The Gospel of God
2 subscribers
2 photos
2 links
የክርስቶስ ወንጌል
Download Telegram
Channel created
Selam endet nachu yabate brukan bekerbu bezih ye telegram chanal menfesawu timhrtoch
Adadis mezmuroch
Koyet yalu mezmoroch
Tiyakena mels
Ena lelochunm programoch yzen enmetalen eskeza dena hunu
Channel photo updated
ጌታ በብዙ ከመከረኝ በጥቂቱ

ራስን መግዛት

፨ብዙዎቻችን ተነክተን አለመንካትን,ተሰድበን አለመሳደብን,ወይ ደግሞ በሚገባን ቀላል አማርኛ ተነቁረን😁 አለመናቆሮን ይሄ ዶሮ መንፈስ😂 በአጠቃላይ ስለ እኛ በሆነ ማንኛውም ጉዳይ ተነስቶ ያንን ነገር አለመመለስን እንደ ትልቅ ሽንፈት ነው ምናየው። ዝም ካልን ሞኝ,ፋራ,ቀልድ ማያውቅ ,ህፃን,ግግም ያለ ሰው ነው መባልን ስለምንፈራ መመለስን እንደ ትክክለኛ ውሳኔ እናየዋለን።
፨አስተዋይ ግን ዝም ይላል
፨መመለስ ትክክለኛ ውሳኔ አይደለም
፨እያመመህም ቻለው
፨ ሠው ስትነሳም ያጨበጭባል ስትወድቅም በአንተ ላይ አስተያየት ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም።
፨ ራስን መግዛትን ተማር።
፨ራሱን የሚገዛ ከተማ ከሚገዛ ይበልጣል።100%
፨ስለተናገርክ አሸናፊ ነህ ማለት አይደለም።ዝም ስላልክም ተሸናፊ አይደለህም።
፨ዝም ያልከው መናገር እና መመለስ ስለማትችል ሳይሆን አስተዋይ ስለሆንክ ነው።
፨ራስህን መግዛትን ለራስህ ደጋግመህ አስተምረው።
፨ ዝም በል።ቀልድ አያውቅም ይበሉህ,ግግም ያለ ሰው😂 ነው ይበሉህ።እንዳንተ ያሸነፈ የለም።
፨ነገርህን ሁሉ እግዚአብሔርን ከማክበር አንፃር አድርገው።በዛ ሠዓት እናውቃለን,እንደኛ ሚናገር የለም,ሞኝ ነው ካሉህ ሁሉ አንተ ነህ አሸናፊው🏆🥇።ዝም ያልከው መናገር ስለማትችል አደለም አስተዋይ ስለሆንክ ነው።
፨ራሳችንን እንግዛ
፨መናገር ማሸነፍ አይደለም ።ዝም ማለት ሞኝነትና መሸነፍ አይደለም።
፨ቢናገር ሊያሳፍርህ ይችላል ምትናገረው ዝምታን የመረጠው ።
፨ራሳችንን እንግዛ በድጋሚ
፨መመለስ እድገትና እውቀት አደለም።አለመመለስ ደግሞ ማነስና ውርደት አደለም በልጦ መገኘት ነው።ተሽሎ መገኘት ነው።
፨መናገር እውቀት ሚመስለን ዝም ማለት ግግምና ሚመስለን ሞኝነታችንን ተረድተን ራስን ወደ መግዛት እንምጣ።
ቶሎ የሚከበንን ኃጢአት ማስወገድ
~~~~

ኢየሱስ ከዮሐንስ እጅ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመናችን ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ ነፃ ወጥተናል። የባሪነት ቀንበራችን ተሰብሯል። ዓለም በባሪነት ውስጥ ቢኖርም፣ እኛ ግን በነፃነት ለመኖር ነፃ ወጥተናል። ክብር ለአዳኛችን ይሁን! ከኃጢአት ነፃ ወጥተናል ማለት የኃጢአት ፈተና የለብንም ማለት አይደለም። ከኃጢአት ነፃ ብንወጣም፣ አሁንም የኃጢአት ፈተና አለብን። ከኃጢአት ጋር ውጊያ አለብን። ኃጢአት ይከበናል። የዓለም ፍቅር ይከበናል። ሥጋዊ አስተሳሰብ ይከበናል። የገንዘብ ፍቅር ይከበናል። የባለጠግነት አሳብ ይከበናል። የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል እንዳንመሰክር ይተበትቡናል። ለእግዚአብሔር መንግስት እንዳንኖር ይጎትቱናል። በሚያታልል ምኞት ይስቡናል።

ጳውሎስም ተከቧል። ግን በእምነትና ለእግዚአብሔር መንግስት በመኖር ድል አድርጓል። ሥጋውን ጎሰመ። ምድራዊ ብልቶቹን ገደለ። ነፍሱ በእርሱ ዘንድ እንዳትከበር እንደ ከንቱ ነገር ቆጠረ (ሐዋርያት 20:24)። ነፍሱን ለወንጌል ሥራ አሳልፎ ሰጠ። ጳውሎስ በኃጢአት ቢከበብም፣ የከበበውን ኃጢአት በእምነት በማስወገድ መንፈሳዊ ሩጫውን በድል አጠናቋል።

📌“ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።” (ሐዋርያት 20፥24)

ከጳውሎስ አጋር ሰራተኛ የሆነው ደማስም በዓለም ተከቧል። ከበባውን ግን በእምነት ድል ማድረግ አልቻለም። ተሸነፈ። የከበበውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻለም። ንጉሱ ሰሎሞንም በኃጢአት ተከቦ ነበር። በዓለም ፍቅር ተከቦ ነበር ነገር ግን ድል ማድረግ አልቻለም። የከበበውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻለም። ተሸነፈ። በመጨረሻም ለጣኦት በመስገድ እግዚአብሔር እጅግ የሚጸየፈውን ኃጢአት ፈጸመ። እስራኤልውያን ከግብጽ ባሪነት ከወጡ በኋላ፣ በኃጢአት ተከበው ነበር። በሥጋ ምኞት ተከበው ነበር። ከመና ይልቅ የግብጽን ዱባና ዓሳ እንዲሁም ሥጋ ተመኝተው ነበር። የከበባቸውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻሉም። ብዙዎቻቸው በምድረ በዳ ወደቁ። እግዚአብሔርንም አስቆጡት። ከግብጽ ቢወጡም ወደ ተስፋይቱ ምድር ከናዓን አልገቡም። በኃጢአት ተሸነፉ።

ጌታችን ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በውኃውና በደሙ ካስወገደ በኋላ የኃጢአት ስርየት ብቻ አይደለም የሰጠን። ተልዕኮም ስጥቶናል (ማቴዎስ 28:18-20)። ያም ተልእኮ ወደ ዓለም ሁሉ እንድንሄድ፣ የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል እንድንመሰክር፣ ነፍሳትን እንድናድን፣ የእሱን ትምህርት እያስተማርናቸው ደቀ መዛሙርት እንድናደርጋቸው ነው። ሆኖም ግን ይህን የጌታን ተልዕኮ እንዳንፈጽም ኃጢአት ይከበናል። የዓለም ፍቅር ይከበናል። የገንዘብ ፍቅር ይከበናል። የሥጋ መሻት ይከበናል። ግን ማሸነፍ እንችላለን። ማስወገድ እንችላለን። ማሸነፍ የምንችለው በአንድ ነገር ብቻ ነው። እርሱም በእምነት ነው። በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ በእምነት መሳተፍና እስከ መጨረሻ ራስን ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል። እጃችንን አጣጥፈን በመቀመጥ የሚከበንን ኃጢአት ማስወገድ አንችልም።

📌የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፦ “...እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብራውያን 12፥1-2)
ጥረታችሁን ሳይሆን መጠራታችሁን አስቡ




#የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ
1ቆሮ 1-30

* መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ብዙዎች በመንፈስ ጀምረው በስጋ የሚጨርሱበት ምክንያት አንዱ ጥረትን ማሰብ ዋንኛ የውድቀት መንደርደሪያ ሲሆን እንመለከታለን Example ሳዖልን ብንመለከት አህያ ፍለጋ በወጣበት እግዚአብሔር እንደቀባው እንመለከታለን ከነገሰ በኋል ግን የእግዚአብሔርን ሀሳብ ከመፈፀም ይልቅ የራሱን ሀሳብ ለማስፈፀም ሲራሯጥ እንመለከታለን በዚህ ምክንያት ከእግዚአብሔር ሀሳብ ወቶ ዘመኑን ሲጨርስ እንመለከታለን.




⛩️⛩️⛩️ ከሰይጣን ጋር ከመሮጥ ከእግዚአብሔር ጋር ማንካሳት ቶሎ ያደርሳል!!!!
1⃣
የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጥ
ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና (1ኛ ዮሐንስ 4፥8)
፦መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላል! ይህ ቀላልአረፍተ ነገር ቢሆንም እጂግ ጥልቅ ነው።ነገር ግን ትርጉሙ ምንድነው? እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ እርሱ ምንድነው የሚመስለው? ወይም ደግሞ ፍቅር ምንድነው የሚመስለው? ለትውልዶችና በሺህ ለሚቆጠሩ አመታት የዚህ መረዳት መገለጥ ለብዙ ሰዎች ግልፅ ያልሆነ ነበር።ምክኒያቱም እግዚአብሔርን ያየው አንድም ሰው አልነበረም (1ኛ ዮሐንስ 4:12)።ስለዚህም እግዚአብሔር ማን እንደነበረና ፍቅር ምን እንደሆነ የነበራቸው መረዳት ከእውነቱ የራቀ ምናባዊ እይታ ብቻ ነበር።
፦ነገር ግን "እኔን ያየ አብን አይቶአል...."ብሎ የተናገረው ኢየሱስ መጣ (ዮሐንስ 14:9)።ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ አምላክ ነበረ (1ኛ ጢሞቴዎስ 3:16)።በገሊላ መንገዶችም በሚመላለስበት ጊዜ እርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር አካላዊ መልክ መገለጥ ነበር።1ኛ ዮሐንስ 4:9እንዲህ ይላል "በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።"ኢየሱስ ለእኛ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር ነበር።እርሱ የተገለጠ ፍቅር ነበር።ይህ ነገር እኔ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ካገኘኋቸው እጂግ አስደናቂ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው።ይህም ወደ እኔ የመጣው በራዕይ መልክ ነበር።ፍቅር እንደ ሰው ሆኖ ከፊት ለፊቴ ሲራመድ አየሁኝ።ያም ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር ! በእውነትም ኢየሱስ ፍፁም የሆነ የፍቅር ምንነት መግለጫ ነው! ከዚህ በተጨማሪ?
፦መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል "ወዳጆች ሆይ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።(1ኛ ዮሐንስ 4:7-8)።ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ፍቅር ለማወቃችን ማረጋገጫው ያን ፍቅር የምናሳይበት መንገድ ነው።ምክኒያቱም ዛሬ እኛ የእርሱ ባህሪ ችሎታና ማንነት መገለጥ ነን።እናተ የእግዚአብሔር ፍቅር ማስረጃ ናችሁ።
፦እስካላሳያችሁት ድረስ የእግዚአብሔርን ፍቅር አውቀዋለሁ ማለት አትችሉም።የእሱ ፍቅር በእናንተ ውስጥ መታየት አለበት። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ በኤፌሶን 3:10 ላይ እንዲህ ሲል የሚናገረውን ያስታውሳል "ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤"የእግዚአብሔር እቅድና ህልም እርሱን፣የእርሱን ፍቅር፣መለኮታዊ ልቀትና ጥበብ በቤተ ክርስቲያን በኩል መግለጥ ነው።ይህም በእናንተ ውስጥ እየተከናወነ ነው።ሃሌ ሉያ!



የእምነት አዋጅ
በውስጤ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልቤ ፈስሷል። የእርሱ ፍቅር ማስረጃ፣የባህሪው፣የችሎታውና የማንነቱ መገለጥ እኔ ስለሆንኩኝ ፍቅሩ በየእለቱ በእኔ ውስጥ ይገለጣል፣በኢየሱስ ስም። አሜን።



ለተጨማሪ ጥናት
ሮሜ 5:5 & የዮሐንስ ወንጌል 4:12-13


የአንድ አመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ሮሜ 1:18-32 & መዝሙረ ዳዊት 35:37

የሁለት አመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
ኤፌሶን 3:1-12 & ትንቢተ ኢሳያስ 46
@Holy_sprit_Jesus
@Holy_sprit_Jesus
@Holy_sprit_Jesus
አምስት የእግዚአብሔር ፍቅር ባህሪያት፦

1. ፍቅሩ ቅድመ ሁኔታ የለውም (ሮሜ 5V8)።
2. ፍቅሩ መስዋዕዊ ነው (ዮሐ. 15V13)።
3. ፍቅሩ ዘላለማዊ ነው (ኤር. 31V3)።
4. ፍቅሩ ርኅሩኅ ነው (መዝሙር 103V8)።
5. ፍቅሩ [ከአንዱ ወደ ሌላው] የሚተላለፍ ነው (1ኛ ዮሐ 3V1)።

__ደስቲን ቤንጅ

@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
@Gospel_of_God
ፍቅር እንደዚህ ነው....

ፍቅር ብቁውን ወይንም ጻድቁን ሰው እወድሃለው የሚል የአንደበት ንግግር ሳይሆን ለኃጢአተኛው ሰው አንድያ የሚወደውን ልጁን እስከ ሞት አሳልፍ የሚሰጥ የእግዚአብሔር የልብ ቋንቋ ነው።

ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10

እግዚአብሔርን ጥላኝ ብትለው ሊጠላህ አይችልም ምክኒያቱም ከእግዚአብሔር ውስጥ ጥላቻን በፍጹም አታገኝም። ያለህ ነገር ሊያልቅብህ ይችላል እግዚአብሔር ግን የሚያልቅበት ፍቅር የለውም እራሱ ፍቅር ነው።

#Binarevivalist
♥️እግዚአብሔር ፍቅር ነው።

የእግዚአብሔርን ፍቅር ለማወቅ ከእግዚአብሄር ጋር በመቆየት አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ብቻ የእግዚአብሄርን ጥልቅ ፍቅር መረዳት ይቻላል። ሰማሪያዊቷ ሴት ከኢየሱስ ጋር በውሀ ጉድጓድ ሳለች ከቆይታዋ ብዛት ነበር የኢየሱስን መሲህነት የተረዳችው። የእግዚአብሄር ፍቅር የተገለጠ ነው። አለምን ሁሉ መውደዱን ልጁን ለሞት አሳልፎ ጨክኖ በመስጠቱ አይተናል።
ይኸው ፍቅሩን ቀምሰን ዛሬም በፍቅሩ ተሞልተን በርሱ ለእርሱ እንኖራለን። የመኖራችን የመጀመርያም የመጨረሻም ምክንያት በምድርም በሰማይም ከቶ አምሳያ የሌለው ወዳጅ። የእናት ፍቅር ባታይ የአባት ፍቅር ባይኖርህ እነሱን የሚተካ ሌላ ታገኝ ይሆናል። ፍጥረት የእግዚአብሔር ፍቅር ባይኖረው ሌላ ምትክ አያገኝም እግዚአብሔር ፍፁም አፍቃሪ ደጋፊ ወዳጅ ፍቅር ነው።

         sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
   @Marcil_Lyrics
@Marcil_Lyrics
@Marcil_Lyrics1
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
                          Join us
🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ
📚የእግዚአብሔር ፍቅር

(የዮሐንስ ወንጌል 4: 17-18)

17፤ ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤

18፤ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።

ጸጋ ተቀርዞ የተቀመጠ ዶክትሪን ሳይሆን አካል ለብሶ የተገለጠዉ ክርስቶስ ነዉ! ይህም ጸጋ ተቀባዩን ሳይሆን የሰጪዉን ብልጽግና የሚያሳይ ቸርነት ነዉ!

ወዳጄ፣ ጸጋ የሰዉን ሁኔታ ገላጭ ክስ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያስረዳ ስጦታ ነዉ።

ብዙ ሰዉ ክርስቶስ ከሳምራዊቱ ሴት ጋር ያደረገዉ ንግግር በመገለጥ የሆነ ማጋለጥ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ክርስቶስ በመገለጥ የሴቲቱን ሀጢአት እያጋለጠ ሳይሆን በመገለጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር እየገለጠ ነዉ።

ክርስቶስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር ያደረገዉ ንግግር ሀጢአቷን ለመግለጥ የተፈለገ ሳይሆን በዚህ ሁሉ ሀጢአት ዉስጥ ብትሆንም እንኳን፣ ከእርሷ ጋር ከመቀመጥና ከማዉራት ብሎም እርሷን ከማፍቀር እንደማይገድበዉ ሊያሳይ የፈለገበት የፍቅር ንግግር ነዉ።

የተወደድነዉ እንድንወደድ የሚያደርገን ማንነት ኖሮን ሳይሆን መዉደድና ማፍቀር የእግዚአብሔር ማንነት ስለሆነ ነዉ። እግዚአብሔር ያለምክንያት ወዶናልና በምክንያት አይጠላንም።

ወዳጄ፣ በየትኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ብትሆን እግዚአብሔር አባትህ ክርስቶስን በወደደበት የፍቅር መጠን አንተንም እንደወደደ በመረዳት በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅር ተመላለስ።

በቢንያም ተስፋዬ

@Excellent_youth
@Excellent_youth
📚ፍቅር የሚገለጠው በድርጊት ነው

ባለስልጣኖች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ቦዲጋርድ ይቀጥራሉ፤ ቦዲ ጋርዱ የሚመጣውን የትኛውም ጥቃት ለመጋፈጥ ሞት እንኳን ቢሆን ለመቀበል ወስኖ የሚገባ ነው፣ ስለ ሃብታሙ ሰው ጋርዱ ሊሞት ይችላል፡፡ሲሞት ግን ከፍቅር የተነሳ ሳይሆን ከሥራው የተነሣ ነው፡፡

ድርጊቱ ላይ ፍቅር የሚባለው ነገር የለውም ነገር ግን ገንዘብ አለው፡፡ ስለዚህ ነፍሱን ስለ ባለስልጣኑ አሳልፎ ቢሰጥ መነሻው ፍቅር እስካልሆነ ድረስ ነው፡፡

ኢየሱስ በምድር ስለእኛ እራሱን አሳልፎ ሲሰጥ መነሻው ፍቅር ነበር፡፡ የክርስቶስ ድርጊት በፍቅር ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እናንተን የወደዳችሁ የፍቅሩ መለኪያ ምንድነው? ኢየሱስ በምድር ሳለ እንዲህ ብሎን ነበር <<፤ አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።>> [ዮሐ 15፥9]

እናንተ የተወደዳችሁ አብ ልጁን በወደደበት መጠን እናንተም ተወዳችኃል፡፡ እንዴት ያለ መወደድ ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን የወደደን ስለወደድነው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር እኛን የወደደን ልጁን በወደደበት ልክ እንጂ እኛ በምንወደው ልክ አይደለም።

አሁን እኛ ያቃተን በፍቅሩ መኖር ነው! ኢየሱስ አብ በወደደው ልክ እናንተን ከወደደ እናንተም በዚህ ፍቅር ሰዎችን መውደድ አለባችሁ፡፡ ወንድሞችን በእናንተ ሁኔታ መውደድ አቁማችሁ በእግዚአብሔር ፍቅር መውደድ ጀምሩ፡፡

ፍቅር ከእናንተ ስላልሆነ አሁን በመውደድ ተቀድማችኃል! ስለዚህ በዚህ ፍቅር ወንድሞቻችሁን ውደዱ፡፡ ከእናንተ አንፃር ሰውን መውደድ አቁማችሁ በእግዚአብሔር ፍቅር መውደድ ጀምሩ፡፡

እናንተ ስትወደዱ እየበደላችሁ፤ እያመጻችሁ፤ እያመነዘራችሁ፤ እየገደላችሁ፤ በእርኩሰት እያላችሁ ነበርና ሰውንም ስትወዱ እየጠላችሁ፤ እየበደላችሁም ቢሆን ውደዱት ምክንያቱም ለመውደዳችሁ ምክንያት እነዚህ ነገሮች ስላልሆኑ! ያለ ምክንያት ሰውን ውደዱ፡፡

@Excellent_youth
@Excellent_youth
📚የወደደኝ ዳግም ላይጠላኝ ነው

ሰው ሰውን ከወደደው በኃላ ድጋሚ ማየት እስከ ማይፈልግ ድረስ ሊጠላው ይችላል። ይሄን የሚያደርገው መጀመሪያ ስላልወደደው አይደለም።

🌟አምላክ እኛን ሲወደን በሁኔታ ላይጠላንና ለእኛ ያለው ፍቅር መባና አስራት ሲናቀርብ እየጨመረ ሌላ ወቅት ላይ የሚቀንስ አይደለም! ምክንያቱም የእርሱ ፍቅር በጥቅም አልተመሰረተምና።

እግዚአብሔር እኛን ስወድ ፍቅሩን ትተን ወጥተን ነበር። ሰው ቢሆን ኖሮ ከንፈሩን እያኘከ ይህን ዓመት ሙሉ አብልቼው እንድህ ያደርገኛል ይላል ምክንያቱም ዛሬ የሚያበላክ ነገ እንድታበላው ነው።

እግዚአብሔር ግን እምቢ ብለን ከወጣንበት ከዔደን ገነት ወደ ምበልጠው መንፈሳዊ ስፍራ በአብ ቀኝ አስቀመጠን። ባይገርማችሁ እነአዳም በዔደን የሚዉሉት ከእንስሳት ጋር እንዲሁም የእግዚአብሔር ድምፅ በዔደን ገነት ሲመላለስ እየሰሙ ነው።

አሁን ግን በእኛ ውስጥ እየኖረ ከእንስሳት ጋር ሳይሆን ከራሱ ጋር አኖረን። ሰይጣን እኛን ማባረር ላይ እውነት መሳይ ውሸት እየላከ ተግቶ ሲሰራ እግዚአብሔር ግን እኛን ለማዳን እውነት የሆነውን ልጁን ይልካል።

🌟ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ምን ያህል እንደወደደን ነው። ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመጣ ኃይሉን እና ንግሲናውን እንደመቀማት አልቆጠረም፤ አንድያ ልጁን እስክ ሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ሲወድ ዳግም ላይጠላን ነው።

@Excellent_youth
@Excellent_youth
📚የክርስቶስ ፍቅር

ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች በተሳሳተ የመነሻ ሃሳብ ጌታን እናገለግላለን እያሉ ይንቀሳቀሳሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ነገር ሲያበላሹ ደግሞ ይታያል።

አንዳንዶች ጥቃትን #በጥቃት ይመልሳሉ፤ ለሚናገራቸው ሁሉ ወዲያው አጸፋውን ይመልሳሉ። ከዚህ በተቃራኒው ጥቃትን #በትዕግስት የሚያሳልፍን አማኝ ወይንም ክፉ ሲናገሩት ጌታ ይባርክህ ብሎ የሚያሳልፍን አማኝ ወይንም ክፉ ሲናገሩት ጌታ ይባርክህ ብሎ የሚያሳልፍን አማኝ ሲያዩ እንደሞኝ ወይንም እንደ ኋላ ቀር ይቆጥሩታል።

በዘመናችን ለራስ ጥቅም የማይሮጥ ሰው በማህበረሰቡ ዘንድ ያልተለመደ እንግዳ ነው። ዓለም ቁጥር አንድ ራስን #ማስቀደም የሚል ፍልስፍና አላት ወይንም ምቹ ጊዜ እስኪገኝ ድረስ ራስን #መደበቅ ሌላው ፍልስፍና ነው።

በመስቀሉ የተቃኘ ሕይወት ያለው እውነተኛ ክርስቲያን ግን ሁልጊዜ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ስለሚለው የሚያስቀድመው #የሌላውን ጥቅም ነው የራሱን ሁሉ እያጣ። ምክንያቱም እንድን እውነተኛ አማኝ የሚያንቀሳቅሰው የክርስቶስ #ፍቅር መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል፤ቃሉ እንዲህ ይላልና፦

"ይህን የምለው ራሳችንን በእናንተ ፊት እንደ ገና ለማመስገን ሳይሆን፣ በእኛ እንድትመኩ ዕድል ልሰጣችሁ ነው፤ ይኸውም በውጭ በሚታየው ለሚመኩት እንጂ በልብ ውስጥ ባለው ነገር ለማይመኩ መልስ መስጠት እንድትችሉ ነው።

ከአእምሮ ውጪ ብንሆን ለእግዚአብሔር ብለን ነው፤ ባለ አእምሮም ብንሆን ለእናንተ ነው።

የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል። በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ።"[ 2ቆሮ 5፥12-15 ]

@Excellent_youth
@Excellent_youth
Forwarded from The Gospel of God
መንፍሳዊ ልምምድ.......

አንድ ልማድ ስትጀምረው እንደማይታይ ክር ነው፤ ያ ክር እርስበርሱ ሲደጋገም ሲጠላለፍ ትንሽ ቆይቶ በቀላሉ የማበጠስ ሀያል ገመድ ይሆናል።

አየህ አሪፍ ልማድን ስትጀምረው እንደ ክሩ ስስ ነው፤ ለመበጠስ ቅርብ ነው፤ ስትደጋግመው ግን አንተ ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይፈጥራል።

ግድ የለህም በጠዋት ተንሰቶ መፀልዩ ፣ BIBLE ማንበቡን፣
ምሽግ መግባቱን ፣ ማምለኩን በቃ የጀመርከውን አሪፍ መንፍሳዊ ልማድ ሳትሰለች በትጋት ደጋግመው ፤ ከዛ መንፈስ ቅዱስ ምን አይነት ከባድ ሰው እንሚያደርግህ ታየዋለህ!
ሁሌም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የጠለቀ ህብረት ይኑራቹ, ሰዓታትን ከ እሱ ጋር አሳልፉ.... እግዚያብሔር ልጁን በናንተ ያክብረዋል...
ሁል ጊዜ በ መንፍስ የምትቃጠሉ ሁኑ.. ሮሜ 12 : 11
Share, Join, share Join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🎊🎊@Thegoldenoil🎊🎊
🎊🎊@Thegoldenoil🎊🎊
share, join share, join share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇☝️☝️☝️👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/gospelofg
ኢየሱስ ይመጣል
በትጋት ወንጌልን በመስበክ ለመንግስቱ የሚመጥን አይነት ኑሮ እየኖርን በንቃት እንጠብቅ
ኢየሱስ ይመጣል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/gospelofg