Grade 12 news
37 subscribers
23 photos
7 links
Download Telegram
የ2017 ዓ.ም የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት መግባት ጀምረዋል።

በሦስተኛ እና አራተኛ ዙር ፈተናቸውን ለሚወስዱ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች አቀባበል ሰኔ 28 እና 29/2017 ዓ.ም እንደሚካሔድ ከዚህ ቀደም በወጣ መርሐግብር መገለፁ ይታወቃል።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 01-08/2017 ዓ.ም በሁለት ዙር ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister
የ2017 ዓ/ም ዘመነ ትምህርት የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቅያ ፈተና ለመፈተን በመቐለ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዛሬ እሁድ ሰኔ 29 / 2017 ዓ/ም መግባት ጀምረዋል ::

ለ11ኛ & 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ኦንላይ የክረምት ትምህርት ለመከታተል 👈

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛዉ ዙር ፈተና ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነዉ

በ2ኛው ዙር ፈተና ላይ የሚቀመጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በዛሬው እለት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ እየገቡ ይገኛሉ።

በበይነ መረብ ከ450 በላይ ተማሪዎችን እንዲሁም በወረቀት ደግሞ ከ8ሺህ በላይ ተማሪዎችን እንደምያስፈትን ከፈተናው አስተባባሪ ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኝ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከማረፍያ ቦታዎች ጀምሮ፣ የምግብ አቅርቦት እንዲሁም የህክምና አገልግሎትን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ቀደም ብሎ ኮሚቴዎችን በማዋቀር በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ለ2ኛው ዙር ፈተና ከጌዴኦ ዞን፣ ከኦሮሚያ ክልል እና ከሶማሌ ክልል ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ተጠቃለዉ የሚገቡ ሲሆን፣ በነገው እለት ቅድመ ፈተና ገለፃ የሚሰጥ ይሆናል።

ለ11ኛ & 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ኦንላይ የክረምት ትምህርት ለመከታተል 👈

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister
ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል።

ተፈታኞች በጠዋት መርሐግብር የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና እየወሰዱ ሲሆን፤ ከሰዓት በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና የሚጠናቀቅ ይሆናል። ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን ሲሰጥ ቆይቷል።

በሦስተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ ተቋማት የገቡ ሲሆን፤ ፈተናው ነገ ሐምሌ 0/2017 ዓ.ም መሠጠት ይጀምራል።

ለ11ኛ & 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ኦንላይ የክረምት ትምህርት ለመከታተል 👈

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister
የ2018ዓ.ም የትምህርት ካላንደር

ለ11ኛ & 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ኦንላይ የክረምት ትምህርት ለመከታተል 👈

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister
#NationalExam🇪🇹

ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት ተማሪዎች ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዕፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀማቸው ከፈተናው መታገዳቸውን የመቱ ዩንቨርስቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኃላ ወጣ ያለ ፀባይ እያሳዩ ነበር " ብለዋል።

ዩኒቨርስቲውም ለፈተናው ከተቋቋመ ኮማንድፖስት ጋር በመሆን የመቆጣጠር ሥራ ሲሰራ እንደነበር በማንሳት፤ ሦስቱ ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አደባባይ ላይ ትንኮሳ መፈፀማቸውን ተበድለናል ብለው በመጡ ሴቶች ቅሬታ እና ዩንቨርስቲውም ባደረገው ማጣራትብ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጧል።

" ትንኮሳ አድራጊዎቹ በአደባባይ ሴቶችን በግድ መሳም፤ ልብሳቸውን መገለብ እና መንካት የማይፈቀድ የአካላቸውን ክፍል በመንካታቸው ሴቶቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብለዋል።

በዚህ የተነሳ የትንኮሳ ወንጀል በፈፀሙ ወንዶች ላይ ከዘንድሮው አመት ፈተና እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ አንዱ ከኢሉ አባቦር ዞን በቾ ወረዳ ሁለቱ ደግሞ ከምስራቅ ወለጋ የመጡ መሆናቸውን ፕረዝዳንቱ አክለዋል።

እርምጃ ከተወሰደ በኃላ በግቢው ሲስተዋል የነበረው የተማሪዎች ሥነ ምግባር መሻሻሉንም ተናግረዋል።

ወደፊትን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠር ትምህርት ቤቶች የፈተና ሥነ ምግባር ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት  አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ሴት ተማሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁና ለትንኮሳ ራሳቸውን እንዳይጋብዙም ጠይቀዋል።

የመቱ ዩንቨርስቲ በዘንድሮው ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ14,000 በላይ ተማሪዎችን ለመፈተን መቀበሉንም ዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አለሙ ድሳሳ አክለው ገልፀዋል።
👏1