ግጻዌ
8.76K subscribers
290 photos
5 videos
13 files
159 links
የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።
Download Telegram
Tëshü፳፩:
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ ታሪክ ተረት ተረት ወይስ
ትንሳኤ አላት የሚባለውስ እውነት ሀሐሰት

ወጣ ወጣና እንደሸንበቆ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ፠
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇☝️☝️☝️☝️☝️☝️
❤️❤️ #ታኅሳስ_19 ❤️❤️
እምብርሃን እስከ ኖላዊ ብርሃን ይትበሃል መዝሙር ዘብርሃን አቅዲሙ ነገረ በኦሪት፡፡
#ዘቅዳሴ
#ሮሜ_13:11-ፍጻሜ፡ወዘኒ ተአምሩ ከመ በጽሐ ጊዜሁ"ከእንቅልፍ የምትነቁበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዕወቁ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ደርሳለችና፡፡............................................................................................ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት የሥጋችሁንም ምኞት አታስቡ፡፡"
#1ኛ_ዮሐንስ_1:1-ፍጻሜ፡
ንዜንወክሙ በእንተ ውእቱ"ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና በጆሮአችን የሰማነውን
........................................................አልበደልንም ብንል ግን እርሱን ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ዘንድ የለም፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_26:12-19፡ወእንዘ አሐውር ሀገረ ደማስቆ"ይህንም ለመፈጸም ከሊቃነ ካህናት ሥልጣን ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ከተማ ሄድሁ፡፡...............................
........................................................ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋራ አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው፡፡"
#ምስባክ
ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ
እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ
ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ፡፡
#ትርጉም
ብርሃንህንና እውነትህን ላክ
እነርሱ ይምሩኝ
ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ መኖሪያህ ይውሰዱኝ፡፡
#መዝ_42:3
#ወንጌል
#ዮሐንስ_1:1-19፡ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ"በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡...........
........................................................በአባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ገለጠልን እንጂ እግዚአብሔርንስ ከቶ ያየው የለም፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘአትናቴዎስ፡፡
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from elam
መዝሙር ዘብርሃን

ከታኅሣሥ ፲፬ - ፳

አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ በአፈ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኀጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ

ትርጉም፦

ለጽዮን የደስታ ቃልን የሚነግራት ወልድ በምስጋና እንደሚመጣ አስቀድሞ በኦሪት ተነገረ ዳግመኛ በዳዊት አንደበት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው አለ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን ለጻድቃን የሚያበራ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ነው የጠፋውን ይረዳ/ይፈልግ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደእኛ መጣ

አጭር መግለጫ

፩ በኦሪት ዘፍጥረት ፫፥፳፪ "አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንዳንዱ ሆነ" ተብሎ የተነገረው፤

፪ በዘፍጥረት ፱፥፳፯ "እግዚአብሔር በሴም ድንኳን ይደር" ተብሎ የተነገረው

፫ በኦሪት ዘጸአት ፫፥፪ ጀምሮ በምሳሌ የተገለጠው

፬ በዘጸአት ፴፫፥፳፫ "ጀርባዬን ታያለህ ፊቴ ግን ለአንተ አይታይም" ተብሎ በምሥጢር የተነገረው

፭ በኦሪት ዘኊልቊ ፳፬፥፲፯ "ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤል ሰው ይነሣል" ተብሎ በምሳሌ የተገለጠው 

፮ በኦሪት ዘዳግም ፲፰፥፲፭ "አምላክህ እግዚአብሔር ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል እሱን ስሙት" ብሎ ሊቀ ነቢያት ሙሴ የተናገረው 

፯ በትንቢተ ኤርምያስ ፴፩፥፲ "አሕዛብ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ  በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶታል፥ ከበረቱበትም እጅ አድኖታል" ተብሎ የተነገረው የማጽናኛ ትምህርትና ሌሎችም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው እንደሚሆንና እኛን እንደሚያድነን አስቀድመው በኦሪትና በነቢያት መጻሕፍት የተመዘገቡ ናቸው። ሊቁም የዘመረው ይህንን እያነጻጸረ ነው። 

የዕለቱ ምንባባት፦

ሮሜ ፲፫፥፲፩ - ፍ፤
፩ዮሐ ፩፥፩ - ፍ፤
ግብ ፳፮፥፲፪ - ፲፱

የዕለቱ ምስባክ፦

ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቅከ 
እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ
ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ መዝ ፵፪፥፫

ትርጉም፦

ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ 
እነሱ ይምሩኝ
አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደማደሪያህ ይውሰዱኝ

ምሥጢር፦

ብርሃነ ረድኤትህን አንድም ቂሮስ ዳርዮስን ዮሴዕ ዘሩባቤልን ላክልኝ 
እነሱ መመስገኛህ ወደምትሆን ወደ ኢየሩሳሌም መርትው ይውሰዱኝ

አንድም ብርሃን ልጅህን ላክልኝ። አንድም ብርሃነ ጽድቅ ክርስቶስ ሆይ ሥጋህን ደምህን ስጠኝ
አንድም ሐዋርያትን ሰባ አርድእትን ላክልኝ
እነሱ መርተው ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያግቡኝ

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፩፥፩ - ፲፱

ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

ከወንጌሉ ንባብ ውስጥ፦

ወሕይወትሰ ብርሃኑ ለእጓለ እመሕያው 
- ሕይወት ግን ለሰው ብርሃን ነው ማለት ሕይወትነቱም ለሰው እውቀት መሆን ነው። እውቀት የሌለው ሕዝብ ይጠፋልና። ሆሴ ፬፥፮

አንድም ሕይወትነቱ ምግብ በመሆን ነው ሥጋውን የበላ ደሙን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለውና

ማወቅ የሚገባንን አውቀን ሥጋውን ደሙን እየተቀበልን በተሰጠን ጸጋና በተፈቀደልን የአገልግሎት ዘርፍ ብንሰማራ በብርሃን እየተመላለስን ነው ሥራችን መልካም ስለሆነ ወደ ብርሃን እንቀርባልን በብርሃን እንመላለሳለን ከጨለማ ሥራ እንርቃለን ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ በተባለው መሠረት መልካሙን ሥራችንን ያዩ ሁሉ ይደሰታሉ እንደእኛ ለመሆንም ይመኛሉ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይሰፋል

በብርሃኑ ብርሃንን እናይ ዘንድ በብርሃን እንመላለስ ዘንድ በብርሃናዊ ዓላማ  ወደ ቤተ ክርስቲያን እንምጣ
Forwarded from ✞ኬብሮን
:
፠ኬብሮን፠


አንተ ሰው !
ቃለ እግዚአብሔርን ተማር !
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር !
ኹልጊዜ ተማር !
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡ ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡ ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


@kebbron
@kebbron
@kebbron
https://telegram.me/ethiopianorthodoxyouth

ቻናላችንን ተቀላቀሉ
join our channel

ግን እኔ ምንድነኝ ? እውነት ለአንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እጨነቃለሁ ?አስባለሁ ?

ከሆነ ብያንስ ይህን Link ለ ፭ [5] ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እልካለሁ .........
.....
ኦርቶዶክሳዊ ወጣት አንተ ነህ! አንቺ ነሽ! እኛ ነን! ይህ ለኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች የተዘጋጀ ቤት ነው ቦታህ እዚህ ና Join አድርግ ቤተክርስቲያን ትፈልግሀለች ና አብረን እንሰራለን። የተማርነው እናስተምራለን ያልተማርነው እንማራለን። ቤተክርስቲያንህን ትወዳለህ? አናግረን ምንም አይኑርህ ግድ የለም በምን ላገልግል በለን።
እንወያይ @Eorthodoxbot
ይቀላቀላሉ
@ethiopianorthodoxyouth
@ethiopianorthodoxyouth
@ethiopianorthodoxyouth
#ታኅሣሥ_26 (ዘሰንበት)
እምኖላዊ እስከ 27 ለታኅሣሥ ኖላዊ ይትበሃል፡፡መዝሙር ዘኖላዊ ኖላዊ ዘመጽአ፡፡
#ዘቅዳሴ
#ዕብራ_13:16-ፍጻሜ፡ወኢትርሥዑ አኃዊነ ምሂረ ነዳያን"ነገር ግን ለድሆች መራራትን ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ....................
................................................መምህሮቻችሁን ሁሉና ቅዱሳንንም ሁሉ ሰላም በሉ በኢጣልያ ያሉ ሁሉ ሰላም ብለዋችኋል፡፡የጌታችን ጸጋው ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን፡፡"
#1ኛ_ጴጥሮስ_2:21-ፍጻሜ፡
ወበእንተ ዝንቱ ተጸዋዕክሙ"ለዚህ ተጠርታችኋልና ክርስቶስም እኮ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምሳሌውን ሊተውላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአል፡፡...........................................................................እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁንም ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመለሱ፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_11:22-ፍጻሜ፡
ወተሰምዐ ዝነገር በአብያተ ክርስቲያናት"ስለ እነርሱ የተነገረውም ይህ ነገር በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተሰማ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት፡፡
.................................................እንደዚህም አድርገው በበርናባስና በሳውል እጅ ወደ ቀሳውስት ላኩት፡፡"
#ምስባክ
ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ
#ትርጉም
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ
የእስራኤል ጠባቂ ሆይ አድምጥ
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ፡፡
#መዝ_79:1-2
#ወንጌል
#ዮሐንስ_10:1-22፡አማን አማን እብለክሙ"እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ በሌላም በኩል የሚገባ ሌባ ወንበዴም ነው፡፡በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው፡፡.............
................................................ሌሎችም ይህ ነገር ጋኔን ከያዘው ሰው የሚገኝ አይደለም ጋኔን የዕዉሮችን ዐይን ማብራት ይችላልን? አሉ፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኩተከ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from elam
መዝሙር ዘኖላዊ

ከታኅሣሥ ፳፩ - ፳፯

ኖላዊ ዘመጽአ ውስተ ዓለም ወልዱ ወቃሉ ለእግዚአብሔር ዘወረደ እምላዕሉ በአቅሙ ክርስቶስ እስመ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ይቤሎ አብ ለወልዱ ወልድየ ንበር በየማንየ

ትርጉም፦

ወደ ዓለም የመጣው እረኛ የእግዚአብሔር አብ ቃሉና ልጁ ነው ከላይ የወረደውም ክርስቶስ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው (ፍጹመ አካል ፍጹመ ክብር ነው) የሰንበት ጌታ እሱ ነውና አብ ልጁን ልጄ በቀኜ ተቀመጥ አለው

የዕለቱ ምንባባት፦

ዕብ ፲፫፥፲፮ - ፍ፤
፩ጴጥ ፪፥፳፩ - ፍ፤
ግብ ፲፩፥፳፪ - ፍ፤

የዕለቱ ምስባክ፦

ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ 
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ መዝ ፸፱፥፩ 

ትርጉም፦ 
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ የእስራኤል ጠባቂ አድምጥ
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ 

ምሥጢር፦

የዮሴፍ በጎች እንዲጠበቁ እስራኤል ዘነፍስን የምትጠብቅ ሆይ ጸሎታችንን አድምጥ ስማ 

በዘባነ ኪሩቤል ተቀምጠህ በአንድነት በሦስትነት የምትመሰገን አቤቱ ሚጠተ ሥጋውን በማድረግ ተገለጥ አንድም በሥጋ ማርያም ተገለጥ አንድም በመምርነት ተገለጥ

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፲፥፩ - ፳፪

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ

የወንጌሉ አጠቃላይ መልእክት

፩ በበሩ የማይገባ በሌላ የሚገባ ሌባ ነው። ይህ ማለት ትንቢት ሳይነገርለት አብ ሳይመሰክርለት የመጣ ሌባ ነው ማለት ነው

ዛሬም በበሩ የማይገቡና በትክክለኛው በር መግባትን የሚከለክሉ በሰፊው መንገድ የሚሄዱና የሚወስዱ ብዙ ናቸው።

እኛን የሚጠቅመን ግን በጠበበው ደጅ መግባቱ ነው እሱ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ያደርሰናልና።

፪ በጎቹ የእረኛቸውን ድምጽ ሰምተው ለይተው ያውቃሉ 

የቤተ ክርስቲያን ድምጽ የሚመስሉ ግን ያልሆኑ ብዙ ድምጾች አሉ እውነተኛውን ድምጽ መስማትና እውነተኛውን እረኛ መከተል ለሕይወታችን ይጠቅመናል

፫ ከእውነተኛው እረኛ በፊት የመጡ ሌቦች ነበሩ

በግብረ ሐዋርያት ፭ እንደተገለጠው ይሁዳ ዘገሊላና ቴዎዳስ ዘግብጽ ክርስቶስ ነን ብለው ተነሥተው ነበር እነሱም ጠፉ የተከተሏቸውም ጠፍተዋል። 
የምንከተላቸው የሚያድኑን እንጂ የሚያጠፉን መሆን የለባቸውም። እንዴት እናውቃቸዋለን ብለን እንዳንጨነቅ አምላካችን ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ብሎናል

፬ በበሩ የሚገባ መውጣት መግባት ይችላል መሰማሪያም ያገኛል

ይህ የሚያሳየን በአባታችን ቤት ያለንን ነጻነትና የዘለዓለም ዕረፍት ነው። የልጅነት መብትና መንፈስ ስላለን የአባታችንን መንግሥት የመውረስ ሥልጣን አለን።

፭ ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ሲመጣ እውነተኛው እረኛ ግን ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲበዛልን መጣ

ነፍሳችንን የሚሰርቁ ለዘላማዊ ሞት በሚዳርግ በኑፋቄ በክህደት ሊያጠፉን የሚተጉ አሉና ከእነዚህ እንራቅ

፮ በጎቹ የእሱ ያልሆኑ ምንደኛ ወይም ሙያተኛ ተኲላ ሲመጣ በጎቹን ትቶ ይሸሻል

በዘመናችን በተኲላዊ ግብር ውስጥ ሆነው የእረኝነት ሥራ የሠሩ እየመሰሉ ትቶ መሸሽ ብቻ ሳይሆን አስመስለው በያዙት የእረኝነት ሥልጣን በጎችን ቆመው የሚያስበሉና ለዚህ ዓላማ እየሠሩ ያሉ ብዙዎች እየሆኑ ስለመጡ ማነው እረኛችን የሚለውን ጠይቆ ምላሽ ማግኘት አስፈላጊ ነው

፯ እረኛው አንድ ነው መንጋውም አንድ ነው

በመጽሐፍ ያለው እውነት ይህ ሆኖ እያለ በተለያየ ምክንያት በልዩነት መንገድ እየሄድን አለመስማማትን መጨቃጨቅን መካሰስን ስም መጠፋፋትን መለያችን ወደ ማድረግ ከፍ እያልን መጥናተናል አይጠቅመንምና ከእንዲህ ዐይነቱ አካሄድ ራሳችን በቃሉ ልጓምነት ልንገታ ግድ ነው።
Forwarded from elam
ጌታችን በቤተ መንግሥት ሲጠበቅ በቤተልሔም በከብቶች በረት ተወለደ ፤ መኳንንት ፣ መሳፍንትና ነገሥታት በወርቅ መጎናጸፊያ ከብርድ ሊታደጉት ሲገባ እርሱ ግን የበጎችንና የአህያዎችን ትንፋሽ መረጠ፡፡

እንኳን ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሰላም አደረሳችሁ፡፡

@gitsawe
ኢትዮጵ-ኤል
@ethiopel
በዚህ ቻናል የተለያዩ ፅሁፎች ማለትም
ስለ ጥንት ኢትዮጵያውያን አባቶች ስልጣኔ፣ ታሪክ፣ፍልስፍና እና ምርምር
ከተለያዩ መፃህፍት የተውጣጡ አጫጭር ፅሁፎች
ወቅታዊ ጠቃሚ መረጃዎች
ግጥሞች
አጫጭርና ተከታታይ ልብወለዶች
እንዲሁም ስዕሎች እና የመፅሀፍ ጥቆማ ይቀርባሉ

join በማድረግ ይቀላቀሉ
ለሌሎችም share ያድርጉ



ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት ☞@ethiopelbot
🎬 በጎል በጎል ሰባ ሰገል Begole Begole | ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ | የጥምቀት መዝሙር | የመዝሙር ግጥሞች | ethiopian ortodox

👤 በጎል በጎል ሰባ ሰገል
📒የመዝሙር ግጥሞች

https://youtu.be/uvNKg4PfiYQ
https://youtu.be/uvNKg4PfiYQ
የዓለምን በደል | yealemn bedele | ማህበር ቅዱሳን | የጥምቀት መዝሙር | የመዝሙር ግጥሞች | ethiopian ortodox
📒የመዝሙር ግጥሞች
🕛 03:47 💾 - MB

🎙ሙሉ ዝማሬውን ምስል ወድምፅ
በዚህ👇 ያገኙታል
https://youtu.be/l955uDogbu0
https://yo
በዮርዳኖስ የተጠመቀው | Be Yordanos Yetetemkaw | በማህበር ፊልጶስ | የጥምቀት መዝሙር | የመዝሙር ግጥሞች | ethiopian ortodox
📒የመዝሙር ግጥሞች
🕛 03:47 💾 - MB

🎙ሙሉ ዝማሬውን ምስል ወድምፅ
በዚህ👇 ያገኙታል
https://youtu.be/J9Oj_r6FR
የመዝሙር ግጥሞችን በ ዮትዮብ በምስልና በድምፅ ለማግኘት ከታች #subscribe ያደረጉ እናመሰግናለን 👇👇 https://m.youtube.com/channel/UCT0ZmyrHuUjn5asLzK-kBTQ
"ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል።

ስለዚህም በመጽሐፍ "አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው" ተብሏል። (መዝ. 136፥8-9) የባቢሎን ልጅ (የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (1ቆሮ. 10፥4) ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።"

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
Forwarded from "ዮአስ" EOTC (yonas)
መስቀል ለምን አንደምንሳለም ያውቃሉ ?
"ተዋሕዶን ልወቃት"-ክፍል 14
@EOTCyoas
መዳን በሌላ በማንም የለም/ሐዋ 4፥12/)
አንዳንዶች የቅዱሳንን ማዳን ለመቃወም "መዳን በሌላ በማንም የለም"/ሐዋ 4፥12/ የሚለውን ይጠቅሳሉ፡፡ አዎ መዳን በሌላ በማንም የለም አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ያለ እርሱ አዳኝ የለም፡፡ ቅዱሳን መላዕክት, ሐዋሪያት ቢያድኑ እንኳን ዋናው ምንጩ( በእነሱ አድሮ የሚሰራው) እሱ ኢየሱስ ነው ለማለት ነው እንጅ ሐዋሪያት እኮ የማዳን ስልጣን ተሰጥቷቸዋል/ማቴ 10፥1/ ሲያድኑም አይተናል "ጴጥሮስና ጳውሎስ በጥላቸውና በቀሚሳቸው ወይም በልብሳቸው ቁራጭ አዳኑ(ሐዋ 5፥15, ሐዋ19፥11) ፣ መላእክት እንደሚያድኑም መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ነግሮናል(መዝ 33፥7)፡፡ ነገር ግን የነሱ የመናፍቃን ችግራቸው የቅዱሳንን ማዳንና የኢየሱስን ማዳን ይቀላቅላሉ እኛ ግን ለይተናል፡፡ የዛሬዎቹ ከአይሁድ የማይሻሉ መናፍቃን ቅዱሳን ሐዋሪያት አያድኑም ይላሉ እንጅ አይሁድ እኮ እነ ጴጥሮስ አንካሳውን ሰው/ሐዋ 3፥2/ እንዳዳኑት (የሐዋሪያትን ማዳን) አውቀዋል፣ ነገር ግን በማን ሀይል በማን ስም እንዳዳኑት/ሐዋ 3፥6/ ምንጩን ሲጠይቋቸው እንድህ ብለው መለሱ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና" /ሐዋ 4፥12/ ብለው መለሱ ትክክል ናቸው፡፡ መናፍቃን ቅዱሳንን አያድኑም ይበሉ እንጅ የእነሱን የራሳቸውን ማዳን አይቃወሙም በየቻናሎቻቸው በየፖስተሮቻቸው የፈውስ ቀን ፣ ኮቴን የነካ እንኳን ይድናል፣ ማንም ማን ሊጨብጠኝ አይችልም፣ እንፈውሳለን፣ እናድናለን ይላሉ፡፡ የራሳቸው ማዳን ይሰብካሉ ቅዱሳንን ግን አያድኑም ይላሉ፡፡ እኛም አንሰማችሁም እንላቸዋለን፡፡