ግጥም
4.21K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#የንስር_እድሜ_ይስጥሽ

ይታደስ አካልሽ - በሺ አመት ዘመንሽ፣
ከርጅና ‘ሚመለስ - የንስር እድሜ ይስጥሽ፣
እዉነተኛዋ ሰው - ካምላኬ ቀጥለሽ፣
የህይወቴ ህይወት - እማ የምወድሽ፣
የኑሮየ ድምቀት - ድንቅ ስጦታ ነሽ::

የመኖሬ ምክኒያት - ምንጯ የህይወቴ፣
የሃሴት የፍቅር - የሰላም ሙላቴ፣
ቀድመሺኝ የመጣሽ - ገፀ በረከቴ፣
ደስታሽ ደምቆ ይብራ - በ ጉሙ ህ-ይወቴ      
እማ ዉዷ እናቴ! . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
መጠማት መራብሽ - ማጣት መራቆትሽ፣
ከሰው በታች ሆነሽ - ክብርሽን ማጣትሽ፣
እማየ ለኔ ነው - ለደካማዉ ልጂሽ፣
ከቶ በምን ቋንቋ - በምን ቃል ልግለፅሽ? እንዴት ልመልሰዉ - በዝቶብኛል ፍቅርሽ!

ይታደስ አካልሽ - በሺ አመት ዘመንሽ!
ከርጅና ሚመለስ - የንስር እድሜ ይስጥሽ!
ከዚህ በላይ እማ - ምን ቃል አለኝ ልጅሽ! . . . . . . . . . . . . . . .

እማ! . . .እማ!
ጭንቀትሽ ተጥሎ - ሸክምሽ ተንከባሎ፣
አለም ላንቺ ክብር ጎንበስ ቀና ብሎ፣
መቸገርሽ ቀርቶ - ቤትሽ ጓዳሽ ሞልቶ፣ ፊትሽ በፈገግታ - በደስታ አብርቶ፣
ጉድለትሽ ድካምሽ- እንግልትሽ ቀርቶ፣
የህይወትሽ ብርሃን - ይታይ ለአለም ፈክቶ፣
በረከት ረድኤቱን - አምልቶ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11🥰1
ማን በገላገለኝ? የእጄን ሠዓት ሠብሮ
በምናልባት አገር
በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ
ማን ያቅዳል ደፍሮ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
👍121
#ወዴት_ነሽ?

የት ብዬ ልፈልግ ወዴት ነሽ ሄዋኔ፣
የአጥንቴ ክፋይ የሰራሽ ከጎኔ፣

ከበረሀው ካለሽ ንገሪኝ መጣለው፣
አሸዋ ንዳዱን ይሁን ችለዋለው፣
ውሀ ጥም ረሀቡን ባንቺ ረሳዋለው፣
ቆላም ሁኚ ደጋ ጥሪኝ እዘልቃለው፣

ቤተመንግስት ሆኚም ብቻ አለው በዪኝ፣
አልፌ ገባለው ህጉ እንኳ ቢያግደኝ፣
እንደ ወንጀለኛ በእስር ቢያስቀጣኝ፣
ይገደል ተብሎ ሞት ቢፈረድብኝ፣
አንዴ ልይሽ እንጂ ይህ አያሳስበኝ፣

ስፈልግሽ ስውል ሰርክ እያካለልኩሽ፣
ባክኜ እንዳልቀር ጥሪኝ አለው ብለሽ፣

ሄደሽም ከሆነ ወደመጣሽበት፣
መኖርሽ ካበቃ ከፍጥረታት ህይወት፣
ንገሪኝ መጣለው ውዴ ካለሽበት፣
አፈር ከጋረደው ከአካልሽ ቅሪት፣
ደራሲው እንዳለው ፍቅርን እስከ ሞት፣
እኔም ነፍሴ ትለፍ ቁጭ ብዬ ካንቺ ሀውልት፣

ጠቁሚኝ ስፍራሽን ወዴት ነሽ የት ልምጣ፣
አቀበቱን ልውረድ ሽቅቡንም ልውጣ፣
ልቤ ለብቻውን ሚያረገውን አጣ፣

አንቺንም እንደኔ ብቻነት ከጎዳሽ፣
አብሬሽ እንድኖር ንገሪኝ ወዴት ነሽ፣
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
12👏3👍1👌1
#ከትላንት_ሳንማር

ሰው ከሰው ተኳርፎ ዘመኑ ቢታደስ
አሮጌ ዓመት ወርዶ አዲስ ዘመን ቢነግሥ
እድሜ ቁጥር እንጂ ቢደመር ቢቀነስ
እኛ ሳንታረቅ እንቁጣጣሽ ቢደርስ
ፍቅር በሌለበት ውብ ድግስ ቢደገስ
የዶሮ የበጉ የበሬው ደም ቢፈስ
የከንቱ ከንቱ ነው ፍቅር ካልታደሰ
አንዱ የአንዱን ጎጆ ከፍቶ እያፈረሰ
መተሳሰብ ሳይኖር ልባችን ሳይቀና
አዲስ ዓመት መጣ ዞሮን እንደገና
ከትላንት ሳንማር በስህተት ተዘፍቀን
በእንቁጣጣሽ ዜማ እንቁ እንናፍቃለን።
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
10🔥1
#ስላንቺ_ልንፏቀቅ

ሰወች ሳይገባቼው ሚስጥሩን ሳያቁ :
ከእሷ ምን አይቶ ነው ሲሉ ቢደነቁ:
አንቺ ግን አደራ ውዴ የኔ ፍቅር:
ጆሮሽን አትስጪ ለሚባለው ነገር:
ከጎንሽ ነኝ ዛሬም አርቅም ያንቺ አጋር:
ፍፁም አያውክሽ አሉባልታ ወሬ:
እኔ አልለውጥም ዛሬም ያውነኝ ፍቅሬ:
መከራ ሳይገርፍሽ ክፉ ቀን ሳይመጣ:
እየተሳሳምን ከሰፈር ስንወጣ:
ትዝ ይልሻል ያኔ?????????
አንድ ቁጥር ነበርን ስትቆሚ ከጎኔ:
ተቃቅፈን ስንዘምት በዚሁ ጎዳና:
እንዳላሉን ያኔ ፍቅራቼው ሲያስቀና:
እንዳ ባወሩበት በዛው ምላሳቼው:
አሁን ቢሞክሩ ሊያረጉኝ የራሳቼው:
ውዴ የኔ ፍቅር እኔን ሰሚኝ እማ:
ፈልገሽ ሳትገቢ ለዋጠሽ ጨለማ:
አልሆንህም በቃ ሂድ አትበይ አትፍሪ:
መቼም አልተውሽም አትጠራጠሪ:
እንኳን ትቼሽ ልሄድ ካጠቀብሽ ልርቅ
ቢቻል አጎንብሼ ስላንቺ ልንፏቀቅ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
4👍3
#ግመልና_መርፌ

ግመል ከሾለከ በመርፌ ቀዳዳ
ያኔ ይሰረዛል የባለጸጋ እዳ
የሚለው ጥቅስ ላይ ገብቶኝ ጥርጣሬ
እግዜሩን ጠየኩት ሽቅብ ተዳፍሬ
እርሱም መለሰልኝ ወርዶ በትህትና
ለአምላክ የሚሳነው ከቶ የለምና
ባይገባኝ ነው እንጂ ነገሩ ተጋርዶ
ኢየሱስ ያለወንድ ሰው ሆኗል ተወልዶ
ለምን ተጠራጠርኩ? በመርፌ ቀዳዳ
የትኛው ይከብዳል? ሀቁን ለሚረዳ?
መወለዱን ካመንኩ ከድንግል በድንግል
ስለምንስ አይሾልክ በመርፌ ውስጥ ግመል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👏10🔥43
#ከዚህም_በላይ_ነሽ

ሳላገኝሽ በፊት…
መውደዴን አብዝቼ…
አንቺን እያሰብኩኝ ቆርቤ ከራሴ
‘’እንዴት ነህ?’’ ለሚሉኝ…
አንገቴን ደፍቼ ዝም ነበር መልሴ
ካገኝሁሽ በኋላ…
ማእረግ እንዳገኘ እግረኛ ወቶአደር
ደረቴን ነፍቼ ቀና ብዬ እያየሁ…
‘’ደህና ነህ?’’ ባይሉ እንኳ
‘’ደህና ነኝ!’’ እላለሁ
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ኩራት ደህንነቴ አንች ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
የሰማዩን ቀለም
የውሃውን ጣእም
ያገር ምድሩን ሽታ
ደስ ይበልም አይበል
ይጣፍጥ ወይም ይምረር
መለየት አቅቶኝ ግራ ገብቶኝ ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
ሰማይ…ሰማያዊ ውሃው ቀለም አልባ
ሀገሬ ምታምር ሽታዋ እንዳ'በባ
መሆኑን አወቅኩኝ ሰላም ከኔ አደረ
ይመስገነው ባንቺ ግራ መግባት ቀረ!
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ስሜት ሕዋሳቴ አንቺ ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
የሰኞ ማክሰኞ የመስከረም ጥቅምት
የሴኮንድ መቶኛ የሽራፊ ሰዓት
ልዩነት ሳይገባኝ ቀን በቃል ሳልቆጥር
እንዲሁ እንደዘበት እየኖርኩኝ ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
ጳጉሜ ተጨምራ…
አስራ ሁለት ወራቶች አንድ ዓመት ሞልተዋል
ሰላሳ ቀናቶች ወር ላይ ተዘርተዋል
ሰኞ ላይ ጀምረው እሁድ የሚያበቁ
ሰባት ቀናት አሉ በስም የታወቁ
ሃያ አራት ሰዓት አንድ ቀን ይባላል
ራሱ ሰዓቱ በስልሳ ተከፍሏል
ስልሳውም በስልሳ ሂደት ይቀጥላል
ይህን ታላቅ እውቀት
ይህን ታላቅ እውነት
ይመስገነውና ይሄው ባንቺ አገኘሁ
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ቁጥሩ ብቻ ሳይሆን…
ጊዜዬም በራሱ አንቺ ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
ከየትኛው አህጉር
ከየትኛው ሀገር
ከየትኛው አፈር
ከየትኛውስ ዘር
መምጣት መፈጠሬን አላውቀውም ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
አህጉሩን ለየሁ
ሀገሬን አገኘሁ
አፈሩን ቀመስኩት
ራሴን አየሁት
ይመስገነውና ዘር የማይለያየኝ
ማንነቴን ያወቅኩ ውብ ኢትዮጲያዊ ነኝ!
ይህ ማለት ምንድን ነው?
እኔን ብቻ ሳይሆን
ሀገሬን ያገኘሁ ባንቺ ነው ማለት ነው!!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሰለሞን ሳህለ
13
#የእድሜ_ፈረስ

ጠዋት የመሰለን የእድሚያችን ነጸብራቅ
ለካስ መሽቶብናል ከአምላክ ሳንታረቅ
ከሰው ተራ ወርደን ከክብር ከፍታ
ስንባዝን በከንቱ ለምድሩ ደስታ
ለብሰን ተከናንበን የበደልን ኩታ
ጠዋት የመሰለን ድንገት ሆኗል ማታ
የእድሜ ፈረስ ፍጥነት እየገሰገሰ
ከንቱ ውበታች ሳይኖር ፈረሰ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
5