ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
9 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#መታረቅ_ከራስ_ነው

በጠለቀ ስሜት ውስጥን በሚጠይቅ
የህይወትን ግጭት ከራስ በሚያስታርቅ
ማሰብ ማሰላሰል እራስን መጠየቅ
በውስጣዊ ውበት ከራስ ጋር መታረቅ
ከአለፈው ልምድ ወስዶ ዛሬ ላይ አስቦ
የነገን ህልም ስሌት በተስፋ ደርቦ
ለተሰጠው እድሜ ምስጋና እየቸሩ
መታረቅ ከራስ ነው መብሰል እያደሩ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌6🔥5👍1🥰1
ሽሽት ሽሽት አለኝ
ግን ወዴት ይሸሻል
ህይወት ያው ህይወት ነው
     ይነጋል ይመሻል
ሰውም እንደዘበት ይቀርባል ይርቃል
እኮ ወዴት ልሽሽ ውስጤ ይጨነቃል
አንድ ፈጣሪ ግን መድረሻዬን ያውቃል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
20👍4🎉2
#ሰውና_ዘመን

ሰው ዘመንን ሲከስ
እድሜም ሲገሰግስ
ከላይ ያለው ሲስቅ
የስሩ ሲጨነቅ
ሰውና ዘመንን ሲጠፋ አስታራቂ
አዋቂነት ጠፍቶ ሲበዛ ታዋቂ ፤
በእንዲህ አይነት ህይወት እድሜ እየለመኑ
አሁን ምን ይባላል ? ማለት ነው ዘመኑ?
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍11🫡3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍5🥰2
ማለፍ ብችል በዝምታ
ቅድሚያ ብሰጥ ለይቅርታ
ሞኝነቴ በዝቶባቸው
ይቅርታዬ ቀሎባቸው
ዳግም ጥፋት እየሰሩ
የልቤን ክር አከረሩ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍13👌94🔥1
በዚህ ድፍረት ግዜ በዚህ መከራ ዓለም
ጥሎ ማለፍ እንጂ መደጋገፍ የለም!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍13
#አፋልጉኝ

ዓመታት ሆኖታል ከቤቱ ከወጣ
ማወቅ አልተቻለም መቼ እንደሚመጣ
አፋልጉኝ ፍቅርን ድንገት ካያችሁት
ወረታ ከፋይ ነኝ ከልቤ መልሱት
ሰው እኮ የጠፋው አፋልጉኝ የበዛው
ተስፋ እየቆረጠ ወጥቶ የሚቀረው
ቀድሞ ፍቅር ጠፍቶ ጥላቻ ነግሶ ነው
አፋልጉኝስ ማለት ዛሬ ፍቅርን ነው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
21👍4😁2
#ሂጅ

ድሮም ልብሽ
አልነበረም እኔጋ
ምን ያደርግልኛል
ነፍስ የሌለው ስጋ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰19
ያምናን ቀን አማሁት ለአፌ ለከት የለው
የዘንድሮው ባሰ እጂ እግር የሌለው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
😁8👍52
#ቀጠሮ

"እንገናኝ" ስልሽ "ደስ ይለኛል" ያልሽው
"የት ይሻላል?" ስልሽ ቦታ ያልመረጥሽው
ፒያሳ ይርቀኛል ቦሌም አልተመቸኝ
ጎተራና ሳሪስ ቄራም ደስ አላለኝ
ሜክሲኮ ፍልውሃ ካዛንችስ አልመጣም
አንችን ለማዝናናት ከተማዋ አትበቃም
ነፍሴ ተጨነቀች ቦታ አላውቅም ውዴ
አልጋዬ ሰፊ ነው ...
                      ...ይመችሻል እንዴ?
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
😁26👍7🥰21👎1
#ህሊና_ሲፈተሽ

ደብቆት ነው እንጂ ከህሊናው ጓዳ
ስንቱ እህህ ይላል በልቶ የቃል እዳ
በመሐላ ወስዶ በክህደት ያልሸጠ
ለገባው ቃልኪዳን በሆድ ያለወጠ
የትኛው ጀግና ነው ለእምነቱ ያደረ?
የሰጡትን እውነት ጸንቶ ያከበረ?
ሁሉን ቤት ይቁጠረው ህሊና ሲፈተሽ
ማን ቃሉን ጠብቆ ማንስ ይሆን አፍራሽ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍13👏1
#የሰው_ቃል_ይቅርብኝ!

ተደግፌ ነበር የሰው አጥር ትላንት
ተሰብሮ ጥሎኛል ሁሉም ሆኖ ወረት
አይ አለማወቄ ከንቱ ነበርኩ እኔ
ፈጣሪ እያለልኝ ፍጡርን ማመኔ
ሰው ቃሉነን ሲበላ ስለምን ማዘኔ
የክርስቶስ ስሙ ሳለ ትልቅ ቅኔ
በል አትዘን ልቤ አትደገፍ ሰውን
ዛሬን አለሁ ብሎ ለነገ ዋስ አይሆን
ውስጥህን አካሚ የህይወት ቃል ትተህ
ከትላንቱ ተማር የሰው ቃል ይቅርብህ
ቃል ተበላ አትበሉ ቃል የበላ ሰው ነው
ዘላለማዊ እምነት ሁሌም ክርስቶስ ነው
እርሱን መመርኮዝን መደገፍ ዘንግቼ
የሰው ቃል ስከተል በከንቱ ቀርቼ
አይቻለሁ ብዙ ሰው ሲጥል ዘንድሮ
መጠበቅ ይሻላል የአምላክን ቀጠሮ
ይዘገያል እንጅ የሚቀድመው የለም
ከእንግዲህስ ወዲያ ሰው አለኝ አልልም
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍14😭2
በዓካል በመንፈሴ ስስ ሆኜ እንደ ክር
አይዞህ ብርቱ ሰው ነህ ትችላለህ ጠንክር
ጀግና ነህ አትፍራ ብለው ያነቃቁኝ
       ከሰው ተጣልቼ....
ሆስፒታል ነኝና ሳልሞት ይጠይቁኝ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
15👍1
#ሁሉን_ችላ_ነዋሪ

ሀገሬ ጨቅላ ናት ክፋት ያልበረዛት
እያስረጇት እንጂ በዘር በመባላት
ደግሞም ከፍ ስትል ሀገሬ ድንግል ናት
ውበቷ ጎምርቶ ሁሉም የሚመኛት
ከሁሉም ከሁሉም ሀገሬ እኮ እናት ናት
በልጆቿ በደል ጨክና የማይከፋት
ሁሉን ችላ ነዋሪ ሀገሬ መሬት ናት
ብሉልኝ የምትል እርሷን እየራባት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰8👍2
#እግዚአብሔር_ሆይ

በመንገዴ አንተ ቅደም
ከአንተ በቀር ተስፋ የለም
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍98
ሞትን አትለምኑ ውሰደኝ ብላችሁ
በተራ በተራ ላይቀር መሄዳችሁ።
ሳይለምኑት መጥቶ በግድ ለሚጠራ
የምን መለመን ነው? ገብቶ በሰው ተራ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍23😁5🥰1
#ጓደኛ

ታማኝ እውነተኛ ገመና ደባቂ
ችግርን ተካፋይ ሚስጥርን ደባቂ
መስታዎት ካልሆነ ስህተትን የሚያሳይ
ለመወደድ ብሎ ከሆነስ አስመሳይ
ለጥቅም ካደረ ከንቱ ጓደኝነት
ነፃነት ያለበት ጌጥ ነው ብቸኝነት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10🔥4👍1🥰1
የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባ ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍114
#ድንቄም_ባለቅኔ

ለፀሐይ ጨረቃ ቅኔ እየዘረፈ
ምነው ለሰው ሲሆን ቀለሙ ነጠፈ
የእኔ ዘመን ጥበብ ሰውን የዘነጋ
ለጨርቃ ውበት እጁን የዘረጋ
ከዋክብትን ጠቅሶ ፀሐይ አወድሶ
ከጨረቃ ደርሶ ሰማያትን ዳሶ
በምናብ ሲዋትት እንቅልፍ አልባ ሌሊት
እንዴትስ አልታየው? የሰው ልጆች ውበት
ማሽቃበጥ ነው እንጂ ህሊና ባይነቃ
ስዎች አይበልጡም ወይ ከፀሐይ ጨረቃ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🔥6😁5👍31
ሰውነቴም ከዳኝ ልቤም አመለጠ
ሀሳቤ በሙሉ ባቺ ተለወጠ።
እባክሺ አቺ ልጂ አትራቂ ከፊቴ
አቺ ብቻ እኮነሺ የኔ መስታወቴ።
መስታወት ፊት እጂ አያሳይም አገር
አምላኬ ጠብቃት የዛቺን ልጂ ነገር።
እኔ ገና ልጂ ነኝ
ትንሺ እደሆሺ
ሌላውን ተይና እኔ ላፍቅርሺ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍115💔3