GOD'S MESSENGERS
160 subscribers
356 photos
35 videos
7 files
16 links
Download Telegram
አንዳንድ ሰዎች የተሸነፍንላችሁ ጉልበታም ሰለሆናችሁ ሳይሆን ሌላ የተሸነፍንበት ጉዳይ ወይም ዓለም ስላለ ነው።ስትራገጥ ያልተራገጠ ሁሉ እግር የሌለው እንዳይመስልህ እግሩን ሌላ አካል እየሄደበት ስለሆነ ነው።ለእግዚአብሔር የተሸነፈን ሰው ማሸነፍ አትችሉም ምክንያቱም የተሸነፈው ለእናንተ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነውና።

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.
ነገህን በማያቁና ጥሪህን ባልተረዱ ናባሎች ራስህን አታድክም!

ነገህን ወይም ጥሪህን በማያውቁ ሰዎች ራስህን አታድክም፡፡የህይወት ትልቁ ችግር ነገህ ባልታያቸውና ጥሪህን በማያቁ ሰዎች መከበብ ነው፡፡የዳዊትን ነገ ወይም የዳዊትን ጥሪ የምታውቀው አቢጊያ እንጂ ናባል አልነበረም፡፡ናባል ዳዊትን በትናትናው ማንነቱ ሲነቀው አቢጊያ ዳዊትን በነገው ንግስናው ልክ ከጥፋት ታደግችው፡፡ዛሬ ሆነው ትናትናህን ከሚያወሩ ከናባል አይነት ሰነፎች እየራክ ዛሬ ላይ ሆነው ነገህ ከታያቸው አቢጊያዎች ጋር ተጣበቅ፡፡ምክኒያቱም በናባል ዘንድ ትናት እንጂ ነገ የለህምና፡፡

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.
በህይወቴ ከተማርኩት እና ከተረዳሁት በጥቂቱ ይህን ልበላችሁ:-
ምንም ነገር ከመስጠትህ በፊት
የምትሰጠው ነገር የምትሰጣቸው ሰወች ዘንድ ያለውን ቦታ እወቅ ! ወዳጄ ያንተን ውድ ነገር  ዋጋውን ለማያከብሩት እንዳትሰጥ መክረሀለሁ ምክንያቱም ትርፉ ኪሳራ ነው ።
#ለሚሸነግሉህ #ለጋስ #ለሚዋሹህ #ቸር #አትሁን

ለሚሸነግሉህ #ቸር መሆን እውነተኛ #ለጋስነት አይደለም።እነርሱም #አታለው እንደተቀበሉህ እንጂ #ወደህ እንደሰጠሃቸው #አይቆጥሩልህምና ከሁሉም ሳትሆን እንዳትቀር ተጠንቀቅ።

በውሸት ለሚደልሉህም #ለጋስ መሆን እውነተኛ #ቸርነት አይደለም።የሚዋሽህ ሰው #የሚራራልህ ሰው አይደለም #በጣፋጭ ቃልና #ብልጠት በሞላባቸው ሃሳብ እየገዛህ እንጂ።

#ሸንጋይ ሰው እና #ውሸተኛ ሰው ትልቁ #ብቃታቸው #ከሁሉም ሰው ጋር #የመኖር አቅም አላቸው።ምክንያቱም በአንተ #ልክ እና አንተ የምትፈልገውን #አይነት መሆን መቻላቸው ነው።እነዚህ መንታ ባህሪያት ለመለየት አይንህ ሊከፈት ይገባል።

በቀሪ ዘመናችሁ የብርሃን አምላክ ከእነዚህ መንታ ባህሪ ካለቸው ሰዎች ይጠብቃችሁ።

አፖስትል ቃልአብ ታደሰ.
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።”
ራእይ 2፥17
ሁሉም ሰው አይጠቅምህም ሁሉም ሰው አይጎዳህም።በህይወት የሚያስፈልገህ ሰዎች ሁሉ ሳይሆኑ አንድ የታመነ ሰው ነው።አንድ ታማኝ ሰው የብዙዎች ዋጋ አይተምነው።በብዙዎች መታጀብ ብዙ ጉልበት እንዳይመስልህ በብዙዎች መክበብ ብዙ ርቅት የሚያስጉዝህ እንዳይመስለህ በብዛቱ ልክ ብክነቱ ያው ነው።እግዚአብሔር በታመኑ ሰዎች ይባርካችሁ።

ሐዋሪያው : ቃልአብ ታደሰ
ዛሬ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህያው የሆነው ወንጌል ተነገረ እግዚአብሄር እረዳን ብዙ ትውልድ ዳነ !

ማቴዎስ 24:14፤ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።”