#ኢትዮጵያዊ_ነኝ!
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣
እንደ አክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣
የጊዜ ሞገድ ያልነቀነቀኝ፣
የመከራ ዶፍ ያላደቀቀኝ፣
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣
ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣
በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣
ራስምታቴን በዳማከሴ፣
ነቅዬ 'ምጥል፣
አገር በነገር የማብጠለጥል፣
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣
በዘብ በኬላ የማልገታ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣
እንደ አክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣
የጊዜ ሞገድ ያልነቀነቀኝ፣
የመከራ ዶፍ ያላደቀቀኝ፣
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣
ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣
በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣
ራስምታቴን በዳማከሴ፣
ነቅዬ 'ምጥል፣
አገር በነገር የማብጠለጥል፣
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣
በዘብ በኬላ የማልገታ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
👍11❤2
#ትንሽ_ነበር_ለካ!!
ለሚሻግት ምግብ አድሮ ላይበላ
እምነቱን ይሸጣል ሰው ሆዱን ሊሞላ
ከሰው በተረፈ በተናቀ እንጀራ
እምነቱን የሚሸጥ እየበላ አደራ
የልብ ድሃ ነው አዕምሮ የሌለው
ስልጣንን ፍለጋ በሆድ የተገዛው
በይሁዳ ሚዛን እራሱን የለካ
ትልቅ ያልነው ሁሉ ትንሽ ነበር ለካ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ብታሙ
ለሚሻግት ምግብ አድሮ ላይበላ
እምነቱን ይሸጣል ሰው ሆዱን ሊሞላ
ከሰው በተረፈ በተናቀ እንጀራ
እምነቱን የሚሸጥ እየበላ አደራ
የልብ ድሃ ነው አዕምሮ የሌለው
ስልጣንን ፍለጋ በሆድ የተገዛው
በይሁዳ ሚዛን እራሱን የለካ
ትልቅ ያልነው ሁሉ ትንሽ ነበር ለካ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ብታሙ
👍21👏8❤4🥰1
#ናፈከኝ
ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ፤
ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ፤
ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ፤
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ፤
የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው፤
ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው፤
በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት፤
ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት።
ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር፥
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር፥
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር፥
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር።
ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ ባስተውለ፥
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ፥
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ፥
አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ፥
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ፥
የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ፥
ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ፤
ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ፤
ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ፤
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ፤
የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው፤
ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው፤
በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት፤
ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት።
ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር፥
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር፥
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር፥
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር።
ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ ባስተውለ፥
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ፥
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ፥
አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ፥
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ፥
የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ፥
ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤11👍11
#እንዳማኝ_በተስፋ_እንደ_ቆቅ_በስጋት
በቀን ተግቶ ሰርቶ ፤ በሌት ተግቶ ማሰብ
ለማይወዛ ግንባር፤ ለማይሞላ ሞሰብ::
ከቅድሟ ጀንበር፥ እስከ መጪው ንጋት
እንዳማኝ በተስፋ፥ እንደ ቆቅ በስጋት::
በወፍጮው ላይ ዱቄት
በዱቄት ላይ አፈር
በመጁ ላይ ሞፈር
ከሞፈሩ ጋራ
ደም የለበሰ ጦር
ከጦሩ ጋር ጋሻው
የማይችለው የለም፤ ያገር ሰው ትከሻው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
በቀን ተግቶ ሰርቶ ፤ በሌት ተግቶ ማሰብ
ለማይወዛ ግንባር፤ ለማይሞላ ሞሰብ::
ከቅድሟ ጀንበር፥ እስከ መጪው ንጋት
እንዳማኝ በተስፋ፥ እንደ ቆቅ በስጋት::
በወፍጮው ላይ ዱቄት
በዱቄት ላይ አፈር
በመጁ ላይ ሞፈር
ከሞፈሩ ጋራ
ደም የለበሰ ጦር
ከጦሩ ጋር ጋሻው
የማይችለው የለም፤ ያገር ሰው ትከሻው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤16👏3
#ናፍቆት
የልቤ ቅኝቱ አንቺ ሆየም አይደል
ከባቲም አይገጥም ይለያል ካምባሰል
የመናፈቅ ቅኝት የእፍቅሮ ማጣት ምት
በነጠላ አመት ውስጥ ማሳለፍ እልፍ አመት
ይከብዳል ሊገለፅ በባቲ አንቺ ሆየ
ደስታን ለረሳ ልብ ከሳቅ ለተለየ
ውዴ ሆይ ልንገርሽ ዛሬስ ተስኖኛል
መጠበቄ በዝቶ መረሳት ወርሶኛል
የሀዘኔ ጫፉ ከራስ ዳሽን ገዝፏል
የመከፋቴ ጥግ ቀይ ባህር ተሻግሯል
ትመጫለሽ ብየ በመናፈቅ ጠኔ
እኔው በራሴ ውስጥ ገብቼ ምናኔ
በእምባ በታነፀ የሀዘን ተራራ
ሰው ከማይደርስበት ከህልም አለም ስፍራ
ሀረግ የወረሳት ጎጆየን ዘግቼ
ባሮጌው ኮቴ ስር ሀብታም ልብ አንግቼ
ስንት ዘመን ኖርኩኝ መኖርን ዘንግቼ
ዛሬ…ከጎጆየ በላይ እኔ ዘምሜያለሁ
የኔ የነበረን ሁሉን ..አጥቻለሁ
ምናልባት አንድ ቀን ስታልፊ በደጄ
ከእርጅና ቡሃላ መቶ አመት ያረጄ
የህይወት ጥላሸት ገፁን የወረሰው
በድንገት ካየሽኝ እኔ ነኝ እሱ ሰው፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዘላለም ምህረቱ
የልቤ ቅኝቱ አንቺ ሆየም አይደል
ከባቲም አይገጥም ይለያል ካምባሰል
የመናፈቅ ቅኝት የእፍቅሮ ማጣት ምት
በነጠላ አመት ውስጥ ማሳለፍ እልፍ አመት
ይከብዳል ሊገለፅ በባቲ አንቺ ሆየ
ደስታን ለረሳ ልብ ከሳቅ ለተለየ
ውዴ ሆይ ልንገርሽ ዛሬስ ተስኖኛል
መጠበቄ በዝቶ መረሳት ወርሶኛል
የሀዘኔ ጫፉ ከራስ ዳሽን ገዝፏል
የመከፋቴ ጥግ ቀይ ባህር ተሻግሯል
ትመጫለሽ ብየ በመናፈቅ ጠኔ
እኔው በራሴ ውስጥ ገብቼ ምናኔ
በእምባ በታነፀ የሀዘን ተራራ
ሰው ከማይደርስበት ከህልም አለም ስፍራ
ሀረግ የወረሳት ጎጆየን ዘግቼ
ባሮጌው ኮቴ ስር ሀብታም ልብ አንግቼ
ስንት ዘመን ኖርኩኝ መኖርን ዘንግቼ
ዛሬ…ከጎጆየ በላይ እኔ ዘምሜያለሁ
የኔ የነበረን ሁሉን ..አጥቻለሁ
ምናልባት አንድ ቀን ስታልፊ በደጄ
ከእርጅና ቡሃላ መቶ አመት ያረጄ
የህይወት ጥላሸት ገፁን የወረሰው
በድንገት ካየሽኝ እኔ ነኝ እሱ ሰው፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዘላለም ምህረቱ
❤21🥰4
#ዝምተኛ_ልቦች
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው
ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጌትነት እንየው
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው
ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ጌትነት እንየው
👍22❤12🥰5🤷♀2🔥1😢1
#አፈቅርሽ_ነበረ
በነበር የሚነግስ ባይኖርም በዚ አለም ፣
መለየትን ሚገልፅ ከነበር ውጭ የለም ፣
መለያየት ሳይሆን ያስታቀፈን እዳ ፣
አለመፋቀር ነው የኔናንቺ ፍዳ ።
ቃል ባጡ ሀረጎች ባልገልፅልሽ ፍቅሬን ፣
የሩቅ ሲሆን ፍቅር ቢጎዳውም ልቤን ፣
ይህን ሁሉ ችዬ እኔ ባፈቅርሽም ፣
ያንቺ ጉዳት እንጂ የኔ አይታይሽም ።
ናፍቆት እንዴት ያማል ትዝታም ያደማል ፣
ከዚሁሉ በላይ
አትወደኝም መባል እንዴት ልብ ይሰብራል ፣
ብወድሽአይደለ በሀሳቤመሀል ምትመላለሺ ፣
ችኩልአይምሮዬን በናፍቆትሽውሀ ምታረሰርሺ ።
እንዴት አልወድሽም ?
በሀገር በምድሩ ያልታየውን ሴራ ፣
ባንቺ መሄድ ልቤ ነበር ቤት ሲሰራ ፣
ነበር ቤት ይሰራል
ግድግዳውን ናፍቆት ጣራውን ትዝታ ፣
ልብ እያፈቀረ አይምሮ አሸንፎ የተለዩ ለታ ።
ወንበዴ ነው ፍቅርሽ አይረጋም ጨርሶ ፣
መታጠፊያ ሲያገኝ ሄደ ተቀይሶ ፣
የቱጋ ነው ፍቅርሽ ፍቅር ትግስት ሲሻ ፣
የፍቅር ክፍያ መታገስ ነበረ እስከ መጨረሻ ።
ብቻ ግን እወቂ
አፈቅርሽ ነበረ !!!
መንገድሽ ጨርቅ ይሁን እንዳትመለሺ ፣
እኔም አንቺን ላስታውስ አንቺም እኔን እርሺ ፣
እጅሽን አልይዝም መንገድሽን አልሰርቀው ፣
ያምኮ ፍቅር ነው
የሚወዱትን ሰው ለሚወደው መተው ።
በይ እንዳይረፍድብሽ ......
ቢያቅትሽ መታገስ የፍቅር ህመሙን ፣
ሲያወራርድብሽ ትዝታ ናፍቆቱን ፣
እኔም ጋ ነበረ ያንቺ አይነት መከራ ፣
ግን አንቺ አስቀመጥው ከስሜትሽ ጋራ ፣
ፍቅርሽ ግብዝ ሆኖ ምላሽ ከጠበቀ ፣
እንለያይ በቃ ማፍቀርሽ ካለቀ ፣
መለየት ወግ አለው አብረው ለነበሩ ፣
እኔ አብሬሽ ነበርኩ
ከ እኔጋ አልነበርሽም እንዲያ ነው ነገሩ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በነበር የሚነግስ ባይኖርም በዚ አለም ፣
መለየትን ሚገልፅ ከነበር ውጭ የለም ፣
መለያየት ሳይሆን ያስታቀፈን እዳ ፣
አለመፋቀር ነው የኔናንቺ ፍዳ ።
ቃል ባጡ ሀረጎች ባልገልፅልሽ ፍቅሬን ፣
የሩቅ ሲሆን ፍቅር ቢጎዳውም ልቤን ፣
ይህን ሁሉ ችዬ እኔ ባፈቅርሽም ፣
ያንቺ ጉዳት እንጂ የኔ አይታይሽም ።
ናፍቆት እንዴት ያማል ትዝታም ያደማል ፣
ከዚሁሉ በላይ
አትወደኝም መባል እንዴት ልብ ይሰብራል ፣
ብወድሽአይደለ በሀሳቤመሀል ምትመላለሺ ፣
ችኩልአይምሮዬን በናፍቆትሽውሀ ምታረሰርሺ ።
እንዴት አልወድሽም ?
በሀገር በምድሩ ያልታየውን ሴራ ፣
ባንቺ መሄድ ልቤ ነበር ቤት ሲሰራ ፣
ነበር ቤት ይሰራል
ግድግዳውን ናፍቆት ጣራውን ትዝታ ፣
ልብ እያፈቀረ አይምሮ አሸንፎ የተለዩ ለታ ።
ወንበዴ ነው ፍቅርሽ አይረጋም ጨርሶ ፣
መታጠፊያ ሲያገኝ ሄደ ተቀይሶ ፣
የቱጋ ነው ፍቅርሽ ፍቅር ትግስት ሲሻ ፣
የፍቅር ክፍያ መታገስ ነበረ እስከ መጨረሻ ።
ብቻ ግን እወቂ
አፈቅርሽ ነበረ !!!
መንገድሽ ጨርቅ ይሁን እንዳትመለሺ ፣
እኔም አንቺን ላስታውስ አንቺም እኔን እርሺ ፣
እጅሽን አልይዝም መንገድሽን አልሰርቀው ፣
ያምኮ ፍቅር ነው
የሚወዱትን ሰው ለሚወደው መተው ።
በይ እንዳይረፍድብሽ ......
ቢያቅትሽ መታገስ የፍቅር ህመሙን ፣
ሲያወራርድብሽ ትዝታ ናፍቆቱን ፣
እኔም ጋ ነበረ ያንቺ አይነት መከራ ፣
ግን አንቺ አስቀመጥው ከስሜትሽ ጋራ ፣
ፍቅርሽ ግብዝ ሆኖ ምላሽ ከጠበቀ ፣
እንለያይ በቃ ማፍቀርሽ ካለቀ ፣
መለየት ወግ አለው አብረው ለነበሩ ፣
እኔ አብሬሽ ነበርኩ
ከ እኔጋ አልነበርሽም እንዲያ ነው ነገሩ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤26👍4
#ይሄ_ሁሉ_ጣዖት
እናት ያበጀችው ከስጋዋ ከፍላ
ያንን ሁሉ ወጣት ፤ ያንን ጅምር አፍላ
በውነት በፍትህ ስም ፥ እየማሉ ከዱት
እንደ ፋሲካ በግ ፥ወደ ካራው ነዱት::
የቀኑ ቀውስነት፤ የሌለው አምሳያ
ዝናብ እንደፈታው ፥ የገጠር ገበያ
ዘመን ተዘባርቆ፥
አገር በግራጁ ፥ ከቀኝ ኪሱ ሰርቆ
ጉዳችን መች አልቆ!
ትናንት አለም አቀፍ ወዛደራዊነት
ዛሬ በየፈርጁ ፥ዘርማንዘራዊነት
ደሞ ያርማው ብዛት፥ የባንዲራው አይነት
ቢያመልኩት አይራራም፥ እጣን እያጨሱ
ሻማ እየለኮሱ
ይሄ ሁሉ ጣኦት፥ የሰው ደም ነው ምሱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
እናት ያበጀችው ከስጋዋ ከፍላ
ያንን ሁሉ ወጣት ፤ ያንን ጅምር አፍላ
በውነት በፍትህ ስም ፥ እየማሉ ከዱት
እንደ ፋሲካ በግ ፥ወደ ካራው ነዱት::
የቀኑ ቀውስነት፤ የሌለው አምሳያ
ዝናብ እንደፈታው ፥ የገጠር ገበያ
ዘመን ተዘባርቆ፥
አገር በግራጁ ፥ ከቀኝ ኪሱ ሰርቆ
ጉዳችን መች አልቆ!
ትናንት አለም አቀፍ ወዛደራዊነት
ዛሬ በየፈርጁ ፥ዘርማንዘራዊነት
ደሞ ያርማው ብዛት፥ የባንዲራው አይነት
ቢያመልኩት አይራራም፥ እጣን እያጨሱ
ሻማ እየለኮሱ
ይሄ ሁሉ ጣኦት፥ የሰው ደም ነው ምሱ ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤10👍5👏5
#ማነው_የተረዳኝ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤26
ናፍቆት በገደለኝ!!
ልትቀብረኝ በመጣህ፣
እኔም ባገኘዉህ፤
ለቀብር ለሰልስት በማታ በካርታ፣
በመክብብ ጨዋታ፤
በምሽት በወጉ፣
ድንኳን ስጠብቁ፤
ደግሞ ተደጋግሞ ለአርባ ለሰማኒያ፣
ከእኔ እንዳትጠፋ፤
ለተስካር ሙት አመት፣
ለሰባት ለአስራ ሁለት፤
ምነዉ በገደለኝ!
ናፍቆት ሞት ቢሆነኝ፤
ሁሌ ሁሌ ሁሌ እንድታባብለኝ፤
ናፍቆት በገደለኝ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ረድኤት ተረፈ
ልትቀብረኝ በመጣህ፣
እኔም ባገኘዉህ፤
ለቀብር ለሰልስት በማታ በካርታ፣
በመክብብ ጨዋታ፤
በምሽት በወጉ፣
ድንኳን ስጠብቁ፤
ደግሞ ተደጋግሞ ለአርባ ለሰማኒያ፣
ከእኔ እንዳትጠፋ፤
ለተስካር ሙት አመት፣
ለሰባት ለአስራ ሁለት፤
ምነዉ በገደለኝ!
ናፍቆት ሞት ቢሆነኝ፤
ሁሌ ሁሌ ሁሌ እንድታባብለኝ፤
ናፍቆት በገደለኝ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ረድኤት ተረፈ
❤22👍4👏1
#እረፉ!
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።
ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
ምክንያት ታመመ መፍትሄ ታመመ
ከጥያቄው በፊት መልሱ እየቀደመ።
ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ድንግርግር ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ፣ ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
“ዘመመ!” ብላችሁ የሰው ቤት አትግፉ
እሾህ ለማሳመር አበባ አታርግፉ።
እረፍ!
“ቆሜያለሁ!” ለማለት አጥሬን አትደገፍ
ለአመዳም ወዘናህ ቆዳዬን አትግፈፍ።
እረፍ!
በመስመርህ ፍካ በድንበርህ ለምልም
በየአልጋህ እደር በየእንቅልፍህ አልም።
እረፊ!
በኩረጃ ንባብ ትርጉም አትግደፊ
በሰባራ መርፌሽ የሰው ልክ አትስፊ።
ማን አንደጠለፈኝ ማን እንደሰበረኝ
ጠያቂ አጣሁ እንጂ መልስማ ነበረኝ።
ምክንያት ታመመ መፍትሄ ታመመ
ከጥያቄው በፊት መልሱ እየቀደመ።
ሌብነት ገነነ
ግርግር ገነነ
ብልጭልጭ ገነነ
ድንግርግር ገነነ
ኪሳራ ገነነ
ደላሎች ገነኑ፣ ደላሎች ጀገኑ
ባልዋለ ገበያ ዋጋ እየተመኑ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤18👍4🔥3
#አንቺ_የለሽበትም!
መስኮት ቀዶ ገባ፣
ንፋስና ውርጩ፤
ለንጋት አዜሙ፣
ወፎቹ ተንጫጩ፡፡
ተነፋፍቀው የኖሩ፣
ተኳርፈው ያደሩ፤
ለወፎቹ ዜማ፣ ግጥም ያወርዳሉ፤
ለቀዘቀዘ ልብ፣ ሙቀት ይረጫሉ፤
ይተቃቀፋሉ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
ከጎረቤት ደጃፍ፣ቡና ይወቀጣል፤
‹‹ቡና ጠጡ›› እያለ፣
እንደመወርወሪያ፣
በመንደሩ መሀል፣ህጻን ልጅ ይሮጣል፡፡
እሱን ተከትለው፤
የመንደሩ ሴቶች፣
ሀሜት አንጠልጥለው፤
ይሽቀዳደማሉ፤
ለነጋው አዲስ ቀን
ንድፍ ያስቀምጣሉ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
ደግሞ ቀኑ ጋመ፣ . . . .
አዳሜ ተነሳ፣
ከትናንት ገንፍሎ፣
እንደልሙጥ ሽሮ፣
መግላሊቱን ጥሎ፤
ተስፋ አንጠልጥሎ፤
ሊረግም - ሊመርቅ
ሊጥል ወይ ሊወድቅ፤
ሊያለቅስ ወይም ሊስቅ፤
በናፍቆት - ሊተያይ፤
ተጣልቶ - ሊለያይ፣ . . . .
አሮጌ ትላንቱን፣ ጎጆው እየጣለ፤
አዲስ ቀኑን ሊያትም፣ አደባባይ ዋለ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
ደግሞ አመሻሽ ላይ፣ . . . .
ተራራው አናት ላይ፣
ሰአሊው ተፈጥሮ፣
አድማስን ወጥሮ፣
ቀለማት ደርድሮ፤
አንዳንዴ በተስፋ፣
ቢጫ እያበዛ፣ ቀይ እያሳነሰ፤
አንዳንዴ በምሬት፣
ቀዩን እያበዛ፣ ቢጫ እየቀነሰ፤
ተቅላሎት ሲሸምን፣ ፍም እያባዘተ፣
የደከመውን ቀን፣ አባብሎ ሲያስተኛ፣ ውበት እየጋተ፡፡
ደግሞ መለስ ብሎ፣
በልቤ የያዝኩትን፣ ማጣት አስተውሎ፣
በረዥም ቡሩሹ፣ ካድማስ ወዲያ በኩል፣ ጨለማን አጥቅሶ፤
ከሰል ሲያስመስለው፣ ሲሰራ ያዋለውን፣ ሲያፈርሰው መልሶ፤
ለጥበብ ምትሀት፣ ልባቸው የገበረ፤
ሰዎች ተሰብስበው፣ ያደንቁ ነበረ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
አላገኘሁሽም፡፡
ቢሆንም አውቃለሁ፣ . . .
የለሽም አልልም እፈልግሻለሁ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በድሉ ዋቅጅራ
መስኮት ቀዶ ገባ፣
ንፋስና ውርጩ፤
ለንጋት አዜሙ፣
ወፎቹ ተንጫጩ፡፡
ተነፋፍቀው የኖሩ፣
ተኳርፈው ያደሩ፤
ለወፎቹ ዜማ፣ ግጥም ያወርዳሉ፤
ለቀዘቀዘ ልብ፣ ሙቀት ይረጫሉ፤
ይተቃቀፋሉ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
ከጎረቤት ደጃፍ፣ቡና ይወቀጣል፤
‹‹ቡና ጠጡ›› እያለ፣
እንደመወርወሪያ፣
በመንደሩ መሀል፣ህጻን ልጅ ይሮጣል፡፡
እሱን ተከትለው፤
የመንደሩ ሴቶች፣
ሀሜት አንጠልጥለው፤
ይሽቀዳደማሉ፤
ለነጋው አዲስ ቀን
ንድፍ ያስቀምጣሉ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
ደግሞ ቀኑ ጋመ፣ . . . .
አዳሜ ተነሳ፣
ከትናንት ገንፍሎ፣
እንደልሙጥ ሽሮ፣
መግላሊቱን ጥሎ፤
ተስፋ አንጠልጥሎ፤
ሊረግም - ሊመርቅ
ሊጥል ወይ ሊወድቅ፤
ሊያለቅስ ወይም ሊስቅ፤
በናፍቆት - ሊተያይ፤
ተጣልቶ - ሊለያይ፣ . . . .
አሮጌ ትላንቱን፣ ጎጆው እየጣለ፤
አዲስ ቀኑን ሊያትም፣ አደባባይ ዋለ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
ደግሞ አመሻሽ ላይ፣ . . . .
ተራራው አናት ላይ፣
ሰአሊው ተፈጥሮ፣
አድማስን ወጥሮ፣
ቀለማት ደርድሮ፤
አንዳንዴ በተስፋ፣
ቢጫ እያበዛ፣ ቀይ እያሳነሰ፤
አንዳንዴ በምሬት፣
ቀዩን እያበዛ፣ ቢጫ እየቀነሰ፤
ተቅላሎት ሲሸምን፣ ፍም እያባዘተ፣
የደከመውን ቀን፣ አባብሎ ሲያስተኛ፣ ውበት እየጋተ፡፡
ደግሞ መለስ ብሎ፣
በልቤ የያዝኩትን፣ ማጣት አስተውሎ፣
በረዥም ቡሩሹ፣ ካድማስ ወዲያ በኩል፣ ጨለማን አጥቅሶ፤
ከሰል ሲያስመስለው፣ ሲሰራ ያዋለውን፣ ሲያፈርሰው መልሶ፤
ለጥበብ ምትሀት፣ ልባቸው የገበረ፤
ሰዎች ተሰብስበው፣ ያደንቁ ነበረ፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
አንቺ የለሽበትም፡፡
አላገኘሁሽም፡፡
ቢሆንም አውቃለሁ፣ . . .
የለሽም አልልም እፈልግሻለሁ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በድሉ ዋቅጅራ
❤14👍1
#ልሂድ_ያልሽ_ለታ
እንዴት ነህ ስትዪኝ ያኔ የመለስኩልሽ
ከሌለሽ የለሁም ብዬ የነገርኩሽ
እንዳትረሺው ብዬ ዛሬም ልድገምልሽ
እውነቴን ነው ፍቅሬ ከሌለሽ የለሁም
አንቺ ስላለሺኝ አሁን ላይ አልሞትኩም
ግን ወዴ ካጣሁሽ በህይወት እያለው
አልቅሰሽ ሳትቀብሪኝ በቁሜ እሞታለው
እስኪ አስቢው ውዴ በቁም ከሞትኩብሽ
አላቅፍሽ፣ አልስምሽ ግጥም አልፅፍልሽ
ባካል አላገኝሽ ወይ አልደውልልሽ
ያለሁበት ጠፍቶኝ ስንከራተትልሽ
እናቴ አልቅሳ በቁሜ አትቀብረኝ
ወይ ድጋሜ አርግዛ እኔኑ አትወልደኝ
ሞትና ቀብሬ ተራርቀውብኝ
እውነት ያበደ ሰው ሆኜ እቀራለውኝ
አንቺ የሄድሽ ጊዜ ገነትንና ሲዖልን እዚው አየዋለው
ገነትን በትዝታ ሲዖልን በእብደት ውስጥ እመለከታለው
ልሂድ ያልሽ ጊዜ ቀኑ ይጨልማል
ጨረቃ ጠዋት ላይ ፀሀይ ማታ ይወጣል
ተፈጥሮ በኔ ላይ ይገለባበጣል
ውዴ ሆይ ልሂድ ያልሽ ለታ
ቀን ላይ እየሞትኩኝ እኖራለው ማታ
አንቺን እያሰብኩኝ ሁሌ በትዝታ
ስለዚህ ፍቅሬ ሞቴ ያማረሽ ጊዜ ምንም እንዳትዪኝ
3 ፊደል ተናግረሽ "ልሂድ" ብቻ በይኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እንዴት ነህ ስትዪኝ ያኔ የመለስኩልሽ
ከሌለሽ የለሁም ብዬ የነገርኩሽ
እንዳትረሺው ብዬ ዛሬም ልድገምልሽ
እውነቴን ነው ፍቅሬ ከሌለሽ የለሁም
አንቺ ስላለሺኝ አሁን ላይ አልሞትኩም
ግን ወዴ ካጣሁሽ በህይወት እያለው
አልቅሰሽ ሳትቀብሪኝ በቁሜ እሞታለው
እስኪ አስቢው ውዴ በቁም ከሞትኩብሽ
አላቅፍሽ፣ አልስምሽ ግጥም አልፅፍልሽ
ባካል አላገኝሽ ወይ አልደውልልሽ
ያለሁበት ጠፍቶኝ ስንከራተትልሽ
እናቴ አልቅሳ በቁሜ አትቀብረኝ
ወይ ድጋሜ አርግዛ እኔኑ አትወልደኝ
ሞትና ቀብሬ ተራርቀውብኝ
እውነት ያበደ ሰው ሆኜ እቀራለውኝ
አንቺ የሄድሽ ጊዜ ገነትንና ሲዖልን እዚው አየዋለው
ገነትን በትዝታ ሲዖልን በእብደት ውስጥ እመለከታለው
ልሂድ ያልሽ ጊዜ ቀኑ ይጨልማል
ጨረቃ ጠዋት ላይ ፀሀይ ማታ ይወጣል
ተፈጥሮ በኔ ላይ ይገለባበጣል
ውዴ ሆይ ልሂድ ያልሽ ለታ
ቀን ላይ እየሞትኩኝ እኖራለው ማታ
አንቺን እያሰብኩኝ ሁሌ በትዝታ
ስለዚህ ፍቅሬ ሞቴ ያማረሽ ጊዜ ምንም እንዳትዪኝ
3 ፊደል ተናግረሽ "ልሂድ" ብቻ በይኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤11👍8🔥6❤🔥2🙏1
#እንዳትመጣብኝ !!
እንዲያ እየወደድኳት
እንዲያ እያፈቀርኳት
ልብ እንዳልሰጠኋት
አወይ አለማወቅ ምን አይነቷ ጅል ናት
በጇ ያለውን ወርቅ እንደመዳብ ቆጥራ
የተሰረቀ ነው የሚጣፍጥ ብላ
ልብን ያህል ነገር አሽቀንጥራ ጥላ
ሄዳ ሄዳ ሄዳ
ዘላ ዘላ ዘላ
ካሻት ጋር ተፋቅራ
ካሻት ጋር ተፋታ
የማታ የማታ ሲጨላልምባት
ድንገት ትዝ ስላት
ልትመጣ ነው አሉ
አረ ውዴት ወዴት ! ወዴት ትመጣለች !!
አትሞክሪው በሏት ንገሯት ከሰማች
አመሏን አውቃለው እብድ ትፈራለች
ያ የምታውቂው ልጅ አሁን የለም በሏት
ንገሯት ! ንገሯት
የባጡን የቆጡን ቅብጥርጥር አርጉላት!
አንቺን የሚያይበት አይኖቹን አጥፍቷል!
አንቺን የሰማበት ጆሮዎቹን ደፍኗል
አንቺን ያቀፈበት ክንዶቹን ሰባብሯል
አረ ምኑ ቅጡ እንዳልነበር ሆኗል
ጨርቁን ጥሎ አብዷል ብላችሁ ንገሯት
እንዳትመጣብኝ እንዳትደርስ አድርጓት !!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
እንዲያ እየወደድኳት
እንዲያ እያፈቀርኳት
ልብ እንዳልሰጠኋት
አወይ አለማወቅ ምን አይነቷ ጅል ናት
በጇ ያለውን ወርቅ እንደመዳብ ቆጥራ
የተሰረቀ ነው የሚጣፍጥ ብላ
ልብን ያህል ነገር አሽቀንጥራ ጥላ
ሄዳ ሄዳ ሄዳ
ዘላ ዘላ ዘላ
ካሻት ጋር ተፋቅራ
ካሻት ጋር ተፋታ
የማታ የማታ ሲጨላልምባት
ድንገት ትዝ ስላት
ልትመጣ ነው አሉ
አረ ውዴት ወዴት ! ወዴት ትመጣለች !!
አትሞክሪው በሏት ንገሯት ከሰማች
አመሏን አውቃለው እብድ ትፈራለች
ያ የምታውቂው ልጅ አሁን የለም በሏት
ንገሯት ! ንገሯት
የባጡን የቆጡን ቅብጥርጥር አርጉላት!
አንቺን የሚያይበት አይኖቹን አጥፍቷል!
አንቺን የሰማበት ጆሮዎቹን ደፍኗል
አንቺን ያቀፈበት ክንዶቹን ሰባብሯል
አረ ምኑ ቅጡ እንዳልነበር ሆኗል
ጨርቁን ጥሎ አብዷል ብላችሁ ንገሯት
እንዳትመጣብኝ እንዳትደርስ አድርጓት !!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዳዊት ተ/ማርያም
❤21👍4👏3
#አትመለስ
ይኸውልህ ውዴ............
የስከዛሬው ፍቅር የስካሁን መውደዴ፥
እንደሻማ ቢቀልጥ ውሀ ቢሆን ባንዴ፥
ምን ሊበጀኝ እንባ ለምንስ መንደዴ?
ካልተመቸህ ልቤ ከጎረበጠብህ፥
ፍቅሬ ካልጣፈጠህ ሀሞት ከሆነብህ፥
መለየትን ወዶ ከሸፈተ ልብህ፥
አልከለክልህም ግዴታም የለብህ።
እግርህን አስሬ አቲድ አልልክም፥
መልሱልኝ ብዬም አማላጅ አልክም።
እውነቴን ነው ውዴ ሁን እንደ ፈቃድህ፥
ከሰለቸህ ፍቅሬ ተሟጦ መውደድህ፥
ሂድ እሸኝሀለሁ ጨርቅ ይሁን መንገድህ።
...... ግና.....
እንዳለፈው ጊዜ ልክ እንደትላንቱ፥
አስሰህ ስትመጣ ሲበቃህ ዙረቱ፥
ያው እንደለመድኩት እጆቼን ዘርግቼ፥
ምቀበልህ መስሎህ ከ'ቅፌ አስገብቼ፥
አትመለስ ከቶ ዳግም ላታገኘኝ፥
በመሀላ ብዛት በቃል ልትደልለኝ።
ባክህ ተለመነኝ
አትድከም አትምጣ በማምዬ ሞቷ፥
ስለማይመለስ አንዴ ከቆረጠ የሴት ልጅ አንጀቷ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ይኸውልህ ውዴ............
የስከዛሬው ፍቅር የስካሁን መውደዴ፥
እንደሻማ ቢቀልጥ ውሀ ቢሆን ባንዴ፥
ምን ሊበጀኝ እንባ ለምንስ መንደዴ?
ካልተመቸህ ልቤ ከጎረበጠብህ፥
ፍቅሬ ካልጣፈጠህ ሀሞት ከሆነብህ፥
መለየትን ወዶ ከሸፈተ ልብህ፥
አልከለክልህም ግዴታም የለብህ።
እግርህን አስሬ አቲድ አልልክም፥
መልሱልኝ ብዬም አማላጅ አልክም።
እውነቴን ነው ውዴ ሁን እንደ ፈቃድህ፥
ከሰለቸህ ፍቅሬ ተሟጦ መውደድህ፥
ሂድ እሸኝሀለሁ ጨርቅ ይሁን መንገድህ።
...... ግና.....
እንዳለፈው ጊዜ ልክ እንደትላንቱ፥
አስሰህ ስትመጣ ሲበቃህ ዙረቱ፥
ያው እንደለመድኩት እጆቼን ዘርግቼ፥
ምቀበልህ መስሎህ ከ'ቅፌ አስገብቼ፥
አትመለስ ከቶ ዳግም ላታገኘኝ፥
በመሀላ ብዛት በቃል ልትደልለኝ።
ባክህ ተለመነኝ
አትድከም አትምጣ በማምዬ ሞቷ፥
ስለማይመለስ አንዴ ከቆረጠ የሴት ልጅ አንጀቷ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🥰12❤8👍6
#ጥቂት_ነው_ምኞቴ
እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ከድፍና ከግፍ
የጠዳ
በረንዳ
እዚያ ላይ መቆየት ፥
ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤
አኔ በህይወቴ
ጢኖ ነው ምኞቴ
ለከርስ ጤፍ እንጀራ
ለነፍስ ባለንጀራ
ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ
በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤
እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ
በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ
ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ
እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት
ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት
ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ
ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍በእውቀቱ ስዩም
እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ከድፍና ከግፍ
የጠዳ
በረንዳ
እዚያ ላይ መቆየት ፥
ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤
አኔ በህይወቴ
ጢኖ ነው ምኞቴ
ለከርስ ጤፍ እንጀራ
ለነፍስ ባለንጀራ
ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ
በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤
እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ
በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ
ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ
እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት
ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት
ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ
ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍በእውቀቱ ስዩም
❤18👍6👏2
#ማን_ይሆን_ታማኙ
ማን ይሆን ታማኙ ቃሉን የማይበላ፣
ፍፁም ከአንድ በቀር የማያስብ ሌላ?
ማን ይሆን ታማኙ የእውነት አፍቃሪ፣
ሲያምኑት የማይከዳ ቃል ኪዳን አክባሪ?
ኧረ ማነው ከቶ በቃሉ የፀና፣
አስከዳር የሚጓዝ በፍቅር ጎዳና?
ወንዶችም ለሴቷ በግጥም በዜማ፣
ሴቶችም ለወንዱ በግጥም በዜማ፣
እሷም እያማችው እሱም እሷን ሲያማ፣
አይኔ ስንቱን አየ ጆሮየም ስንቱን ሰማ፣
ለሰው አይነገር የዘንድሮውማ።
ከዳችኝ ተወችኝ አፈረሰች ቃሏን፣
ሰባራ ልብ ይዠ ቀረሁኝ ባዶየን፣
እያለ ያማታል ሳይፈትሽ እራሱን፣
በውስጡ አምቆ በደሉን ክፋቱን።
እሷም ልክ እንደሱ በስንኝ ቀምራ፣
የውስጧን መከፋት የልቧን ሰባራ፣
ህይወቴ ጨልማ ሆናለች መራራ፣
እያለች ስታማው አንዱ በአንዱ ሲስቅ፣
ጥፋተኛው ማነው ታድያ እንደት እንወቅ?
ለማንስ እንዘን በማንስ እንሳቅ?
…………እናማ
ሌሎችን ከመውቀስ ከማማረር ይልቅ፣
እኔ ማነኝ ብለን ልባችን እንጠይቅ።
ትዝብት እና ትችት ከእኛው እንጀምር፣
በቅድሚያ እንዘጋጅ ሳንያዝ በፍቅር።
ዘላለም አይጠፋም እሱ ከዚች ምድር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ማን ይሆን ታማኙ ቃሉን የማይበላ፣
ፍፁም ከአንድ በቀር የማያስብ ሌላ?
ማን ይሆን ታማኙ የእውነት አፍቃሪ፣
ሲያምኑት የማይከዳ ቃል ኪዳን አክባሪ?
ኧረ ማነው ከቶ በቃሉ የፀና፣
አስከዳር የሚጓዝ በፍቅር ጎዳና?
ወንዶችም ለሴቷ በግጥም በዜማ፣
ሴቶችም ለወንዱ በግጥም በዜማ፣
እሷም እያማችው እሱም እሷን ሲያማ፣
አይኔ ስንቱን አየ ጆሮየም ስንቱን ሰማ፣
ለሰው አይነገር የዘንድሮውማ።
ከዳችኝ ተወችኝ አፈረሰች ቃሏን፣
ሰባራ ልብ ይዠ ቀረሁኝ ባዶየን፣
እያለ ያማታል ሳይፈትሽ እራሱን፣
በውስጡ አምቆ በደሉን ክፋቱን።
እሷም ልክ እንደሱ በስንኝ ቀምራ፣
የውስጧን መከፋት የልቧን ሰባራ፣
ህይወቴ ጨልማ ሆናለች መራራ፣
እያለች ስታማው አንዱ በአንዱ ሲስቅ፣
ጥፋተኛው ማነው ታድያ እንደት እንወቅ?
ለማንስ እንዘን በማንስ እንሳቅ?
…………እናማ
ሌሎችን ከመውቀስ ከማማረር ይልቅ፣
እኔ ማነኝ ብለን ልባችን እንጠይቅ።
ትዝብት እና ትችት ከእኛው እንጀምር፣
በቅድሚያ እንዘጋጅ ሳንያዝ በፍቅር።
ዘላለም አይጠፋም እሱ ከዚች ምድር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤20👍3🔥3
#ሳታውቅ_በስህተት
ካፌ ተቀምጣ ጥንዶቹን እያየች
አንተን እያሰበች ደግሞ እየናፈቀች
አንዳንድ ጊዜ ጸጉሯን
እንደገና ሐብሏን በእጇ እየፈተለች
"ምናለ በኖረ ምናለ ባቀፈኝ" ብላ እየተመኘች ባለችበት ቅጽበት በለችበት ሰዓት
አንድ ሠውዬ መጥቶ ወንበሩን ጠየቃት
አንተ እንደሁ የለህም ምናለ ቢቀመጥ?
ይ…ሄ…ው…ተ…ቀ…መ…ጠ
ሐብል የሚያይ መስሎ
መንታ ጡቶቿ ላይ ዐይኑ እንደፈጠጠ
እሱ እንዳንተ አይደለም…
እሳት ነው ምላሱ ወሬ ማያልቅበት
ደቂቃም አልሞላው…
ከንፈሯን ሲያስከፍት ሳቅ ባሕር ሲከታት ሳታውቀው ነው እሷ ሳታውቀው በስህተት ቁጥሯን የሰጠችው በጠየቃት ቅጽበት
ከዛ በሆነ ቀን…
የሆነችው ሁሉ የሰራችው ስህተት
አውቃ ነው አውቃ ነው
አውቃ ነው በድፍረት
ባክህ ይቅር በላት…..
ያንተን የጀርባ እድፍ ሰይጣን ነው ሹክ ያላት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህለ
ካፌ ተቀምጣ ጥንዶቹን እያየች
አንተን እያሰበች ደግሞ እየናፈቀች
አንዳንድ ጊዜ ጸጉሯን
እንደገና ሐብሏን በእጇ እየፈተለች
"ምናለ በኖረ ምናለ ባቀፈኝ" ብላ እየተመኘች ባለችበት ቅጽበት በለችበት ሰዓት
አንድ ሠውዬ መጥቶ ወንበሩን ጠየቃት
አንተ እንደሁ የለህም ምናለ ቢቀመጥ?
ይ…ሄ…ው…ተ…ቀ…መ…ጠ
ሐብል የሚያይ መስሎ
መንታ ጡቶቿ ላይ ዐይኑ እንደፈጠጠ
እሱ እንዳንተ አይደለም…
እሳት ነው ምላሱ ወሬ ማያልቅበት
ደቂቃም አልሞላው…
ከንፈሯን ሲያስከፍት ሳቅ ባሕር ሲከታት ሳታውቀው ነው እሷ ሳታውቀው በስህተት ቁጥሯን የሰጠችው በጠየቃት ቅጽበት
ከዛ በሆነ ቀን…
የሆነችው ሁሉ የሰራችው ስህተት
አውቃ ነው አውቃ ነው
አውቃ ነው በድፍረት
ባክህ ይቅር በላት…..
ያንተን የጀርባ እድፍ ሰይጣን ነው ሹክ ያላት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሰለሞን ሳህለ
👍9❤4🥰2😢1