ግጥም
4.26K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ተመልሼ_አልመጣም

ከወንጌል ቃል ሁሉ:እግዜር ካስተማረው
ነብስያዬን ገዝቶ:ቀልቤን የማረከው
ከልቡ የሆነ :ይድናል የሚለው !!

ምክንያቱም አለሜ : ምክንያቱም ህመሜ
የእውነትን ካልኖርኩ :እኔ አልድንም ፆሜ
ፀሎትም አይሰምር: አይፈይድም ስግደት
ሰደቃም አያርግ:ይስሙላ ካለበት

እናልሽ:አለሜ :
ከወንጌል ቃል ሁሉ :እግዜር ካስተማረው
ነብስያዬን ገዝቶ:ቀልቤን የማረከው
ከልቡ የሆነ:ይድናል የሚለው!!!

ስለዚህ መሻትሽ:ከልብሽ ከሆነ
በፍቅራችን ቅጠል አንቺም:ትድኛለሽ የኔም ነብስ ዳነ !!
ግና ነብስያዬን:ፍፁም ካልወደድሻት
ውዴ ቀረሽብኝ:አንቺም ቀረሽባት!

ደግሞ ካንቺ እርቄ: ከሸሸሁኝ በጣም
ውዴ ካለሽበት:ተመልሼ አልመጣም
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ዳዊት ጥዑማይ
5👍2👎1👏1
#የሐውልት_ላይ_ፁሁፍ

"ፀሀፊው በምን አረፈ?"
ተብላችሁ ብትጠየቁ
ኑሮውን ስትዘክሩ፣
እንዲህ ብላችሁ መስክሩ
ፀሀፊው ነብይ ነበረ
ብዕሩ ቀለም ተሞልታ
ልቦናው በሀሳብ ታጭቆ
እንዲፅፍ የተፈጠረ
አንጋሹ ቀቢው በርክቶ
ከፍ ከፍ አድራጊው በዝቶ
በእብሪት እንደታበተ
ጥቂት መስመር እንደጫረ
በሆነ መድረክ እግርጌ
ጭብጨባ ጨፍልቆት ሞተ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ቴድሮስ ፀጋዬ
👍8🔥21
አንቺን ነበር የፈለኩት
ላንቺ ነበር የተሳልኩት

ወይ አለችኝ ህልም ብላ
ጋኔል አለች ጨለም ብላ
መቼ ሰማች ወይብላ

የጠራናት ከአመት ቁስል
ሞተን ቆየን መጣሁ ስትል

ደከምኩኝ እስካለሽ
ተብከነከንኩ በየአፍ
ይቅናህ በይኝ እንዳገኝሽ
አልደረስኩም ስንቱን ባልፍ

ደሜን ማነው ያባከነው
ሞቴን ብቻ ሚመነዝር
አንቺን ከእኔ እያራቁ
ቃሉን ደግመው የሚያሰምር
ማነው አንቺን የሚያፈቅር ?
ማነው አንቺን አምኖ ሚያድር
ማነው ላንቺ የሚሰክር ?

ከእኔ ብቻ ዕንባ ዕንባ
ከእኔ ሌላ ህመም አለ?
ወይ'ብላም አጠራኝም
ኮሶ ብቻ መድን ካለ

ኑሮሽን እንድሸከም
ወንድሞቼን ፈለኳቸው
ተከዜ ላይ ጎርፉን ሆነው
ወድቀው ነው ያየኋቸው

ሶስት አይን ጥቁር ያላት
ሀዘን ጫንቃ የበዛባት
ይቺ ሀገር ሀገር ሳትሆን
የሲኦል በር ማለፊያ ናት !
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ግዕዝ ሙላት
👍75👏4
#ፍቅር_እና_ቅናት

እባክህ ፍቅሬ ሆይ እመነኝ አትቅና፤
በሄድሁበት ሁሉ አልረሳህምና፤
አትቅና ውደደኝ ከልቤ ስወድህ፤
እንኮንስ እርቄህ ጎንህ ስር ተኝቸ ትናፍቀኛለህ፤

ስትል ውስጤ እረክቶ ታንጾ መንፈሴ፤
ፍጹም እንዳልቀና ቃል ገባሁ ለራሴ፤

ኳላ ሱስ ሆኖባት…
የኔ በእሷ መቅናት…

አሁን የማትቀና ከቤቴ ስወጣ፤
ስለማትወደኝ ነው አለች ተገልብጣ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
14😁8👍4
#ቶሎ_ቶሎ_ምጪ

ውዴዋ!!! ስሚኝማ ማሬ ፣
እንዴው አትሳቂብኝ ይህን መናገሬ፣
ካንቺ ጋራ ስሆን እኔ ሌላ ሰው ነኝ፣
እንኳን ፖለቲካ ምግብ ትዝ የማይለኝ፣
እናም ስሚኝማ ሁልግዜ ተከሰቺ፣
ፓለቲካ አስጥለሽ ልቤን አስደስቺ፣
በማላውቀው ጉዳይ ገብቼ ስዛክር፣
ልክ አንቺ ስትመጭ ይዘሽልኝ ፍቅር፣
እንኳን የማላውቀው ግሙ ፖለቲካ፣
ምግብንም ይረሳል እጄ ሌላ አይነካ፣
እናም ጥበብዬ የእኔ ፍቅር ሸጋ፣
ቶሎ ቶሎ ምጪ ሌሊቱ እንዲነጋ፣
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍1311🥰3
#በትን_ያሻራህን_ዘር

በጓጥ በስርጓጉጡ
በማጥ በድጡ
እንደ ተንጋለልክ፣እንደ ዘመምክ
ትንፋሽህን እንደቋጠርክ
ልል ቀበቶህን እንዳጠበክ
የተልእኮህን አባዜ
የህይወትህን ቃል ኑዛዜ
ወርውር
የእጅህን ዘገር
በትን !
ያሻራህን ዘር
ይዘኸው እንዳትቀበር።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍91🥰1
#ቀቢፀ_ተስፋ

ፍቅረኛ የያዘች ለታ፣
አንጀቴም ይቆርጥልኛል ልቤም ያገኛል እፎይታ።
የሚል ተስፋ ቃል ሰንቄ ጉልበት ለግሶኝ እምነቱ፣
ቀን ቆጥሮ ተምሞ ሲነጉድ ግዜው ደረሰ ሰዓቱ፣
ፍቅረኛም ያዘች ልጅቱ፣
ግና ሚያስተዛዝበው በሷ ላይ የሚጨክነው ከየት ተገኝቶስ አንጀቱ።

ተስፋን ማያጣው ይህ ልቤም አልቆርጥም ብሎኝ ለዘበ፣
ዳግም እንዲም ሲል ሀሰበ።
ፍቅረኛ መያዝን እንደው ማን አረገው ትልቅ ጉዳይ፣
የኔም ፍቅረኛ ነበረች እስኪጠቡን ምድር ሰማይ፣
ባለሀገሩ እስኪያውቅልን እስክትሞቀን ድረስ ፀሀይ።
እኔ እንደሆንኩ ተስፋ አላጣም እሷ እንደሆን ሰርክ አዲስ ነች፣
ከኔም ጋር እንደተጣላች ነገ ከሱም ትጣላለች።

ይብላኝልኝ ገሩ ልቤ እንዳሰበው መቼ ቀና፣
ጆሮ ስሎ ሲጠባበቅ ተለያዩ የሚል ዜና፣
የወጠነው ፈሩ ለቆ እንኳን እሷ ልትጣላ፣
ባለማመን በደመነፍስ ድል ያለውን ሠርጓን በላ።

ያ የካበው የእምነት ጡብ ድንገት ባንዴ ቢናድበት፣
መደበቂያ የሚለው ሰው ጎኑ ቢያጣ ሚገባበት፣
ልቤ ፍቅሯ ስልብ አድርጎት ተስፋን መቁረጥ መች ታደለ፣
ማያባራን ቀቢፅ ተስፋ እንዲ ብሎም አስከተለ።

ይሁን ታግባ ምንም አይደለ፣
አልቆጥርባት እንደበደል።
ባለትዳር የተባሉት ቀን ወር ዓመት ሲደረደር፣
አይቻለሁ ሲሳናቸው ለቃላቸው ታምኖ ማደር።
እኔ እንደሆን ተስፋ አላጣም እሷ እንደሆን ሰርክ አዲስ ነች፣
እኔን እንደተወችኝ እሱንም ትፈታዋለች።

አወየሁ ተላላው ልቤ የገዛ የራሱ ተስፋ ሁሌ እየጣለው ተብትቦ፣
እየጠበቀ ባለበት ፍቺዋን በጉጉት ስቦ፣
አንጀቱን መቁረጥ ተስኖት ነገን ሲጠብቅ በተስፋ፣
ድንገት አግኝቷት አረፈው መንታ ልጆቿን ታቅፋ።

ድጡን ሲያልፈው ከማጡ ጉድባውን ሲዘል ሸለቆ፣
ቀላል ነው ያለው አቅሎት ይባስ በፍቅሯ ተጨንቆ፣
ምፅዓት ሆኖ ቢታየው መለየት በቁም ቢቀብረው፣
እንዲ የሚልን ተስፋ ቃል እንዳዲስ በልቡ አኖረው።

ሴቶች ወልደው ሲስሙ ሲጫናቸው ሀላፊነት፣
ከሩቅ ቀልብን የሚስበው የገፃቸው ጥዑም ውበት፣
ሚያስጎመጀው ተክለ ሰውነት፣
ስለማይከርም እንደፊቱ ያኔ ሸጋ እንደነበረው፣
የባሎችን ፍቅር ስሜት ታዝቤያለሁ ሲቀይረው።

ፍቅሬን ያገባት ባሏም በድንገት ውበቷን ሲያጣው፣
ሌላ ሴትን ከከጀለ ትችላለች ከልቧ ውስጥ የዛን ለታ ልታስወጣው።

እንዲህ እንዲያ የበዛበት፣
ሰበብ አስባብ የሞላበት፣
በቃ አክትሟል የሌለበት፣
ተላላ ነው የኔ እኔነት።

እንደዚሁ ነኝ እኔ በቃ አያልቅብኝ ቀቢፅ ተስፋው፣
አረ አይሆንም ማለት ከብዶኝ በምናልባት እየለፋው፣
ሰው ስከተል ከራሴ ጋር ሳልገናኝ ስንቴ ጠፋው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሄኖክ_ብርሃኑ
👍11😢32👏2
ብሶቴን ልደብቅ አረቄ ብጠጣ
ሸሽጌ ያኖርኩት ይብስ ገሀድ ወጣ
ለሰው ያልነገርኩት በውስጤ ያኖርኩት
በስካር አንደበት ጉዴን ዘረገፍኩት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
😁22👌7🍾5👍21
ሰላም Family እንዴት ናችሁ? የግጥም ፖስት ላሻሽል አስቤ ነበር እስኪ VOTE አድርጉ
Anonymous Poll
16%
በሳምንት 2 ፖስት
48%
በሳምንት 3 ፖስት
4%
በሳምንት 1 ፖስት
32%
በእስከዛሬው ይቀጥል
👍81
#ያልታደለች_እናት

ሳቋን ለገሰችው
መልኳን አተመችው
ሳጠግብ አጉርሳ ከዚህ አደረሰችው
አደገልኝ አለች ጦሮ ሊያሳርፈኝ
የልፋቴን ዋጋ ፈጣሪ ሊክሰኝ

ግና መቼ ሊሆን ከልቧ ያለመችው
በእርሱ ስትሰቃይ ዕድሜዋን ፈጀችው
ዕድሜዋን ፈጀችው!
ውጥኗን ቀጨችው!
መኖር እንዳልጓጓች ሞቷን ናፈቀችው
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኪሩቤል አሰፋ
😢185🥰3👏1
#አፋልጉኝ
💚💚💚💛💛💛
ስህተቱን አራሚ
ሌሎችንም ሰሚ
ፍፁም ነኝ የማይል በእብሪት ተወጥሮ
በሀሳብ ልእልና የሚያከብር ተከብሮ
ሲሰራ የሚሳሳት ፍጥኖ ደግሞ አራሚ
የእርሱን ብቻ ሳይሆን የሰው ሀሳብ ሰሜ
በሰውነት ሚዛን እራሱን የለካ
የግል አቋም ያለው የሌላ ሳይነካ
አፋልጉኝ ጠፋብኝ
ካያችሁ ንገሩኝ
ወረታ ከፋይ ነኝ
ይህን ሰው ላሳዬኝ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
11👍8👏4
#ጊዜ_በረርክ_በረርክ

ጊዜ በረርክ በረርክ
ጊዜ በረርክ በረርክ
ግና ምን አተረፍክ
ግና ምን አጎደልክ?
ሞትን አላሸነፍክ
ሕይወትን አልገደልክ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍103🔥2
#ይድረስ_ለእናቴ_ልጅ

ደምህ እና ደሜ
ከገነቱ ጠበል ከጊዮን ተቀድቶ
ስጋዬ እና ስጋህ
ከበረከት አፈር ከኤደን ተቦክቶ
ያውም በእግዜር ቃል
በተስፋዋ ምድር ሰው ሆኖ እነዳልኖረ
ያ ሁሉ ፍቅራችን
በትንሽ የዘር ክር ስለምን ታሰረ?

አንተ'ኮ ክብሬ ነህ
የመጎሴ ሚስጥር ህመሜን ታማሚ
እኔ'ኮ ደስታህ ነኝ
ከባድ ሀዘንህን ቀሎኝ ተሸካሚ፡፡

ያ'ንተ ዘር የኔ ዘር
ትሁፊቴ ትሁፍትህ ባህልህ ባህሌ
ዘመናት ስንኖር
ሳቄ ሳቅህ ነበር በደልህ በደሌ፡፡

ግሸን ስታስቀድስ
ለዱኒያ ዱአ ነጃሽ ካድሜአለሁ
እዛ'ና እዚህ ሆነን
በቁልቢ ስትምል በፂሆን ምያለሁ፡፡

ባ'ክሱም ስመፃደቅ
በ'ላሊበላ አለት ኩራት ተሰምቶሀል
በጀጎል ሳቅራራ
በፋሲለደስ ጌጥ አምረህ ሸልለሀል፡፡

ታዲያ ምነው ዛሬ
ዘመን ባጎደፈው በማይድን ነቀርሳ
በዘር አቅላሚዎች
አንድነትን ጠልተን ተለየን በጎሳ?

እባክህ ወንድሜ
ለባለቀን ብለህ ከፍቶህ አታስከፋኝ
አንተ ነህ ደስታዬ
ሲረግጡን ተረግጠህ ሲገፉን አትግፋኝ፡፡

ባይሆን ከረገጠን
ከገፋን ባለቀን ደም እየጨለጠ ከሰከረ ነፍሱ
በአንድነት ጠበል
ተጠምቀን እንዳን
ለለከፈን ሴጣን ፋቅራችን ነው ምሱ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11👍5👏2
መኖር በሰው ፍቃድ ሆነና ዘንድሮ
ማስተዋል ተሳነን ልባችን ታውሮ።
ጌታ የሰጠውን ፍጡር ከነጠቀ
አትጠራጠሩ ይህ ዘመን አለቀ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍236🥰1
ግጥም
ሰላም Family እንዴት ናችሁ? የግጥም ፖስት ላሻሽል አስቤ ነበር እስኪ VOTE አድርጉ
1 ሺ ሰው አይቶታል VOTE ያደረገ ሰው ግን 111 ሰው ነው 🤔
🥰10
#ወህኒ

ካቻምና በመስቀል ድፎ ባርኬአለሁ።
ዘንድሮ በጩቤ አጥንት ወግቻለሁ።

          ለምን እንዳትሉ፤
           በቃ ሆነ በሉ፤
           የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አምና ደግ ነበርኩ ፣ ክፉ ሰው ዘንድሮ
ትናንትና ምሁር ፣ ዛሬ ግን ደንቆሮ ።

            ለምን እንዳትሉ ፤
            በቃ ሆነ በሉ ፤
            የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

መሆን አምሮኝ ያውቃል፤ ፖለቲከኛ ሰው ፣ ኃያል የጦር መሪ ፤
ተመኝቼም ነበር ለመሆን አዝማሪ ፤
ገጣሚ ለመሆን ስንኝ ቋጥሬአለሁ ፤
ደራሲ ለመሆን ተስዬም አውቃለሁ ፤
ሞዴል አርሶአደርም ለመሆን ፈልጌ ፣
አስጠምጄ ነበር ከ 4 ኪሎ ግርጌ ።
ኢንጂነር ዶክተርም ልሆን ነበር እኮ ፤
እንደዚህ ሆንኩ እንጂ ነገር ሌላ ታኮ ።

            ለምን እንዳትሉ፤
            በቃ ሆነ በሉ ፤
            የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አንድ ሰው አንድ ነው ከንግዲህ አትበሉ ፤
            የሰው ልጅ ወህኒ ነው ፤
እልፍ አዕላፍ ሰዎች ታስረው የተጣሉ ፣
መውጫ አጥተው ነው እንጂ፣አንድ ሰው ውስጥ አሉ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ይስማዕከ ወርቁ
👏11👍81
#እቅፍ_አርጎ_የሚይዝ

ቢኒያም በለጠ ና ጀግናው ና ወንዱ ፡
አላስኬድም አለ ችግር በመንገዱ ፤
ውሀ ሆነው ቀርተው ሀገር የሚንዱ ፡
ምነው እንደ ቢኒ ሺዎች ቢወለዱ ፤

በምድር እየኖረ በሰማይ ቤት ሰሪ ፡
ማንአለ እንደቢኒ ለነፍሱ አዳሪ ፤
ዛሬም እንደ ቢኒ ሳይል ቤት ትዳሬ ፡
እቅፍ አርጎ የሚይዝ ትሻለች ሀገሬ ፡
በተግባር የሆነ ያይደለ በወሬ ፤

በስምንተኛው ሺህ ሰዉ በከፋበት ፡
ቢኒያም በለጠ ተከሰተ ድንገት ፤
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ክንፈ ጀማነህ
👍13👏4
አውቆ እንዳላወቀ ሰምቶ እንዳልሰማ ሰው
ያረገኝን ሁሉ በደሉን ስረሳው
እሱው ይከሰኛል እሱው ይወቅሰኛል
በኔ ችሎ ማለፍ ሞኝ ነህ ይለኛል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
15
#የኑሮ_ኳስ_ሜዳ

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ተጫዋች ነው እንጂ መሀል ዳኛ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ይሯሯጣል
ይራሱን ጎል ሰርቶ
የራሱን ያገባል የራሱን ይስታል
ሁሉም በጨዋታው ራሱ ተጠምዶ
አንዱ ያንዱን ላይዳኝ በኑሮ ተገዶ
ሁሉም ይራገጣል
እውነትን ጠልዞ ሀሰትን ይገባል

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
ቢደክሙ ቢጎዱ ተቀያሪ የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም.....
ሁሉም ሰው የራሱን 90 ደቂቃ
ተጫውቶ ሲያበቃ
ትንፋሹን ጨርሶ ድካሙን ተቋቁሞ
ሜዳውን ይለቃል በራሱ ሜዳ ላይ ራሱን ሰይሞ

በዚህች ትንሽ ሜዳ በዚህች ከንቱ ዓለም
መሸናነፍ እንጂ አቻ ውጤት የለም
በዚህች ከንቱ ዓለም....
የዚህ ሁሉ ልፋት ፍሬ የሚያገኘው
የሜዳ አሯሯጡ ብቃት ሚመዘነው
ሀሰት አሽሞንሙኖ እውነት ማስመሰል ነው
በዚህች ከንቱ ዓለም....
ውሸት እውነት እንጂ እውነት ውሸት የለም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ልዑል ሀይሌ
👍144
#መለየት

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   በእውቀቱ ስዩም
🥰10👍7💔3
#ሰው_መስለሺኝ_ነበር

እስኪ ስሚኝ ውዴ
ልጠይቅሽ አንዴ
ላንቺ የሰው ልጅ ማለት ትርጉሙ ምንድነው?
ፍቅርና ክብር ተስፋስ ምን ማለት ነው?
ስላንቺ ሳወራ ስላንቺ ስናገር
ለካስ አላውቅሽም ሰው መስለሺኝ ነበር
ለኔ እንኳን ግድ የለም ኃላ እንዳትጎጂ
መናቁን ተይና ሰው ማክበር ልመጂ
ለኔ ሲሆን ጊዜ ስጠራሽ ብውልም
እየቻልሽ አትችዪም እያለሽ የለሽም
ከቻልሽ አገናዝቢ ካልገባሽ ጠይቂ
ትንሽ የሚባል ሰው እንደሌለ እወቂ
ህሊና ላለው ሰው ትርግሙ ለገባው
እሺ ብሎ መቅረት እምቢ እንደማለት ነው
እኔ እኮ የሚገርመኝ ታሪክ እንደሰራ
አላፊ በሆነው በመልኳ ስትኮራ
ትመጪያለሽ እያልኩ በተስፋ ብኖርም
ባትመጪም ቅጠሪኝ ማለት ግን አልችልም
እናም አንዴ ስሚኝ ይጠቅምሻልና
ማስመሰሉን ትተሽ ሰው ሁኚ እንደገና።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ጉልላት አበበ
👍217👏2