ግጥም
4.24K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ፍቅር_አለቀሰ

ፍቅርን ስፈልገው ቀናቶች አለፉ
ፈለኩት ፈለኩት ድካም ሆነ ትርፉ
አጋጣሚ ሆኖ ተደብቆ አየሁት
አላምን ስላልኩኝ ምክንያቱን ጠየኩት!
ፍቅር አንተ ነህ ወይ? ብየ ብጠይቀው
ምንም መልስ ሳይመልስ እንባ ተናነቀው
ግራ ገባኝና ባግራሞት አየሁት
ቆይ! ፍቅር ደስታ ነው ሲባል ሰምቻለሁ
ታድያ ያንተ ለቅሶ ከየት የመጣ ነው?
ፍቅርም መለሰልኝ አይኑን መሬት ተክሎ
መናገር ጀመረ ቃላትን ቀጣጥሎ
ደስታማ ደስታ ነኝ ላወቀው ሚስጥሬን
ከደስታም በላይ ነኝ ከተረዱኝ እኔን
ያስለቀሰኝ ነገር ሆድ ሆዴን ያባሰው
በኔ ስም መነገድ መች አቆመ ሰው
አፈቀርኩሺ ብሎ ሲዋሻት በኔ ስም
ማሬ ውዴ ብላ ከድታው ስቴድ እሷም
በኔ ሲጫወቱ የሀሰት ጨዋታ
በኔ ሲባልጉ በኔ ስም ሲምታታ
በውሼት አለም ሆነው በኔ ስም ሲጠሩ
እንደት አላነባ? ካልረባ ነገሩ!
ብሎ መለሰልኝ ፍቅር በቀስታ
አንገቱን ቢያስደፋው የሀሰት ጨዋታ!
በፍቅር አስኪ አሁን መቀለድ ይብቃ!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
5👍1
#መልክአ_ሕይወት

ቧልትን ከፈገግታ
ሳቅን ከፌዝ ጋራ
ባንድ ላይ ቀይጠን፥
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን ባሕር ላይ ፥ ብናንቆረቁርም
ባሕሩ ሰፊ ነው፤ መልኩን አይቀይርም::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
👍3