Grace Commission
2.54K subscribers
8 photos
4 links
የታረቀ ማኅበረ ሰብ _ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥20
Download Telegram
የልጁ መልክ

የክርስትና ዋና ግብ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን መምሰል ነው። ይህ የእግዚአብሔር ዐላማ፣ ከመፈጠራችን በፊት የታቀደ ነው። እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና።" ሮሜ 8፥26

እንዴት ያለ ድንቅ ውሳኔ ነው!

ይህን ዘላለማዊ ዐላማ እውን ለማድረግ፣ እግዚአብሔር ዛሬም እየሠራ ነው፤ በክርስቶስ በኲል በእኛ ውስጥ የጀመረው ሥራ ገና አልተጠናቀቀምና።

ሕይወታችን በምንም ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ፣ እግዚአብሔር ዐላማውን አይተውም። በምናልፍበት በእያንዳንዱ ሁኔታ፣ የራሱን ዕቅድ እየፈጸመ ነው። ሁሉንም ነገር፣ ሁሉንም አጋጣሚ ወደ አንድ ክቡር ፍጻሜ ለማምራት ይጠቀምበታል። እኛ ዝም ያለ በሚመስለን ጊዜም እንኳ፣ ርሱ ያለማቋረጥ እየሠራ ነው።

ስለዚህ ልጁን የማይመስል ነገር ሁሉ ከሕይወታችን እየጠረበ ይወገዳል። ክርስቶስም በሕይወታችን በሁሉ ነገር ቀዳሚ ስፍራውን እንዲይዝ ያደርጋል። አሜን!

ኢየሱስን የማይመስል ማንኛውም ባሕርይ፣ አስተሳሰብ እና አኗኗር ከእኛ ላይ፣ ደረቅ ቅጠል ከዛፍ ላይ እንደሚረግፍ ይርገፍ! የክርስቶስ መልክ ግን በእኛ ውስጥ ዕለት ዕለት ይገለጥ። አሜን!

* ከላይ ያለው ታሪክ የተወሰደው፣ ሮናልድ ደን "ሰማዩ ዝም ሲል" በሚል ርእስ ከጻፈው መጽሐፉ ነው።
11🔥8👏2
#ወንጌል ለሁሉም፤ ሁሉም #ለወንጌል!
3👍3
"ስለ ነገሮች የምናውቀው ዕውቀት እጅግ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም፣ ማን መሆናችንን ማወቅ በጣም የላቀ ዕውቀት ነው። ምክንያቱም፣ ማንነትን ማወቅ ራስን ማወቅ ነው፤ ራስን ማወቅ የተፈጠርንለትን ዐላማ ማወቅ ነው፤ የተፈጠርንለትን ዐላማ ማወቅ አካሂያዳችንን ማሳመር ነው" _ብሬኒ ብራውን
11👍3
ጌታ እንዴት ቸር ነው?

የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ለ2018 ዓ.ም. ለሚያደርገው የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት፣ የራሴ መጽሐፍ እና ኹለት አርትዖት የሠራሁላቸው መጻሕፍት በዕጩነት ቀርበዋል። እነዚኽን መጻሕፍት አንብባችሁ ከተጠቀማችሁ ድምፅ በመስጠት እንድታበረታቱን እጠይቃለኹ።

👉 የእኔ እና የእኅት ኤልሳ ጀንበሬ መጽሐፍ በመንፈሳዊ እድገት ዘርፍ ዕጩ ኾኖ ቀርቧል፦
👉 የፓስተር መኳንንት ዓለሙ ደግሞ በተግባራዊ ነገረ መለኮት ዘርፍ ዕጩ ኾነው ቀርበዋል።
👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZMqmGgXJMRGUIvi6ZrTucv_j4H8vTTTe1vt-hpvod4AHvnQ/viewform
6
2👍2
4👍3
የመጽሐፌን ጥቂት ኮፒዎች በሚከተሉት አድራሻዎች ማግኘት ይቻላል፦

👉 ስታዲየም መሠረተ ክርስቶስ መጻሕፍት መሸጫ ሱቅ
👉 አያት _ +251946627622
👉 ኻያ ኹለት _ +251911112308

ይህ መጽሐፌ ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ለ2018 ዓ.ም. ለሚያደርገው የመጽሐፍ ዕውቅና ሥነ ሥርዐት ዕጩ ኾኗል። ያነበባችሁት እና ድምፅ ያልሰጣችሁ ወገኖች ድምፅ እንድትሰጡ አበረታታለኹ።
👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZMqmGgXJMRGUIvi6ZrTucv_j4H8vTTTe1vt-hpvod4AHvnQ/viewform
4