በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጎሮ ጤና ጣቢያ EPAQ Cluster አባል ተቋማት በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶር ፅጌሬዳ ክፍሌ ጎሮ ጤና ጣቢያ የኢትዮጵያ ጤና ጣቢያዎች ጥምረት ለጥራት ክላስተር ፕሮግራሙን በወጥነት በመተግበር ከተቋሙ አልፎ የአባል ጤና ጣቢያዎች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲያሻሽሉ ያስቻለ ጠንካራ አደረጃጀት መሆኑን ገልፀዋል። ዶር ፅጌሬዳ አክለውም ጎሮ ጤና ጣቢያ በብዙ ፕሮግራሞችና ኢንሼቲቮች በሀገር አቀፍ እውቅና ያለው ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች ተቋማትም ይህንን ልምድና ተሞክሮ ወስደው በመተገበር ማስፋትና እየሰጡ ያሉትን የጤና አገልግሎት ጥራት በስታንዳርዱ መሰረት ማረጋገጥ እንዲችሉ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት EPAQ Cluster እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ የተሰራ ምርጥ ተሞክሮ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም በመድረኩ ተሳታፊዎች በጎሮ ጤና ጣቢያ የመስክ ምልከታ (Site Visit) ያደረጉ ሲሆን በተቋሙ እየተሰጠ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትና የSBFR ፕሮጄክት ትግበራ ያስገኘውን ለውጥ አድንቀው ወደ ራሳቸው ተቋማትም እንደሚያሰፉ ያላቸውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጎሮ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ እንዳላማው እርቅይሁን በቀጣይ EPAQ Cluster EPAQ Cluster አባል ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅትና ትብብር በማጠናከርና አብሮ በመስራት ከዚህ በበለጠ ጥራት ያለው በመረጃ የተደገፈ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰራ ገልፀዋል ።
Email: ghcdire@gmail.com
Telegram: https://t.me/GoroPHCU
Facebook: https://www.facebook.com/share/1B4gWe7v2Q/
Website: https://ghcdd.gov.et
ለበለጠ መረጃ በ0986200277 ይደውሉ

Goro Health Center
Center of Excellence

👏4
❤1
Goro Health Center - Dire Dawa pinned «በተቋማችን የሚሰጠውን አገልግሎት እንዴት ይገልፁታል»
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ! Congratulations!
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በተካሄደ የ2018 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም የግምገማ ተቋማችን ጎሮ ጤና ጣቢያ በበጀት ዓመቱ ከከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል በአገልግሎት አሰጣጥ በ1ኛ ደረጃ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ የእውቅና ምስክር ወረቀትና ሜዳልያ ሽልማት ተቀብለናል፡፡
ይህንን ውጤት በማስመዝገብ ከፍተኛውን ሚና የተወጣችሁ መላው የተቋማችን ሰራተኞችና የስራ ክፍል አስተባባሪዎች የአንበሳው ድርሻ የእናንተ ነውና ከልብ እናመሰግናለን።
በቀጣይ 2019 በጀት ዓመት የተቋማችንን አሰራር በቴክኖሎጂ በማዘመንና የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል ተቋማችንን የአገልግሎት ልህቀት ማዕከል በማድረግ በጤና ቢሮና በአስተዳደሩ የተሰጠንን ኃላፊነት በላቀ ደረጃ እንደምንፈፅም ያለንን ቁጠኝነት እያረጋገጥን በጤና ቢሮ ለተሰጠን እውቅና እናመሰግናለን።
በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!
Congratulations all!

❤6👏6