ግጻዌ
8.56K subscribers
290 photos
5 videos
14 files
161 links
የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።
Download Telegram
ቤተ ክርስቲያን ፍቺን የምትፈቅደው መቼ ነው?

የሰርግ ወቅት እየደረሰ ነውና እጅግ ደማቅ እና ያማረ ሰርግ እንድናዘጋጅልዎ ያናግሩን!

በበዓለ ሃምሳ ሰርጋችሁን ለማድረግ እየተዘጋጃችሁ ያላችሁ ጥንዶች ይደውሉልን። ሰርግዎን እጅግ ባማረ እና ደማቅ ሁኔታ ከሌሊት ጀምሮ እናዘጋጅልዎታለን።

እርስዎ ልብስዎን ለብሰው በሰርግዎ ቀን ብቻ ስለመገኘት ያስቡ። የሰርግ ዝግጅት ጭንቀቱን ለእኛ ይተዉት!

📞 0991135756

ከታች ባሉት የማህበራዊ ሚዲያ መስፈንጠሪያዎች(Links) ያገኙናል። ያናግሩን! 👇

https://linktr.ee/betedokimaseotcweddings

Book Your Wedding with us!
we craft the best orthodox weddings!
.
.
ቤተ- ዶኪማስ ኦርቶዶክሳዊ ሰርግ አጋፋሪ
| Bete - Dokimas EOTC Wedding Planners |

ከታች ባለው verified የቴሌግራም አካውንት ይጻፉልን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Betedokimaseotcweddingplanners
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


@betedokimaseotcweddings
@betedokimaseotcweddings   
@betedokimaseotcweddings

#dokimas #eotc
3👍2
"ብክይዎ ወላህውዎ እለ ታፈቅርዎ"
"የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት"
.....................................................

  የክርስቶስን ሕማም በመዘከር የሚታወቀው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ "ብክይዎ ወላህውዎ እለ ታፈቅርዎ | የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት" ብሎ ያውጃል።

  ሕዝቡም እንዲህ ብሎ ተሰጥኦውን ይመልሳል:-

  ዬዬዬ አማኑኤል አምላክነ | ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን

  ዬዬዬ ኢየሱስ መድኃኒነ | ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ

  ዬዬዬ ክርስቶስ ንጉሥነ | ወየው ወየው ወየው ንጉሣችን ክርስቶስ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዬዬዬ ብላ በዐቢይ ዜማ የምታዜመው የሙሽራዋ ክርስቶስ መከራን እያሰበች ስታለቅስ ነው። አሁንም ከዕንባ እና ከስግደት ጋር መከራውን እያሰብን ከእናታችን ቤተ ክርስቲያን ጋር ለምንወደው ለሚወደን አምላካችን እናለቅሳለን!

የእኛን ኃጢአት ተሸክሞ የሕማም ዋጋ በከፈለበት ዘባኑ ላይ በኃጢአት እየተጨማለቅን ሸክሙን ሕማሙን ስላከበድንበት ስለ ኃጢአታችንም እናለቅሳለን!

ወዮ ለእኛ የእሾህ አክሊሉ ላይ እሾህ ለጨመርን! ወዮ ለእኛ ከልቶስጥራ እስከ ቀራንዮ የሚሰቀልበት መስቀልን ተሸክሞ የተጓዘበትን የሕማም መንገድ ላረዘምን!

.....................................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ሕማማት ሳምንት , 2017 ዓ.ም

👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
7👍7😢3
እመብርሃን ሆይ የራስሽ ጉዳይ!
...........................................

  ሁሉም ሰው የሚጨነቅበት፣ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ የሚነጫነጭበት አንዳች ችግር፣ አንዳች ምሬት አያጣውም አይደል? አንዳንድ ሰው ደግሞ እግዚአብሔር ፊት ሄዶ መነጫነጩ ብቻ በቂ አይሆንለትም። ያገኘው ሰው ሁሉ ፊቱን አይቶ ምሬቱን፣ ኃዘኑን እስኪያውቅበት ድረስ የሚከፋ ሰው አለ። የሚገርማችሁ እኔም እንደዚያ አይነት ሰው ነኝ። አይክፋኝ እንጂ ከከፋኝ "ምነው ፊትህን ጣልከው" የሚለኝ ሰው ከመብዛቱ የተነሳ የጣልኩትን ፊት መሬት ላይ ልፈልገው ምንም አይቀረኝ!

  ታዲያ ከዕለታት በአንድ ፊቴን በጣልኩበት ቀን እጅግ ከምወደው ጓደኛዬ፣ እኩያዬ ሲሆን መምህሬ ጋር ስለ ሥራ ጉዳይ ልናወራ ተገናኝተን ቁጭ አልን። ምንም እንዳልተፈጠረ ለማውራት ብሞክርም የጣልኩት ፊቴ ሊነሳ ስላልቻለ "ምን ሆነህ ነው" ብሎ ይጠይቀኝ ጀመር። "እሱን ተወውና ስለ ሥራችን እናውራ" ብዬ ላስቀይስ ስሞክር አስቆመኝ እና "መናገር ካልቻልክ አላስጨንቅህም ግን ማሰብ ያለብህ ነገር ከአንተ አቅም በላይ በሆኑ እና መፍታት በማትችላቸው ችግሮች እንዲች ብለህ እንዳትጨነቅ። ለእመብርሃን ሂድና ይሄ የራስሽ ጉዳይ ነው አያገባኝም በላት፤ የእኔ እርዳታ ወይም ይህን ችግር ለመፍታት እኔ ሳስፈልግሽ ግን ጥሪኝ እተባበርሻለሁ በላት። ለእርሷ የራስሽ ጉዳይ ብለህ ሰጥተህ አንተ ዕረፍት ታደርጋለህ አበቃ። እመብርሃን ያለህበትን ምሬት እና ኃዘን የማትረዳ ይመስልሃል? የራስሽ ጉዳይ ብለህ ለእርሷ ኃላፊነቱን ካስረከብክ የማትወጣው ይመስልሃል? የራስሽ ጉዳይ ብለህ ስታስረክባት የእውነት የራሷ ጉዳይ የማታደርገው ይመስልሃል? ሁሉ በእጇ፣ ሁሉ በደጇ፣ ክርስቶስም ልጇ መሆኑን ረሳኸው እንዴ?

  ከዚያ ግን የራስሽ ጉዳይ ብለህ ለእርሷ ከሰጠሃት በኋላ ችግሩ በእመብርሃን እጅ የተያዘ አንተ የማትጨነቅበት ጉዳይ መሆኑን አምነህ መቀበል አለብህ። ኃዘንህን እና ምሬትህን ለእርሷ እና “ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል” (መዝ 55፥22) ለተባለለት ልጇ ከሰጠህ በኋላ የሚፈጠረው አስከፊም ይሁን አስደሳች ነገር እመብርሃን ጉዳዩን በመፍታት ሂደት ላይ የሚፈጠር አንድ ሁነት መሆኑን በማመን ምንም ቢፈጠር ከነልጇ ታመሰግናታለህ፣ ታወድሳታለህ ማለት ነው።" ብሎ በደቂቃዎች ንግግር አጽናናኝ።

አንድ ሰው ከአቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ሲጠይቀን "ወግድልኝ ይሄ ከአቅሜ በላይ ነው የራስህ ጉዳይ" እንደምንለው ሸክሙ ሲከብድብን፣ ኃዘኑ ሲበረታብን የኃዘንን ጥግ ለምታውቀው እመአምላክ " እመብርሃን ሆይ ይሄ ከአቅሜ በላይ ነው የራስሽ ጉዳይ!!" ብሎ ማስረከብ እንዴት ያለ ማስተዋል ነው?

.............................

ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ሚያዚያ, 2017 ዓ.ም
.
.
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
42👍13🥰2🙏1
መልክዐ ጥበብ.pdf
12.7 MB
⭐️⭐️ + መልክዐ ጥበብ + ⭐️⭐️

እነሆ በ ጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው "መልክዐ ጥበብ" መጽሔት ወደ እናንተ ምትደርስበት ሰዓት አሁን ሆነ።

መልክዐ ጥበብ የተሰኘች የግቢ ጉባዔያችን ዲጂታል መጽሔት ለንባብ ፀሐይ ትበቃ ዘንድ አስጀምሮ ላስፈጸመን ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው። በጎደለው በአፈ መላዕክት ይሙላልን!

በማንበብና ለወዳጆቻችሁ #share በማድረግ ጥበብ የምታሰማውን አውታር እናስተጋባላት!!


መልካም ንባብ!!!
🗒🗒🗒🗒🗒🗒🗒🗒🗒🗒🗒

⭐️ +Malkaa Ogumma+ ⭐️

Barruun "Malkaa Ogumma " kan hawwii guddaan eegamaa ture yeroon isin bira ga'u amma.

Malkaa ogumma kan jedhamtu barruun dijiitaalaa yaa'ii mooraa keenyaa dubbisaaf akka ooluuf(gahuuf) kan nu jalqabsiisee nu xummursiise Waaqa keenya Waaqa Ol’aanaa ta’eef galanni haa ta’u. Wanta hanqate afaan ergamootaa nuuf yaa guutu!

Dubbisuun Hiriyyoota keessaniif #share gochuun, sagalee oogummaan dhageessistu yaa dhageechisnu


#share #read
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @jitgibigubae  👈
👉 @jitgibigubae  👈
👉 @jitgibigubae  👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
👍2