ግጥም
4.24K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ናፍቆት አቃጠለኝ
      ልክ እንደ ውሃ ጥም
                 የሚጠጣ ቢሆን
                        ባደረኩት ግጥም💋
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👍1
የድሀ ፍቅር

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ

ክፍል 1

ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግኩበት ስም የለውም ማለቴ አዲስ አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ ነው አባቴን
አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም አንድ ወንድም አለኝ ናቲ ይባላል ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት አልፈልግም ትላለች እናቴ ያገኘችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ መልስ ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር ትፈልጋለች በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች የ10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው ከትምህርት ቤት እንደተመለስኩ የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ ግዴታዬ ስለሆነ በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት
አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን ሜላት የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር ክንፍ ብለናል የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት በደረጃና በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን አላማና ፍላጎት
ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን ሁለት ወር ክረምት ሜላት ከቤት ብዙም መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም ብቻ ተመስገን ነው ።
ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዩ ልብስም እቃም ታመጣለች የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት ግን አልፈለኩም እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር ዝም የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት መጣ.......
ይቀጥላል.....

@gitm_post

Like እና Share
13🔥2👍1
#በያኔው_ፈገግታ

ሳቃችን ተሟጦ አልቆብን ፈገግታ
ድሮ በሳቅነው ነው ያለን በትዝታ
በያኔው ፈግግታ አለን እስከ ዛሬ
አዲስ ሳቅ ናፎቆናል እባክሽ ሀገሬ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍11
የሰው እንባ ደርቆ በዐይን ሞልቶ ባይፈስ
ብዕር ሰው ወክሎ በየቀኑ ያልቅስ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍4
የድሀ ፍቅር

ክፍል 2

ክረምት አልቆ መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋ አዲስ አመት ተጀመረ የማትሪክም ውጤት መጣ በሚገርም ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ነበር ያለፍኩት ደስ የሚል ዜና እናቴ ይሄንን ስትስማ የሚሰማትን ደስታ ሳስብ በጣም ተደሰትኩ ሜላትም አልፋለች በከፈተኛ ውጤት ባይሆንም ጥሩ ሰርታለች ሁለታችንም ተደሰትን ኦ አምላኬ ነገን አንተ ታውቃለህ አልኩ በልቤ!! ሜላቴ እናቴጋ መሄድ አለብኝ አልኳት አብረን እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት እናቴ ጋ ሄድን እናቴ ገና ከውጪ ስታየኝ ፊቴ በደስታ መሞላቱን ስታይ እልልታዋን አቀለጠችው ተንበርክካ ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ አለች!! የደስታ እንባ በጉንጮቻ ላይ ኮለል ብለው ወረዱ እኔም ተንበርክኬ እናቴን አቀፍኳት በደስታ ተላቀስን እናቴ ገና አኮራሻለው አልኳት በጆሮዋ የደስታ እንባ እየተናነቀኝ ሜላት ፍዝዝ ብላ የሚሆነውን ሁሉ ታያለች እሷም ግን በቁሟ እንባዋ ይወርድ ነበር እኔና እናቴ ተቃቅፈን ተነሳን እናቴ በቃ ቤተክርስትያን ተሳልሜ ልምጣ ገብርኤል ስለቴን ሰምቷል ብላ ነጠላዋን አንጠልጥላ ከቤት ተመስገን ተመስገን!!እያለች ሄደች ናቲ "አይገርምህም እኔም እንዳንተ ጀግና ነው የምሆነው" ብሎ መጥቶ ተጠመጠመብኝ ጎበዝ እንደዚህ አስብ እሽ ብዬው መጣሁ እዚሁ ሁን ብዬው ሜላትን ልሽኝ ወጣሁ ሜላት የሆነ ነገር ውስጧን እየከነከነው ነው ግን ምን እንደሆን አላውቅም ወደ ኪሷ ገብታ 20 ብር አውጥታ እንካ አለችኝ ምን ላድርገው አልኳት ካፌ ገብተን ትንሽ እናውራ አለችኝ እሽ አልኳትና ብሩን ወደ ኪሴ ከተትኩት ካፌ ገብተን ሻይ አዘዝን ታውቃለህ ፍቅሬ የናንተ ቤተሰብ በጣም ያስቀናል አለችኝ መሬት መሬት እያየች እኔ አሁን እቤት ስገባ ማለፍና መውደቄን እንኳን አልጠየቅም እንኳን ይሄን ያክል ፍቅር ላይ ይቅርና አሰቀንታችሁኛል አለችኝ እንዳቀረቀረች እኛ ቤት ንፁህ ፍቅር እንዳለ አውቃለው የእሷን ስትነግረኝ ግን ግራ ገባኝ ብቻ በፍረሀት ለምን? አልኳት እ! አለች እኛ ቤት ማንም ስለምንም አይጨነቅም ትማራለህ ካልተሳካልህ የፈረደበት የአባቴ ካንፖኒ አለ እዛ ትገባለህ በቃ ይሄ ነው አለችኝ በንዴት አሁን ደግሜ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ዝም አልኩ ለማንኛውም እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት የሰጠችኝን ብር ከኪሴ አውጥቼ ከፍዬ ከካፌው ወጣን እሷን ታክሲ አስይዤ ቻው ተባብለን ተለያየን ወደ ቤት እየተመለስኩ ብዙ ነገሮችን አሰብኩ ለምን ቤተስብ ፍቅር የለውም? ለነገሩ ገንዘብ ስላላቸው ባይማሩስ ሜላትም ዝም ብላ ነው የምትደክመው ምናለ እኔ የእነሱ ቤተሰብ በሆንኩ! አይ ተመስገን እንኳንም አልሆንኩ የእናቴ ፍቅር ከገንዘብ በላይ ነው እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ እቤት ስደርስ እናቴ ቡና አቀራርባ ሻማ ገዝታ ጠበቀችኝ ደስ አለኝ እናቴ እወድሻለው ብዬ ግንባሯን ስሜ ተቀመጥኩኝ እናቴ ደስ ስላላት ደስ ብሎኛል በቃ እናቴ ከዛም ከዛም ብላ ያጠራቀመቻትን ብር ሰብስባ ዬኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ ሜላት ዬኒፎርሙን ቀድማ አሰፍታ አመጣችልኝ በጣም ደነገጥኩ እኔ ከዚህ በላይ እንድትረጂኝ አልፈልግም አልኳት ሜላት ግን በቃ እሽ ብላ ዬኒፎርሙን ሰጥታኝ ከቤት ቻው ብላ ሄደች እናቴ ደነገጠች እኔም ተከትዬ ሳልሸኛት ፈዝዤ ቀረሁ..........

ይቀጥላል.....

@gitm_post

share and  like
👍9🥰3
ቢታሰር ቀለበት በጣት ተለክቶ
ማጥበቂያ ልብ ነው እንዳይላላ ሰፍቶ።
ልብ ካልታሰረ በፍቅር ሰንሰለት
ሰውን አይመራውም ተራ ነው ቀለበት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍17👏4
#በተግባር_መኖር_ነው

ትልቅ የመሰለን ያከበርነው ሁሉ
መታመን ከበደው ከንቱ ሆነ ቃሉ
መናገር ምን ገዶ ቃላት አሳምሮ
በተግባር መኖር ነው ያቃተን ዘንድሮ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10
መለየት ተስኖን ህልምና ቅዠትን
ፍችው ትርጉም አጣ ተዘበራርቆብን።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6
የድሀ ፍቅር

ክፍል 3

ድንገት ታናሽ ወንድሜ ገፍትሮኝ ወደ ውጪ ሲሮጥ ብንን እንደማለት አልኩ እንደዛው እንደቆምኩ ብዙም ሳልቆይ ታናሼ ምን እንዳላት ባላውቅም ሜላትን ይዟት መጣ እስኪ ዞር በል እንግባበት ብሎኝ ይዟት ገብቶ ያለችው መቀመጫ የኔ የበሰበሰች ፈራሽ ላይ ተቀመጭ አላት እኔ አሁንም ፈዝዣለው እማዬ ቡና አፍይ እስኪ አላት እናቴ እሽ ብላ ተፍ ተፍ ማለት ጀመረች አቦ አትቁምብና ና ተቀመጥ አለኝ እሽ ብዬ ሜላት ስር ቁጭ አልኩ ለማየት ፈራኋት እንዳቀረቀርኩ ይቅርታ አድርጊልኝ ሜላት አጥፍቻለው አልኳት አይ ችግር የለውም አለችኝ ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ አየኃት እውነትሽን ነው አልኳት አዎ አልችኝ እጆቿን ያዝ አድርጌ ሜላትዬ እውድሻለው አፈቅርሻለው ግን በገንዘብ እንድትረጂኝ ሳይሆን ንፁህ ፍቅርሽን ነው የምፈልገው አልኳት ዓይን ዓይኗን እያየሁ እየውልህ የኔ ውብ እኔ እየረዳሁህ አይደለም ማደርግ ስለፈለግሁ እንጂ ደግሞ ካንተና ከእናንተ ቤተሰብ የማገኘው ፍቅር ከሺ ሚልዮን ብር በላይ ደስታን ይሰጣል አትበሳጭብኝ ይቅርታ እሽ አለችኝ ታናሽ ወንድሜ ጣልቃ በመግባት እድሜ ለኔ መለስኩልህ ፈዛዛ ይኸኔ እቤቷ ደርሳ ነበር አለኝ ተሳሳቅን ቡና ተፈላ ቤት ያፈራውን ቀማመስን በቃ ደስተኛ ሆነን አመሽን በጣም ማምሽት ሰለማይፈቀድ ሜላቴንም ወደ ቤቷ ሸኘኃት እኔም እሷን ሽኝቼ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ወደ ቤቴ ተመለስኩ እናቴም ዩኒፎርም ስለተገዛላት ያለው ብር ለደብተርና እስክርቢቶ ይሆናል ተመስገን አለች ዞር ብላ አንተ ከዚህ በኋላ እንደዚህ ጮኸህ ስትቆጣ መስማት አልፈልግም አለችኝ እሽ አልኳት ቀናቶች ሄደው የትምህርት መሳሪያዎቼን አሟልቼ ትምህርቴን ጀመርኩ ሜላቴም እኩል ጀመርን አንድ ክፍል መሆን ፈልገን ነበር ግን አልተሳካም መምህሮቹ አልፈቅድ አሉ ይሁን ብለን በክፍል ተለያየን ግን እርፍት ሲሆን እኔ ቀድሜ ከወጣሁ እነሱ ክፍል በር ላይ እጠብቃታለው እሷም ከቀደመች እንደዛው ደስ የሚለው ሁላችንም ዩኒፎርም ስለምንለብስ የድሀ የሀብታም ልጅ ብሎ ነገር የለም የሚበላ ስንፈልግ ሜላት ብር ሰጥታኝ እኔ እከፍላለው እኔና ሜላት ተለያይተን አናውቅም እኔም ከእሷ ውጪ እሷም ከእኔ ውጪ ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኛ የለንም ተማሪዎች ሁሉ ይቀኑብናል እሷ ቆንጆ ነገር ስለሆነች ሌሎች ይመኟታል እሷ ግን ከኔ ውጪ ማንንም አትፈልግም እኔም እንደዛው ከትምህርት ቤት ውጪ እኔ እናቴን ለማገዝ ስራ ስለምሰራ ብዙም አንገናኝም ጥናት ካለብን ግን አብረን እናጠናለን ጥናት ስንጨርስ ወክ አድርገን እንለያያለን እናቴም አብሮነታችን በጣም አስደስቷታል ደስተኛ ነች እኔም እንደዛው አንድ ቀን ፈተና ስለደረሰ ስናጠና ቆይተን ልሸኛት ወጥቼ ሻይ ቡና እንበል ብላኝ ካፌ ውስጥ ተቀምጠን ያላሰብነው ሰው ድንገት መጣብን..........

ይቀጥላል......

@gitm_post

share & Like
👍6🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍4
Thanks All Sub...🫶

እወዳችኋለሁ

❤️❤️❤️
🥰91
#ከቶ_አይገባኝም

ጌታ ፍቅርህ እንጂ ያኖረኝ በጸጋ
ስራዬ እኮ አይደለም የጸሎቴ ዋጋ
በቸርነትህ ነው ዛሬን የደረስኩት
ድቅድቁን ጨለማ ባንተ ተሻገርኩት
ምህረትህ እኮ ነው ጻድቅ ያስመሰለኝ
ስራዬ መች ሆኖ በክብር ያቆመኝ
እንደ በደሌማ ድክመቴን ብትቆጥር
ከቶ አይገባኝም ጌታ ያንተ ፍቅር!!!
በሃጢአት ወድቄ ሲያገለኝ ሁሉም ሰው
ዛሬም አይዞህ ባዬ ያልተወኝ ጌታ ነው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
15
የድሀ ፍቅር

ክፍል 4

እኔና ሜላት ፈተና ስለደረሰ ሰናጠና አምሽተን ልሸኛት እንደወጣሁ ካፌ ሻይ ብና እንበል ብላኝ ገብተን ቁጭ እንዳልን ድንገት የሜላት አባት ከፊት ለፊታችን ድቅን አሉብን እኔ ሰለማላውቃቸው ዝም አልኩ ሜላት ተርበተበተች ማ? ማነው አልኳት ?በጣቶቿ አፏን ተመተመች ዝም በል ለማለት ነበር ሜላት ከመቀመጫዋ ተነስታ አ.. አባቢ አለች እየተርበተበተች አባቢ ስትል ቀልቤ ግፍፍ አለ ደግነቱ ዩኒፎርሜን ከላይ ያለውን አላወለቅሁትም ነበር የየየክፍሌ ተማሪ ነው ስናጠና ቆይተን ሻይ ቡና እንበል ብለን ነው አለች እየተርበተበተች አባቷም ሰላምታ አይቀድምም ልጄ አሉ ይቅርታ አባቢ ብላ አቅፋ ሳመቻቸው እኔም ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሰላም አልኳቸው የሜላት አባት ሰላም ብለውን በጊዜ ግቢ ቻው ብለውን ሌላ ወንበር ወደ አለው ጓደኛቸው ሄዱ እኔና ሜላት ደንግጠናል ያዘዝነው መጥቶልን ቶሎ ቶሎ ጠጣን አባቷ ቀድመው ሂሳብ ከፍለውልን ስለነበር ቻው ብለናቸው ተያይዘን ወጣን ሜላት ፊቷ ላይ የፍረሀት ስሜት ይነበባል ሜላቴ ምን ሆንሽ? ምን እያሰብሽ ነው አልኳት አባቢ አለች አባትሽ ምን አሁን እቤት ስገባ ጭቅጭቁ አይጣል ነው አለች በፍረሀት አይቆጡሽም አስጠኒዬ ነው በያቸው ባይሆን ሁለተኛ አብረን እንዳያዩን እንጠነቀቃለን አልኳት እሽ አልችኝና ግንባሯን ለመጀመርያ ጊዜ ስሜ ተለየኃት ሜላትን በታክሲ ሽኝቼ እኔ ወክ እያደርግሁ ወደ ቤት ተመለስኩ ግን የሜላትዬ ፍርሀት እኔን አሳሰበኝ አባቷ ይቆጡ ይሆን ? ብዙ ነገሮችን አሰብኩ  ምክንያቱም የሜላት ቤተሰቦች ሀብታም ስለሆኑ ልጃቸው ደግሞ ከእንደኔ አይነት መናጢ ድሀ ጋር የፍቅር ግንኝነት እንዳላት ቢያውቁ ከባድ ነው የሚሆነው አምላኬ አደራህን ብዬ እቤቴ ገባሁ መንጋት አይቀር ነጋ ጠዋት ትምህርት ቤት ቶሎ ሄድኩ በሩ ላይ ጠበቅኋት እሷም እንደምጨነቅ ስለገባት በጠዋት መጣችልኝ ደስ አለኝ ቶሎ ብዬ ምን ተፈጠረ አልኳት ሰላም በለኝ እንጂ ቅድሚያ አለችኝ አቅፌ ሳምኳት ምንም አልተፈጠረም አባቢ ምንም አላልኝም አለችኝ በጣም ተደሰትኩ ለሚቀጥለው እንጠነቀቃለን አልኳትና ተያይዘን ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ ገባን እኔና ሜላቴ ፍቅራችንን በድብቅ አድርገን መዝናናትም ስንፈልግ ደበቅ ያለ ቦታ እየሄድን እንዝናናለን አብዛኛውን ጊዜ ግን እኛ ቤት ነው የምናሳልፈው አመቱ አልቆ ተፈትነን ውጤት መጣ ሁለታችንም አልፈናል ደስ የሚል ነገር ተመስገን አልተነጣጠልንም ሁለት ወር ክረምትን ያው እንደተለመደው እኔ እናቴን በማገዝ አሳለፍኩ ከሜላትም ጋ አልፎ አልፎ እቤት እየመጣች ካልሆንም ማታ ማታ እነሱ ሰፈር ቤተክርስቲያን ውስጥ እንገናኛለን በቃ ደስ በሚል መዋደድና መፈቃቀር አብረን ቀጠልን አዲሱ አመት ገብቶ ትምህርት ጀመርን 12ኛ ክፍልን በጣም መጠናት እንዳለበት ስለማምን ብዙ ጊዜያችንን በጥናት ነው የምናሳልፈው ሜላትም ከኔ ጋር ታጠናለች በርትተን መማር እንዳለብን ሁለታችንም እናምናለንና ስለዚህ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል እናጠናለን እኔ ስናጠና ስለ ትምህርት ወክ ስናደርግ ስለ ነገ ተስፋ ነው የማስበው ወደፊት ምን ማድርግ እንዳለብኝና ምን መሆን እንደምችል ብዙ ነገር ሜላትን እንደማገባት ነው የማምነው ሁሌም ስለያት ወይ ግንባሯን ወይ አንገቷ ስር ስሜ እለያታለው አንድ ቀን ማታ ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ሜላት ፊቷን ጥላዋለች አኩርፋለች ምነው ሜላትዬ ምን ሆነሽ ነው አልኳት ሳመኝ አለችኝ ዓይን ዓይኔን እያየች እ!! አልኳት ሳመኝኝኝኝ! አልቸኝ ግንባሯን ሳምኳት ኡፍ ብላ ተበሳጨች ትዝ ሲለኝ እእእ አልኩ በእጆቼ ጉንጭና ጉንጯን ያዝ አድርጌ በስሱ ከንፈሯን ሳምኳት ደስ አላት ምን ዋ ጋ አለው ታዲያ ባልስማት  ይሻል ነበር አባቷ......

ይቀጥላል.....

@gitm_post

Share & Like
👍7🥰1
የዘንድሮ ፈረስ አይቀድምም ጋሪውን
አታውቀውም እና ሒያጅና ቀሪውን
     አልሰማሁም አትበል
እያነባህ ጠብቅ መርዶ ነጋሪውን
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍81
#አፍቅሮተ_ነዋይ

ወዳጅ መስሎ ስሞ እውነትን የሸጠ
በሰላሳ ዲናር ክብሩን የለወጠ
ይሁዳ ቢሆንም በዓለም የታወቀ
ለብቻው ክህደትን በአዋጅ ያጸደቀ
ከእርሱ በወረሱት አፍቅሮተ ነዋይ
ስንቶች ተፈጥረዋል ወዳጅን አታላይ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌9
የድሀ ፍቅር

ክፍል 5

ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ድንገት አጠገባችን መኪና ሲጥጥ ብሎ ቆመ ደንግጠን ዞር ስንል የሜላት አባት መኪና ነበር ነይ ግቢ የሚል አጭር ቃል ሜላትም እሽ ብላ ቻው ብላኝ ወደ መኪናው ገባች አባቷ እኔን ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ ወይኔ አምላኬ ምናለ ባልሳምኳት ብታኮርፍ ይሻል ነበር ብዬ አሰብኩ ቀኑ አርብ ስለነበር ቅዳሜና እሁድ እንዴት ሊያልፍ ነው ስልክ እንኳን የለኝ ብቻ ጨነቀኝ እቤት ገብቼ ለእናቴ የተፈጠረውን ነገርኳት አዘነች ግን በቃ አይዞህ አምላክ ያለው ይሆናል አለችኝ እሽ አልኳት በማግስቱ እነ ሜላት ሰፈር ቤተክርስቲያን ሄድኩ ሜላት የለችም ጨነቀኝ ምን ተፈጥሮ ይሆን አላውቅም ሜላት ግን የለችም እሁድም አላገኝኋትም ይበልጥ ጨነቀኝ ሰኞ ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ትምህርት ቤት ሄድኩ ሜላት ግን የለችም ተደውሎ ወደ ውስጥ እየገባሁ እያለ አንድ መኪና መጥቶ በር ላይ ሲቆም ሰማሁ ዞር ስል የሜላት ወንድም ሜላትን ይዞ መጣ ተንደርድሬ ሄጄ ሰላም ልላት ስል ዝም ብላኝ በቆምኩበት ትታኝ ገባች ፈዝዜ ቀርሁ ለምን አልኩ ወንድሟ ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ እኔም ቀስ እያልኩ ሜላት በቃ ተለየችኝ ተለያየን እያልኩ ወደ ክፍሌ አመራሁ እኛ ክፍል በር ላይ ስደርስ ሜላት ከየት እንደመጣች ሳላውቅ መጥታ ተጠመጠመችብኝ ከንፈሬን አንገቴን አይኔን ሁሉ ነገሬን ሳመችኝ ደህና ነህ ይቅርታ ይቅርታ እሽ አለችኝ ምን ተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው አልኳት ለዕረፍት ሰአት እነግርሀለው አሁን እንግባ መምህር ሳይገባ አለችኝ እሽ አልኳትና እሷም ወደ ክፍሏ እኔም ወደ ክፍሌ ገባን የእረፍት ሰአት ደርሶ ሜላትን አግንቻት የተፈጠረውን እስክትነግረኝ ቸኩያለው በጣም ጨንቆኝም ነበር መማር ሳይሆን መፍዘዝ ሆነ ሰአቱን መግፋት ብችል ገፍቼ አሳልፈው ነበር ግን አልቻልኩም የእረፍት ሰአት ደረሰ መድረስ አይቀር ወጥቼ ልክ ሳገኛት ተጠምጥሜ ሳምኳት ምንድነው የተፈጠረው ንገሪኝ አልኳት እሽ አለችኝና ቁጭ አልን ሜላት ከቤተሰቧ ጋር ትልቅ ብጥብጥ እንደተፈጠረና ሁለተኛ ከኔ ጋር ከታየች ችግር እንደሚፈጠር ነግረዋት ሰለነበር አንተንም እንዲጎዱህ ስለማልፈልግ ነው የጠፋሁት ጠዋትም ወንድሜ እንዳያይህ ብዬ ነው ዝም ብዬህ የገባሁት ከዚህ በኋላ ከትምህርት ቤት ውጭ መገናኝት የምንችል አይመስለኝም ምናልባት ማታ ማታ ቤተክርስቲያን እንገናኛለን አለችኝ እሽ ብቻ አንቺ ምንም አትሁኚብኝ አልኳት ሜላትም ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ትንሽዬ ስልክ አውጥታ በዚህ ስልክ እንደዋወል አለችኝ እሽ አልኳት በቃ ከልቤ እንደምወዳትና ብትለየኝ እንደምጎዳ በደንብ ገባኝ ከዚይች ቀን ጀምሮ በስልክ ወይም ትምህርት ቤት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ መገናኝት አቆምን ሜላት ማጥናት ትታለች በቃ ከእኔ ጋር ለምዳ ብቻዋን ማጥናት አልቻለችም የማትሪክ 12ኛ ፈተና እየደረሰ ነው እኔ በጥናት ተወጥሪያለው ሜላት ግን ማጥናት ትታ እቤት ነው የምትውለው እኔም በምን መልኩ ላስጠናት እንደምችል ግራ ገብቶኛል ማታ ነው ስልክ ደወልችልኝ አወራን ምንም እንዳላጠናች ነገረችኝ አጥኚ ነገ ከትምህርት መልስ እንደምትቆይ ተናገሪና እናጠናለን አልኳት እሽ ብላኝ ቻው ተባብለን ስልኩ ተዘጋ በድጋሚ ስልኬ ጮኸ የማላውቀው ስልክ ነበር.....

ይቀጥላል.......

@gitm_post

Share & Like
👍11🔥2
ቤተሰብ React ቀንሳችኋል

እስኪ 20 የተለያዬ React አድርጉ ከዚያ ምርጥ ግጥም እለቅላችኋለሁ
🔥18🥰5👏5👌43👍1🖕1👀1🫡1😘1
#ቀልባቸው_ተወስዶ

ሞልተሽ በጎዳናው መልተሽ በመንገዱ
ሌሎች ትኩረት ሰጥተው እንዴት ይራመዱ
ቀልባቸው ተወስዶ በውበትሽ ፈዘው
ሁሉም አድናቂሽ ነው ያንቺ ነው ጎዳናው
ስንቱ ተላተመ ስንቱ ሰው ሰመጠ
አረማመድሽ ላይ ትኩረት እየሰጠ
አፍዝ አደንግዝ ነው መልክሽ አስገራሚ
ኬሬ ዳሽ ነው ጆሮሽ ማንንም አትሰሚ
ተመላለሽበት ጎዳናው የግልሽ
ግድ አይሰጥሽ ከቶ ማንም ቢከተልሽ
ጥላሽን ዘርግተሽ ከቤትሽ ውጪና
ሁሉም እግሩ ይጋጭ ልማዱ ነውና
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍17
አቅቶኛልና ጌታ ሆይ አበርታኝ
አንተ ከተውከኝ ነው ጠላት የሚረታኝ።
ይግረመው ይድነቀው ዛሬም ተሻግሬ
የጠላትን ወጥመድ በስምህ ሰብሬ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
14😇5👍2