ግጥም
4.22K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ግመልና_መርፌ

ግመል ከሾለከ በመርፌ ቀዳዳ
ያኔ ይሰረዛል የባለጸጋ እዳ
የሚለው ጥቅስ ላይ ገብቶኝ ጥርጣሬ
እግዜሩን ጠየኩት ሽቅብ ተዳፍሬ
እርሱም መለሰልኝ ወርዶ በትህትና
ለአምላክ የሚሳነው ከቶ የለምና
ባይገባኝ ነው እንጂ ነገሩ ተጋርዶ
ኢየሱስ ያለወንድ ሰው ሆኗል ተወልዶ
ለምን ተጠራጠርኩ? በመርፌ ቀዳዳ
የትኛው ይከብዳል? ሀቁን ለሚረዳ?
መወለዱን ካመንኩ ከድንግል በድንግል
ስለምንስ አይሾልክ በመርፌ ውስጥ ግመል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👏11🔥54
#ከዚህም_በላይ_ነሽ

ሳላገኝሽ በፊት…
መውደዴን አብዝቼ…
አንቺን እያሰብኩኝ ቆርቤ ከራሴ
‘’እንዴት ነህ?’’ ለሚሉኝ…
አንገቴን ደፍቼ ዝም ነበር መልሴ
ካገኝሁሽ በኋላ…
ማእረግ እንዳገኘ እግረኛ ወቶአደር
ደረቴን ነፍቼ ቀና ብዬ እያየሁ…
‘’ደህና ነህ?’’ ባይሉ እንኳ
‘’ደህና ነኝ!’’ እላለሁ
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ኩራት ደህንነቴ አንች ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
የሰማዩን ቀለም
የውሃውን ጣእም
ያገር ምድሩን ሽታ
ደስ ይበልም አይበል
ይጣፍጥ ወይም ይምረር
መለየት አቅቶኝ ግራ ገብቶኝ ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
ሰማይ…ሰማያዊ ውሃው ቀለም አልባ
ሀገሬ ምታምር ሽታዋ እንዳ'በባ
መሆኑን አወቅኩኝ ሰላም ከኔ አደረ
ይመስገነው ባንቺ ግራ መግባት ቀረ!
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ስሜት ሕዋሳቴ አንቺ ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
የሰኞ ማክሰኞ የመስከረም ጥቅምት
የሴኮንድ መቶኛ የሽራፊ ሰዓት
ልዩነት ሳይገባኝ ቀን በቃል ሳልቆጥር
እንዲሁ እንደዘበት እየኖርኩኝ ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
ጳጉሜ ተጨምራ…
አስራ ሁለት ወራቶች አንድ ዓመት ሞልተዋል
ሰላሳ ቀናቶች ወር ላይ ተዘርተዋል
ሰኞ ላይ ጀምረው እሁድ የሚያበቁ
ሰባት ቀናት አሉ በስም የታወቁ
ሃያ አራት ሰዓት አንድ ቀን ይባላል
ራሱ ሰዓቱ በስልሳ ተከፍሏል
ስልሳውም በስልሳ ሂደት ይቀጥላል
ይህን ታላቅ እውቀት
ይህን ታላቅ እውነት
ይመስገነውና ይሄው ባንቺ አገኘሁ
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ቁጥሩ ብቻ ሳይሆን…
ጊዜዬም በራሱ አንቺ ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
ከየትኛው አህጉር
ከየትኛው ሀገር
ከየትኛው አፈር
ከየትኛውስ ዘር
መምጣት መፈጠሬን አላውቀውም ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
አህጉሩን ለየሁ
ሀገሬን አገኘሁ
አፈሩን ቀመስኩት
ራሴን አየሁት
ይመስገነውና ዘር የማይለያየኝ
ማንነቴን ያወቅኩ ውብ ኢትዮጲያዊ ነኝ!
ይህ ማለት ምንድን ነው?
እኔን ብቻ ሳይሆን
ሀገሬን ያገኘሁ ባንቺ ነው ማለት ነው!!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሰለሞን ሳህለ
14
#የእድሜ_ፈረስ

ጠዋት የመሰለን የእድሚያችን ነጸብራቅ
ለካስ መሽቶብናል ከአምላክ ሳንታረቅ
ከሰው ተራ ወርደን ከክብር ከፍታ
ስንባዝን በከንቱ ለምድሩ ደስታ
ለብሰን ተከናንበን የበደልን ኩታ
ጠዋት የመሰለን ድንገት ሆኗል ማታ
የእድሜ ፈረስ ፍጥነት እየገሰገሰ
ከንቱ ውበታች ሳይኖር ፈረሰ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
7
#ህገ_ሰካራም!

‹‹ነገሩ ነው እንጂ ፤ አረቄ አያሰክርም
አሳሪ ከሌለ ፣ ገመድ ሰው አያስርም
ወዳጅ ዘመድ እንጂ….
አፈር ሰው አይቀብርም ፡፡››
ይላል የሰከረ !
አረቄ ቤት ሆኖ ፣
መተዳደሪያውን ፤ ህግ እያዋቀረ፡፡
እንደሰካራም ህግ፤ እንደስካር ወሬ
አረቄ ቤት ሆኜ...
አረቄ እየጠጣሁ፤ በነገር ሰክሬ
ስለ ሰካራም ህግ ፤ ላውራሽማ ፍቅሬ፡፡

እዚህ አረቄ ቤት...
ከተሰበሰበው ፤ የሰካራም አባል
ስሙን የማላውቀው፤ ‹‹ሰካራም›› የሚባል
አንድ የሰከረ ሰው፤ እንደተናገረው
ሀገርሽ ሀገሬ….
‹‹መልሱን ጠጣንበት›› ፣
በሚለው ህግ ነው ፣ የሚተዳደረው፡፡
‹‹ለመብራት›› እያሉን ፤ ገንዘብ እያዋጣን፤
‹‹ለመንገድ›› እያሉን ፤ ገንዘብ እያዋጣን፤
‹‹ለውሀ›› እያሉን ፤ገንዘብ እያዋጣን
ለምን መብራት ጠፋ?
ለምን ውሃ የለም?
እንዴት መንገድ አጣን? ፣ ብሎ ከመጠየቅ፤
ሳይሻል አይቀርም….
መልሱን ጠጣንበት፤ የሚል ህግ ማፅደቅ፡፡

ወንጀለኛው ሁላ….
ዳኛውን ጠብቆ ገንዘብ ካቀበለ
በ ሺህ ምስክር ፊት…
የመሰረትነው ክስ፤ ‹‹ውድቅ›› ከተባለ
ለምን እዴት? የሚል…
የከሳሽ ጥያቄ ፤መልስ ካልተሰጠው፤
በሰካራም አንቀፅ…
መልሱን ጠጣንበት!
የሚለው ህግ ነው ፤የሚረጋገጠው፡፡
እንደ ህገ መንግስት…
ተፈፃሚነቱ፤ ቢሰራም ባይሰራም
መልሱን ጠጣንበት!
ብሎ ያፀደቀው፤ ህግ አለው ሰካራም፡፡
እንደሰካራም ህግ፤ እንደስካር ወሬ
አረቄ ቤት ሆኜ...
አረቄ እየጠጣሁ፤ በነገር ሰክሬ
እኔን አረቄ ቤት፤ምን እንደወሰደኝ
አረቄ መጠጣት ፤ማን እንዳስለመደኝ፤
አትጠይቂኝ ፍቅሬ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በላይ በቀለ ወያ
5👏1🥴1