹሉም ከቀራንዮ ሲሸሽ ርሱ ግን ሳይሸሽ በመቅረቱ ጌታም እንዲኽ ለሚወድደው ለዮሐንስ ፍቅሩን ሊገልጽለት ከስጦታ ኹሉ የላቀች ስጦታው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን “እናትኽ እነኋት” በማለት ሲሰጠው፤ እናቱንም “እነሆ ልጅሽ” በማለት ዐደራ ሰጥቷታል፡፡

ይኽ የአደራ ቃል ሊፈጸም ጌታችን ካረገ በኋላ ዐሥራ ዐምስት ዓመት በዮሐንስ ቤት ኑራለች፤ በመኾኑም ዮሐንስን በሃይማኖት በምግባር ለምንመስል ለእኛ ለክርስትያኖች ያደራ እናታችን ያደራ ልጆቿ ነንና በልቡናችን ቤት ዘወትር ከብራ ትኖራለች (ዮሐ ፲፱፥፳፮-፳፯)፡፨
የመድኀኔ ዓለም ይቅርታ ከኹላችን ጋር ይኹን፨
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ዐርብ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ እንዲህ አለ ‹‹አውቀውስ ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት" 1ኛ ቆሮ 1፥18
ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። +++

            + ዛሬ ሚያዝያ18 ቀን።
+ እንኳን ለሰሞነ ሕማማት ለመጨረሻ ቀን ለቀዳም  ሥዑር በሰላም አደረሰን።

                + ቅዳሜ

+ በዚች ቀን አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃዶ፤ በመስቀሉ ሰላም አደረገ ትንሣኤውን ገለጠ" ቅዱስ ያሬድ። እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት ወይም መገለጫ የሆነ ልምላሜ ያለውን ቆጽለ ሆሣዕና ወይም ቄጤማ ግጫ ይዘን የምሥራች እንባባላለን፡፡ ኤፌ. 2፤14-15 "ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናግሮሙ፣ ያለ ምሳሌ አልተናገረምና እንዳለ" ማቴ 13፤34-35 በኖኅ ጊዜም ርግብ "ሐጸ ማየ አይኅ፣ ነትገ ማየ አይኅ፣ የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ" እያለች ቈጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ለኖኅ አብስራዋለች፡፡ ዘፍ. 8፤8-11
ርግብ የካህናት፣ ኖኅ የምእመናን፣ ኖኅ እጁን ዘርግቶ ርግብን እንደተቀበላት ካህናትም በየመንደሩ እየዞሩ ክርስቶስ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ በማለት ቄጤማ ሲያድሉ ምእመናንም እጃቸውን ዘርግተው መቀበላቸው የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢገኝ የወይራ ልምላሜ ቢታጣ ግጫን እየታደልን የምሥራች መባባላችን ነፍሳት ከሲኦል ለመውጣቸው መታሰቢያ ነው፡፡ ይህን ቈጽለ ልምላሜ ይዞ ተድላ፣ ደስታ መግለጽ ከጥንት ጀምሮ ሲያያዝ የመጣ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ለዚህ በመጀመሪያዪቱ ቀን ከበጎ እንጨት ፍሬን የሰሌንና የተምር ዛፍ ልምላሜ ይዛችሁ በየዓመቱ ሰባት ቀን ተድላ፣ ደስታ ታደርጋላችሁ ብሏል፡፡ ዘሌ. 23፤40-44

               + አክፍሎት

+ አክፍሎት ማለት ማካፈል፣ ማጠፍ፣ መደረብ፣ ሁለቱን ቀን አንድ አድርጎ መጾም፣ ጌታ ከተያዘበት እስከተነሣበት ድረስ ይህ ሥርዓት የመጣው በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት  እመቤታችን፣ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ትንሣኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሣኤ በመቆየታቸው ምክንያት ነው፡፡ በሀገራችን ብዙ ሰዎች ሐሙስ ማታ የቀመሱ እሑድ የትንሣኤ ዕለት ብቻ እህልና ውኃ የሚቀምሱት፤ ያልተቻላቸው ግን ዓርብ ማታ የቀመሱ እስከ ትንሣኤ ይሰነብታሉ፡፡ የሁለት ቀን ማክፈሉ እንኳ ቢከብድ ቅዳሜን ማክፈል ሥርዓት ነው፡፡ ቅዳሴው በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ በልቶ ማስቀደስና መቁረብ እንዳይሆን፡፡

                +የዕለቱ ስንክሳር።

+ በዚች ቀን የአርማንያ ሰው የፋርስ ኤጲስቆጶስ የከበረ ስምዖን በሰማዕትነት ዐረፈ ከእርሱም ጋራ መቶ ሃምሳ ሰማዕታት።

 + ይህም ቅዱስ ትከሻ ነቃይ የተባለ የሐርመዝ ልጅ ሳቦር ግዛት ውስጥ ይኖራል ይህም ሳቦር ሌላውን ንጉሥ ድል በሚያደርግ ጊዜ አሥሮ ትክሻውን ይመዝዘዋልና ትከሻ ነቃይ ተባለ። ይህም ከሀዲ ለጣዖት እንዲሰግዱ እያስገደደ ምዕመናንን በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃያቸው።

 + ይህም የከበረ አባ ስምዖን ለንጉሥ ሳቦር መልእክት ጽፎ ላከለት እንዲህ የሚል "የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃቸው ከሰው ተገዢነት ድነዋል የክብር ባለቤት የክርስቶስ ተገዥ ናቸውና። ስለዚህ ተገዥ መሆን ከተሠራው ሕግ አብዝቶ መገበርም አይገባቸውም። የሕያው እግዚአብሔርን ሕግ ለለወጡ ከሀድያን አይገዙም። ስለ እርሳቸው ደሙን በአፈሰሰ በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም እንዲሞቱ እነርሱ ይመርጣሉ"። ንጉሥ ሳቦርም መልእክት በአነበበ ጊዜ በዚህ አባት ላይ እጅግ ተቆጣ በሁለት ሰንሰለትም አሥሮ በእሥር ቤት ጣለው በዚያም ሃይማኖታቸውን ክደው ሰማይን ያመለኩ እነርሱም በሌላ የታሠሩ ብዙ እሥረኞችን አገኘ። ይህ ቅዱስም ገሠጻቸው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው መሰገሩ ራሶቻቸውንም ቆረጡአቸውና የሕይወት አክሊል ተቀበሉ።

 + ከዚህም በኋላ ይህን አባት ወደ ምስክርነት ሸንጎ አቀረቡት ከእርሱም ጋራ መቶ ሃምሳ ሰዎች አሉ እነርሱም አንገታቸውን እስከ ቆረጡአቸውና አክሊል እስከ ተቀበሉ ድረስ ያጽናናቸው ነበር። ከእርሳቸውም አንዱ ሰይፍን ከመፍራት የተነሣ ደንግጦ ሃይማኖቱን ሊክድ ወደደ በዚያ ከቆሙት አንዱ "አትደንግጥ የሰይፍ በትር ዓይንህን ከሸፈንክ ምንም አይደለም ጽና። ከሰማዕታት ጋራ ተቆጥረህ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ጋራ ለዘላለም ነግሠህ ትኖራለህ" ብሎ አጽናናው። እንዲሁም አደረገ የሕይወት አክሊልንም ተቀበለ። ስሙ ባሴቅ የተባለ ያንን ያጥናናውን ሰው ከሰሱት ንጉሡም አስቀርቦ ምላሱን አስቆረጠው። ቆዳውንም አስገፈፈውና ነፍሱን አሳለፈ የድል አክሊልንም ተቀበለ።

 + ከዚህም በኋላም የከበረ ስምዖንን ወደ እርሱ አቅርቦ "ለአማልክት ስገድ ያለዚያ በጽኑ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። ቅዱስም ትእዛዙን አልሰማም ሥቃዩንም አልፈራም ያን ጊዜም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዝዞ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕታትን አክሊል ተቀበለ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ19 ስንክሳር።

                      + + +
+ የዕለቱ ምስባክ፦" አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ። ወተንሣእኩ እስመ እግዚአብሔር አንሥአኒ። ኢይፈርህ እምአእላፍ አሕዛብ መዝ3፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማቴ27፥62-ፍ.ም። መልካም በዓልና የአክፍሎት ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ስምዖን ዘአርማንያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት "*+

=>ቅዱስ ስምዖን የአርማንያ ሰው ቢሆንም ሰማዕትነትን
የተቀበለው በሃገረ ፋርስ (በአሁኗ ኢራን አካባቢ) ነው::
ፋርስ ከ1ኛው መቶ ክ/ዘ እስከ ተንባላት (መሐመዳውያን)
መነሳት (7ኛው መቶ ክ/ዘ) ድረስ ባለው ጊዜ ብዙ
ሰማዕታት ለክብር በቅተውባታል::

+ብዙዎቹ የዚያው (የፋርስ) ዜጐች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ
የተሰዉት ከሌላ ሃገር መጥተው ነው:: ፋርሳውያን
አብዝተው ፀሐይን ያመልኩ ነበርና ክርስቲያኖቹን
የሚያሰቃዩት ይህቺውን ፍጡር እያመለኩ እንዲንበረከኩ
ነበር::

+ቅዱስ ስምዖንም ከፋርስ ግዛቶች በአንዱ ኤዺስ
ቆዾስነትን (እረኝነትን) ተሹሞ ነበርና የመከራው ተሳታፊ
ሆኗል:: በጊዜው ክርስትና እንደ ዛሬው "ሠርግና ምላሽ"
አልነበረምና ቅዱስ ስምዖን (እረኛው) እና 150 የሚያህሉ
ልጆቹ (መንጋው) ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ሆነዋል::

+በእምነታቸው ጸንተው በመገኘታቸውም እንዲገደሉ
ተወስኖባቸው 151ዱም ተሰውተዋል::

=>አምላከ ሰማዕታት በጽናታቸው አጽንቶ ከበረከታቸው
ይክፈለን::

=>ሚያዝያ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት (አርማንያዊ)
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (የስምዖን ማሕበር)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ:
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
የትንሣኤ በዓል እና የፋሲካ በዓል አንድ ስላልሆኑ እሑድ ስለሚከበረው የጌታችን የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ በተለምዶ "እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ!" ይባላል። ይኽ ግን ስሕተት ነው። የትንሣኤ በዓል እና የፋሲካ በዓል ኹለቱ የተለያዩ በዓላት ናቸው።
ፋሲካ የሚባለው በአጭሩ የአይሁድ የቂጣ በዓል ነው። ሉቃ 22:1። ጌታችንም ይህን በዓል አክብሮታል:- "የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ" እንዲል ቅዱስ ወንጌል። ዮሐ 2:13።

በኦሪት ዘሌዋውያን 23:5 ላይ "በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።" እንዲሁም በኦሪት ዘኍልቍ 9:5 ላይ "በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።" ተብሎ እንደተጻፈው የአይሁድ የመጀመሪያው ወር ሚያዝያ ነው። ሚያዝያ 14 የአይሁድ ፋሲካ (ፍስሕ) ወይም ኒሳን ይባላል። አባቶቻችን በጉባኤ ወስነው በደነገጉልን መሠረት ፍስሕ (የአይሁድ ፋሲካ) ከዋለበት ቀን ቀጥሎ ያለው እሑድ "የጌታችን ትንሣኤ" ይሆናል። ይኽም በጉባኤ ኒቂያ የተወሰነ ሲሆንበመጽሐፈ ዲዲስቅልያ አንቀጽ 31 ላይ ተጽፎ የሚገኝ ነው። ፍስሕ ከዋለበት ቀን ቀጥሎ ያለው እሑድ "የጌታችን ትንሣኤ በዓል" ይሁን ተብሎ የተወሰነበትም ምክንያት:-
1ኛ. የአይሁድ ፋሲካ ለጌታችን ትንሣኤ ምሳሌ (ጥላ) ስለሆነ። ጥላው (ምሳሌው) መቅደም አለበት።
2ኛ. ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ በሥልጣኑ የተነሣው ከአይሁድ የፋሲካ በዓል በኃላ ነው።
3ኛ. ጌታችን የተነሣው እሑድ ስለሆነ ነው።

በአቡሻኸር የዘመን አቆጣጠር ስናየው የኹለቱ በዓላት ልዩነቱ የበለጠ ግልጽ ይሆንልናል። የትንሣኤ በዓል የሚውልበትን ቀን ቀንና ዕለት ለማወቅ በቅድሚያ በዓለ ፍስሕ የሚውልበትን ቀንና ዕለት ማወቁ ይጠቅማል። በዓለ መጥቅዕ በዋለ በ190ኛው ቀን በዓለ ፍስሕ (የአይሁድ ፋሲካ) ይውላል።
ይኽም (ፍስሕ=መጥቅዕ +190) ማለት ነው። ለምሳሌ በዚህ ዓመት በ2011 ዓ.ም መጥቅዕ 5 ነው። ፍስሕ 195 ይሆናል-በ30 ስንገድፈው ቀሪው 15 ነው። የፍስሕ ኢይወርድና ኢይዐርግ (መጋቢት 25---ሚያዚያ 23) ስለሆነ በዓለ ፍስሕ (የአይሁድ ፋሲካ) በዚህ ዓመት ሚያዝያ 15 ነው። ሚያዝያ 15 ደግሞ የዋለው ማክሰኞ ቀን ነው። (ዕለቱ ማክሰኞ መሆኑን በስሌት ማወቅ ይቻላል።) ወይም በዓለ መጥቅዕ ከዋለበት ከጥቅምት 5 ቀን ጀምረን 195ቱን ቀናት ስንደምር ፍስሕ ሚያዝያ 15 ቀን በዕለተ ማክሰኞ ውሎ እናገኘዋለን።

ስለዚህ በአጭሩ በዚህ ዓመት በ2011 ዓ.ም ፍስሕ (የአይሁድ ፋሲካ) በዚህ ዓመት ሚያዝያ 15 ቀን ማክሰኞ ቀን ሲውል የትንሣኤ በዓል ደግሞ ፍስሕ ከዋለበት ቀን ቀጥሎ ባለው እሑድ ይውላል-ቀኑም ሚያዝያ 20 ነው። ስለዚህ አንድ ሰው እሑድ ስለሚከበረው የጌታችን የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ "እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ!" ቢል ሚያዝያ 15 ቀን ማክሰኞ ለዋለው ለአይሁድ የቂጣ በዓል እንኳን አደረሳችሁ እያለን ነው ማለት ነው። ይኽ ደግሞ ስሕተት ነው። የፋሲካ በዓል ሚያዝያ 15 ቀን ማክሰኞ ዕለት ውሎ አልፏል። የትንሣኤ በዓል ደግሞ ገና ወደፊት እሑድ ሚያዝያ 20 ቀን ይውላል።

1ኛ ወደ ቆሮ 5:7 "እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፣ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና።"

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን!
Forwarded from ምክረ አበው
ቀዳም ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)

#ቀዳም_ሥዑር ይባላል፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

#ለምለም_ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

#ቅዱስ_ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

(ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)
Forwarded from ምክረ አበው
የበዓለ ፋሲካ ድርሳን

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥
እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡
ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥
እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡
በጾም የደከመ ቢኖር፥
አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡
በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥
ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡
በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥
እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡
በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥
አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡
እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥
ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡
እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥
ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡
ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡
በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡
መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡
ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡
ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡
ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡
ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡
እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡
እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡
መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡
ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡
ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡
ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥
ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡
ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥
ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡
ማንም ሞትን አይፍራ፥
የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡
ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡
በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡
ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡
ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም!
ከንቱ አድርጓታልና መረራት!
ሸንግሏታልና መረራት!
ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤
ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ?
ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቿልና፡፡
ለእርሱም ክብርና ጽንዕ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይኹን፥ አሜን!
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን
💛 🍒 💛

ቀዳም ስዑር ፦

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ትባላለች። ቀዳም ስዑር ማለት የተሻረችው ቅዳሜ ማለት ነውና፡፡ በቀዳሚት ሰንበትና በሰንበተ ክርስቲያን ጾም የማይጾም የማይሻር የእረፍት በዓል ቢሆንም ከስቅለቱ ሃይልና ታላቅነት የተነሳ ቅዳሜ ተሽራ የክርስቶስ መከራ እየታሰበ በክርስቲያኖች ዘንድ ይጾምባታል፡፡

ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

ቄጤማ ለምን እናስራለን?
💛
በቀዳም ስዑር ዕለት ቀሳውስትና ዲያቆናት በየቤቱ እየዞሩ ቄጤማ ለምእመናን ይሰጣሉ። እኛም በራሳችን እናስረዋለን የዚህ ትውፊታዊ ታሪክና ትርጉም በአጭሩ እንዲህ ነው፦

በኖኅ ዘመን የነበረው ትውልድ በኃጢአት ሥራው እግዚአብሔርን በማሳዘኑና ንስሐም ለመግባት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ኖኅ ከጥፋት ውሃ የሚድንበትን መርከብ እንዲሰራ ተነግሮት ከሰራ በኋላ ከተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ለዘር የሚሆኑ ወንድና ሴት ወደ መርከቡ እንዲያስገባ ታዘዘ።

ኖኅም እንደታዘዘው አደረገ እሱም ከሚስቱና ሶስት ልጆቹም ከነሚስቶቻቸው ወደ መርከቡ ገቡና ተዘጋ። (ዘፍ.፮፥፮-፳፪, ፯፥፩-፲፩) በዚህ ጊዜ መሬት ተከፈተ ሰማይም ተነደለ ከታች ወደ ላይ ውኃ እየፈለቀ ከሰማይም እንደ እሳት የሚያቃጥል ዝናም ሳያቋርጥ ፵ ቀን ፵ ሌሊት ዘነመ። ዓለሙ ተጥለቀለቀ ወደ መርከቡ ከገቡት በስተቀር የተፈጠሩት ፍጥረታት በሙሉ አለቁ። (ዘፍ፡፯፥፲፯-፳፫)

ከአርባ ቀን በኋላ ውኃው እየጎደለ መጣ ታላላቅ ኮረብቶችም እየታዩ መጡ። ኖኅም ማረፊያ እናገኝ ዘንድ ውኃው ከምድር ጎድሎ እንደሆነ አይተሽ ነይ ብሎ ካልተመለሰው ቁራ በኋላ ርግብን ላካት። እሷም እንደተላከች ውኃው በጣም ስላልጎደለ የምታርፍበት ቦታ አጥታ ደክማ ተመለሰች። እንደገና ከሳምንት በኋላ ቆይቶ ለሁለተኛ ጊዜ ቢልካት ውኃው ጎድሎ በውኃው ተውጠው የነበሩት ዛፎች ብቅ ብቅ ብለው ስላገኘች ለምለም የሆነውን የወይራ ቅጠል
(ቄጤማ) በአፏ ይዛ ወደ ኖኅ ተመለሰችና የጥፋት ውኃ ጎደለ የኃጢአት ባሕር ደረቀ ስትል አበሰረችው። (ዘፍ፡፰፥፲፩)

በዚህ ምክንያት ነው ቤተክርስቲያንም ይህን ምሳሌ አድርጋ የተላከችው ርግብ የውኃውን መጎደል ለኖኅ እንዳበሰረችውና ለምለም ቄጤማ በአፏ ይዛ በመምጣት የምስራች በመንገር ኖኅን ደስ እንዳሰኘችው ሁሉ ፤ ቤተክርስቲያንም ፭ ሺህ ፭ መቶ ዘመን ተዘግቶ የነበረው የገነት በር በክርስቶስ ስቅለት ተከፈተ ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከዲያብሎስ ባርነት ወደ ዕረፍት ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ተሻገርን ስትል ለሚከተሏት ምእመናን የተባረከውን ለምለም ቄጤማ ይዛ ታበስራለች።

ካህናቱም ቤት ለቤት እየሄዱም ፦ "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ" ማለትም ፦ "አዳም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቀ ሞት ጠፋ ኃጢአት ተደመሰሰ፡፡" እያሉ ቄጤማውን ያድላሉ። ምእመናንም ለቤተክርስቲያን የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ከትንሥኤውም በኋላ ገብረ ሰላም የተባለ ግብር (ድግስ) ለካህናቱ ያገባሉ።

እንግዲህ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተገኘው ቃል መሠረት የርግብን ሰላም ሰላማችን አድርገን ቄጤማውን ከካናት እጅ ተቀብለን በበጋም ሆነ በክረምት ልምላሜ የማይለየውን ቄጤማ ተቀብለን ራሳችን ላይ እናስረዋለን። ይህም የሚያመለክተው በክርስቶስ መከራና ሞት ከጨለማውና ከደረቁ እሳት ከሲዖል ወጥተን ልምላሜ ወደ ማይለየውና ጥንተ ቦታችን ወደ ሆነው ገነት መግባታችንን ለማብሰር የደስታ ማብሰሪያ የሆነውን ቄጤማውን በራሳችን ላይ እናስረዋለን።
💛
የአበው በረከት ይደርብን እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ይቆየን!

💛 🍒 💛

✞ገብረ ሰላመ በመስቀሉ!
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን
                          
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። +++

            + ዛሬ ሚያዝያ20 ቀን።
+ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችንለአምላካችን ­ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል በሰላም አደረሰን­።


                       + + +
+ የዕለቱ አንገርጋሪ፦ ሃሌሉያ "ዮም ፍስሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እም ሙታን ቀደሳ ወአክበራ እም ኵሎን መዋዕል አልዓላ አማን ተንሥአ እም ሙታን"። ትርጉም፦ በክርስቲያን ሰንበት ዛሬ ደስታ ሆነ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና የክርስቲያን ሰንበትን ቀደሰ አከበረ ከሁሉ ዕለታትም ከፍ ከፍ አደረጋት በእውነት ከሙታን መካከል ተነሳ። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።

                     + + +
+ "ሰላም ለትንሣኤሁ ፍጹም በሥጋ ወነፍስ ወዐፅም። ትርጉም፦በሥጋ፣በነፍስና በጥንት ለኾነ ፍጹም ትንሣኤው ሰላምታ ይገባል"። አባ ጊዮጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።

                       + + +
+ "ሰላም ለትንሣኤከ እንተ ተጠየቀ ቦቱ። ዜና ትንሣኤሆሙ በክብር ለቅዱሳን ዘሞቱ። ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ቀርነ መንግሥቱ። በዓለ ትንሣኤ ፋሲካነ ዝንቱ። እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ ። ትርጉም፦ ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ ስለፍጹም ሃይማኖት በክብር ለሞቱ ቅዱሳን ሁሉ። የትንሣኤያቸው መረጃ (መተማመኛ) ለሆነው ትንሣኤህ ሰላምታ ይገባል። ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ለዳዊት የመንግሥቱ መለከት አዋጅ ነጋሪ ነህ። ስለዚህ የትንሣኤህ በዓል የደስታ በዓላችን ነው። ሥርዓተ ሕጉ የእሥራኤል ሥርዓት ነውና። መልክአ ኢየሱስ።

                    + ትንሣኤ

+ ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀል ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና።

 + በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን ሙታንና ሕያውን ደስ አላቸው በዚች በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ቅዱስ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸው ነውና። ለእርሱም ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት29 ስንክሳር።

                  +የዕለቱ ስክርሳር።

+ በዚች ቀን ደንደራ ከሚባል አገር ደግሞ እልበደራ ከሚባል አገር ቅዱስ በብኑዳ በሰማዕትነት ዐረፈ። ይህ ቅዱስ ለብቻው የሚኖር ዕውነተኛ ተጋዳይ ነው እግዚአብሔር መልአክም ተገልጦለት "የመቀደሻ ልብስ ለብሰህ ወርደህ ለመኰንኑ ተገለጥለት" አለው። በዚያን ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ከመርከብ ወርዶ ወደዚያች አገር ወደብ መድረሻው ጊዜ ነበር። ይህንንም ባሕታዊ ፈልጎት አላገኘውም ነበር። እነሆ ቅዱስ በብኑዳም በፈቃዱ መጥቶ ወደ መኰንኑ ሔዶ "በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን በግልጥ እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በታላቅ ቃል ጮኸ። መኰንኑም ፈልጎ ያጣው የታወቀ ባሕታዊ መሆኑን በአወቀ ጊዜ እንዲአሠቃዩት በእግር ብረትም አሥረው ከጨለማ ቤት እንዲጥሉት አዘዘ። በዚያን ጊዜም ብርሃን ወጣ የእግዚአብሔር መልአክ ከሕማሙ ፈወሰው አበረታው አጽናናውም።

 + በዚያችም አገር ስሙ ቄርሎስ የሚባል ምዕመን ሰው ነበር ከእርሱ ጋራም ሚስቱና ዐሥራ ሁለት ጐልማሶች ልጆቹ አሉ። እነዚህን ሁሉንም የከበረ በብኑዳ አስተማራቸው አጽናንቷቸውም ራሶቻቸውን ቆርጠዋቸው በሰማዕትነት ሙተው አክሊል ተቀበሉ።

 + አርያኖስም ተቆጥቶ በቅዱሱ አንገት ከባድ ደንጊያ ሰቅለው ወደ ባሕር ይጥሉት ዘንድ አዘዘ በእግዚአብሔር ኃይልም ከድንጋዩ ጋራ ዋኘ። ደግሞ ከሰሎን ዛፍ ላይ ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ ያቺም ሰሌን ዐሥራ ሁለት ዘለላን አፍርታ ለመጪው ትውልድም መታሰቢያ ሆነች። ከዚህም በኋላ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ20 ስንክሳር።

                         + + +
+ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ24፥1-13።

                       + + +
+ የዕለቱ ቅዳሴ ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ።  ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ117፥24-25 ። የሚነበው፡ወንጌል ዮሐ20፥1-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የ­ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መል­ካም የብርሃነ ትንሣኤ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን
💛 🍒 💛

"ልብሱን ጥሎላት ወደ ውጪ ወጣ፡፡"

💛

በምሽት መርሐ ግብራችን አስደናቂውን የሥጋዌ ምስጢር በትንቢታዊው የብሉይ ታሪክ ይዘን እንቀርባለን፡፡

🍒