♥የፍቅር ጥግ♥
[ጉልላት አበበ]
ክፍል 8
...ለምሳሌ እነ ቲጂ እነ መክሊት ሆን ብለው ወንድ የሚያጠምዱት ሳያውቁ ነው??
አንድ ሰው ሰውን የሚገድለው ሰው መግደል ሀፂያት መሆኑን ሳያውቅ ነው??
ናርዲ ያስረዳልኛል ያለችውን ምሳሌ በሙሉ ዘረዘረች
ህይወት እያዳመጠቻት ነበር
"አዎ ሳያውቁ ነው!! " ህይወት ተመቻችታ ተቀመጠች
" ምን መሰለሽ ናርዳዬ ሶቅራጠስ ማለት የፈለገው እውቀት እና አንቺ የምትዪው እውቀት በመጀመሪያ...."የናርዲ ስልክ አቋረጣት
"ቀጥዪ በኃላ አነሳዋለሁ " አለች ናርዲ
" እሺ ልቀጥል እውቀት ለሶቅራጦስ ሁለት ትርጉም አለው በእነዚህ ትርጉሞች አንፃር ነገሮችን ስታዪ ምን ያክል እውነት እንደሆነ...." የናርዲ ስልክ በድጋሚ ጠራ
ናርዲ እየተነጫነጨች ወደ ተሰካው ስልኳ አመራች
"ኦ ማይ ጋድ!! ናሆሜ ነው" አለች
ህይወት ከናርዲ በላይ ደነገጠች
"አንሺው ህይወት ካለች የለችም በዪው" አለቻት
እሺ ብላ አነሳቺው
"ሄለው"
"ናርዲ የናዝሬቷ" አላት ድምፅ እንደሰማ
"ናሆሜ የአዲስ አበባው" አለች ፈገግ እያለች
ምንም እንኳን ጥሩ ጓደኝነት ቢኖራቸውም ፡ ምንም እንኳን እሷ በልቧ ደብቃ ብታፈቅረውም ፡ ምንም እንኳን መክሊትና ቲጂ ፕሮጀክታቸው አድርገውት ቢያቅታቸው ፡ ምንም እንኳ ሂዊ እንደ ማንኛውም ወንድ ብትንቀው ናሆሜ ለናርዲ የገነት ቅብ ሲኦል ነው
ከላይ ሲያዩት የሚግባባ ፡ ቀላል ፡ የሚሸነፍ ቢመስልም ግን እሱ ሩቅ ነው የማይደረስበት
ናሆሜን ትወደዋለች ግን ደግሞ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆና
"ናርዲ ምነው መደወል አልነበረብኝም እንዴ? ዝም አልሽ" ደነገጠች
"አይ ! እንገናኝ እንዴ ማለቴ አንድ ግቢ ሆነን ካርድ እንዳይቆጥርብህ..ማለቴ መደወልህን ጠልቼ አይደለም .."
ሂዊ ሳቀች (የሂዊ ሳቅ በስልኩ ጆሮዎች ናሆሜ ጋር ደረሰ)
ናርዲ የምታወራው ጠፋባት
እሱ ደውሎ እሷ ላግኝህ ማለቷ ቆጫት (ምናለ ትንሽ ብጠብቅ ?ሊያገኘኝ አይደል እንዴ የደወለው?!)
ናሆም በህይወት ሳቅ ተናዷል
"እሺ ናርዲዬ እኔም ትንሽ ደብሮኛል ፡ ባገኝሽ ደስ ይለኛል"
"እናቴ ትሙት አይደብርህም!"
"እሺ (ሳቀ) ..ከስንት ደቂቃ በኃላ ልምጣ)
"አሁን ! ማለቴ ከ30 ደቂቃ በኃላ"
ናሆሜ ስልኩን ዘጋው
"እንዴ? ምን ሆነሻል አንቺ ! ምን ብሎሽ ነው እንደዚህ?" ሂዊ ጠየቀቻት
ናርዲ ሳትመልስላት ፍራሿ ላይ ተወረወረች፡ ሁለት እጆቿን ዘርግታ በፀጥታ ለሰከንዶች ቆየች
ወንዶች
ተሰብስበው የናሆሜን ስልክ ሲያዳምጡ የነበሩት ጓደኞቹ ልክ ስልኩን እንደዘጋው ዳዊት
" እሺ ናርዲዬ አለ እኮ" (ሁላቸውም ሳቁ)
"ትንሽ ደብሮኛል ..ባገኝሽ ደስ ይለኛል" ቃል እየሳቀ ይናገራል እየተናገረ ይስቃል
ናሆሜ እንደ ማፈር ብሎ ፍራሹ ላይ ተኛ
"ቆይ ምን ያንቀጠቅጥሀል? ከምኔው ከምኔው!" ልኡሌ
ኸረ ዘፈኑን እንበለው
ተሰባስበው " ከምኔው ከምኔው ነውሳ
ልበ ቢስ የሆንኩት በናርዲ የተነሳ
( እያ ጭብጨቡ)
ከምኔው ከምኔው ከምኔው ነው ደግሞ
እንዳልተው ያረገኝ በናርዲ አዳክሞ
(ናሆሜም ተነስቶ ከነሱ ተቀላቀለ)
ምኔው ለምጄ ለምጄ
አረፍኩ ወድጄ
(ሁላቸዌም አንድ ላይ ተሳሳቁ)
ሴቶች ዶርም
"ይህንን ልትለብሺ ባልሆነ? " አለቻት ህይወት በናርዲ አለባበስ ደንግጣ
" አዎ ! ምነው? ማንነቴ እኮ ነው" መለሰችላት
ናርዲ የኦሮሚያ ባህላዊ ልብስ ነበር የለበሰችው
"ልክነሽ ግን ዛሬ የብሔርብሔረሰቦች ቀን ነው እንዴ?"
"አትሳሳች ጓደኛዬ ማንነታችን ውበታችን ነው! በእርግጥ አንቺ ይህንን አትወጂም!"
"ኖ ናርዲዬ እኔ ችግሬ ከልብሱ ጋር እኮ አይደለም ፡ ታውቂያለሽ የኦሮሞ የትግሬ የአማራ የጉራጌ ልብስ ብለን መከፋፈል ልዩነታችንን የበለጠ ያጎላዋል! የኦሮሞ ልብስ መልበስ እኮ እኔ ኦሮሞ ነኝ ማለት አይመስልሽም?!"
"በእርግጥ በእሱ በኩል ከታሰበ አዎ ! ግን እንደዛ ማሰቡ በራሱ ዘረኝነት ነው!
አስበሺዋል አንቺ የመቀሌ ልጅ ሆነሽ ስለ ናዝሬት ስለ ኦሮሚያ ባህል፡ ቅርስ፡ አለባበስ ቁንጅና እኔ ካላሳየሁሽ አንቺ በእኔ ልብስ ካላጌጥሽ እኔ በአንቺ ልብስ ካላጌጥኩ ምኑ ላይ ነው ፍቅራችን?"
ሂዊ ተነስታ የናርዲን ባህላዊ ልብስ አስተካክላ ጉንጯን ሳመቻት
" አምሮብሻል ናርዲዬ! ይቅናሽ እሺ"
ተቃቀፉ
"በቃ ልሂድ ሰአት ደርሷል" አለቻት
ወንዶች ዶርም
"አንተ ተነስተህ አትዘገጃጅም?" ኘለው ቃል በእግሩ እየነካካው
"ምንድነው ምዘገጃጀው ፈተና የምገባ መሰለህ እንዴ?"
(ሁላቸውም ሳቁ)
ልኡሌ እየሳቀ " ከሰላሳ ደቂቃ በኃላ ያለችህ ለምን ይመስልሀል?"
ማንንም ሳይጠብቅ እራሱ ቀጠለ
"አስር ደቂቃው ለልፒስቲክ አስር ደቂቃው ለዶድራንት.."
"ግን ምን የምትለብስ ይመስላቹሀል?" ዴቭ
ተከታትለን እንሹፋቸው እንዴ?
"አሳይመንቱስ?"
"ናሆሜ ሲመለስ ሰራ ሰራ ያደርገዋላ!"
"ሲያምርህ ይቅር እሺ እሱ ዛሬ ምንም አይሰራም! እኛ ነን የእሱን የምንፅፍለት" አለ ቃል የናሆሜ ሎከር እየከፈተ
" መፃፉንስ ትፅፋለህ፡ ግን መልሱ ከየት ታመጣለህ?"
"እሱም አለ ለካ..."
"ምን እያደረክ ነው ? ሎከሩን ለምንድነው የምትከፍተው?" ናሆሜ
"እኔ ከሆነ ልብስ አልቀይርም"
አስገድደው ልብስ አስቀየሩት አስገድደው ፀጉሩን አስታጠቡት አስገድደው ዶድራንት ነሰነሱበት
የቀጠሮው ሰአት ደረሰ
.
.
.
.
ይቀጥላል
ሼር አድርጉ

ኦሪዮንን እና የፍቅር ጥግ የምትከታተሉት ልጆች ብዛታችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ
የፍቅር ጥግ የምትከታተሉ 🙏 ተጫኑ
ኦሪዮንን የምትከታተሉ👍
ሁለቱም የምትከታተሉ❤️
የፍቅር ጥግ የምትከታተሉ 🙏 ተጫኑ
ኦሪዮንን የምትከታተሉ👍
ሁለቱም የምትከታተሉ❤️
♥ኦሪዮን♥
ክፍል ፬ (4)
ከዚህ በፊት ይተዋወቁ ነበር?
ከማን?
ከኦሪዮን
(ፍቅር ሀሳቧ ክላስ ውስጥ የለም)
ከዚህ በፊት ቢተዋወቁ እንኳን ትነግረኝ ነበር ቢያንስ ስልኩ ይኖራት ነበር ፡ ቢያንስ ይደዋወሉ ነበር
ቢተዋወቁስ እኔ ከተዋወቅነው ገጠመኝ ይበልጣል? (ፈገግ)
ፍቅር በሀሳብ ወደ ኃላ ነጎደች
ይህ ታሪኳ ደስም ይላታል ይቆጫታልም
(ሁለት ስሜት ማስተናገድ ይቻላል?)
" የስምንተኛ ክፍል ሚንስትሪ ውጤታቸውን መቀበል ምክንያት አድርገው ያዘጋጁት ፕሮግራም ላይ መምህራንን ጋብዘዋል ፡ ሁሉም የስምንተኛ ክፍል መምህራን ሲሆኑ በፕሮግራሙ አዘጋጆች አንድ መምህር ከሀይስኩል መርጠው መጋበዝ እንዳለባቸው ወስነው ነበር
ፍቅር ይሄንን አታውቅም ነበር
የፍቅር ውጤት የግቢው ሁለተኛ (ከዮናታን ቀጥሎ) እና ከሴቶች አንደኛ ነበርና ከመምህራኑ ፊት ለፊት ሁለቱ የውጤት ሰቃዮች ተቀምጠዋል
አሁን የቀረው ተጋባዡ መምህር ብቻ ነው ;-ኦሪዮን
ከጥቂት መጠበቅ በኃላ ልክ ኦሪዮን እንደመጣ ፕሮግራሙ ተካሄደ ፡ (ወደፊት አልቀደመም ወደኃላ አልዘገየም)
ኦሪዮን ንግግር እንዲያደርግ በፕሮግራሙ አዘጋጆች ቢለመንም አሻፈረኝ አለ
(ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም ) ነበረ መልሱ
(ይህ ግን ለፍቅር እና ጓደኞቿ ንቀት ነበረ)
ኦሪዮን ለተማሪዎቹ የተዘጋጀውኝ ሽልማት በፕሮግራም አስተናባሪው ጥሪ ከተደረገለት በኃላ ሰጠ
(ተማሪዎቹ ንግግር ባለመድረጉ ተከፍተዋል በተለይ ፍቅር)
ፍቅር ሽልማቷን ከኦሪዮን እጅ ስትቀበል ፈገግ እንኳን አላለችም
ኦሪዮን ጫጫታ አይወድም ፡ ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ክብር ብቻ ብሎ ነበር የተገኘው
ለመቅረት ወስኖም ነበረ
እንደምንም መጥቶ እሱ የሚመለከተውን ካደረገ በኃላ ከፕሮግራሙ ወጥቶ ትምህርት ቤቱን ለብቻው መቃኘት ጀመረ
እጆቹን እራሱ ላይ ያደርጋል ፡ በእግሩ መሬት ይደበድባል፡ ወደ ሰማይ አንጋጦ ይመለከታል
(ፍቅር በአይኗ ትከታተለው ነበረ )
"ምን ሆነሻል?" አጠገቧ የነበረው ተማሪ
"ማን ነኝ ብሎ ነው የሚያስበው? አየኸው ሲጠበርር?"
" አንቺ ምን አገባሽ?"
ፍቅር ተነስታ ተከተለችው
ከጫጫታው እርቆ ነበር (ብቻውን መሆን ፈልጓል)
ተከተለቺው
"ጎበዟ ተማሪ ! እንዴት ነሽ?" ኦሪዮን በፈገግታ ተቀበላት
"ምን ያደርጋል? በአንተ እጅ ሽልማቱን መውሰዴ ቀኔን አበላሸው!"
(ፍቅር ለስድብ ታጥቃ ነው የመጣቺው)
"ምነው ምን አጠፋው?" ኦሪዮን ግራ በተጋባ መንፈስ
"ጉረኛ ነህ በጣም! ላንተ ነው እንዴ ተማሪዎች እንደዚህ ያካበዱት? ኦሪዮን ኦሪዮን የሚሉት አንተን ነው? ቀላል ነህ እሺ! አንተም ብሎ መምህር!"
"ነይ እስኪ ቁጭ በይ" ኦሪዮን አጠገቡ ባለው አግዳሚ ወንበር ተቀመጠ
"ካንተ ጋር ለሰከንድ እንኳን አልቀመጥም እሺ! እያየሁህ እኮ ነው ከመጀመሪያ ጀምሮ ..በመጀመሪያ አረፈድክ ከዛ መጥተህ እንኳን ንግግር አድርግልን ብለው ሲለምኑህ ተጠባረርክ ይህም ሳያንስህ ጭራሽ ፕሮግራማችንን አቋርጠህ እዚህ ትንዘላዘላለህ"
ኦሪዮን ሳቀ " ሳላውቀው አግብቻለሁ እንዴ? አንቺ ለምንድነው ከመጀመሪያው ጀምረሽ የተከታተልሺኝ?" አላት
"ሰው መስለኸኝ !" ፍቅር ፊቷ ቀይ ሆኗል
"እሺ ! ቁጭ በይ ካጠፋሁም ይቅርታ እጠይቃለሁ"
ኦሪዮን ሊያረጋጋት ሞከረ
"ነገርኩህ እኮ ከገባህ! ባዶ ነህ" የበለጠ እየቀረበቺው ጮኸችበት
ኦሪዮን ከተቀመጠበት ተነሳ " አይገርምሽም ጮህሺብኝ እንጂ እስካሁን አልተናገርሺኝም! ምን እንደሆንኩ እንኳን አልጠየቅሺኝም"
ፍቅር ጥላው ሄደች
ኦሪዮን በተፈጠረው ነገር ተናደደ "ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው?"
ስልኩን አውጥቶ ፕሮግራም አስተናባሪው ጋር ደወለ
"እባክህ ፕሮግራሙ ከማለቁ በፊት ለ 3 ደቂቃ ንግግር አደርጋለሁ "
ስልኩን ዘጋው
ለፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ቡና እና ዳቦ እየታደለ ነበር፡ የፕሮግራሙ መሪ ወደ መድረክ ወጥቶ
"በመጨረሻም ሰርፕራይዝ አለ ! እስኪ እንደማመጥ"
አንፃራዊ ፀጥታ ሰፈነ
"ሁለት ፕሮግራም ቀርተውናል በመጀመሪያ በተማሪ ዮናታን ምርጥ ግጥም ይቀርባል ፡ከዛ ቀጥሎ ተወዳጁ መምህራችን ወደ መድረክ ወጥተው የሚነግሩን ነገር ይኖራል " (ሞቅ ያለ ጭብጨባ)
ፍቅር ጀብደኝነት ተሰማት
"የታባቱ ሰራሁለት! ይንጠባረራል እንዴ?!" ለብቻዋ ፈገገች
ኦሪዮን ግጥሙ እንዳበቃ ወደ ነበረበት ወንበር ተመለስ
ፍቅር ወደ እሱ እያየች ለመሽኮርመም ያደረገችው ጥረት አንዴም አልተሳካም ፡ፍፅሞ ወደ እሷ አልተመለከተም
ኦሪዮን ወደ መድረኩ ተጠራ
" ምናልባት አሁን ላይ ይህንን መናገር አልነበረብኝም ግን በቃ ይቅርታ አድርጉልኝ : እናንተ ገና ወጣቶች ናችሁ ይህ በጣም ደስ ይላል ያላችሁ ተነሳሽነት ፓወር አቅም ይህ ሁሉ ተስፋ ነው! የሚሆን ..የሚሳካ ተስፋ..ግን አለ አይደል አንዳንዴ
ይህ የእናንተ ብቻ ችግር አይደለም ፡ ማለቴ የሰው ልጆች ሁሉ ችግር ነው ፡ እኛ ሁሌም የምናየው ህልማችንን ብቻ ነው ! ማለቴ ጥናቃቄ ይጎለናል
እስኪ አስቡት አንድ ህልም ያለው ተማሪ ህልሙን እያሰበ ብቻ አስፓልት ላይ ቢጓዝ ከዛ መኪና መጥቶ...(አልጨረሰውም)
ስሜቴ ጥሩ አይደለም ፡ ንግግር ያላደረኩት በዚህ ምክንያት ነው ፡ እኔ ወደዚህ ስመጣ ያስተማርኩትን ልጅ በአይኔ እያየሁ በመኪና አደጋ አጣሁት
አልናገርም ብዬ ነበረ ግን አንድም የትም መቼም ቢሆን ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ ለማሳሰብ ሲሆን
ሁለት ደግሞ (ወደ ፍቅር እየተመለከተ ) አለመናገሬን በስህተት እንዳትረዱት"
ከመድረኩ ወረዶ ከግቢው ለመውጣት ጉዞ ጀመረ
ፍቅር አንገቷን ደፋች ፡ ፕሮግራሙ በሀዘን ድባብ ተፈፀመ
"አለመናገሩ ልክ ነበረ ፡ ይህ ሁሉ መዐት ይዞ ምጣቱ እንኳን ክብር ያለው ሰው ነው" ፍቅር ለብቻዋ ታወራለች
"ኦሪዮን.. ኦሪዮን .." እየተከተለቺው
ሰምቶ እንዳልሰማ ዝም ብሏት መንገዱን ቀጠለ
.
.
.
.
.
.
.
.
https://telegram.me/gullea
like
Comment
share
አድርጉ

ክፍል 9
ወንዶች ዶርም
........
"ተከታትለን እንሹፋቸው እንዴ?"
"አሳይመንቱስ?"
"ናሆሜ ሲመለስ ሰራ ሰራ ያደርገዋላ!"
"ሲያምርህ ይቅር እሺ እሱ ዛሬ ምንም አይሰራም! እኛ ነን የእሱን የምንፅፍለት" አለ ቃል የናሆሜ ሎከር እየከፈተ
" መፃፉንስ ትፅፋለህ፡ ግን መልሱ ከየት ታመጣለህ?"
"እሱም አለ ለካ..."
"ምን እያደረክ ነው ? ሎከሩን ለምንድነው የምትከፍተው?" ናሆሜ
"እኔ ከሆነ ልብስ አልቀይርም"
አስገድደው ልብስ አስቀየሩት አስገድደው ፀጉሩን አስታጠቡት አስገድደው ዶድራንት ነሰነሱበት
የቀጠሮው ሰአት ደረሰ
ይህንን ቦታ ተማሪዎች "ላቭ ሴንተር " ይሉታል ፡ ምናልባት ፍቅረኛሞች የሚገናኙበት ቦታ ስለሆነ ይሆናል
የግቢው ምርጥ ምርጥ ጥንዶች ልክ ከምሽቱ 1 ሰአት ሲሆን ይሽሸጉበታል
የግቢው ሰላም ፎረሞች ( የፍቅር ጠላቶች ይሏቸዋል ጥንዶቹ ) መጥተው እስኪበትኗቸው ፍቅራቸውን ይለዋወጣሉ
ካገኟቸው የሚያበሩባቸው ባህሪ ባውዛ አይጣል ነው
ይህ ቦታ ቀን ቀን የሁሉም ተማሪ ቢሆንም ማታ ማታ ለፍቅረኛሞች ብቻ የተሰጠ ነው
ያወራሉ ፡ ከመተቃቀፍ የዘለለ ይተሻሻሉ ፡ ይሳሳማሉ
ናሆሜ በቀን እዚህ ቦታ የቀጠራት ሌላ የተሻለ ቦታ ያለ ስላልመሰለው ነው
"በሌላ ታስበው ይሆን እንዴ ?" እየጠበቃት ያስባል
"አይ ትክክል ነኝ! እና ላይብረሪ ልቀጥራት ነበር?" በምናቡ ብቻውን ያወራል
(ፍርሀቱ ይሆን?)
ናሆሜ በቀጠሮው ሰአት ቀድሞ ተገኘ
(ይህ የሁልጊዜ ተግባሩ ነው! ለሰአት ከሰው እኩል ክብር ይሰጣል
ጊዜ ጌታ ነው ይላል ደጋግሞ)
ናርዲ ብዙም ሳትቆይ ናሆሜ ባልጠበቀው አቅጣጫ በጀርባው በኩል ከተፍ አለች
"ሰላም ሰላም" (ፈገግታ)
"በስመአብ! " አስደነገጥሺኝ እኮ
"እናቴ ትሙት ! ይቅርታ "
(እናቴ ትሙት የምትለው ከልቧ ስታዝን ነው ! ቃሏ ከእውነቷ በላይ ሲሆን ፡ ማስረዳት ሲያቅታት ፡ ልቧ ሲከፈት ብቻ እናቴ ትሙት ትላለች)
ናሆሜ ተነስቶ አቀፋት
"እውነት በጣም አምሮብሻል " አይኖቿን እያየ
" ታንክዩ" አለቺው ለጥንዶች በተሰራው ወንበር እየተቀመጠች
" 'ገለቶማ ' ብትዪኝ የበለጠ ደስ ይለኝ ነበር እውነትም የናዝሬት አዳማ ልጅ ነሽ " (ተሳሳቁ)
" አየሽ ናርዲ እኛ ከቤታችን ውጪ ነው እየኖርን ያለነው : ባይገርምሽ እየኖርን ያለነውን እንኳን በቅጡ አናውቀውም :
የእውነት እንደዚህ በራስሽ ልብስ ተውበሽ ሳይሽ ደስ ነው ያለኝ ፡
በሌላ አታስቢውና ለአንቺ ያለኝ ክብር ነው የጨመረው፡
( በለቧ "እናቴ ትሙት! አላስበውም" አለች ) አስበሺዋል እኛ ኢትዮጲያዊያን በመምሰል እና በመሆን መሀል ውስጥ እኮ ነን ፡፡ እስኪ በእጃችን ያለው የትኛው ነው? የእኛ ወይስ የነሱ?
የእኛን ጭራሽ አናውቀውም ወይም በጭራሽ አንወደውም ፡ የእነሱን ለመምሰል (መሆን አንችልም ታውቂያለሽ ምክንያቱም እነሱ ሊሆኑ የሚችሉት እነሱ ብቻ ናቸው) እና የእኛ ለመምሰል መላላጥ ምንድነው ትርጉሙ? "
(ናሆሜ ለውይይት ያለው ፍቅር ከምንም በላይ ነው፡ በተለይ ስለ ሀገር ጉዳይ ከሆነ ፡
አሁን እራሱ በስሜት ውስጥ ሆኖ ነው የሚያወራው ፡ ስለ ሀገሩ ማውራት ስለትውልዱ ማሰብ የሁልጊዜ ስራው ነው)
ናርዲ የናሆም ከልብ የመነጨ የአድናቆት ስሜት መላ አካላቷን ሲወራት ይታወቃታል ፡
መደነቋ አስደስቷታል፡
ናሆሜ አለች አይኖቹን እያየች
" ናሆሜ እኔ እንደማስበው ብዙ ችግሮች ያሉብን ይመስለኛል በተለይ ይቅርታ አድርግልኝና የዚህ ዘመን ትውልድ ይህቺን ሀገር አንመጥነውም !
እሱ ብቻ አይደለም ለክፍለዘመኑም ብቁ አይደለንም " አለች
( ግን እኮ እሱም የዚህ ትውልድ አንድ አካል ነው ፡፡ ቅር ይለው ይሆን? ካንተ ውጪ ልበለው እንዴ?)
" ለምን እንደዛ አልሽ?" ጠየቃት
"አየህ ችግሮቻችን ሁሉ የመነጩት ከምንም ሳይሆን ከአይምሮአችን ማነስ ፡ ከአስተሳሰባችንን መድቀቅ የመነጨ ነው፡፡
እስኪ አስበው ወንዶች ሴቶችን የሚያደንቁት ተገላልጠው ሲያገኟቸው ነው፡ ሴቶች ወንዶችን የሚወዷቸው በወሬያቸው መሀል እንግሊዘኛ ሲጨምሩ ነው!
ጭራሽ እኮ ሌሎቹ ገጠሬ ፡ ፋራ ነው ስማቸው!
እሱን ተወው አንዷ የትግራይ ልጅ የትግራይ ባህላዊ ልብስ ለብሳ ወክ ብታደርግ ምን እንደምትባል ታውቃለህ? ስሟ ብሄርተኛ ነው!!
በጣም የሚያስቀኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ?
ጭራሽ ባህላዊ ልብስ ስትለብስ እዛው ተወልደው ያደጉት ልጆች ልክ እንደ ውጪ ሰው ካንተ ጋር ፎቶ ልነሳ የሚሉት ነገር "
ናሆሜ ሳቀ ፡ እረጅም ሳቅ
ሳቁ ግን የቁጭት ነበር፡ ከልቡ እንዳልሆነ፡ ምን ማለት እንዳለበት አላወቀም
" እኔ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ? የሆነ ነገር ተፈጥሮ ከአሜሪካ ወይም ከአንዱ የአውሮፓ ሀገር ባህላችንን፡ አለባበሳችንን ፡ አመጋገብ ስርአታችንን ብንቀያየር፡ ማለቴ የእኛ የእነሱ ሆኖ የእነሱ የእኛ ቢሆን ምን ይፈጠራል ብለሽ ታስቢያለሽ? "
"በእርግጠኝነት አሁንም እኛ የእነሱን እንኮርጅ ነበር "
(ለረጅም ሰአት ተሳሳቁ)
የዘቀጠ ትውልድ!!
"ለማንኛውም ደስ ብሎኛል : ገና እንደመጣሽ በቁምነገር አዛግኩሽ ይቅርታ"
"እናቴ ትሙት ችግር የለውም" (ከልቧ ነው)
"እኔ ለውይይት እና ለክርክር ልዩ ቦታ አለኝ ፡ በጣም ነው የምወደው፡ ባይገርምሽ አንድ ቀን.." ዝም አለ
ናርዲ እጁን ስትይዘው ነበር ያቆመው
"እ ቀጥላ የምን ጀምሮ መቆም ነው"
"እሺ ልንገርሽ ፡ ክላስ ውስጥ እየተማርን ነበረ ፡ እና ከኛ ክላስ ጀርባ በኩል ተማረዎች ገራሚ ክርክር ይዘው ነበረ ፡
የተቀመጥኩት ከኃላ ነበርና ሙሉ ለሙሉ እያዳመጥኳቸው ነበር: እና ከትምህርቱ በላይ ንግግራቸው ሳበኝ "
"ለመሆኑ በምን ነበር የሚከራከሩት?"
"እሱ ነው ቀልቤን የሳበው ፡ እኔ የምፈልገው ርዕስ ነበረ ፡ምን መሰለሽ ክርክራቸው ' የሰው ልጅ በተፅዕኖ ውስጥ ነው ! ምንም ቢያደርግ ልክ ነው ምክንያቱም ድርጊቱ የእሱ ብቻ ሳይሆን የተፅዕኖው ነው የሚል ነበረ"
" ዋው ገራሚ ርዕስ ነው!"
"በጣም! እና ምን ባደርግ አሪፍ ነው ጭራሽ ክላስ ውስጥ እንዳለው እረስቼው ድምፄን ከፍ አድርጌልሽ "ኖ እንደዛ መደምደም አንችልም ተፅዕኖ የሰውን ልጅ ከቨር ሊያደርገው አይችልም!" አላልኩም?
(ሳቅ )
"ወይኔ!( እጇን በአፏ ጭና)
መምህሩ ምን አለህ? በጌታ"
"ምንም አላለኝም አስፈቅጄው ወጣሁ"
"እንደዚህ መወያየት የምትፈልግ ነገር ከሆነ አንድ ጎበዝ ጓደኛ አለቺኝ፡ ታውቃታለህ መሰለኝ ..እ. ህይወት ትባላለች"
አያት
አየቺው
.
.
.
.
ይቀጥላል
Share

የፍቅር ጥግ በዩቲዩብ ቻናላችን ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰአት ሙሉውን ታሪክ ይቀርባል
ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ጠብቁ
ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ጠብቁ
#ቁርጥራጭ ሃሳቦች
የሰማንያ ትዳር የሚባለው የተጀመረው በዳግማዊ ሚሊንክ ግዜ ሲሆን ባልና ሚስት በትዳር የተወሰነ ግዜ ከቆዩ በኃላ ቀድሞ ውሉን የሚያፈርሰው ሰማንያ ብር እንዲቀጣ ይወሰንበት ስለነበር ምንምኳ ህጉ ቆይቶ ቢፈርስም ስያሜው ግን እስከዛሬም ድረስ አለ ።
ምንጭ የበውቀቱ ስዩም የሎጋው ሺቦ ታሪክ ፅሁፍ

አስገራሚ እውነታዎች
• ፈረንሳይኛ፤ ከ600 ዓመታት በላይ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል፡፡
• ኤልቪስ ፕሪስሊ 8ኛ ክፍል ሳለ፣ በሙዚቃ ትምህርት ዝቅተኛ ውጤት “C” ነበር ያገኘው፡፡
• አንድ አማካይ የ4 ዓመት ሕጻን፣ በቀን ከ400 በላይ ጥያቄዎችን ይጠይቃል፡፡
• ቀንድ አውጣ ለሦስት ዓመታት እንቅልፉን ሊለጥጥ ይችላል፡፡
• ዝሆኖች መዝለል የማይችሉ ብቸኛ እንስሳት ናቸው፡፡
• አንዳንድ ድመቶች ለሰዎች አለርጂክ ናቸው፡፡
• አብርሃም ሊንከን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከመሆኑ በፊት የአገሩ የነፃ ትግል ሻምፒዮና ነበር፡፡ በ300 ገደማ የነፃ ትግል ግጥምዎት ላይ ተሳትፎ በአንዱ ብቻ ነው
የተሸነፈው፡፡
• እ.ኤ.አ በ1930 በሚያዝያ ወር አንደኛው ቀን ላይ ቢቢሲ ‹‹ዜና የለም›› ሲል አስታውቆ ነበር፡፡ በምትኩም የፒያኖ ሙዚቃ ለቋል፡፡
• እንደ ጣት አሻራ ሁሉ፣ የእያንዳንዱ ሰው የምላስ አሻራ የተለያየ ነው፡፡
• በ16ኛውና በ17ኛው ክ/ዘመን፣ ቱርክ ውስጥ ቡና ሲጠጣ የተያዘ ማንኛውም ሰው ለሞት ይዳረግ ነበር፡፡
• የዛሬ 3ሺ ዓመት ገደማ፣ አብዛኞቹ ግብፃውያን የሚሞቱት በ30 ዓመት ዕድሜያቸው ነበር፡፡
• ኮካኮላ መጀመሪያ ላይ ሲፈጠር ቀለሙ አረንጓዴ ነበር፡፡
• በዓለም ላይ ከአምስት ሰዎች አንዱ (1.1 ቢሊዮን ሕዝብ) የቀን ገቢው ከ1 ዶላር በታች ነው፡፡
• ሕጻናት ቢያንስ አንድ ወር እስኪሆናቸው ድረስ እንባ አያነቡም፡፡
• ማር የማይበላሽ ብቸኛ ምግብ ነው፡፡ 3 ሺ ዓመት ያስቆጠረ ያለችግር ሊበላ ይችላል።
#ምንጭ የቲ እና አዲስ አድማስ ጋዜጣ
=====

ሰላም ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች😍😍😍
እስካሁን በትዕግሥት ለጠበቃችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏

¤ አላገኝሽም....¤
(ገጣሚ ጉልላት አበበ)
~
እሩቅ ሆነሽ ማፍቀርሽን
ስትነግሪው አንቺ እንደሰው፣
እዪው ልቤን ሲብረከረክ
እዪው ልቤን አቅም ሲያንሰው።
~
ላግኝሽ ብል የማልችለው
የማልሆነው ልሁን ብዬ፣
ያይንሽ ብርሀን ፍንጣቂ
ዘልቆ ገብቶ ከህሊናዬ ።
[ራሴን ጥዬ ሙሉ ክብሬን
ምን ይባላል ብስት አቅሌን?]
~
ለማልፈታው ድርብ ቅኔ:
ያንቺነትሽ ውብ ቋጠሮ፣
ከግርማሽ ፊት ደርሶ መቆም
እንዴት ይቻል ይህ ተፈጥሮ?።
[የሰማዩ ውዱ አባቴ~
በፀና ቃል የነገርከን
እውነት እውነት እኔ እና እሷን
ባንድ አፈር ነው የፈጠርከን!?]
~
እያሰብኩሽ ብቻ መኖር
እያሰብሺኝ እኔን ላፍታ፣
ይህ ነው በቃ የኔ መውደዴ
የማፍቀሬ ውብ ገፅታ።
ውብ ተፈጥሮሽ አለመፍራት
አለመኖር በሰቀቀን ፣
እስከዚህ ነው የኔ ልኬ
እስከዚህ ነው የኔ መጠን።
~
የእኔ እንደሆንሽ ስትነግሪኝ
መሬት ጠቦኝ ፡ ሰማይ ቀርቦኝ
ስትደሰች በመኖሬ ፣
ካርያም ነው የምመለስ
አድማሳትን አሻግሬ።
ባለመኖር ስወላገድ
ሰው ለመሆን ስንገዳገድ
መቃብሬን ሊያፋጥኑ ሲጠቋቀሙ ከላዬ
ማን ነበረ የኔ ጋሻ ማን ነበረ ጠበቃዬ?
~
ከሰውነት ተራ ወጥቼ
ከሰውነት ተራ ስሸሽ
ከሰውነት ተራ ወጥተሽ
ሰው ያስባልሺኝ አንቺ አይደለሽ?
[ የሰማዩ ውዱ አባቴ~
በላዬ ላይ አንግሰሀት
በልቧ ላይ ሁሌ ብገኝ
ለሷ ኖሬ ለሷ ብሞት
በፍርድ ቀን አትጠይቀኝ።]
~
በሀሳብ ሆኜ የፈራሁት
ያን ውብ ገላ ውብ ምሳሌ፣
እሳት ሆኖ ካነደደው
ስትዳብሺኝ መላ አካሌ ።
ይቅርብኝ አላይሽም
አላገኝሽም እንደ ሰው፣
ይህ ኑረቴ ለዘላለም
አንቺን ማሰብ መች አነሰው!!!?
ኣ
ላ
ገ
ኝ
ሽ
ም።
[ ተፃፈ በጉልላት አበበ 2013ዓ.ም ]
(ገጣሚ ጉልላት አበበ)
~
እሩቅ ሆነሽ ማፍቀርሽን
ስትነግሪው አንቺ እንደሰው፣
እዪው ልቤን ሲብረከረክ
እዪው ልቤን አቅም ሲያንሰው።
~
ላግኝሽ ብል የማልችለው
የማልሆነው ልሁን ብዬ፣
ያይንሽ ብርሀን ፍንጣቂ
ዘልቆ ገብቶ ከህሊናዬ ።
[ራሴን ጥዬ ሙሉ ክብሬን
ምን ይባላል ብስት አቅሌን?]
~
ለማልፈታው ድርብ ቅኔ:
ያንቺነትሽ ውብ ቋጠሮ፣
ከግርማሽ ፊት ደርሶ መቆም
እንዴት ይቻል ይህ ተፈጥሮ?።
[የሰማዩ ውዱ አባቴ~
በፀና ቃል የነገርከን
እውነት እውነት እኔ እና እሷን
ባንድ አፈር ነው የፈጠርከን!?]
~
እያሰብኩሽ ብቻ መኖር
እያሰብሺኝ እኔን ላፍታ፣
ይህ ነው በቃ የኔ መውደዴ
የማፍቀሬ ውብ ገፅታ።
ውብ ተፈጥሮሽ አለመፍራት
አለመኖር በሰቀቀን ፣
እስከዚህ ነው የኔ ልኬ
እስከዚህ ነው የኔ መጠን።
~
የእኔ እንደሆንሽ ስትነግሪኝ
መሬት ጠቦኝ ፡ ሰማይ ቀርቦኝ
ስትደሰች በመኖሬ ፣
ካርያም ነው የምመለስ
አድማሳትን አሻግሬ።
ባለመኖር ስወላገድ
ሰው ለመሆን ስንገዳገድ
መቃብሬን ሊያፋጥኑ ሲጠቋቀሙ ከላዬ
ማን ነበረ የኔ ጋሻ ማን ነበረ ጠበቃዬ?
~
ከሰውነት ተራ ወጥቼ
ከሰውነት ተራ ስሸሽ
ከሰውነት ተራ ወጥተሽ
ሰው ያስባልሺኝ አንቺ አይደለሽ?
[ የሰማዩ ውዱ አባቴ~
በላዬ ላይ አንግሰሀት
በልቧ ላይ ሁሌ ብገኝ
ለሷ ኖሬ ለሷ ብሞት
በፍርድ ቀን አትጠይቀኝ።]
~
በሀሳብ ሆኜ የፈራሁት
ያን ውብ ገላ ውብ ምሳሌ፣
እሳት ሆኖ ካነደደው
ስትዳብሺኝ መላ አካሌ ።
ይቅርብኝ አላይሽም
አላገኝሽም እንደ ሰው፣
ይህ ኑረቴ ለዘላለም
አንቺን ማሰብ መች አነሰው!!!?
ኣ
ላ
ገ
ኝ
ሽ
ም።
[ ተፃፈ በጉልላት አበበ 2013ዓ.ም ]
ነገሮችን ሁሉ ከአእምሮ ጋር በሚያያዝ መልኩ ለመተርጎም እንሞክራለን። በዚሁ አካሄዳችን የጽናትን ሁሳብ ስንመለከት በምን መልኩ ውስጣችንን ሊጎዳ እንደሚችል ማሰብ ይኖርብናል። እስኪ ማንም ለቁም ነገር ባይፈልግህ ወይም አንተ ልታደርገው የተገባህ ነገር በተደጋጋሚ ለሌላ ሰው ታልፎ ቢሰጥ አለመስራትህ ከሚያስደስትህ ይልቅ አለመታመንህ ሊያምህ ይችላል። እምነትን ምንገበየው ደግሞ አንዱ መንገድ ታማኝ ማንነት የሚያሰጠንን ጽናት መያዝ ነው። ችግር ሚፈጠረው ግን ወጥ የሆነ ማንነትን ለመያዝ ከወላዋይነት ስንሸሽ ድንበሩን ጥሰን ግትርነት ጋር እንደርሳለን። ግትር መሆን ማለት በአጭሩ በቂ ምክንያት ተሰጥቶንም አለመንቀሳቀስ ነው። ይሄ እጅግ የከፋ ነው።
ስለዚህ "ባላንሱን" ማወቅ ይኖርብናል። ከወዲህ በኩል ምክንያታዊነትን እና ተራማጅነትን መያዝ ከግትርነት ይጠብቀናል። ከወዲያ ደግሞ በቃል አለመጽናትን በሀሳብ አለመዝለቅን መራቅ አለብን። ይህ ካልሆነ የአእምሮአችን ጤና ከግንኙነቶቻችን ጋር እጅግ የተቆራኘ በመሆኑ የባህርይ ችግራችን መልሶ የኛኑ ጤና ይነሳናል። ጭንቀት ድብታ ሊሰፍርብን ሰፊ እድልም ይኖረዋል።
ጀምሮ መቀጠል ተናግሮ መተግበር አስቦ ማድረግ እጅግ ከባድ ቢሆንና ፍጹም መሆን ባንችልም ቢያንስ ልንታመን ሚያበቃን ያህል መሆን ይኖርብናል።
ይህን ሀሳብ ስናጠቃልል የመጨረሻው ነጥብ ሊሆን የተገባው እጅግ ግልጽ የሆነው የአለመጽናት በሽታችን ሚገለጥበት ስፍራ ላይ ጥቂትም ቢሆን ማውራት ይጠበቅብናል። በሀሳብና በአቋም አለመርገጥ በቃላት ከሀሳብና ከቃላት ጋር አለመስማማትን በቂ በሚባል ደረጃ ጀምረናል። ቀረን ምለው ቢኖር ቃላት ከተግባር ጋር እንዲሁም ተግባር ከሌላ ተግባር ጋር ሚያጋጥማቸውን መፋለስ ነው። ኤመርሰንን "ምትሰራው እጅግ ይጮሃልና ምታወራውን መስማት አልቻልኩም" ያስባለው ይሄ ስፍራ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ መፋለስ በግንኙነቶቻችን ያጋጥሙናል። በርግጥ ምናስተውለው ከሰው በኩል ሲደርስብን እንጂ የኛን ጥፋት ለማስተዋል እጅግ ታውረናል። የሆነው ሆኖ ጓደኛ ለማቆየት ወይም ስሜቱን ላለመጉዳት ስንል የውሸት ተስፋዎችንና የሀሰት ፍቅሮችን እያዘነብን እንከርምና ብዙ ሳይቆይ በአንደበታችን ከሰቀልነው ፎቅ ላይ ስራችን ያለ ርህራሄ ይፈጠፍጠዋል። (እንዳልኩት አይምሮህ ሚያስታውሰው የፈጠፈጡህን ብቻ ነው) ስለዚህ ከኛ በኩል ስንነሳ ለማንም ሰው መራራ እውነታ ወይም ከባድ ሀቅ ለጊዜው ቢያስከፋና ቢያቃቅር እንኳ ከዚህ ሁሉ አድነዋለው ሚለን ውሸታም አንደበት የኋላ ኋላ ማይሽር ቁስል ሰውየው ላይ በስማችን እንዲፈረም ያደርጋል። ይህን ካስተዋልን እንግዲህ በጊዜውና በቦታው መነገር ያለበትን ነግረን መፍትሄ መፈለጉና ርቀት መጠበቁ እጅግ የተሻለ አማራጭ ነው። ከሰው ወደኛ ለሚመጣው ደግሞ ሁል ጊዜም ሰዎች ሌላውን ላለመጉዳት ወይም መልካቸውን ላለመበላሸት ከሁለት በአንዱ ወይም በሁለቱም አንድ ላይ እየተመሩ ሚኖሩ ፍጡራን ስለሆኑ ሚነግሩህን ከነዚህ አንጻር ተመልክተህ ብዙ ላለማመን ሞክር ተጨባጭና ቀጣይነት ያለው ቃላቶቹንና ቅጽበታዊ ተግባሮቹን ሚያጸና ባህርይ እስክትመለከት ድረስ። ለኔ ይህን ያህል ቦታ አለው ብለህ ለመደሰት አትቸኩል።
እንግዲህ አንድ ሆነን ሳለን ብዙ እንሆናለን አንድ አንደበት እርስ በርስ ሚዋጉ ቃላትን ያፈልቃል አንድ አካል እጅግ የተራራቁ መልኮችን ያሳያል የሰውን እንደ አመጣጡ መመለስንና መረዳትን እየተማርን የራሳችንን ማንነት ደግሞ መልሰን ወደ አንድነት ለመመለስ መሮጥ ይኖርብናል። በዚህ ሂደት ምናስመዘግበው ለውጥ ሁሉ በቅርብም ይሁን በሩቅ ብዙ ዋጋ ይከፍለናል። አዲስ በመሸለምም ይሁን ጉዳትን በመቀነስ መልካም ይሆንልናል። በአእምሮአችን ጤና በግንኙነቶቻችን መዓዛ በስራችን ውጤታማነት ብዙ መኸር አጫጆች እንሆናለን።
© The Bored Therapist
ከመፅሐፍ ቤት

ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው አለ
የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ
ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?
ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?
‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት፡፡
በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡
ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡
ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አወከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት፡፡
ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ
እኔም ለምን አልኩት
እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡
ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው፡፡
ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም፡፡
📚📖 ከመፃህፍት አለም📖📚
📚꧁༻༒༺꧂📚

ስንዱ አበበ ስለ መኖርና አለመኖር ይህን
ታስባለች ።
✨# ስንዱ ፡- አለመኖር የሚባል ነገር የለም፡፡ አንዴ ከተፈጠርክ በኋላ መኖር ብቻ ነው
የምትችለው፡፡ ቦታና ቅርጽ ልትቀይር ትችል ይሆናል እንጂ አለመኖር የለም፡፡ የት ሔደህ ነው
የማትኖረው? መሬት ውስጥ ተቀበርህ እንጂ አልኖርክም ማለት ነው እንዴ? እኔ
በዘለዓለማዊነት አምናለሁ፡፡ እንኳን አንተ የተፈጠርከው ያልተፈጠሩትስ የሉም እንዴ? አንተ
“ተፈጠርኩ” ብለህ ልደትህ በሚከበርበት ቀን ነው እንዴ የተፈጠርከው? ያኔ ነው “ሀ”
ብለህ መኖር የጀመርከው? ከዚያ በፊትስ? እናትና አባትህ አልነበሩም እንዴ? የእነሱ
መገናኘት አንተን አምጥቶሃል፡፡ ከሌለ ነገር ላይ ተቀጥለህ ነው የመጣኸው? አባትና
እናትህ ያሉ ናቸው ። ስለዚህ አንተ ሳትወለድ በፊትም በሌላ ቅርጽ ነበርክ፡፡
ካሁን ቀደምስ በምድር ላይ በሌላ ቅርጽ ኖረህ ቢሆን? በአንበሳ ወይም በእጽዋት መልክ
ኖረህ ሊሆን ይችላል፡፡ አፈር ውስጥስ ሕይወት የለም? ተቀብረህ ስጋህ ፈራርሶ አፈር ሲሆን
አፈሩ የትም አይሄድም? ምንም አያበቅልበትም? የልደትህ ቀን ሰው ሆነህ የመጣህበት
እንጂ የተፈጠርክበት ቀን አይደለም፡፡ ዘጠኝ ወር በእናትህ ሆድ ውስጥ ሰው ሆነህ እኮ ነው
የነበርከው፡፡ ከሞትክ በኋላም ወይም ትል ትሆናለህ ፤ ወይም አፈር ትሆናለህ፡፡ አለመኖር
የሚባል ነገር የለም፡፡ ተፈጥረሀል፡፡ ዘለዓለም ትኖራለህ፡፡ ቆመህም፣ ሞተህም ትኖራለህ፡፡
ሞት ፎርምህን ነው የሚያስቀይርህ እንጂ ወደ አለመኖር አይወስድህም።
!!

#Platonic_Love - (Classical Philosophy)
(ፕላቶአዊ ፍቅር)
____
ግሩም ከሆነ የፍልስፍና እሳቤዎች አንዱን ፕሌቶ ከክርስቶስ ልደት 385 ዓመታት በፊት በጻፈው The symposium መጽሐፍ ውስጥ እናገኘዋለን። ይህ መጽሐፍ በታላቁ የቲያትር ደራሲ አጋቶን ቤት ስለተዘጋጀ የራት ግብዣ ያትታል። ብዙ ጠቢባን ጣፋጭ ምግብን ሊመገቡ፣ ወይን ሊጠጡ እና ቁምነገር ሊያወጉ ታደሙ፡፡ በወንበሮቻቸውም ላይ እንዳሉ የተጠበሱ ምግቦችን እና ጣፋጭ አትክልቶችን መመገብ ጀመሩ፤ ግማሾቹ የወይኑ ስካር በአናታቸው ላይ ይወጣ ጀምሯል። እናም የድግሱ አዘጋጅ የነበረው አጋቶን ሁሉም እየተነሱ ስለ ኤሮስ ወይም ስለ ፍቅር የሚስማቸውን እንዲናገሩ ጋበዛቸው፡፡ እናም ፕሌቶ ንግግር ማድረግ ጀመረ፤ ፍቅርን በሁለት ከፈለው -
የመጀመሪያው ምድራዊ ፍቅር ሲሆን፣ ሁለተኛው ፍጹም ንጹህ የሆነ መለኮታዊ ፍቅር ነው፡፡
ምድራዊ ፍቅር የፍቅር መነሾ ነው፡፡ ልክ መስላል ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ እንደምንወጣው ሁሉ፣ ይህም ወደ ፍጹማዊ ፍቅር የሚያደርስ ጅማሮ ነው:: በውስጡም ወሲባዊ ፍላጎት እና ምኞትን ይይዛል። ይህ ፍቅር የሚገናኘው ከሰውነት አቋም እና ከፊት ማማር ጋር ስለሆነ፤ ቆዳ ሲሸበሸብ፣ ጸጉር ሲሸብት የሚጠፋ ፍቅር ነው።
ንጹህ ፍቅር - በአንጻሩ ከነፍስያ ጋር ይቆራኛል። በዚህ ፍቅር ውስጥ ስንሆን ከፊት ገጽታም በላይ ጠልቀን የምንገባበት እና ስለ ሰውነት መቀየር ግድ የማይሰጠን እንሆናለን፡፡ ይህ ሁለት ነፍሶች በፍቅር የሚወድቁበት ቦታ ነው።
ዛሬ ላይ እንደዚህ አይነቱን ፍቅር ለመግለጽ platonic love የሚል ቃልን እንጠቀማለን፡፡
ፕሌቶ የፍትወት ፍላጎትንም ይቅር አስፈላጊ አይደለም አላለም። ይልቁኑ አንድን ሴት በመልኳ ተማርከን ልንቀርባት እንችላለን፤ ሆኖም ይህን ምድራዊ ፍቅር ንጹህ ወደሆነው መለኮታዊ ፍቅር ማሻገር ይጠበቅብናል፡፡ ፍቅራችን ከሰውነቷ ጋር ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህም በላይ ነፍሶቻችን ሊቆራኙ ይገባል። በእርጅና ዘመናችን አብሮን የሚሆን እና ከውበታችን መክሰም ጋር የማይጠፋ ፍቅር ውስጥ መሆን አለብን።
እውነተኛ ፍቅር እውር አይደለም፤ ሆኖም በማስተዋል እና በጥበብ ይመራል፡፡ ከመልክ፣ ከቁንጅናም በላይ ይሄዳል። የተጣመሩ ነፍሳት ፍቅራቸው ከምድራዊው ዓለም አይደለም።
_
https://t.me/gulilatab
#ዋቢ(Reference)
- Classical Philosophy
- ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጥስ
metsihafbet

Telegram
Gulilat Abebe
😂
7⃣ ዐይን-ገላጭ የጃፓኖች የሕይወት ጭብጥ!
1⃣
፨ በሕይወት ውስጥ ዓላማህን ድረስበት።
፨ ሰርክ ማለዳ የመንቃትህን ምክንያት እወቅ።
፨ አስፈላጊነትህን (ለዓለም)፣ ጥንካሬህን፣ ዝንባሌህን የተወዳጀ የሆነ ነገር አስስ። ይሄ ነው ለሕይወትህ ትርጉም የሚሰጣት።
2⃣
፨ መለወጥ የማይቻልህን ነገር ተወው፣ ልቀቀው።
፨ ካንተ ቁጥጥር ውጪ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን እና ያም ያለ መሆኑን ተረዳ። ሂድ እና መቀየር በምትችለው ነገር ላይ ትኩረት አድርግ።
3⃣
፨ በጎዶሎነት ውስጥ ሠላምን አግኝ።
፨ ራስህ እና ሌሎችን ጨምሮ በሕይወት ውስጥ ምንም ነገር ፍፁም አለመሆኑን ተገንዘብ።
፨ ለእንከን-የለሽነት ከመትጋት ይልቅ ሕይወትን ልዩ በሚያደርጋት ጎዶሎነት ውስጥ ደስታን አጣጥም።
4⃣
፨ በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ።
፨ ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት-ብስለትህን እና ራስ-ገዝነትህን አሳይ።
፨ ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ።
5⃣
፨ ራስህን ከማንም ጋር እንዳታወዳድር።
፨ ሁሉም የተለየ ጊዜ-ቤት እና ልዩ ጎዳና አለው።
፨ ራስህን በሌላው ለመለካት ከመሞከር ይልቅ በራስህ መሻሻሎች ብቻ ማተኮርህ አስፈላጊ ነው።
6⃣
፨ ሰርክ በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ውስጥ መሻሻሎችን ፈልግ!
፨ ጥቃቅን ለውጦች እንኳ መጠራቀም ችለው በጊዜ ሂደት ውስጥ ግዙፍ ለውጥ ያመጣሉ።
7⃣
"ተማሪዎቹ ሲዘጋጁ መምህሩ ይገኛል። ተማሪው የምር ዝግጁ ሲሆን ግን መምህሩ ይሰወራል።"
―Teo Te Ching
👉 (እንዴት) ስለመማር እና በዘዴው ስለመጠበብ ማወቂያ መንገድ ነው። ከዕውቀቱ ለመድረስ ሶስት ደረጃዎች አሉት።
፨ SHU: የአንዱን አዋቂ (master) ትምህርት በመከታተል መሰረቶቹን መቅሰም!
፨ HA: ከአዋቂው የተቀሰመውን ትምህርት ከሙክረት በማዋሃድ የተግባር ልምምድ መጀመር።
፨ RI: ይሄ ደረጃ የሚያጠነጥነው ፈጠራዎች ላይ እና ትምህርቶቹን በተለያዩ መስኮች የመተግበር ችሎታ ላይ ነው።

🌗በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ በስተመጨረሻም ቀናቶቹ ሁሉ ትርጉም አልባ ሆኑበት፡፡
📍የ”አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ይመስለኛል፡፡ እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው፡፡ ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አያምንም ነበር። ሃይማኖቶች እግር ይከዳቸዋል፡፡ …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም፡፡ በዚህች ሰከንድ በሰውነታችን ውስጥ ህዋሳት እየሞቱ እራሳቸውን ባያድሱ ህልው መሆን አንችልም፡፡ ሞት እንደብዙዎቻችን እምነት፣ የህይወት ማብቂያ አይደለም፡፡ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ መሸጋገርያ ድልድይ እንጂ ፣ የብዙዎቹ ሐይማኖቶች መሠረቱ ይሄ ነው ። እኛ ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም፣ ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ። ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡
💡ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ። በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል።የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነው። ሞትና ሕይወትም ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ ለሕያዋን ሁሉ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ አስር ዓመትም፣ መቶ ዓመትም፣ ሺ ዓመትም በሕይወት ብትኖር ከሞት ጋር ክርክር የለህም፣ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን በማስተዋል ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡
🔑ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ህይወት በትክክለኛው መንገድ ከተኖረ ሞት አይፈራም። ህይወትን ከኖራችሁ ሞትን በፀጋ ትቀበላላችሁ ምክንያቱም እንደ እረፍት፣ እንደ እንቅልፍ ትመለከቱታላችሁ። ከህይወት ጫፍ መድረስ ከቻላችሁ ሞት ውብ እረፍት ፣ ብረከት ይሆናል። በተቃራኒው ካልኖራችሁ ግን በርግጠኝነት ሞት ጊዜያችሁን ፣ የህይወት እድሎቻችሁን ይነጥቃችኋል። ካልኖራችሁ ነገ የሚባል ነገር የለም ፍርሃት ይነግሳል። ፍርሃቱ የሚመጣው በሞት ሳቢያ ሳይሆን በደንብ ህይወትን ካለመኖር ነው።"
ሁማኒቲይ😍