ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
9 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#አትፅናኝ

ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።

አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።

በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መዘክር ግርማ
👍71👏1
#የፈጣሪ_ቅኔ

" አፈር ነበርክና ትሆናለህ አፈር "
እንዲል ቃለ-እግዚአብሔር
ጭቃ ቤት ውስጥ ሆኜ የማስበው ሁሉ
ከስንት ሰው አካል እንደተሰራ ነው
ግድግዳው በሙሉ፡፡

እግዜር ግን ሲገርም!!!

የተጠናወተው የሙስና አባዜ -
የሰው ባለ-ጊዜ
በእሳትና ሴራ
ፎቅ ቤቱን ሊሰራ
የድሆች ቤት ሲያፈርስ፣
ገበያ ሲያተራምስ፣
አንዳንዴም ሲያቃጥል
በሳት- እያጋየው፤
የነገው 'ራሱን በአሽሙር አሳየው፡፡
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አማኑኤል አለሙ
👍17👌41
አውቆ እንዳላወቀ ሰምቶ እንዳልሰማ ሰው
ያረገኝን ሁሉ በደሉን ስረሳው
እሱው ይከሰኛል እሱው ይወቅሰኛል
በኔ ችሎ ማለፍ ሞኝ ነህ ይለኛል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍187👏2🤬1
"#ግርማሞት"

በቡጢኞች ዘመን በካልቺኞች ዓለም
እንደ እንካ ሠላንቲያ ጣፍጦ ሚጥም የለም።
እኮ እንዴት ካላችሁ
ስሙኝ ልንገራችሁ።

በሠላምታ ነስቶ ነገርን ካከለ
ለጠብ መጠንሰሻ ወትሮስ ስድብ እንጂ
ሠላምታ መች አለ።

ዘማኒው ሰው ግን ጥል በእጅጉ የሻተው
እንካ ሠላንቲያን ፈጥሮ ሲፈላለጥ ኖረው።

ታዲያን ከዚህ በላይ ምን ነገር ይጥማል
በሠላም ሸፍኖ ለጠብ አሸጋግሮ ሺ-ፀብን
ይፈጥራል።

ታዲያን ከዚህ በላይ ምን ነገር ይጥማል
አሁንም መልሶ እንካ ሠላም ብሎ እርድናን ይተክላል።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መልአኩ ስብሐት ባይህ
👍31
#አታልቅስ_አትበሉኝ

አትሳቅስ በሉኝ
ግዴለም ከልክሉኝ፤
የፊቴን ፀዳል
አጠልሹት በከሰል፤ የግንባሬን ቆዳ
ስፉት በመደዳ፤
ጨጓራ አስመስሉት።
ግዴለም።
አትጫወት በሉኝ
ዘፈኔን ንጥቁኝ ግዴለም።
ብቻ ፤
አታልቅስ አትበሉኝ
አትጩህ አትበሉኝ ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍81👏1😁1
የውበትሽ ቅኔ ቢቋጠር ቢፈታ
ማረፊያው መርገፍ ነው የማታ የማታ
የዛሬው አጃቢ ተከታይ ከሗላሽ
መቼ ይፈልጋል ለማየት ከፊትሽ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍102👎2🥰2
#ፍርሀት_አዶከብሬ

ፍርሀት አዶከብሬ
አያ አይምሬ
የቁም መቃብሬ
የቅዠት ሀገሬ፡፡
ከስጋ ከነብሴ ከደሜ ቆንጥሬ     
     ከአጥንቴ ሰንጥሬ
ምስህን ሰጥቼህ ላመልህ ገብሬ
ያው ነህ አንተ ግና
ልጓምህ አይላላ፡፡
ትጋልበኛለህ በእሾህ በቆንጥር ላይ
ጨለማ እንደግራር በቅሎበት በሚታይ
አንዲት ዘሀ - ጮራ
     በማትደፍርበት
እውነት - ፍቅር - ውበት
      በተቀበሩበት፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍74🤔1
አህያ ሁን አለኝ : አህያ ሆንኩለት
አሰሱን ገሰሱን : እንድሸከምለት
መጋዣ ሁን ብሎ : ፈረሱ አደረገኝ
በየዳገቱ ላይ : ወስዶ እሚጋልበኝ
እንጃ ግን ሰሞኑን : በግ ነህ ተብያለሁ
ሊያርደኝ ነው መሰለኝ : አሁን ፈርቻለሁ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     
   ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
😁32👍54
#ታማሚ_ሀኪም_መድኃኒት

በሽታ ያጠቃው የታወከ ስጋ
ከህመሙ እንዲድን ተንፏቆ ይሄዳል መድኃኒት ፍለጋ
መዳንን የሚሻ ሀኪም ዘንድ ይቀርባል ከመድኃኒት ቀድሞ
ሀኪም ባዘዘለት መድኃኒት መስራት ይድናል ታክሞ
ለፈውስ ነው ብሎ ያገኘውን ሁሉ ከመሰልቀጥ ይፁም
ባኪም ያልታዘዘ መድኃኒት የዋጠ አይድንም በፍፁም
በሽተኛ ትውልድ
ሀኪም ባዘዘልህ በሽታህ ቢሆን ሰድል
መድኃኒቱን ስትይዝ ሃኪሙን አትበድል
ብታውቅማ ኖሮ 
ከመድኃኒት ይልቅ ሀኪም ነው ትልቁ 
ለያዘህ በሽታ መድኃኒት ማወቁ
ብታወቅማ ኖሮ
ከመድኃኒት በፊት ሀኪሙ ነው ውዱ
ፈውስ እንዲሆንህ መድኃኒት አምጦ መዳኒት መውለዱ
መዳኒት ልጅዋ ነው ሀኪሟም እማምላክ
መዳንን ከፈለክ ሁልጊዜም ወደሷ በሽቶችህን ላክ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አስታውሰኝ እረጋሳ
👍234👎2👏1
#መቼ_ይፈውሳል

በህይወት ውጥንቅጥ ያኮረፈ ስሜት፣
በሀሰት ጭብጨባ የተደበቀ እውነት፣
በግዜ ወለምታ ጉዳት ያጋጠመው፣
ወጌሻው ማን ይሆን አሽቶ የሚያድነው?
በማስመሰል ዜማ በግፍ ቅኝት ክራር፣
በውብ ቃል አስውበው ቢባል ፍቅር ፍቅር
መቼ ይፈውሳል ቃል ብቻ ቢንጋጋ
በደልን የሚሽር የእውነት ቀን ካልነጋ
የመከፋት ምንጩን ልብ ሆኖ መነሻው
ይቅርታ ብቻ ነው ለመርዙ ማርከሻው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍167
#ፍቅር_ጥላ_ሲጥል

በገና ቢቀኙ
ሸክላ ቢያዘፍኑ
ክራር ቢጫወቱ…..
ለሚወዱት ምነው
ሙዚቃ ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ
ጌጥ ውበት ቢፈጥሩ
ቤት ንብረት ቢሠሩ
አበባ ቢልኩ
ምነው ቢናፍቁ
አገር ቢያቋርጡ
ቢሄዱ ቢርቁ
አመት ቢጠብቁ
ለሚወዱት ምነው?
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገብረ ክርስቶስ ደስታ
👍141
#መሄድሽን_ሳስብ

ያለፉትን ቀኖች
ዳግም አልፌያቸው
.......ከኋላቸው ሄጄ
አንቺን የምትመስል
........አንቺኑ ወድጄ
መኖርን እያሰብኩ
በጣም እስቃለሁ
ለካ...
ወደኋላ መኖር
የህልም እንጀራ ነው፤
ለነገሩ...
ለነገሩ ያው ነው
ካላንቺ መኖሩም
ያው አለመኖር ነው።
ብቻ...
ጩህ... ጩህ... ይለኝና
ዝም ባለ ልቤ
ዝም'ብዬ ጮሀለው
በጠራራ ፀሀይ
ቀኔን አጨልማለሁ፤
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ!!
ዝም ብሎ መጮህ
ዝም ብሎ ማውራት
ሰሚ በሌለበት
ሳይጠሩ መጣራት።
ብቻ...
መሄድሽን ሳስብ...
እኔ የማላውቀው
ደርሶ ያላማከረኝ
ቅልስልስ እንባዬ
ባይኔ ስር ይፈሳል
ችሎ ላይመልስሽ
አመለኛው እግሬ
ቁጭ ብሎ ይነሳል፤
ጉድ እኮ ነው ጎበዝ!!
ያላዘዙት እንባ
ካይን አልፎ ሲያነባ
ያላነሱት እግር
ቁጭ ብሎ ሲዳክር፤
ብቻ...
ትንግርት ነው ሁሉ
አንቺ ከሄድሽ ወዲያ
የሚሆነው ሁሉ፤
ግና ምን ዋጋ አለው...
ከኛ ፍቅር በላይ
ከኛ ምኞት በላይ
የሱ ትክክል ነው¡¡
በዝች ግዑዝ አለም...
አንቺ አንቺን ሆነሽ
እኔ እኔን ሆኜ
ጊዜን ብንተውንም
ደራሲና አዘጋጅ
እግዚአብሔር ነውና
ከሱ ውጪ አኖንም።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አዱኛ አስራት
👍139
#በኪሱ_ልክ_ነው!

የሰካራም ሕጉ ፍርድና ችሎቱ
ሰፈር መረበሹ ወድቆ መነሳቱ
ልኬቱ መስፈርቱ የህይወት ቅኝቱ
በጠጣው መጠን ነው ያለው ልዩነቱ
ግራ ቀኝ ፔንዱለም የሚወዛወዘው
በኪሱ ልኬት ነው ሁሉም የሚሰክረው
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
19👍9
#እሳት_ወይ_አበባ

ይቅር ብቻ አንናገርም፥
እኔና አንቺ አንወያይም፥
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም.....ዝም፡፡
አበባ አንሆን ወይም እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን ባጫረው መአት
እድሜአችንን እንዳማጥናት....
እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ -እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን ፥ እየቃተትን ስናነባ፡፡
ፈራን፤ አዎን ፍቅር ፈራን፥
የነፍስን አንደበት ዘጋን፥
የእድሜ ጠብታችንን ምጥ፥ የጣር ፅንሳችንን ልሣን፥
ልጅነት የለገሠንን
በመለኮት የቀባንን
በእሳቱ ያጠመቀንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ፥ በሥልጣን ያላበሰንን
ፈራን፥ አዎን እውነት ፈራን
የስሜት እስትንፋስ ነሳን፡፡
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
11👍7
#ጥሬ_ጨው

መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
10👍4
#ኑ_እውሸት_እንስራ !

ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!
ቅጥፈት ነው እንዳይሉ፤
የእውነት መአዛ ያውዳል በሩቁ
ሀቅም ነው እንዳይሉ፤
መጠርጠር አይቀርም እያደር ሲነቁ!
እስከ ጊዜው ድረስ ...
እስኪተላለቁ እርስ በ'ርስ ተጋጭተው
ወይ እስኪያስተውሉ ከሰመመን ነቅተው ...
ከጓዳቸው ገብተን
የቻልነውን በልተን
ቀሪውን ሸክፈን አርገን በስልቻ
እንጓዝ በስውር እንሂድ ለብቻ
በጊዜ እናምልጥ እንምጠቅ እንብረር፤
አሻራ ሳንተው ...
ክንፋቸውን ሰርቀን ፥ ከአይን እንሰወር!
ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍182
#የማንችለው_በዛ

በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
ጥርስ ከላይ ከላይ በማስመሰል ስቆ
ልብ እህ እህ ይላል በስቃይ ዋይታ
ለማለፍ ሲያጣጥር ሁሉን በዝምታ።
የደረሰበትን በጥርስ ሳቅ ከልሎ
ውስጥ እረመጥ ፈጀው የማይቻል ችሎ።
ላያስችል አይሰጥም ይባል ነበር ድሮ
የማንችለው በዛ እንጃልኝ ዘንድሮ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰11👍63
#ቀረሽ_እንደዋዛ

እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ስልክ እንጨቶች
እንደ ዛፍ ሀረጎች
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ
ስጠብቅ ስጠብቅ
˝ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት አይኔ ሟሟ እንደ በረዶ˝
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ፡፡
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገብረ ክርስቶስ ደስታ
👍7🔥62
#ተስፋ_ስንት_ያወጣል?

ሰው በሰው ጨክኖ ቀን፡ሲለብስ ጥቀርሻ
ህልሙ የጨለመበት፡ያስሳል መሸሻ

እግሩን፡ተከትሎ
ተስፋን፡አንጠልጥሎ
አዲስ፡ቀንን ስሎ።
በሄደበት መንገድ፡በጀመረው ጉዞ
ወየው ማለት ሆኗል፡ሰው ሬሳውን ይዞ።
ወየው…ወየው…ወየው
ሰውስ ስንቱን፡ አየው።
ተስፋ ስንት ያወጣል፡ምንድነው ተመኑ?
በይሆናል ምኞት፡ስንቶቹ በከኑ።
ስንቶችስ ስመጡ፡ስንትቹ ረገፉ
እነማን ሲሄዱ፡እነማን ተቀጠፉ።
ወይታ ብቻ ሆነ፡ዝም ብሎ ለቅሶ
ለደጋፍ የሚሆን፡ጉልበታችን አንሶ
              በደላችን፡ብሶ
              አቅማችን፡ኮስሶ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አረጋኸኝ ሙሉ (ዛኪ)
👍72
#ጆሮዬን_መልሺ!

ይመስለኝ ነበረ...
ልቤን የሰወርሽው፥ እንዳያስብ ሌላ
ዓይኔን የጋረድሽው፥በመውደድሽ ጥላ፣...

ይመስለኝ ነበረ ...
ከንፈሬን ያሸግሽው ፥ የሰው እንዳይነካ
አሁን ሳስተውለው ...
ጆሮዬን ጨምረሽ ፥ ወስደሽዋል ለካ!

ዘፈን እንዴት ላድምጥ? ...
ፍቅርን አስቀይሜ ፥ ቃል ኪዳኔን ጥዬ
አምባሰል ነሽ ባቲ ፥ ኧረግ አንቺ ሆዬ!

ክራር ጤና ነሳኝ ...
መሰንቆና ዋሽንት ፥  ከበሮ ድለቃ ...
እንዳውም ይቅርብኝ!  ኃጢኣት ነው ሙዚቃ፨

ለደስታ ካልሆነኝ
                ዝንቱ ከንቱ ውእቱ
ጥርቅም!  ....  ኤ--ታ--ባ--ቱ!!

ዋ! ሞኙ!
ዋ!  እኔ!
ያበጀሁኝ መስሎኝ ፥ ያቀናሁ በቤቴ
ባሳብ ለሚዋልል ፥ ርብሽብሽ ስሜቴ
ፀጥታን ላጣጥም ፥ እፎይ ከማለቴ፣ ...

ናፍቆትን ቀስቅሶ ፥ በንፋስ ጣት ንዝረት
በሽንቁር ሾላኪ ፥ ፉጨት - ርግብግቢት፣...
ጥሩሩን አጥልቆ
ስውር ሰይፉን ታጥቆ፣ ...
ዜመኛው ዝምታሽ ፥ ሊሸርፈኝ ይከንፋል
ትዝታ እንደ ዘፈን ፥ ተጫውቶ መች ያልፋል?!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
      ✍️ በርናባስ ከበደ
👍102👏2
#ህልፈተ_ዓለም

ደረሰ ይሉናል ዓለም ማለፊያዋ፣

የሰው ነገር ዋ ፣
ጊዜው መቼ ገና ፣
መች ደረሰና።
ሰው ነው በገዛ እጁ የራሱ መፍረሻ
ሌላ .....ነገር ሲሻ
አይበቃኝም ብሎ፣ ሲሰስት ሲሻማ
የሌሎቹን ኣለም፣ ሲናጠቅ ሲቃማ
ይፈጥራል ጦርነት......
ይጠዛጠዛሉ ኣለማት ካለማት።

ከመሬት ጨረቃ ከጨረቃ መሬት
.......ያቶሚኩ ርችት
ይለካል - ይመጣል
የከዋክብት መስመር ጉዟቸው ይናጋል።

እየተፋለሰ ኣንዱ ኮከብ ካንዱ
ኣለማት ሲፈርሱ፣ ኣለማት ሲናዱ
ህልፈት የሚመጣው
ወዮ! ያን ጊዜ ነው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገብረክርስቶስ ደስታ
5👍2