ግጥም
4.24K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ህገ_ሰካራም!

‹‹ነገሩ ነው እንጂ ፤ አረቄ አያሰክርም
አሳሪ ከሌለ ፣ ገመድ ሰው አያስርም
ወዳጅ ዘመድ እንጂ….
አፈር ሰው አይቀብርም ፡፡››
ይላል የሰከረ !
አረቄ ቤት ሆኖ ፣
መተዳደሪያውን ፤ ህግ እያዋቀረ፡፡
እንደሰካራም ህግ፤ እንደስካር ወሬ
አረቄ ቤት ሆኜ...
አረቄ እየጠጣሁ፤ በነገር ሰክሬ
ስለ ሰካራም ህግ ፤ ላውራሽማ ፍቅሬ፡፡

እዚህ አረቄ ቤት...
ከተሰበሰበው ፤ የሰካራም አባል
ስሙን የማላውቀው፤ ‹‹ሰካራም›› የሚባል
አንድ የሰከረ ሰው፤ እንደተናገረው
ሀገርሽ ሀገሬ….
‹‹መልሱን ጠጣንበት›› ፣
በሚለው ህግ ነው ፣ የሚተዳደረው፡፡
‹‹ለመብራት›› እያሉን ፤ ገንዘብ እያዋጣን፤
‹‹ለመንገድ›› እያሉን ፤ ገንዘብ እያዋጣን፤
‹‹ለውሀ›› እያሉን ፤ገንዘብ እያዋጣን
ለምን መብራት ጠፋ?
ለምን ውሃ የለም?
እንዴት መንገድ አጣን? ፣ ብሎ ከመጠየቅ፤
ሳይሻል አይቀርም….
መልሱን ጠጣንበት፤ የሚል ህግ ማፅደቅ፡፡

ወንጀለኛው ሁላ….
ዳኛውን ጠብቆ ገንዘብ ካቀበለ
በ ሺህ ምስክር ፊት…
የመሰረትነው ክስ፤ ‹‹ውድቅ›› ከተባለ
ለምን እዴት? የሚል…
የከሳሽ ጥያቄ ፤መልስ ካልተሰጠው፤
በሰካራም አንቀፅ…
መልሱን ጠጣንበት!
የሚለው ህግ ነው ፤የሚረጋገጠው፡፡
እንደ ህገ መንግስት…
ተፈፃሚነቱ፤ ቢሰራም ባይሰራም
መልሱን ጠጣንበት!
ብሎ ያፀደቀው፤ ህግ አለው ሰካራም፡፡
እንደሰካራም ህግ፤ እንደስካር ወሬ
አረቄ ቤት ሆኜ...
አረቄ እየጠጣሁ፤ በነገር ሰክሬ
እኔን አረቄ ቤት፤ምን እንደወሰደኝ
አረቄ መጠጣት ፤ማን እንዳስለመደኝ፤
አትጠይቂኝ ፍቅሬ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በላይ በቀለ ወያ
7👏2🥴1
"ይሄንን ገለባ፣ መሄጃህ ወዴት ነው?
   ብለህ  አትጠይቀው፣
የነገው ንፋስ ነው፣
መንገዱን  የሚያውቀው"
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
8👍2👏1
#እንዲህ_ያደርገኛል

እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት
እንዲህ ያረገኛል
ሰውነቴ ሁሉ ጆሮ ይሆንና
የብናኝ ኮሽታ ገዝፎ ይሰማኛል
ኮቴ እንደመብረቅ
እንደ አንዳች ፍንዳታ
የጆሮዬን ታንቡር ደርሶ ይጠልዘኛል
እመጣለሁ ብላ የቀጠረቺኝ ለት
እንዲህ ያደርገኛል
ጥሞናዬ ረቅቆ መንፈሴን አምጥቆ
የሷን ኮቴ ናፍቆ
የፍቅሬን አካሄድ የሰበር ስካዋን
ከእርምጃዎች ሁሉ ከዳናዎች አውቆ
በናፍቆቷ ደጋን በጉጉት ፍላጻ
ተወርዋሪው ልቤ ተወጥሮ ከረሮ
ጅስሜ እንዳሞራ እንደብርቱ ንስር
ክንፍ አውጥቶ በርሮ
ምድርና ሞላዋን ዓለምን ይቃኛል
ከፍቅሬ በስተቀር
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ውእቱ ይለኛል
እመጣለሁ ብላ የቀጠረቺኝ ለት
እንዲህ ያረገኛል
በፍቅሯ ልዕልና በፍቅር ጽናቴ
ከመንደሬ ገዳም ከጎጆ ባዕቴ
ከመላክ .......... ረቅቄ
ከጻድቅ .......... ጸድቄ
.......እጠብቃታለሁ
እመጣለሁ ብላኝ መች ተኝቼ አውቃለሁ
ዓለም ጊዜ ፀሀይ ሁሉም ቀጥ ብለው
የኪዳኔን ታቦት ጽላቴን አክብረው
ይማፀኑልኛል ይማልዱልኛል
«ይህ ምስኪን ጻድቅ ሰው
ከአለም የመነነው
በአቱን የዘጋው
ፀሀይን አስቁሞ ጊዜን የገዘተው
እመጣለሁ ብለሽ እንዳትዘገይ ነው
እንዳትቀሪበት ነው»
ብለው ይሉልኛል
ጨረቃ ከዋክብት ይማልዱልኛል
የፍቅር ብርታቴን ሁሉም ያውቁልኛል
ከአይን ያውጣህ ከአይን ያውጣህ
ከአይን ያውጣህ ይሉኛል
አንዳንዴም ሽው ሲል እንዲህ እሆናለሁ
ከቤቴ ቁጭ ቡዬ በሀሳብ እመጥቃለሁ
እሷን እየጠበቅሁ እፈላሰማለሁ
እላለሁ..............
«ይህ ሁሉ ጥሞና ይሄ ሁሉ ብቃት
ለሌላም ለሌላም ቢሆን ምናለበት
አዬ ጊዜ ደጉ አዬ ወጣትነት»
እላለሁ............
እድሜ ለሷ ፍቅር መንፈሴን ቀጥቅጦ
ልቤን ለሚገዛው
በሌላማ ጊዜ በጥልቅ ለመመለጥ
አይምሮዬን ባዝዘው መች እሺ ይለኛል
መቼ እሺ እላለሁ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አበባዉ መላኩ
5
#ብቸኛ_ነበሩ!

በስህተት ተባብሮ ፣ በደቦ ከሚፈርድ፤
የብቻህን ሃሳብ ፣ ዝምታህን ውደድ፤
አለምን ጠቃሚ ፣ ሆነው የተገኙ፤
በመልካም ስራቸው ፣ አንቱ የተሰኙ፤
ብቸኛ ነበሩ ፣ ሁሉም የተዋቸው፤
በደቦ ተባብሮ በግፍ የጣላቸው፤
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍7