ግጥም
4.19K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ስሞት_አታልቅሱ!

ጎርፍ በላዬ ሲሄድ ዝም ካላችሁኝ፤
ምጠጣው አጥቸ ከንፍሬ እንዲህ ደርቆ ካላጠጣችሁኝ፤
ስትበሉ እያየሁ ወስፍቴ እየጮከ ካላበላችሁኝ፤
ምለብሰው አጥቸ እንዲህ ስንቀጠቀጥ፤
ልብስክን በሳጥን ቆልፈህ ካስቀመጥህ፤
ለምን ትጮሀለህ?፤
ለምን ታነባለህ?፤
ለምንስ ደረትክን ትደቁሰዋለህ?፤
"ማን ገደለው?" ቢሉህ እስኪ ማን ትላለህ?፤

እንባ ምን ሊጠቅመኝ እንባ ምን ሊፈይድ?፤
ያለቀሰ ሳይሆን በቁም ሚረዳ ነው ባምላክ የሚወደድ፤

እናልህ ወገኔ...
ደረትክን አትድቃ ሙሾው ገደል ይግባ፤
ገለከኝ አታልቅስ ይቅርብኝ ያዞ እንባ።
ከልብ ካዘናችሁ በነፍሴ ድረሱ፤
እናተ ገላችሁ ስሞት አታልቅሱ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
14🔥1
#ምን_ተሰማሽ_ውዴ?

ውብነትሽም ፈክቶ ደምቀሽ በደስታ፣
መጠውለግ እንዳለ ተዘናግተሽ ለአፍታ፣
በፍካትሽ ኮርተሽ እብሪት አንቀባሮሽ፣
ነገሽን በመርሳት ዛሬን ተመክተሽ፣
መጸውለግ ሲመጣ ጊዜውን ጠብቆ፣
ወዝሽ ላይሰነብት ላይሸኝሽ አርቆ፣
ሁሉን በውበትሽ፣
ስንቱን በፈገግታሽ፣
ሴሰኛን በዳሌሽ፣
ገፍትረሽ በጡትሽ፣
ሰካራም በጠላሽ፣
ቅብጥብጥ! ሲያረግሽ፣
አስቀሽ አላግጠሽ ውበት አመፃድቆሽ
ምን ተሰማሽ? ውዴ ዛሬ ሲሸሽ ጥሎሽ!?
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍114🥰1
#የንስር_እድሜ_ይስጥሽ

ይታደስ አካልሽ - በሺ አመት ዘመንሽ፣
ከርጅና ‘ሚመለስ - የንስር እድሜ ይስጥሽ፣
እዉነተኛዋ ሰው - ካምላኬ ቀጥለሽ፣
የህይወቴ ህይወት - እማ የምወድሽ፣
የኑሮየ ድምቀት - ድንቅ ስጦታ ነሽ::

የመኖሬ ምክኒያት - ምንጯ የህይወቴ፣
የሃሴት የፍቅር - የሰላም ሙላቴ፣
ቀድመሺኝ የመጣሽ - ገፀ በረከቴ፣
ደስታሽ ደምቆ ይብራ - በ ጉሙ ህ-ይወቴ      
እማ ዉዷ እናቴ! . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
መጠማት መራብሽ - ማጣት መራቆትሽ፣
ከሰው በታች ሆነሽ - ክብርሽን ማጣትሽ፣
እማየ ለኔ ነው - ለደካማዉ ልጂሽ፣
ከቶ በምን ቋንቋ - በምን ቃል ልግለፅሽ? እንዴት ልመልሰዉ - በዝቶብኛል ፍቅርሽ!

ይታደስ አካልሽ - በሺ አመት ዘመንሽ!
ከርጅና ሚመለስ - የንስር እድሜ ይስጥሽ!
ከዚህ በላይ እማ - ምን ቃል አለኝ ልጅሽ! . . . . . . . . . . . . . . .

እማ! . . .እማ!
ጭንቀትሽ ተጥሎ - ሸክምሽ ተንከባሎ፣
አለም ላንቺ ክብር ጎንበስ ቀና ብሎ፣
መቸገርሽ ቀርቶ - ቤትሽ ጓዳሽ ሞልቶ፣ ፊትሽ በፈገግታ - በደስታ አብርቶ፣
ጉድለትሽ ድካምሽ- እንግልትሽ ቀርቶ፣
የህይወትሽ ብርሃን - ይታይ ለአለም ፈክቶ፣
በረከት ረድኤቱን - አምልቶ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11🥰1
ማን በገላገለኝ? የእጄን ሠዓት ሠብሮ
በምናልባት አገር
በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ
ማን ያቅዳል ደፍሮ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
👍121
#ወዴት_ነሽ?

የት ብዬ ልፈልግ ወዴት ነሽ ሄዋኔ፣
የአጥንቴ ክፋይ የሰራሽ ከጎኔ፣

ከበረሀው ካለሽ ንገሪኝ መጣለው፣
አሸዋ ንዳዱን ይሁን ችለዋለው፣
ውሀ ጥም ረሀቡን ባንቺ ረሳዋለው፣
ቆላም ሁኚ ደጋ ጥሪኝ እዘልቃለው፣

ቤተመንግስት ሆኚም ብቻ አለው በዪኝ፣
አልፌ ገባለው ህጉ እንኳ ቢያግደኝ፣
እንደ ወንጀለኛ በእስር ቢያስቀጣኝ፣
ይገደል ተብሎ ሞት ቢፈረድብኝ፣
አንዴ ልይሽ እንጂ ይህ አያሳስበኝ፣

ስፈልግሽ ስውል ሰርክ እያካለልኩሽ፣
ባክኜ እንዳልቀር ጥሪኝ አለው ብለሽ፣

ሄደሽም ከሆነ ወደመጣሽበት፣
መኖርሽ ካበቃ ከፍጥረታት ህይወት፣
ንገሪኝ መጣለው ውዴ ካለሽበት፣
አፈር ከጋረደው ከአካልሽ ቅሪት፣
ደራሲው እንዳለው ፍቅርን እስከ ሞት፣
እኔም ነፍሴ ትለፍ ቁጭ ብዬ ካንቺ ሀውልት፣

ጠቁሚኝ ስፍራሽን ወዴት ነሽ የት ልምጣ፣
አቀበቱን ልውረድ ሽቅቡንም ልውጣ፣
ልቤ ለብቻውን ሚያረገውን አጣ፣

አንቺንም እንደኔ ብቻነት ከጎዳሽ፣
አብሬሽ እንድኖር ንገሪኝ ወዴት ነሽ፣
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11👏3👍1👌1
#ከትላንት_ሳንማር

ሰው ከሰው ተኳርፎ ዘመኑ ቢታደስ
አሮጌ ዓመት ወርዶ አዲስ ዘመን ቢነግሥ
እድሜ ቁጥር እንጂ ቢደመር ቢቀነስ
እኛ ሳንታረቅ እንቁጣጣሽ ቢደርስ
ፍቅር በሌለበት ውብ ድግስ ቢደገስ
የዶሮ የበጉ የበሬው ደም ቢፈስ
የከንቱ ከንቱ ነው ፍቅር ካልታደሰ
አንዱ የአንዱን ጎጆ ከፍቶ እያፈረሰ
መተሳሰብ ሳይኖር ልባችን ሳይቀና
አዲስ ዓመት መጣ ዞሮን እንደገና
ከትላንት ሳንማር በስህተት ተዘፍቀን
በእንቁጣጣሽ ዜማ እንቁ እንናፍቃለን።
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
7🔥1