#አድዋ
ታሪክ በሰራ ተራራሽ ፣ በኮረብታና ተረተሩ
በሸለቆና በጋራሽ ፣በሰማይና በምድሩ
በአምባላጌ በእንጢቾ ፣ በአባ ዳዕሮ ጉብታ
በእንዳ ኪዳነምሕረት ፣ በኣዲ አቡን ምከታ
በማርያም ሸዊት ሸለቆ ፣ በአዲፍቼና ሰማያታ
በመቀሌው ምሽግ ድርሳን ፣ በእንዳየሱስ ኮረብታ
በአባ ገሪማ ፍልሚያሽ ፣ በዓድዋ እቶን ወላፈን
በሶሎዳ ተራራ ክንድሽ ፣ ግብርሽ ዛሬም ይትረፈን
የሚያሳድደን መከራ ፣ በድልሽ መጀን ይለፈን
ያስተባበርሽው ሕብረት ፣
አንድ ያደረግሽው አንድነት ፣ በጽኑ ክንዱ ይቀፈን
ባንቺ መድኃኒት እንዳን ፣ እናትነትሽ ያትርፈን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ አበባው መላኩ
ታሪክ በሰራ ተራራሽ ፣ በኮረብታና ተረተሩ
በሸለቆና በጋራሽ ፣በሰማይና በምድሩ
በአምባላጌ በእንጢቾ ፣ በአባ ዳዕሮ ጉብታ
በእንዳ ኪዳነምሕረት ፣ በኣዲ አቡን ምከታ
በማርያም ሸዊት ሸለቆ ፣ በአዲፍቼና ሰማያታ
በመቀሌው ምሽግ ድርሳን ፣ በእንዳየሱስ ኮረብታ
በአባ ገሪማ ፍልሚያሽ ፣ በዓድዋ እቶን ወላፈን
በሶሎዳ ተራራ ክንድሽ ፣ ግብርሽ ዛሬም ይትረፈን
የሚያሳድደን መከራ ፣ በድልሽ መጀን ይለፈን
ያስተባበርሽው ሕብረት ፣
አንድ ያደረግሽው አንድነት ፣ በጽኑ ክንዱ ይቀፈን
ባንቺ መድኃኒት እንዳን ፣ እናትነትሽ ያትርፈን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ አበባው መላኩ
🔥6👍4❤2
#ባክህ_ቶሎ_አትምጣ...
ጥሩ እንዳደረጉ እንደሰሩ ደህና
ብለው ይፀልያሉ ጌታ ሆይ ቶሎ ና፣
እኔ ግን ምስኪኑ ሀጢያተኛ ልጅህ
ይችን ፀሎት ፀለይኩ ወድቄ ከደጀህ፣
አምላኬ...
ካለሁበት ሀጢያት ነብሴን ሳላወጣ
በንስሀ ፀፀት እራሴን ሳልቀጣ
ባክህ ቶሎ አትምጣ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ እዮብ ዘ-ማርያም
ጥሩ እንዳደረጉ እንደሰሩ ደህና
ብለው ይፀልያሉ ጌታ ሆይ ቶሎ ና፣
እኔ ግን ምስኪኑ ሀጢያተኛ ልጅህ
ይችን ፀሎት ፀለይኩ ወድቄ ከደጀህ፣
አምላኬ...
ካለሁበት ሀጢያት ነብሴን ሳላወጣ
በንስሀ ፀፀት እራሴን ሳልቀጣ
ባክህ ቶሎ አትምጣ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ እዮብ ዘ-ማርያም
👍17❤5😭5👏4😢2
#በመንገዴ
ሁሉም ሲተራመስ……
በመታየት ዘመን ~ ሲሯሯጥ ለታይታ፤
ነብሴ ስትደበቅ……
ካንቺ ብሌን ውጪ ~ መታየቷን ፈርታ፤
ሰ'ው ስጋን ያያል ~ ነብስ ተደብቃ፤
በዚህ ሁሉ መሀል……
ነብሴን ነው 'ምታየው~ነብስሽ አጮልቃ፤
እንዲህ በመንገዴ
የዘነጠ ወጣት ~ መልካም የለበሰ፤
ጎጆ በሌለበት ~ ጎጆ የቀለሰ፤
ወዘናው ያማረ ~ ዓማርጦ የጎረሰ፤
እንዲህ በመንገዴ
ዓይናማ ሚመራ ~ የታወረ መሪ፤
አስራ አራቱ ሀብታም……
መሆኛ መንገዶች~ሚናገር መካሪ፤
እንዲህ በመንገዴ፤
በህዝብ ላቦት ላይ~ሀብቱን የዘረጋ~የሰባ ነጋዴ፤
ሁሉም ኣይኖቼ ላይ~ትምክህቱን ይሰራል፤
ቀኔን ለማጨለም………
ጉድለቴን አግዝፎ ~ ሊያሳየኝ ይጥራል፤
እግዚኦ! ላንቺ መውደድ
ይህን ሁሉ እንዳላይ……
የፍቅርሽ ግድግዳ ~ ሆኖልኛል ተገን፤
ኣቤት! ስትጋርጂኝ…………
ስቄ ነው ማልፋቸው~እግዚሃብሄር ይመስገን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ምስክር ይብራ
ሁሉም ሲተራመስ……
በመታየት ዘመን ~ ሲሯሯጥ ለታይታ፤
ነብሴ ስትደበቅ……
ካንቺ ብሌን ውጪ ~ መታየቷን ፈርታ፤
ሰ'ው ስጋን ያያል ~ ነብስ ተደብቃ፤
በዚህ ሁሉ መሀል……
ነብሴን ነው 'ምታየው~ነብስሽ አጮልቃ፤
እንዲህ በመንገዴ
የዘነጠ ወጣት ~ መልካም የለበሰ፤
ጎጆ በሌለበት ~ ጎጆ የቀለሰ፤
ወዘናው ያማረ ~ ዓማርጦ የጎረሰ፤
እንዲህ በመንገዴ
ዓይናማ ሚመራ ~ የታወረ መሪ፤
አስራ አራቱ ሀብታም……
መሆኛ መንገዶች~ሚናገር መካሪ፤
እንዲህ በመንገዴ፤
በህዝብ ላቦት ላይ~ሀብቱን የዘረጋ~የሰባ ነጋዴ፤
ሁሉም ኣይኖቼ ላይ~ትምክህቱን ይሰራል፤
ቀኔን ለማጨለም………
ጉድለቴን አግዝፎ ~ ሊያሳየኝ ይጥራል፤
እግዚኦ! ላንቺ መውደድ
ይህን ሁሉ እንዳላይ……
የፍቅርሽ ግድግዳ ~ ሆኖልኛል ተገን፤
ኣቤት! ስትጋርጂኝ…………
ስቄ ነው ማልፋቸው~እግዚሃብሄር ይመስገን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ምስክር ይብራ
🔥9👍6❤1
#የፍቅር_ሞረድ
ብእረኛ ባሎችሽ፣ አግብተው የፈቱሽ፣ ፈትተው ያላገቡሽ
ርእስ እየሰጡ፣ አሽቀንጥረው ጣሉሽ
ያገኘሁት ልብሽ፣ ከሰውዳር ተጥሎ
ተፅፎበት ነበር -ነዝናዛ -ጨቅጫቃ-ሻካራ ነሽ ተብሎ
ነዝናዛ-ጨቅጫቃ ሻካራ ነሽ ተብሎ።
ይነዝንዘኝ እቱ፣
ይጨቅጭቀኝ እቱ፣
ሽክረትሽ ጣፋጩ።
መሸረፍ መሳሉን፣ ተዪው ለጨባጩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በረከት በላይነህ
ብእረኛ ባሎችሽ፣ አግብተው የፈቱሽ፣ ፈትተው ያላገቡሽ
ርእስ እየሰጡ፣ አሽቀንጥረው ጣሉሽ
ያገኘሁት ልብሽ፣ ከሰውዳር ተጥሎ
ተፅፎበት ነበር -ነዝናዛ -ጨቅጫቃ-ሻካራ ነሽ ተብሎ
ነዝናዛ-ጨቅጫቃ ሻካራ ነሽ ተብሎ።
ይነዝንዘኝ እቱ፣
ይጨቅጭቀኝ እቱ፣
ሽክረትሽ ጣፋጩ።
መሸረፍ መሳሉን፣ ተዪው ለጨባጩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በረከት በላይነህ
👍7❤3
#ይናገራል_ፎቶ
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳሙኤል አለሙ
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳሙኤል አለሙ
👍10❤4🔥4
#ጠብቂኝ_አልልም
አንድ ቀን
መጣለው ያልሽው ቃል ልቤ ከተዋህደ፥
ዘመን ጉድፉ አርጎኝ ስንቴ ጥሎኝ ሄደ፥
ስንት ዜ የጣፍኩት መናኛ ኑሮዬ ስንቴ ተቀደደ፥
በእምነት የካብኩት የልቤ የተስፋ ካብ ስንት ዜ ተናደ፥
በቀን መፈራረቅ የፀና ጉልበቴ ስንት ጊዜ ራደ፥
እኮ
ስንቴ?
ስንቴ?
ግዴለም፦
አትደንግጭ የኔ አለም፥
ይህንን ስትሰሚ አትራጅ የኔ ውድ፥
ወትሮም ዘመን ሯጭ ነው ተይው ጥሎኝ ይሂድ፥
ብቻ፦
የመምጣትሽ ወራት ከእድሜዬ ድር ረዝሞ፥
ጠባቂሽ የኔ ልብ እንዳይጎድል ታሞ፥
ናፋቂሽ የኔ አካል እንዳይጫጭ ዘሞ፥
ብዬ የሰጋሁ እለት፦
ከመጠበቅ ይልቅ መፈለግ ሲቀለው አካሌ በተራው፥
ከቤቴ የመጣሽ ለት ከቤትሽ መጥቼ እንዳላጣሽ ፈራው፥
ብቻ ያኔም ቢሆን፦
ልፈልግሽ እንጂ ጠብቂኝ አልልም፥
ልቤ ይህን ያውቃል
የመቅጠርን ያህል መጠበቅ አይቀልም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ቢንያም በሀይሉ
አንድ ቀን
መጣለው ያልሽው ቃል ልቤ ከተዋህደ፥
ዘመን ጉድፉ አርጎኝ ስንቴ ጥሎኝ ሄደ፥
ስንት ዜ የጣፍኩት መናኛ ኑሮዬ ስንቴ ተቀደደ፥
በእምነት የካብኩት የልቤ የተስፋ ካብ ስንት ዜ ተናደ፥
በቀን መፈራረቅ የፀና ጉልበቴ ስንት ጊዜ ራደ፥
እኮ
ስንቴ?
ስንቴ?
ግዴለም፦
አትደንግጭ የኔ አለም፥
ይህንን ስትሰሚ አትራጅ የኔ ውድ፥
ወትሮም ዘመን ሯጭ ነው ተይው ጥሎኝ ይሂድ፥
ብቻ፦
የመምጣትሽ ወራት ከእድሜዬ ድር ረዝሞ፥
ጠባቂሽ የኔ ልብ እንዳይጎድል ታሞ፥
ናፋቂሽ የኔ አካል እንዳይጫጭ ዘሞ፥
ብዬ የሰጋሁ እለት፦
ከመጠበቅ ይልቅ መፈለግ ሲቀለው አካሌ በተራው፥
ከቤቴ የመጣሽ ለት ከቤትሽ መጥቼ እንዳላጣሽ ፈራው፥
ብቻ ያኔም ቢሆን፦
ልፈልግሽ እንጂ ጠብቂኝ አልልም፥
ልቤ ይህን ያውቃል
የመቅጠርን ያህል መጠበቅ አይቀልም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ቢንያም በሀይሉ
👍5❤2🔥1
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
ታዲያ ምን ማለት ነዉ?
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
ታዲያ ለምንድን ነዉ?
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን_ትዝታ_እንጂ .....
ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ኤፍሬም ስዩም
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
ታዲያ ምን ማለት ነዉ?
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
ታዲያ ለምንድን ነዉ?
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን_ትዝታ_እንጂ .....
ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ኤፍሬም ስዩም
❤18👍6👏2💔2🔥1
#ሴትነት
ሴትነት በእኔ እምነት
ባጭር ቃል ውሀነት
ወሀ ሁኖ መኖር
ኖሮ ሁሉን ማኖር
ህይወትን ማሳመር
በዚህ በህዋ አለም
ውሀን የሚመስል
ያልተፈታ ረቂቅ
ከሁሉ የሚልቅ
የሁሉ መሰረት
የሚያኖር ደግነት
ሁሉን እንኩ ማለት
ፍቅር ለጋስነት
ማንቃት ማነቃቃት ማብቃት
የለ እንደ እናትነት
የለ እንደ ሴትነት
ውሀነት እናትነት ሴትነት
ሰው የመሆን ትርጉም ሰው የመሆን ልኬት
ለፈጣሪ ታምኖ አደራ መሰጠት
ታጭቶ ለሚስትነት ታጭቶ ለእናትነት
ይች ናት የእኔ ሴት ይች ናት የእኔ እናት
በልቤ በአካሌ በአምሮዬ ሳልኳት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መልካም የሴቶች ቀን
ሴትነት በእኔ እምነት
ባጭር ቃል ውሀነት
ወሀ ሁኖ መኖር
ኖሮ ሁሉን ማኖር
ህይወትን ማሳመር
በዚህ በህዋ አለም
ውሀን የሚመስል
ያልተፈታ ረቂቅ
ከሁሉ የሚልቅ
የሁሉ መሰረት
የሚያኖር ደግነት
ሁሉን እንኩ ማለት
ፍቅር ለጋስነት
ማንቃት ማነቃቃት ማብቃት
የለ እንደ እናትነት
የለ እንደ ሴትነት
ውሀነት እናትነት ሴትነት
ሰው የመሆን ትርጉም ሰው የመሆን ልኬት
ለፈጣሪ ታምኖ አደራ መሰጠት
ታጭቶ ለሚስትነት ታጭቶ ለእናትነት
ይች ናት የእኔ ሴት ይች ናት የእኔ እናት
በልቤ በአካሌ በአምሮዬ ሳልኳት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
መልካም የሴቶች ቀን
❤25👍4❤🔥1👏1
#ለጤዛ_ተዋድቀን
"እድሚያችን ሰባ ነው ቢበዛም ሰማንያ"
ይህም ኑሮ ሆኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ጥዋ: ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የትገብተን እንረፍ?
በዶፍ ዝናብ አገር ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን ያከትማል አንድቀን::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዪም
"እድሚያችን ሰባ ነው ቢበዛም ሰማንያ"
ይህም ኑሮ ሆኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ጥዋ: ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የትገብተን እንረፍ?
በዶፍ ዝናብ አገር ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን ያከትማል አንድቀን::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዪም
👍7🔥6❤3
#የባከነ_ሌሊት!!!!
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ ወይ ፅድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው።
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ።
አንዲት ሴት- አዳሪ ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ ወይ ፅድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው።
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ።
አንዲት ሴት- አዳሪ ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
👍17👏7❤3🔥3
#መለያየት_ማለት
ይኸው ትላንትና ከትላንትም በስትያ
ያዩሽ ሰዎች ሁላ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ አለም!! ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለኔ ና ላንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት.....
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ህይወት
ዘወትር....ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ህይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በታስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው....
ልቤና ልቦናው ተጣብቀዋል በያችቸው
እንጂ በኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት....
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ኤፍሬም ስዩም
ይኸው ትላንትና ከትላንትም በስትያ
ያዩሽ ሰዎች ሁላ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ አለም!! ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለኔ ና ላንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት.....
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ህይወት
ዘወትር....ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ህይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በታስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው....
ልቤና ልቦናው ተጣብቀዋል በያችቸው
እንጂ በኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት....
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ኤፍሬም ስዩም
👍25❤1
#አቅፌ_ልሸኘው
ህልሜን ካመከነ ማገሬን አላልቶ፥
ቃሉን ካፈረሰ አደራውን በልቶ፥
መውደዴን በመውደድ ካልመለሰች ልቡ፥
ፍቅሬን ረግጦ መሄድ ከሆነማ ሀሳቡ፥
ክፉ ሳልናገር መጥፎ ቃል ሳይወጣኝ፥
ፊቴን ሳላጠቁር ማኩረፍም ሳይቃጣኝ፥
ደረቴን ሳልደቃ አመድ ሳልነሰንስ፥
ከመሬት ሳልተኛ ጥቁር ልብስም ሳለብስ፥
አንገቴን አልደፋ ከቶ ለምን ብዬ፥
ቀን ጨለመብኝ አልል አይፈስም እንባዬ።
ጌታ ካልፈቀደ ካልሰጠኝ አጣፍጦ፥
መች በግድ ይሆናል ፍቅርን ተለማምጦ።
ደስታው ደስታዬ ነው ሀዘኑም ሀዘኔ፥
ሀሴት ካደረገ በመራቁ ካይኔ፥
መሄድ ከኔ መሸሽ ከሆነ ሚመኘው፥
ላፍታ አይከፋብኝ
ሁሌ እያፈቀርኩት አቅፌ ልሸኘው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ህልሜን ካመከነ ማገሬን አላልቶ፥
ቃሉን ካፈረሰ አደራውን በልቶ፥
መውደዴን በመውደድ ካልመለሰች ልቡ፥
ፍቅሬን ረግጦ መሄድ ከሆነማ ሀሳቡ፥
ክፉ ሳልናገር መጥፎ ቃል ሳይወጣኝ፥
ፊቴን ሳላጠቁር ማኩረፍም ሳይቃጣኝ፥
ደረቴን ሳልደቃ አመድ ሳልነሰንስ፥
ከመሬት ሳልተኛ ጥቁር ልብስም ሳለብስ፥
አንገቴን አልደፋ ከቶ ለምን ብዬ፥
ቀን ጨለመብኝ አልል አይፈስም እንባዬ።
ጌታ ካልፈቀደ ካልሰጠኝ አጣፍጦ፥
መች በግድ ይሆናል ፍቅርን ተለማምጦ።
ደስታው ደስታዬ ነው ሀዘኑም ሀዘኔ፥
ሀሴት ካደረገ በመራቁ ካይኔ፥
መሄድ ከኔ መሸሽ ከሆነ ሚመኘው፥
ላፍታ አይከፋብኝ
ሁሌ እያፈቀርኩት አቅፌ ልሸኘው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👏13❤6😭5👍1
#እስከዚህም_ፍቅርሽ
እስከዚህም ፍቅርሽ:
ከሰንደል ጭስ በላይ:
ደምቆ የማይገዝፈው:
ምንሽን ልፃፈው ?
እስከዚህም ፍቅርሽ
በጧት የረገፈው:
ከዕድሜ እሬሳ ውጭ
ዋኝታ ምኑን ታውጣው
ነብሴ ከባለፈው ?
እስከዚህም ፍቅርሽ:
ዘመን ያሳረጠው:
ምኑን አስታውሼ
ሣጌን እየማኩኝ :
እንባዬን ልዋጠው ?
እስከዚህም ፍቅርሽ
ሲነድፍ ያለሰንኮፍ:
መታሁ ቢልም ለኮፍ:
እንኳንና ሰምበር
ስምሽስ ማን ነበር ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ኑረዲን ኢሳ
እስከዚህም ፍቅርሽ:
ከሰንደል ጭስ በላይ:
ደምቆ የማይገዝፈው:
ምንሽን ልፃፈው ?
እስከዚህም ፍቅርሽ
በጧት የረገፈው:
ከዕድሜ እሬሳ ውጭ
ዋኝታ ምኑን ታውጣው
ነብሴ ከባለፈው ?
እስከዚህም ፍቅርሽ:
ዘመን ያሳረጠው:
ምኑን አስታውሼ
ሣጌን እየማኩኝ :
እንባዬን ልዋጠው ?
እስከዚህም ፍቅርሽ
ሲነድፍ ያለሰንኮፍ:
መታሁ ቢልም ለኮፍ:
እንኳንና ሰምበር
ስምሽስ ማን ነበር ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ኑረዲን ኢሳ
👍10❤2
#የፍቅር_ቃጠሎ
ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ፤
አይንሽ የጠዋት ጨረር
የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የሥንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ፤
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጀ ነሽ አንቺዬ
እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ፤
ሆነሻል ሙቀቴ፤
ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ፤
የሞቀው ምላስሽ፤
ማርኮኝ በከንፈርሽ፤
እጄን ሰጥቻለው፤
እስረኛ ሆኛለው፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ፤
ልቤን አስፈራርቶ፤
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ፤
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ፤
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረ ክርስቶስ ደስታ
ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ፤
አይንሽ የጠዋት ጨረር
የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የሥንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ፤
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጀ ነሽ አንቺዬ
እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ፤
ሆነሻል ሙቀቴ፤
ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ፤
የሞቀው ምላስሽ፤
ማርኮኝ በከንፈርሽ፤
እጄን ሰጥቻለው፤
እስረኛ ሆኛለው፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ፤
ልቤን አስፈራርቶ፤
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ፤
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ፤
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረ ክርስቶስ ደስታ
👍12❤2🔥2
#ግን_አንድ_ሰው_አለ
እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ ፥እንዳስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንዳመዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ
ያይንሽ ከረጢቱ ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሆነሽ
መጣፍሽን ከፍተሽ
ያለፈውን ዘመን ፥ ከፍተሽ ስታነቢ
የኔን ቃል አስቢ፦
ስንቶች አፈቀሩት ፥ በሐቅ በይስሙላ
የገፅሽን አቦል፥ የውበትሽን አፍላ
ግን አንድ ሰው አለ
ከሌሎች ወንዶች ጋር ፥ ያልተመሳሰለ
በእፁብ ድንቋ ነፍስሽ ፥ ፍቅር የነደደ
የመልክሽ ፀደይ ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ ፤ጥሎሽ ያልነጎደ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ ፥እንዳስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንዳመዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ
ያይንሽ ከረጢቱ ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሆነሽ
መጣፍሽን ከፍተሽ
ያለፈውን ዘመን ፥ ከፍተሽ ስታነቢ
የኔን ቃል አስቢ፦
ስንቶች አፈቀሩት ፥ በሐቅ በይስሙላ
የገፅሽን አቦል፥ የውበትሽን አፍላ
ግን አንድ ሰው አለ
ከሌሎች ወንዶች ጋር ፥ ያልተመሳሰለ
በእፁብ ድንቋ ነፍስሽ ፥ ፍቅር የነደደ
የመልክሽ ፀደይ ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ ፤ጥሎሽ ያልነጎደ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
👍12👏5❤1
#የዘመን_ፈተና
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
የሰው ሃሳብ መብላት፤
የሰው ቃል መጠጣት ፤
የሰው ህልም ማየት፤
መቆም የሰው ቁመት፡፡
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
በሰው አድማስ ማሰስ፤
በሰው ድምፅ መቀደስ፤
በሰው ሽንፈት መፍረስ፤
መሾም በሰው መንገስ፡፡
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
የሰው ፍርሃት መራድ፤
የሰው ንዴት ማበድ፤
የሰው እዳ መክሰር፤
የሰው ሞት መቀበር፡፡
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
ታመሃል ሲሉ እህ ዳንክ ሲሉ አሃ፤
ገነት ሲስሉልህ በጠፉ በረሃ፤
አጣህ ሲሉህ እህ አለህ ሲሉ አሃ፤
ሆድክን ሲሞሉልህ በቀቢጸ አመሃ፤
ሄድነ ሲሉህ እህ ቀረን ሲሉ አሃ፤
አለን ሲሉ እህ ሄድነ ሲሉ አሃ፤
ቆምነ ሲሉ እህ ሮጥን ሲሉ አሃ፤
እህ አሃ እህ አሃ እህ እህ አሃ አሃ፤
በመንገድ በርግገህ በመንገድ ቀረሃ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ ባዬ
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
የሰው ሃሳብ መብላት፤
የሰው ቃል መጠጣት ፤
የሰው ህልም ማየት፤
መቆም የሰው ቁመት፡፡
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
በሰው አድማስ ማሰስ፤
በሰው ድምፅ መቀደስ፤
በሰው ሽንፈት መፍረስ፤
መሾም በሰው መንገስ፡፡
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
የሰው ፍርሃት መራድ፤
የሰው ንዴት ማበድ፤
የሰው እዳ መክሰር፤
የሰው ሞት መቀበር፡፡
ከራስ ጋር መግባባት ከራስ ጋር መስማማት፤
የራስ ህይወት መኖር መሞት የራስን ሞት፤
የዘመኑ ረሃብ የዘመኑ ቅቅት፡፡
ታመሃል ሲሉ እህ ዳንክ ሲሉ አሃ፤
ገነት ሲስሉልህ በጠፉ በረሃ፤
አጣህ ሲሉህ እህ አለህ ሲሉ አሃ፤
ሆድክን ሲሞሉልህ በቀቢጸ አመሃ፤
ሄድነ ሲሉህ እህ ቀረን ሲሉ አሃ፤
አለን ሲሉ እህ ሄድነ ሲሉ አሃ፤
ቆምነ ሲሉ እህ ሮጥን ሲሉ አሃ፤
እህ አሃ እህ አሃ እህ እህ አሃ አሃ፤
በመንገድ በርግገህ በመንገድ ቀረሃ፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ ባዬ
👍12❤1👏1
#ትወጂኛለሽ
እኔ እየፈራሁሽ፣ ልቤ እየደፈረሽ
እኔ እየናቅኩሽ ፣ ልቤ እያከበረሽ
እኔ እየጠላሁሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ከራሴ ስጣላ...
እኖራለሁ እንጂ ፣ የልቤን ሀቅ ይዤ
አንድም ቀን አልፎልኝ....
ልቤን እንደልቤ ፣ አላውቅም አዝዤ፡፡
አንቺም ልክ እንደኔ...
ልብሽን እንደልብ ፣ ማዘዝ አትችይም
ልብሽ ይወደኛል ፣ ጠላሁህ ብትይም፡፡
ባትወጂኝም እንኳን...
የመጥላትሽ መጠን ፣ የቱን ያህል ቢያክል
አንቺን አላምንሽም ፣ ልብሽ ነው ትክክል፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እኔ እየፈራሁሽ፣ ልቤ እየደፈረሽ
እኔ እየናቅኩሽ ፣ ልቤ እያከበረሽ
እኔ እየጠላሁሽ ፣ ልቤ እያፈቀረሽ
ከራሴ ስጣላ...
እኖራለሁ እንጂ ፣ የልቤን ሀቅ ይዤ
አንድም ቀን አልፎልኝ....
ልቤን እንደልቤ ፣ አላውቅም አዝዤ፡፡
አንቺም ልክ እንደኔ...
ልብሽን እንደልብ ፣ ማዘዝ አትችይም
ልብሽ ይወደኛል ፣ ጠላሁህ ብትይም፡፡
ባትወጂኝም እንኳን...
የመጥላትሽ መጠን ፣ የቱን ያህል ቢያክል
አንቺን አላምንሽም ፣ ልብሽ ነው ትክክል፡፡
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍25❤4🔥4👏1😍1
#ጨረቃ_ናት_ፍቅሬ
ባልዳብስሽ እንኳ:
ሳላይሽ ከከረምኩ ይለኛል ቅር ቅር
ህይወቴ ይዛባል ይላል ምንቅርቅር
ሰላም ነስተሽኛል:
ልክ እንደ ምትሀት እንደ መስተፋቅር፣
የኔ እንደማትሆኚ እያወኩኝም እንኳን
ስንት ዘመን ሆነኝ:
ልቤ ላይ ከጣልኩኝ የምኞቴን ድንኳን፣
ደግሞ አንዳንድ ግዜ:
ብሶት ይወረኛል ለራሴ አዝናለሁ
መዝጊያዬን ቆልፌ እንሰቀሰቃለሁ፣
ይኸው ዛሬ ከፍቶኝ...
ወደ ውጭ ወጥቼ ከፍቼ የቤቴን በር
ጨረቃን እያየሁ ግጥም ልፅፍ ነበር፣
ግና የሀሳቤን መቼ ከወንኩና
ፈዝዤባት ቀረሁ መፃፌን ተውኩና፣
ይገርማል አንዳንዴ...
ስንት ዘመን ሙሉ:
በፍቅርሽ ሰቀቀን ስንገላታ ኖሬ
በ2 ደቂቃ ተፋሁሽ አንቅሬ
በይ ደህና ሰንብቺ:
ከእንግዲህ በኋላ ጨረቃ ናት ፍቅሬ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ እዮብ ዘ-ማርያም
ባልዳብስሽ እንኳ:
ሳላይሽ ከከረምኩ ይለኛል ቅር ቅር
ህይወቴ ይዛባል ይላል ምንቅርቅር
ሰላም ነስተሽኛል:
ልክ እንደ ምትሀት እንደ መስተፋቅር፣
የኔ እንደማትሆኚ እያወኩኝም እንኳን
ስንት ዘመን ሆነኝ:
ልቤ ላይ ከጣልኩኝ የምኞቴን ድንኳን፣
ደግሞ አንዳንድ ግዜ:
ብሶት ይወረኛል ለራሴ አዝናለሁ
መዝጊያዬን ቆልፌ እንሰቀሰቃለሁ፣
ይኸው ዛሬ ከፍቶኝ...
ወደ ውጭ ወጥቼ ከፍቼ የቤቴን በር
ጨረቃን እያየሁ ግጥም ልፅፍ ነበር፣
ግና የሀሳቤን መቼ ከወንኩና
ፈዝዤባት ቀረሁ መፃፌን ተውኩና፣
ይገርማል አንዳንዴ...
ስንት ዘመን ሙሉ:
በፍቅርሽ ሰቀቀን ስንገላታ ኖሬ
በ2 ደቂቃ ተፋሁሽ አንቅሬ
በይ ደህና ሰንብቺ:
ከእንግዲህ በኋላ ጨረቃ ናት ፍቅሬ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ እዮብ ዘ-ማርያም
👍14❤6👏2
#ቢታነፅ_ቢወቀር
እኔም አንድሰሞን
ልክ እንደሶሎሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል"
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር::
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጉዋሮ በር በኩል: ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ እንደቆቅ አጠመድሁ::
ከፀሓይዋ በታች :ግልገል ፀሃይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ "የነበረው "አንቱ "ሆኖ ታየኝ::
ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ : ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም : ካልወደደ በቀር::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
እኔም አንድሰሞን
ልክ እንደሶሎሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል"
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር::
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጉዋሮ በር በኩል: ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ እንደቆቅ አጠመድሁ::
ከፀሓይዋ በታች :ግልገል ፀሃይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ "የነበረው "አንቱ "ሆኖ ታየኝ::
ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ : ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም : ካልወደደ በቀር::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በዕውቀቱ ስዩም
👍11❤5👏1
#የፍቅር_ዘመኑ
ወጣቱ .........
አስር – ከሰባቱ
ፀሐይን በጉያህ
ጨረቃን በኪስህ
ዩኒቨርስን ጠቅላዩን
በመዳፍህ ይዘህ
ፍቅርን በቃጠሎ
በትንታግ ታውቃለህ።
ወሬዛው........
ሰላሳ – ካምስቱ
ፀሐይ በቦታዋ
ጠዋት ትወጣና ማታ ትጠልቃለች
ጨረቃም በምሽት
በፀሐይ ዳረጎት በልመና ጨረር
አንሳ ታበራለች።
ፍቅርም እንደልምዱ
ከልቦናህ ያድራል ከተፈጥሮ ግንዱ።
አዛውንቱ .......
ሰባ – ከስምንቱ
ፀሐይ ከቦታዋ
ጥልቁን ትርቃለች
ጨረቃም ተማፅና ጨለማ መግፈፊያ
ብርታቷን ታጣለች።
– በፈንታው –
ትዝታ ክራሩን
ያለፈ ቅኝቱን
ፊትህ ላይ ያከርራል
ዘላለሙን ላይለቅ ፍቅርን ያላዝናል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዮሐንስ ሀብተማሪያም
ወጣቱ .........
አስር – ከሰባቱ
ፀሐይን በጉያህ
ጨረቃን በኪስህ
ዩኒቨርስን ጠቅላዩን
በመዳፍህ ይዘህ
ፍቅርን በቃጠሎ
በትንታግ ታውቃለህ።
ወሬዛው........
ሰላሳ – ካምስቱ
ፀሐይ በቦታዋ
ጠዋት ትወጣና ማታ ትጠልቃለች
ጨረቃም በምሽት
በፀሐይ ዳረጎት በልመና ጨረር
አንሳ ታበራለች።
ፍቅርም እንደልምዱ
ከልቦናህ ያድራል ከተፈጥሮ ግንዱ።
አዛውንቱ .......
ሰባ – ከስምንቱ
ፀሐይ ከቦታዋ
ጥልቁን ትርቃለች
ጨረቃም ተማፅና ጨለማ መግፈፊያ
ብርታቷን ታጣለች።
– በፈንታው –
ትዝታ ክራሩን
ያለፈ ቅኝቱን
ፊትህ ላይ ያከርራል
ዘላለሙን ላይለቅ ፍቅርን ያላዝናል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ዮሐንስ ሀብተማሪያም
❤5👍3😁2