Gurage News Network GNN - ጉራጌ ኒውስ ኔትወርክ
1.02K subscribers
395 photos
32 videos
639 links
GNN is a trusted media platform dedicated to delivering up-to-date news, stories, and analysis with accuracy and integrity. Our coverage is rooted in truth, facts, and credible sources, ensuring that our subscribers and followers receive reliable info.
Download Telegram
ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ያለው የውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ ወደ ከረረ ደረጃ መሸጋገሩን ተከትሎ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የተቃውሞ መግለጫ አወጡ።

ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተመርጠናል" የሚሉ አካላት በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው በጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አዳራሽ ስብሰባ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ድርጊቱ "የሥልጣን ወረራ" መሆኑን የጠቀሱት ጄነራሉ፣ ለሚከተለው ማንኛውም ዓይነት ቀውስ ተጠያቂው ይህ በጉልበት ሥልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሰው አካል መሆኑን አስታውቀዋል።
🙏1
በፖሊስ አባል ህይወቱ ለጠፋው ግለሰብ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ተሰጠ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በፖሊስ አባል ህይወቱ ያለፈው የአቶ ተገኝ ባልቻ ቤተሰቦች፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ርክክብ ተደረገ።
የህወሓት የካቢኔ ስብሰባ እና የክልሉ ፕሬዚዳንት ማሳሰብያ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማክሰኞ ዕለት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ ዛሬ የካቢኔ አባላትን ጥሪ አድርጌ ሥራ ጀምሪያለሁ ብሎ ስብሰባ መቀመጡ ተሰማ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸዉ ፤ በክልሉ ሕዝባችን ላይ ለሚደርሰዉ ጥፋት ተጠያቂዉ ራሱ በጉልበት የአስተዳደሩን ሥልጣን ለመያዝ እየሞከረ ያለዉ አካል ሲሉ በጽሑፍ አጋርተዋል።

«በቅርብ ቀናት የተፈጠሩትን ሁኔታዎች ተከትሎ፤ ሊመጣ የሚችልን ጉዳት ለማስቀረት፤ ይህንኑ ችግር በትግራይ ዉስጥ በዉይይት እና በጋራ መግባባት ለመፍታት የቀረበዉን ጥሪ ወደ ጎን በመተዉ ተምርጫለሁ የሚል አካል፤ ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ. ም የፀጥታ አካላትን ጥበቃ ተደግፎ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስተዳደር የካቢኔ መሰብሰብያ አዳራሽ ላይ ስብሰባ ጀምሯል፤ ይህ ደግሞ በቀጣይ አደገኛ አካሄድ የጀመረበት መሆኑን ያሳያል። በዚህ ምክንያትም ለሚከተለዉ ማንኛዉም ችግር ፤ የጊዜያ አስተዳደሩን ሥልጣን በጉልበት ለመያዝ እየሞከረ ያለ አካል መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ።» ብለዋል።

«በ 2012 ዓ.ም በትግራይ ክልል ብቻ ምርጫ ከተካሄደ እና በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከተመረጠና ከሦስት ዓመት በኋላ አለመግባባት ሲመጣ ፤ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግርይ (ህወሓት) ምክር ቤቱን እንደሚያስመልስ መግለፁ ይታወቃል። በዚህ ሳምንት ማክሰኞ እንደታየዉ ህወሓት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን፤ ፕሬዚዳንት አድርጌ መርጫለሁ ብሎ ዛሬ የካቢኔ አባላትን ጠርቼ ስብሰባ ጀምሬያለሁ ብሏል።»

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ቀደም ሲል ጀምሮ የህወሓት አካሄድ ትክክል አይደለም፤ ይህ ክልሉን ወደ ሌላ ችግር የሚያስገባ ነዉ፤ መፍትሄዉም ንግግር እና ዉይይት ነዉ ሲሉ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ተነግሯል።
ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህወሓት ሊቀመንበር ሆነዉ የተመረጡ ዕለት እና ዛሬ በመቀለ ሰማይ ላይ የጦር ጀት ሲያንዣብብ እንደነበር የዓይን እማኞች የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
በማህበር ተደራጅተው የመኖርያ ቤት መስርያ ቦታ ለማግኘት ጥያቄ ያቀርቡ መምህራን ምላሽ እንዳላገኙ አስታወቁ፡፡

ወልቂጤ | May 12/2026 (GNN) በጉራጌ ዞን በማህበር የተደራጅ መምህራን ለሚመለከተው አካል የመኖርያ ቤት መስርያ ቦታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ካቀርቡ እርጅም ጊዜ ቢቆጠርም አሁንም ምላሽ የሚሰጠን አካል አልተገኘም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በዞኑ በተለይም በወልቂጤ ከተማ የሚሰሩ መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው አሰራር መሰረት በማህበር ተደራጅተው፤ የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ፈፅመው ለሚመለከታቸው አካል ካሳወቁ ከአራት አመት በላይ ቢሆንም ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የከተማው አመራር በተገኙበት መድረኮች በተለያዩ ጊዜ ቅሬታቸውን ማንሳታቸውን በመግለፅ ጥያቄያቹህ ይመለሳል በትግስት ጠብቁ ከተባልን አራት አመት አልፎል ብለዋል፡፡

ቅሬታቸውን ለጂኤንኤን ያደረሱት በከተማው ከአራት አመት በላይ በመምህርነት ያገለገሉ መምህራን በተለይም በሀገር አቅፍ ደረጃ በልዩ ሁኔታ ለመምህራን የቤት መስርያ ቦታ መስጠትና ቤት ለመገንባት የተለያዩ ድጋፎች በሚደረጉበት ወቅት በማህበር ተደራጅተው የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ፈፅመው ቢጠባበቁም መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል አለማግኘታቸው ተናግረዋል፡፡

እንዲያውም በቅርብ የከተማው ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በተገኙበት ቅሬታቸውን በድጋሚ በመድረክ ማንሳታቸውን የገለፁት መምህራኑ ከንቲባው በምላሻቸው ከዚህ በፊት በከተማው ለሚገኙ መምህራን በግቡርየ ክፍለ ከተማ የቤት መስርያ ቦታ ቢሰጣቸውም እስከ አሁን ቤት አልሰሩም ለእናንተም ቦታ ቢሰጣችሁ የተለየ ነገር አታደረጉም የሚል ተስፍ አስቆራጭ መልስ ሰጥተዋል ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነቱ አሳሳቢ ደረጃ በደረሰበት በዚህ ወቅት በከተማ ቤት ተከራይቶ በመምህረነት እየሰሩ የተረጋጋ ኑሮ መኖር ከባድ መሆኑ እየታወቀ የከተማ አስተዳደሩ ጥያቄቸውን በችለተኝነት እያየው ይገኛል ብለዋል፡፡

የከተማው መሬት በህገወጥ ደላሎች በህገወጥ መልኩ ከአመራሮች ጋር በመመሳጠር እየተሸጠ፤ ትውልድ የሚቀርፁ መምህራን በመንግስት በልዩ ሁኔታን የተቀመጠን አቅጣጫና ትዛዝ ግን ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ቅሬታቸውን ለዞኑ ብሎም ለክልሉ መምህራን ማህበር ማድረሳቸውን የተናገሩት መምህራኑ እስከ አሁን መፍትሄ እንዳላገኙም አንስተዋል፡፡


For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
ለምርጫ ቦርድ 11 ቢልዮን ብር ለምርጫ ማስኬጃ ተመድቦ እያለ ለፓርቲዎች ግን 170 ሚልዮን ብር ብቻ መመደቡ ፍትሀዊ አይደለም ተባለ፡፡

አዲስ አበባ | May 12/2026 (GNN) መንግሥት ለምርጫ ቦርድ ምርጫ ማካሄጃ 11 ቢሊዮን ብር መድቦ እያለ፣ ቦርዱ ለፓርቲዎች የበጀተው 170 ሚሊዮን ብር ኢፍትሐዊ ብቻ ሳይሆን በምርጫው ሒደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ፍላጎት ያለው ይመስላል ተብሏል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ማስፈጸሚያ የሚለቀው የበጀት ክፍፍል ቀመር ግልጽነት የጎደለው እንደሆነ፣ መለቀቅ ከሚገባው ቀን የዘገየና በመጠንም አነስተኛ መሆኑን ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው አገራዊ ምርጫን በተመለከተ አከናወንኳቸው ያላቸውን ቅድም ምርጫ ተግባራት ይፋ ሲያደረግ ነው ቅሬታው የተሰማው፡፡

በዚህም የፓርቲ ተወካዮች ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በተሟላ ሁኔታ ድጋፍ እያቀረበ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለምርጫ ቦርድ ለምርጫ ማካሄጃ 11 ቢሊዮን ብር መድቦ እያለ፣ ቦርዱ ለፓርቲዎች የበጀተው 170 ሚሊዮን ብር ኢፍትሐዊ ብቻ ሳይሆን በምርጫው ሒደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ፍላጎት ያለው ይመስላል ተብሏል፡፡

ምርጫ ቦርድ አስፈላጊ ላልሆኑ ድግሶች በየሆቴሉ ከፍተኛ ገንዘብ እያወጣ፣ ነገር ግን ለምርጫው አስፈላጊ ለሆነው የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ገንዘብ በልኩና በጊዜው እየተከፈለ አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በምርጫ ቦርድ በኩል ይደረግ የነበረው ድጋፍ ግልጽ በሆነ መመርያ ፓርቲዎች በሚያቀርቧቸው ዕጩዎችና የአካታችነት ስብጥር መሠረት በመቶኛ ተሠልቶ ይሰራ ነበር፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ፣ ከዚህ በፊት ከነበረው አሠራር በተለየ የግልጽነት ችግር ያለበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በሰንጠረዥ ተከፋፍሎ ፓርቲዎች የሚጠቀሙበት የበጀት መጠን ግልጽ በሆነ መንገድ መቅረብ ነበረበት በማለት ተናግረዋል፡፡ በዚህም ቦርዱ ለመንግሥት ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ ማቅረቡን ገልጸው፣ በአጠቃላይ ለፓርቲዎች የቀረበው በጀት እጅግ አናሳ በመሆኑ ጉዳዩ ለምርጫ ቦርድ መቅረቡን አስረድተዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ከምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚተላለፈውን በጀት በተመለከተ ሲያስረዱ፣ ችግሩ በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ በስፋት እንደሚነሳ፣ የምርጫ ድጋፍ ገንዘብ ክፍያ መዘግየትና የተለቀቀው ድጋፍም የጊዜውን የኑሮ ሁኔታ ያላገናዘበና ዝቅተኛ መጠን ያለው መሆኑን፣ ለፓርቲዎች በየዓመቱ ከሚለቀቀው መደበኛ በጀት ሁለተኛ ምዕራፍ አለመለቀቁን ተናግረዋል፡፡

አክለውም አሠራሩ የቀመር ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ፣ በምክር ቤት ከፀደቀው 11 ቢሊዮን ብር ውስጥ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ያህል እንደተላለፈ በግልጽ ሊነገር ይገባል ብለዋል፡፡

ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ከሚመድበው ዓመታዊ መደበኛ በጀት ውስጥ የመጀመሪያው ዙር 30 በመቶ መለቀቁን፣ ነገር ግን ሁለተኛ ዙር እስካሁን አለመለቀቁንና በዚህ ጉዳይ ላይ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
በሌሞ ወረዳ በሙሰኛ አመራሮች የተሳሳተ ወሳኔ የወል መሬቶች እንዲሸጡ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡

ሆሳዕና | May 12/2026 (GNN) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሌሞ ወረዳ የጋራ መሬቶች ያለህዝቡ ፍቃድ በጥቂት ሙስና በለመዱ አመራሮች አማካኝነት እየተሸጡ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከወረዳ እስከ ዞንና ክልል በጥቅም ሰንሰለትና በቡድንተኝነት በተሳሰሩ አመራሮች እንዲሁም በድለላ በከበሩ እራሳቸውን ባለሀብት ብለው ከሚጠሩ ግለሰቦች ጋር በመሆን ለህዝባዊ ልማት መወያል ያለባቸው የወል መሬቶች በእራሳው ፈቃድና ውሳኔ እየሸጡ ይገኛሉ ብለዋል የጂኤንኤን ምንጮች፡፡

በ“ኢንቨስትመንት” ስም የሚካሄደው ያልተገባ አካሄድ እንዲቆም ቢጠየቅም የሕዝብን መሬት ለግል ጥቅምና ለደላላ ባለሀብቶች አሳልፎ የመስጠት አሰራር ህዝቡ እንዳሳዘነውም ተነግሯል። የወረዳው አመራሮች ወሳኝ የሆኑ ተግባራትን የልማት ስራዎችን እርግፍ አድርገው በመተው ከጥቅም ተጋሪ ባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር የመንግስት የግጦሽ መሬቶችን፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት እና የወል መሬቶችን እንደየግል ንብረቶቻቸው ሽጠው እየጨረሹት ይገኛል ተብሏል።

የቡድንተኝነቱና የሙሰኝነቱ ትስስር ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ የተዘረጋ የጥቅም ሰንሰለት መፍጠሩ በዚህ ወረዳ የሚሰሩ ህገወጥ ድርጊቶች በግልፅ ያሳያሉ ተብሏል። ይህ አደገኛ አሰራር የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቢይዘውም፣ ከዞን እስከ ክልል ባሉ በተለይም በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ባሉ ከፍተኛ አመራሮችና በደላላ ባለሀብቶች ግፊት ተጠያቂነት እንዳይረጋገጥ ተደርጓል። ይህም ዞኑም ሆነ ክልሉ ለሕግ የበላይነትን ሳይሆን ለጥቅም ትስስርን እንደ መርህ እንደሚጠቀሙ ማሳያ ይሆናል።

በከፍተኛ አመራሮች ጫናና ሽፋን ተደረጎላቸው ስር በሰደደ የሙስና ድርጊት የሚሳተፉ አመራሮች በዚህ ወቅት የሚጠየቁ ባይመስላቸውም በሂደት መጠየቃቸው አይቀርም፡፡

የወረዳው ሕዝብ ለዘመናት የጠበቀው መሬት ዛሬ ለአመራሮችና ለባለሀብቶች የኪስ ማድለቢያ መሆኑ እጅግ የሚያስቆጭ አሳዛኝ ነው። ሌላው በውጭ የሚኖሩ የወረዳው የዲየስፖራ አባላት በወረዳው የልማት ስራዎች ለማከናውን በሚያደረጉት ጥረትና ፍላጎት በእነዚሁ አመራሮች ድክማትና ቢሮክራሲ ውጤታማ መሆን አልቻሉም፤ቅሬታ አቅርበው የሚሰባቸው አመራር አጥተዋል ተብሏል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
በአዲስ አበባ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጉቦ እና የእጅ መንሻ፤ አካውንት ቁጥር እስከ መስጠት መደረሱን ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ | May 12/2026 (GNN) በከተማዋ ጉቦ እና እጅ መንሻ መጠየቅ፤ አገልግሎት መስጠት ላይ እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉ ሲገለጽ ጉቦ ጠይቀው የተገኙት ላይም የሚወሰድባቸው እርምጃ እና የሚወሰኑ ውሳኔዎች ቀለል ያሉ ናቸው ተብሏል፡፡

ይህ መሆኑ ጉቦ ጠያቂዎቹ የበለጠ እየተደፋፈሩና ና ቅጣቱ ሌሎችን ሊያስተምር እንዳልቻለ ተጠቅሷል፡፡

ይህንን ተግባር ለማስቆምም ምን እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤት አባላት ተይቀዋል፡፡

ችግሩ መኖሩን ያመኑት ምላሽ የሰጡት የሥራ ኃላፊዎች ይህንን ስር የሰደደ ሌብነት ለማስቆም የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ጥቆማዎች፣ ግምገማዎች እና የኦዲት ሪፖርቶችን በመንተራስ ችግሮቹን ለመፍተታ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በ9 ወር ውስጥ 420 የሚሆኑ ባለሞያዎች እና አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተጠቁሟል፡፡

ጉቦኝነት እና ሌብነት በከተማዋ እየተፈፀሙ ይገኛሉ ያሉት የስራ ሀላፊዎች፤ ባለሞያው እና አመራሩ ‘’ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል’’ በሚል ብሒል ያደገ ስለሆነ ችግሩን እንዳከፋው አንስተዋል፡፡

በሙስና እና በሌብነት ተሰማርተው በሚገኙት ላይ ሚወሰደው እርምጃና ተጠያቂነታቸው ቀድሞ ከነበረው ተሻሽሏል ብለዋል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
ለእርጅም ጊዜ ጥያቄ ሲነሳብት የቆየው የቀደሞ ተፈራ ሆቴል ይዞታ ለሶስተኛ ጊዜ ለሌላ ባለሀብት ተላልፎ ተሰጠ፡፡

ወልቂጤ | May 14/2026 (GNN) በከተማውም በዞኑም ማህበረሰብ ዘንድ መነጋገርያ ሆኖ የቆይው የቀድሞ ተፈራ ሆቴል ይዞታ እንደ ገና ለሌላ ሶስተኛ ባለሀብት ተላልፎ መሰጠቱ ተነግሯል፡፡

ሆቴሉ እንደፈረሰ 1.2 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገበ ተወላጅ ባለሀብት ቦታው ተረክቦ እንዲያለማ በወቅቱ ቢነገርም ቆራጥና ህዝባዊ አመራር ባለመኖሩ ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱ ይነገራል፡፡

ነገር ግን ቦታው ለኢንጂነር ሳሙዔል(ለሰንሻይን ኮንስትራክሽን) ተሰጠ መባሉ ብዙዎች ጥሩ ውሳኔ መሆኑን በደስታ ሲያጋሩት ታይተዋል፡፡ ነገሩ እንደተባለው ሳይሆን ወሬ ሆኖ ቀረ የተባለውም ተረሳ፡፡

በህዝብ ዘንድ ጥያቄ ሲያጭር የቆየው ይህ ወሳኝ ቦታ ቀጥሎም ለአትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ተሰጠ ተብሎ በሰበር ዜና ተነገረ፤የመሰረት ድንጋይ ተጣለ ለከተማው እድገት አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደረግ ሆቴል ሊገነባ መሆኑ በተስፍ ተወራ፡፡

ፈተና የበዛበት ብዙ አሻጥሮች በውስጡ የያዘው ቦታው የተባሉት ሁለቱን ባለሀብቶች እቅዳቸው መሰረዛቸው ተነገር፡፡ለቦታው ከተማው ከአንዴም ሁለቴ የሊዝ ጨረታ አወጣበት ነገር ግን አግባብ አይደልም መባሉን ተከትሎ ጨርታውም ተሰረዘ፡፡

አይረሴው ተፈራ ሆቴልን የሚተካ ለወልቂጤ ከተማ እድገት አስተዋፆ ያለው ባለሀብት እንድይዘው ብዙ ተባለ ሳይሳካ ብዙ ቆየ፡፡ በምርጫ ዋዜማ በጉራጌ ዞን የትልልቅ ፕሮጀክቶች የመሰረት ድጋይ ሲጣል ማየት የተለመደ ነው፤ ግንባታውን ሲሰራ ሲመረቅ ማየት ግን አልታደለም፡፡

ታድያ አሁን በአዲስ መልክ የከተማው ወጣት ባለሀብት ዩሃንስ ሀይሌ ኮንስትራክሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ ትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች በመስራት የሚታወቅ ባለሀብቱ ቦታው እንደተረከበው ተገልፆል፡፡

ይህ ባለሀብት በወልቂጤ ከተማ ስራኖ ሆቴል በመገንባት ለከተማው መልካም ገጽታን የሰራ ባለሀብት መሆኑም ይነገራል፡፡ አነጋጋሪው ቦታ ኬር ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተረክቦ ኬር ሎጅ ሊገነባ መሆኑ በአዲስ መልክ በተስፋ ተነግሯል፡፡

ከአመታት በፊት ሆቴሉ ሲፈረስ 1.2 ቢልዮን ብር እንደመስፈርት ተቀምጦለት የነበረው ቦታው፤ በዚህ ወቅት ግን ለኬር ሎጅ 950 ሚልዮን መውረዱ ግን ግልፅ አይደለም፡፡ አነጋጋሪው ቦታ እንዴትና በምን መስፈረት ወደ ኢንቨስትመንት ተቀየረው የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ግን አሁንም በግልፅ አልተመሱም፡፡ባለሀብቱ በዋቤ ወንዝ አካባቢ ዘመናዊ ሎጅ ሊገነባ ነው ተብሎ የመሰረት ድጋይ ከተጣለ አንድ አመት ማለፉ ይታወስ ነው፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
🛑 ከሰይዶ ማርሻል የማናጅመንት ቡድን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ! 🛑

በመጀመሪያ መላው የሰይዶ ማርሻል ቤተሰቦች እና የማርሻል አርት ስፖርት አፍቃሪያን፣ ላለፉት ጊዜያት ሁሉ ስለምታሳዩት ተከታታይ እና ያላሰለሰ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን። የእናንተ ድጋፍ ለስፖርተኛችን ትልቅ ብርታት ነው።

እንደሚታወቀው ሰይዶ ማርሻል በቲክቶክ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን በማፍራት በማርሻል አርት ዘርፍ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለ ወጣት እና ብርቱ ስፖርተኛ ነው። በቅርቡ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በንቃተህሊና እና በጆኒ ጁጁትሱ መካከል በተካሄደው ፍልሚያ ጂኒ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ፣ ለሰይዶ ማርሻል የ"እንፋለም" ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

ሰይዶ ይህንን የውድድር ጥሪ በታላቅ ስፖርታዊ ጨዋነት ተቀብሎ ዝግጅት መጀመሩ ቢታወቅም፣ በአሁኑ ወቅት ከአዘጋጆቹ ጋር እየተደረገ ስላለው ድርድር እና እየተሰራጩ ስላሉ የተሳሳቱ መረጃዎች እውነታውን ለደጋፊዎቻችን ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

1. ስለ ፕሮፌሽናል ድርድር እና መብት፦ ማንኛውም ፕሮፌሽናል ውድድር የራሱ የሆነ የውል ስምምነት እና የክፍያ ድርድር አለው። የሰይዶ ማርሻል ስም እና ተከታይ ለዝግጅቱ ዋነኛ የገቢ ምንጭ መሆኑ ግልጽ ነው። በዚህም መሰረት፣ ከጠቅላላው የዝግጅቱ ገቢ 10 በመቶ (10%) ብቻ እንዲከፈለው ያቀረብነው ጥያቄ፣ ስፖርተኛው ካለው ተፅዕኖ እና ወደ ዝግጅቱ ከሚመጡት ስፖንሰሮች አንጻር ሲታይ እጅግ አነስተኛ እና ተገቢ ክፍያ ነው።

2. ስለ ስም ማጥፋት ዘመቻው፦ አዘጋጆቹ በድርድር ጠረጴዛ ላይ በሰለጠነ መንገድ ከመነጋገር ይልቅ፣ የጥቅም ጥያቄውን ባለመቀበል የልጁን ስም የማጥፋት ዘመቻ መጀመራቸው እጅግ አሳዝኖናል። "ውድድሩን ፈርቷል"፣ "አቅም የለውም" በሚሉ መሰረተ ቢስ ወሬዎች ህዝቡን ለማነሳሳት የሚደረገው ጥረት ፍጹም ከእውነት የራቀ ነው። ሰይዶ ለማንኛውም ፈተና ዝግጁ መሆኑን በተግባር ያሳየ ስፖርተኛ እንጂ የሚፈራ አይደለም።

3. አቋማችን፦ እኛ እንደ ማናጅመንት ቡድን፣ የሰይዶን ፕሮፌሽናል መብት የማስከበር ግዴታ አለብን። ስፖርተኞች የሚገባቸውን ክብር እና ጥቅም ሳያገኙ፣ በስማቸው ብቻ ሌሎች እንዲበለፅጉ መፍቀድ ተገቢ አይደለም ብለን እናምናለን። ስፖርተኛው መብቱ ተከብሮለት በሙያዊ ብቃት እንዲወዳደር ማድረግ የአዘጋጆቹ ኃላፊነት ነው።

መልዕክታችን፦ አዘጋጆቹ ከዚህ መሰል የኋላ ቀር ስም የማጥፋት ተግባር ተቆጥበው፣ በሙያዊ መንገድ ድርድሩን እንዲቀጥሉ እንመክራለን። ለደጋፊዎቻችንም እውነታው ይህ መሆኑን እንድትረዱልን እንጠይቃለን።

ለእውነት እና ለስፖርታዊ ጨዋነት እንቆማለን!
የሰይዶ ማርሻል ማናጅመንት ቡድን
በግቡርያ ክፍለ ከተማ ህገወጥ የመሬት ወረራ ተባብሶ መቀጠሉን ተገለፀ፡፡

በወልቂጤ ከተማ በግቡርየ ክፍለ ከተማ ህገወጥ የመሬት ወረራ እንዲባባስ አመራሩ በበላይነት ስለሚመራው ነው ተብሏል፡፡

ወልቂጤ | May 16/2016 (GNN) በክፍለ ከተማው ግለሰቦች፣ ነጋዴዎችና የመንግስት ሰራተኞች ሳይቀር ህጋዊነቱን በልተረጋገጥ መሬት ገንዘባቸውን ያፈሳሉ፤ቤቶች ይገነባሉ፡፡ በህግወጥ ደላሎች አማካኝነት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚሩ ዜጎች ህጋዊ ያልሆኑ መሬቶች ህጋዊ ናቸው በሚል አሳሳች ግፊት መሬት ይገዛሉ፡፡

የከተማው አመራር በተለይም የማዘጋጃ ቤታዊ ሃላፊዎች የመሬት ወረራው ከማስቆም ይልቅ የዚሁ አካል በመሆን ሀላፊነታቸው ተጠቅመው ህገወጥ ንግድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የአንድ ግለሰብ መሬት በበርካታ ግለሰቦች ስም ይመዘገባል፤ መርካታ ጊዜ ይሸጣል፡፡ የጂኤንኤን ምንጮች እንደሚያስረዱት ለምሳሌ ከአንድ ባለመሬት ነኝ ከሚል ግለሰብ በህገወጥ መልኩ አንድ መሬት ከአምስት ጊዜ በላይ ለአምስት የተለያዩ ግለሰቦች በአንዴ ሲሸጥ በከተማው መዘጋጃ ቤት የተፈረም የመሬት ማረጋገጫ ወረቀት ሁሉም ግለሰቦች ያገኛሉ፡፡ መሬቱ አምስቱም ግለሰቦች የእኔ ነው በሚል ይጋጫሉ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ፡፡

እንዲህ አይነት የሌብነት ስራ ህገወጥ ነጋዴዎችና አመራሩ ተባብረው የሚፈፅሙት ወንጀል በክፍለ ከተማው ማየት የተለመደ ነው፡፡ ለአመራሩ ሙስና ያልከፈለ የትኛውም ዜጋ ህጋዊ ቢሆንም በከተማው መሬት ማገኘት የማይታሰብ ነው፡፡

አመራሩ ህጋዊ ነው በሚል ሸንሽኖ የሸጠው፤ ለነጋዴዎችና ለግለሰቦች አሳልፎ የሰጠው ህገወጥ መሬት ተብሎ ኪሳራ ውስጥ የገቡ ከፍተኛ ገንዘብ የከሰሩ ግለሰቦች አሉ፡፡

በክፍለ ከተማው በህጋዊ መንገድ ተደራጁ ተብለው የተደራጁ የሚጠበቅባቸው ክፍያ የከፈሉ፤ ከአመራሮች ቅርበት ስለሌላቸው ብቻ ገንዘባቸው ተበልተው ዛሬ ነጋ እየተበሉ ከ7 አመት ጀምሮ እስከ አሁን እየተንገላቱ የሚገኙ ወጣቶች አሉ፡፡

በርካታ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ከ7 ዓመት በፊት ለሁለተኛው ዙር መሬት ድርሻ አምስት አምስት ሺ ብር ቡክ አስከፍተዋቸው መሬት ታገኛላቹህ ተብለው እስካሁን መሬት አላገኙም፡፡ ከአመታት በፊት አምስት አምስት ሺ ብር ያለውና የሌለው ተበድሮ ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ አድረገዋል ነገር ግን እነዚህ ወጣቶች ጉዳያቸው ተረስቶ ብራቸውም ተበልቶ ለማን እንደሚያናገግሩ ጋራ ገብቷቸው ተቀምጠዋል፡፡

በጣም የሚያሣዝነው በመጀመርያው ዙር ጉልበተኞቹ በዘመድ እና በጓደኝነት በጥቅማጥቅም ስለተደረገ ለእኛ እዳይደረሰን ተደረገ ይላሉ። በክፍለ ከተማው በህገወጥ መሬት ሽያጭ የተነሳ በርካታ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው፤ በዚህም በበርካታ ግለሰቦች መካከል ጥልና ግጭት ተነስቶ ወደ ፍርድ ቤት ያመሩ ጉዳዮች በርካታ ናቸው፤ የእነዚህ ሁሉ ችግር መነሻና ምክንየት ህገወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ከአመራሩ ጋር በሚሰሩት ያልተገባ ስትት ምክንያት ነውም ተብሏል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
👍4
ከአመራሮች ጋር ቁርኝት ያላቸው ወጣቶች ከየማደያው ነዳጅ በበርሜል ቀድተው እየወሰዱ ነው ተባለ፡፡

ወልቂጤ | May 16/2016 (GNN) በወልቂጤ ከተማ የተወሰኑ ወጣቶች ከአመራሮች ጋር ባላቸው ትስስርና ቅርበት የተነሳ ከየማደያው ያለ ከልካይ ነዳጅ በበርሜል ቀድተው እየወሰዱ ናቸው ተብሏል፡፡
በከተማው የነዳጅ እጥረት አባባሽና ህገወጥ ንግድ ከመቆጣጠር ይልቅ፤ወጣቶች በግልፅ ህገወጥ የነዳጅ ንግድና ዝውውር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ ከአመራሮች ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ነዳጅ በህጋዊ መንገድ ከማድያዎች ከማግኘት ይልቅ፤በከተማው በህገወጥ ነጋዴዎች እጅ ማገኘት ቀላልና የተለመደ ሆኗል፡፡ በህገወጥ የነዳጅ ንግዱ አመራሩ በዚህ መልክ የሚሳትፍ ሲሆን የተወሰኑ ጉልበተኛ ነን የሚሉ ወጣቶች በህገወጥ ነዳጅ ንግድ ከመሳተፍ ባለፈ የኮንትሮባንድ ስራ ላይ በቀጥታ ይሳተፋሉ የሚጠይቃቸው አካል የተለም ተብሏል፡፡
አመራሩ ለወጣቶቹ ህገወጥ ንግድ የሚፈቅዱት ገንዘብ ከማግኘት ባለፈ ወጣቶቹ ለተለያዩ ዝግጅትቶ በአስባባሪነትና በጥበቃ በታማኝነት ይጠቀሟቸዋል፡፡
የከተማው ንግድና ኢዱስትሪ ፅህፈት ቤትና ከንቲባዉ ቢሮ ይህ ህገወጥ ንግድ በሚገባ የሚያውቁት ፍቃድ የሰጡት ድርጊት ነው የሚመስለው ይላሉ በየማደያው ውስጥ የሚሰሩ የጂኤንኤን ምንጮች፡፡ ለህገወጥ ንግድ እራሳቸው ያደራጁት ወጣቶቹ በተለይም አመራሮች ሲቀያየሩና አዳዲስ ሹመቶች ሲኖሩ ጊዜ አይወሰድባቸውም ቶሎ ከአመራሮቹ ጋር የጀመሩት ስራቸው ያሰቀጥላሉ፡፡
በዚህ መልኩ ሀብት የሚያካባቱ አመራሮችና ግለሰሰቦች የከተማው ልማት ወደ ኋላ ከመጎትት ባለፈ ህገወጥነትና ሌብነት አለማምደወዋል፡፡ በከተማው ስለአመረሩ ዝርፍያ፤ለህዝቡ አለመታምን መስማት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ተራውን ጠብቆ ዘርፎ ዳር ለመያዝ የሚጥር አመራር የከተማው አመራር ግብ እየሆነ ነው፡፡ በህጋዊነት በስርዓት ስርቶ መለውጥ ተስፍ ወደ ማስቆርጥ እየደረሰ ነው፡፡የከተማው ወጣት ከአመራሮች ምን ይማር፣ህዝባዊነት ወይስ ቡደንተኝነት፤የአብዛኛው የከተማው ወጣት ጥያቄ እየሆነ መጥቷል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
ከቡታጅራ ከተማና አካባቢው ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

‎ቡታጅራ | May 16/2016 (GNN) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በልማትና መልካም አስተዳደር፤ በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ከዞኑ ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ አካሄደዋል፡፡

‎ርዕሰ መስተዳድሩ ‎በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለማስቆም መንግስት በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው ወጣቱ ሰላምን ሊያደፈርሱ የሚችሉ ምክንያቶችን በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ በመለየትና ከአሉባልታ በመራቅ በየአካባቢው ሠላም እንዲሰፍንና የህዝባችን ሰላም እንዲረጋገጥ አጋዥ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

‎ቡታጅራ ከተማ በሰላማዊነቷና እያስመዘገበች ባለችው ዕድገት ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ መሆን እየቻለች የምትገኝ ለወደፊቱም ከዚህም በላይ ትልቅ ተስፋ ያላት ከተማ ናት፡፡ የዞኑ አካባቢዎች የመልማት ፀጋ ያለው ምቹ መሆኑን ይህ ተስፋና የመልማት አቅም በይበልጥ ለማሳደግ ወጣቱ ከመንግስትና ከህዝቡ ጋር ለአካባቢው ሰላም ዘብ መቆም፣ በልማቱም ረገድ በየተሰማራበት መስክ አምራችና ውጤታማ በመሆን የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

‎በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለማስቆም መንግስት እየሰራ ነው የተባለ ሲሆን የህዘቡን ሰላም የሚያደፈርሱ አካላት ሲኖሩም በህግ አግባብ ማረም እንዲቻል ወጣቱ የሰላም ዘብ በመሆንና ከመንግስት ጎን በመቆም የአካባቢውን ሰላም በአስተማማኝ ደረጃ ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል፡፡

የለውጡ መንግስት እውን እንዲሆን ወጣቱ የነበረውን ሚናና የከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም፤ በሂደትም በአካባቢው ለተመዘገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጤቶች የወጣቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተብራርቷል፡፡

የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት መድረክ ላይ የነበሩት ወጣቶች አብዛኞቹ የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑና ለአመራሮች ቅርበት ያላቸው እንጂ ስለአካባቢው የሰላም ችግር የሚያሳስባቸው ወጣቶች አልተሳረፉም ብለዋል የሚድያችን ምንጮች፡፡ በዞኑ ያለው የፀጥታ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈታ በአመራሮች ላይ ግፊት ሲያደረጉ የነበሩ ወጣቶች ከታሰሩ ወራት ቢቆጠርም የሚስተዋለውም ችግር አልተፈታም፤ በመድረኩ የተነሱ ነገሮች ዘላቂ ለውጥ የሚያመጡ አይደሉም ተብሏል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
ልዩ ዘገባ - በኮንቶማ ተወላጆች ላይ የሚደረግ ወከባ እየባሰ መቀጠሉንና በ17 የኮንቶማ ዜጎች የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው ተነገረ፡፡

ቡታጅራ | May 16/2026 (GNN) በማረቆ ልዩ ወረዳ በኮንቶማ ህዝብ ላይ የሚፈፀም እስርና እግልት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን 17 ዜጎች ላይ የእርስ ማዘዣ ወጥቶባቸው አካባቢያቸውን ለቀው ሄደዋል ተብሏል፡፡

የኮንቶማ ህዝብ ያላበመነበት በከተማ ማስፋፋት ስም ህዝቡ የመበተኛ አጀንዳ ስለተቃወመ ለእስርና ለእንግልት እየተዳረገ ይገኛል፡፡ የማረቆ ልዩ ወረዳ አመራሮች ከተማ እናስፋፋለን ብለው ከእንሴኖ ከተማ አጠገብ የሚገኘው የቀርጠፋ ቀበሌ ህዝብ ለማፈናቀል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

በቀበሌው 95 ፐርሰንቱ የኮንቶማ ህዝብ ሲሆን ቦታው እጅግ ለምና በአመት ሶስቴ የሚመረተበት፤ የከረሰ ምድረ ውሃ በቅርብ ያለው የህዝቡ የኑሮና የኢኮኖሚ መሰረት የሆነ ቦታ ያለ ጥናትና ህዝቡ ፍቃድ ከተማ እናስፋፋለን በሚል የኮንቶማ ህዝብ የመበተን ሴራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የህዝቡን ፍላጎትና ጥያቄ ያልሆነው አጀንዳ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም በጉልበት ለማስፈፀም ዜጎች እየታሰሩና እየተገላቱ ይገኛሉ ሲሉ የህዝቡ ተወካዮች ለጂኤንኤን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በልዩ ወረዳው የመሸጉ ታጣቂዎች በኩኖቀርጠፋ ቀበሌ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከባድ የትኩስ ድምፅ ሲያሰሙና አካባቢውን ሲየሸብሩ አምሽተዋል ተብሏል፡፡ ህዝቡ በአካባበው ለሚገኘው ለአድማ ብተና ሀይል በተደጋጋሚ ቢደወልም የመጣ ሀይል አልነበረም፤ የኮንቶማ ህዝብ ሰላማዊ ህዝብ ነው የጠየቀው ጥያቄ የለም፤ ጥናታዊ ያልሆነ የከተማ ምስረታ ግን ተቃውሟል፡፡

በዚህ ምክንያት እየተነገላታ ይገኛል፡፡ ታጣቂዎቹ ሰሞኑ ታስረው የተፈቱ ሰዎች ደጅ ላይ ነው ሲተኩሱ ያመሹት፤ ማታ ሲደወልላቸው ያልመጡት የፀጥታ ሀይሎ ጠዋት በፓትሮል አከባቢውን ሲያውኩና ግርግር ሲፈጠሩ ቆይተዋል፡፡

የኮንቶማ ህዝብ ጩኸት፤ አዲስ የሚመሰረት ከተማ አንፈልግም፤ እንሴኖ ከተማ ቅርባችን ነው፤ ህዝባችን በአመት ሶስቴ አምርቶ የሚጠቀመው መሬት ልንነጠቅ አይገባም፤ ይህ ከተማ መመስረት ሳይሆን የኮቶማ ህዝብ ሆን ተብሎ ለመበተን የሚደረግ ሴራ ነው በሚል እስከ ክልሉ ድረስ ጩኸታቸውን እያሰሙ መሆኑ ለጂኤንኤን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

እንሴኖ ከተማ ለእኛ 500 ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው፤ ሌላ አዲስ ከተማ የኮንቶማ ህዝብ አይፈልግም ብሎ በነቂስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ በተደጋጋሚ አቤቱታ አስገብተናል ብለዋል።

የክልሉ ኮንስትራክሽን ቢሮ አብዛኛው ባለሙያ የኮንቶማ ህዝብ ጥያቄ የማይቀበሉ የማረቆ ተወላጆችና እነሱ የሚደግፉ በመሆኑ የህዝብን አቤቱታ ከማዳመጥና ትክክለኛ ውሳኔ ከመስጠት ይልቅ ለቅሬታ የሄዱ ሰዎችን ንግግር ሪከርድ እያደረጉ ለማረቆ ወረዳ አመራር እየላኩ ግጭት እንዲፈጠር እያረጉ ይገኛሉ። የማረቆ ልዩ ወረዳ አመራሮች ከክልሉ ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለሙያዎች በሚያገኙት መረጃ የኮንቶማ ህዝብ እያንገላቱ ይገኛሉ፡፡

የልዩ ወረዳው አመራር ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከሊቱ 9:30 ላይ ቀርጠፋ ቀበሌ በመግባት ህዝብን በማወክ ባለፈው ታስረው ከተፈቱት መካካል ሁለት ሰዎችን ይዘው ሄደዋል። አሁንም ብዙ ሰው እናስራለን እያሉ እየዛቱና እያስፈራሩ ሄደዋለ። በ17 ሰዎች ላይ የእስር ማዘዣ አውጥተው ለማስር እየፈለጉ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ዜጎች አካባቢያቸው ለቀው እየሄዱ ነው፡፡

የታሰሩት ሁለቱ ዜጎች ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ታስረው የተፈቱ ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ ያለ ወንጀላቸው በተደጋጋሚ እየታሰሩ የሚገኙት የኮንቶማ ህዝብ ተወካዩ አቶ ሙላቱ ለሜ ናቸው፡፡

ከአራት ወር እስር በኋላ እንደጋና የታሰሩት የ80 አመት ሽማግሌው አቶ ሙላቱ ለሜ የሞተር አደጋ ደርሶባቸው ህክምና እየተከታተሉ ባለበት ወቅት ነው በድጋሚ የታሰሩት ተብሏል። ከአቶ ሙላቱ ጋር አብረው ታስረው የነበሩት አቶ ብርሃኑ ሲሆኑ ሁለቱም ከሁለት ቀን በፊት ማታ ደጃቸው አምጥው ጥለዋቸው ሄደዋል ተብሏል፡፡

የማረቆ ልዩ ወረዳ አመራር ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለይም የልዩ ወረዳ አስተዳደር አቶ ጀማል አማሮ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የኮንቶማን ህዝብ ለመበተንና ከሌላው ህዝብ ጋር ለማጋጨት ሴራ ላይ ተጠምደዋል፡፡

የወረዳው አመራሮች በልዩ ወረዳው በሚገኙ የኮንቶማ ቀበሌዎች ሆቤ፣አሌመናና ቀርጠፋ ቀበሌዎች ከ95% በላይ የኮንቶማ ህዝብ የሚገኝባቸው ቀበሌዎች እንደሆነ ይታወቃል ነገር ግን የአመራሩ ሴራ የተቃወሙ ዜጎች በእስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ በዚህ አመት ከወራት በፊት የኮንቶማ ተወላጆች ከ30 በላይ ያለመጥረያና ያለወንጀላቸው የልዩ ወረዳው አመራር አስሮ እያሰቀየ እንደነበር GNN በዘገባው ይፋ ማድረጉን ይታወሳል።

በተለይም ከተማ እንመሰርትበታል በሚሉት ቀበሌ የከርሰ ምድር ውሃ በቅርብ ስለሚገኝ አረሶ አደሩ በዓመት ሶስት ጊዜ አምርቶ ከእራሱ አልፎ ለአጓራባች ወንድም ህዝብ የገበያ ንረትን ከማረጋጋቱም በላይ ብዙ ወጣት እንዳይሰደድ ትልቅ እድል የፈጠረ ወሳኙ ቦታ ነው።

አጀንዳቸውም ከተማ መመስረት ሳይሆን የኮንቶማን ህዝብ ለማፈናቀልና ለመበትን የተደረገ ሴራ ነው፤ህዝቡን ሳያወያዩና ማንም ሳያውቅ በአመራሩ የተዘጋጀ ሀሰተኛ የአርሶ አደር ስም ዝርዝር ለክልል በመላክ በህዝብ ስም እስከ መዋሸት ደርሰዋል፡፡ የህዝቡ ተወካዮች ከሶስት ጊዜ በላይ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ ህዝቡ አቤቱታ አሰምቷል። በጣም የሚገርመው የክልሉ አመራርና ባለሙያ ያስገባውን አቤቱታ ታች ወርዶ ከማጥራት ይልቅ አቤቱታ ያመጣውን አርሶ አደር በቪዲዮ እየቀረፁ ለልዩ ወረዳ አስተዳዳር እየለኩ ጭምር ሽፍጥ እየሰሩ ናቸው።

የኮንቶማ ህዝብ የገበያም የከተማ ችግር የለበትም፤ ይህ ለህዝብ ታስቦ ሳይሆን ከወንድም መስቃን ህዝብ ለማቀቃር በልዩ ወረዳው አመራሮች የተፈጠረ አጀንዳ ስለሆነ አንቀበልም እያለ ይገኛል፤ የአርሶ አደሩን የማፈናቀል አጀንዳ አንቀበልም፤ አቤቱታችንን ለሚመለከተው ሁሉ እናሰማለን የሚል አቋም ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ የክልሉ መንግስትም ህዝባዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በጥቂት ከወረዳ እስከ ክልሉ በተደራጁ አመራሮች የኮንቶማ ህዝብ መፈናቀል አይገባውም ብለዋል፡፡

For more info:

1) Telegram channel: https://t.me/gnntv2024
2) YouTube channel: https://youtube.com/@tiyanewsnetwork-2828?si=OhhtadsfXhK63Doj
🔥2