ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
9 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ልብሽ ከወደደኝ በይኝ ወድካለሁ
ያው እድለኛ ነሽ መውደድ መታደል ነው።
                   
ካልወደድሺኝ ደሞ ውስጥሽ አያመንታ
ፍቅር በፍቅር እንጂ ሲሆን በይሉኝታ
ፍሬ መች ያፈራል የማታ የማታ።
                                          
ግን እየወደድሺኝ አትበይ አልወድክም
ስሜትን በማፈን ጎጆ ፀንቶ አያውቅም።
                                          
ሳትወጂኝም ደሞ አትበይ ወድካለሁ
ይህንም ታውቂያለሽ ...
ማስመሰል ካረጀ ጧሪ ዘመድ የለሁ።
                                         
እናም እኔ ዛሬ ላንቺው ሹክ የምልሽ
አልስማማ ብለው አፍሽና ልብሽ
ቡጢ ተጨባብጠው ከፀፀት ሳይጥሉሽ
ጎጆሽ እንዲቃና ፍቅር ተረብርቦ
ጥሪና አስማሚያቸው .....
ልብሽን ካራምባ አፍሽን ከቆቦ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሄኖክ ብርሀኑ
👍21
#የመጀመሪያ_ቀን

አየችው ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆው ተጋጨ
አየችው ተያዩ
አያት ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው
አየችው ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ
ታፋቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ገብረ ክርስቶስ ደስታ
👍152
#አ_ል_ገ_ጥ_ም_ም

እዪው ያን ገጣሚ
ጆሮው ስር እያለች ምትወደው ፍቅረኛ
ብዕሩን ወድሮ
ሩቅ ይማግጣል ጨረቃን ሊተኛ

ከዕለታት አንድ ቀን
ያ አፍቃሪ ገጣሚ ገጣሚ ነው ሲባል
በስንኙ ምስጠት
ባለቤቱን ፈትቶ ጨረቃን ያገባል

ከዕለታት አንድ ቀን
ያገባት ጨረቃ
በዕልፍ ገጣሚዎች ስንኝ ተወድሳ
ውበቷ የሁሉም መሆኑ ሲገባው
ጨረቃንም ፈታ መግጠሙንም ረሳ

ያ ምስኪን አፍቃሪ
ባበጃጀው ስንኝ
ባለቤቱን ትቶ በፍቺ ከተቀጣ
አ-ል-ገ-ጥ-ም-ም ካንቺ ጋር
ጨረቃን ልፈታ
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ልዑል ሀይሌ
👍9👏4
#እየጠበኩሽ_ነዉ

በሄድሽበት እንደ መንገድ
በቆምሽበት እንደ ጥላ
ንፁህ ነፍሴ ተከትላሽ
አንቺን አምና አንቺን ብላ
ሲመሽ ሲመሽ በህልሜ ላይ
ዘላለሜን እያየሁሽ
ተመልሼ ማልመልሰዉ
ሙሉ እድሜየን ያዉ ሰጠሁሽ

እየጠበኩሽ ነዉ...
በቸኮለዉ በዚህ ዘመን
መጣደፉ በበዛበት
አሁን አለ ያልነዉ ነገር
ትንሽ ቆይቶ በሌለበት
አንቺን የሚል የኔ ፍቅር
አንቺን የሚል የኔ አንደበት
ብቻ ፀንቶ ይጠብቃል
ዉብ ፍቅርሽን በቅንነት

እየጠበኩሽ ነዉ...
ደማቅ ፀሃይ ይሄዉ ገባች
ጨለማዉን አስከትላ
ብርቱ ክንዴን ሊፈትነዉ
የእድሜየ ጎርፍ ወንዙን ሞላ
በልጅነት ጨዋታችን
በዉሃ የተጫወቱ
ዉሃ አጣጬን ስጠብቅሽ
ትዳር ጎጆ መሠረቱ

እየጠበኩሽ ነዉ...
በመንገዱ ግራና ቀኝ
የበቀሉት አበባዎች
ቢራቢሮ የሚጠሩ
የልጅነት እምቡጥ መልኮች
ድንገት በፀሃይ ሳይደርቁ
ድንገት በንፋስ ሳይረግፉ
እንደጠበኩሽ ነይና
ከድካማቸዉ ይረፉ!!!
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ሰለሞን ሳህለ
👍202
#ተስፋሽን_ፈራሁት

የደጅሽ አበባ፣ እምቡጥ ሲይዝልሽ፤
የአንቀልባሽ ህጻን፣ ጠብቶ ሲያገሳልሽ፤
ደስታሽን አይቼ፤
ተስፋሽን ቃኝቼ፤
....................ነገሽን ፈራሁት

እምቡጥን የሚያመክን፣ አመዳይ ትላትል፣ ተምች በሞላበት፤
እምቡጥ የሚቀጥፍ፣ ሰው በሚኖርበት፤

.........በእኔና አንቺ አለም፤
ማንቦጥ መታጨት ነው፣
መውለድ መከተብ ነው፣
.........የዘላለም ሀዘን፣ የዘላለም ህመም።
          @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በድሉ ዋቅጅራ
👍7
የእግዛብሄር ዝምታ ሃቅ ያመላክታል
ሌላው ሌላው ጩኸት መንገድን ያስታል
ለጸሎትህ ምላሽ ለእንባህ ማበሻ
ከቃላት መልስ ይልቅ፤የእግዜርን ዝምታ በልቦናህ እሻ!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሚስጥረ አደራው
16👍3
#እኔ_እወድሻለው

ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ሚልዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ፡፡
እኔ እወድሻለው
የሠማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ጽጌረዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደሎሚ ሽታ፡፡
እንደ ከርቤ ብርጉድ
እንደ እጣን ጢስ እንጨት
ውዴ እወድሻለው አበባ እንዳየ ንብ፡፡
እንደቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ
በፍቅርሽ ልቅመሰው፡፡
ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኳር
አማርኛ አይበቃ
ወይ ጉድ
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር
እኔ እወድሻለው
እንደማታ ጀንበር
እንደጨረቃ ጌጥ
እንደ ተወራርዋሪ ኮከብ
እኔ እማልጠግብሽ
ስወድሽ ፤ስወድሽ፤ ስወድሽ ፤ስወድሽ ፡፡
ጡት እንዳየ ህጻን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነው፡፡
ጣይ ላይ እንዳለ ቅቤ
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው
አፈር መሬት ትቢያ ውሃ እንደሚበላው
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
እኔ እወድሻለው
አይኖችሽን ባይኔ ደጋግሜ እያየው
ስወድሽ ሰወድሽ
ውድ እወድሻለው፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገብረ ክርስቶስ ደስታ
👍11👏63
“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
  — ሉቃስ 2፥11።

እንኳን ለብርሐነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ❤️
12👍1
#ለምን_ነው_የተውኸኝ?

በሰደድ እሳት ውስጥ : እንደ መራመዴ
እንዴት አይሞቀኝም? ይቅርና መንደዴ።
ግግር በረዶ ላይ : በባዶ እግሬ ቆሜ
ለምን ያተኩሳል?  ሥጋዬ እና ደሜ ።
ሁሉም በወረፋው : ወር ተራ ሲደርሰው
እንደ ጉሊት ሸቀጥ  ፡  ክበህ ስታፈርሰው
በምን ሃጥያቴ ነው : የነጠልኸኝ ከሰው??
ምነው እኔ ብቻ?  ያለሁ በእርጋታ
ልድን እወዳለሁ : ማረኝ የኔ ጌታ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍19🔥53👏1
#ደቃቃ_ጎልያዶች

ምን ከንቱ ቢመስል ፥ ነገር ሲጀማምር
ንቀህ አትጣለው ፥ በውል ሳትመረምር።
ድራጎን አይደለም ፥ ዳይኖሰር፣ አንበሳ
ቁጭ ብድግ አርጎ ፥ ያሳየን አበሳ።
ባክቴርያና ቫይረስ ፥ ባይን የማናያቸው
የሰው ልጅ ደመኞች ፥ ጥቃቅኖች ናቸው።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍18🥰2
#የኗሪ_ታዛቢ!

ተይ በሏት ይችን ሰው፥ ምከሯት ትታረም
አጀብ አያሰኝም ፥ጅብ ካህያ መክረም!¡
ታግሼው ነው እንጂ!
እስስት አመልሽን ፥ ስታግለበልቢኝ
ፈርቼሽ አይደለም ፥ እንዳሻሽ ስትገልቢኝ።
ተቻችሎ መክረም!
አንቺ ትብሺ አንተ ፥
በሚል የጋራ ሀሳብ ፥ ፍቅር ካላሰረን
ቤታችን ፈረሰ፥ አውላላ ላይ ቀረን።
እወቂበት በቃ!
ማን የገነባውን ፥ ማን አፍርሶ ያልፋል
በመቻቻል ሲሆን ፥ የኔም ልብ ይሰፋል።
መቼስ ምን ይደረግ!
ጊዜ ላይቀይርሽ !
ታጥቦ ጭቃ አመልሽ ፥ ቀኔን እያስረጀው
(ትኖሪያለሽ እንጂ)
ባኗኗሪነት ነው ፥ እድሜዬን ምፈጀው።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ዳግም ህይወት
👏7👍4
#ቦክቶ_ተጋግሮ_ነው

ይሄ ሁሉ ችግር ይኼ ሁሉ ጣጣ፣
ምንጩ የሰው ልጅ ነው ከየትም አልመጣ፤
በዘመናት ክፋት በዘመናት እርሾ፣
ቦክቶ ተጋግሮ ነው ይኼ ሁሉ ቁርሾ፤
የሰው ልጅ መከራ እራሱ ሰው ሆኖ፣
መጥፊያውን ያበጃል በተንኮል ተክኖ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍1510👏5
15M dollar invest የተደረገበት Airdrop ነው አሰራሩ በጣም ቀላል ነው
https://sosovalue.com/join/QCCH7ZLW

ሊንኩን ስትነኩት ወደ website ይወስዳችኋል
ከዛ email and Password ታስገባላችሁ
Then ባስገባችሁት email የሚላክላችሁን Verification Code ስታስገቡ ጨረሳችሁ
#አትፅናኝ

ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።

አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።

በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መዘክር ግርማ
👍71👏1
#የፈጣሪ_ቅኔ

" አፈር ነበርክና ትሆናለህ አፈር "
እንዲል ቃለ-እግዚአብሔር
ጭቃ ቤት ውስጥ ሆኜ የማስበው ሁሉ
ከስንት ሰው አካል እንደተሰራ ነው
ግድግዳው በሙሉ፡፡

እግዜር ግን ሲገርም!!!

የተጠናወተው የሙስና አባዜ -
የሰው ባለ-ጊዜ
በእሳትና ሴራ
ፎቅ ቤቱን ሊሰራ
የድሆች ቤት ሲያፈርስ፣
ገበያ ሲያተራምስ፣
አንዳንዴም ሲያቃጥል
በሳት- እያጋየው፤
የነገው 'ራሱን በአሽሙር አሳየው፡፡
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አማኑኤል አለሙ
👍17👌41
አውቆ እንዳላወቀ ሰምቶ እንዳልሰማ ሰው
ያረገኝን ሁሉ በደሉን ስረሳው
እሱው ይከሰኛል እሱው ይወቅሰኛል
በኔ ችሎ ማለፍ ሞኝ ነህ ይለኛል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍187👏2🤬1
"#ግርማሞት"

በቡጢኞች ዘመን በካልቺኞች ዓለም
እንደ እንካ ሠላንቲያ ጣፍጦ ሚጥም የለም።
እኮ እንዴት ካላችሁ
ስሙኝ ልንገራችሁ።

በሠላምታ ነስቶ ነገርን ካከለ
ለጠብ መጠንሰሻ ወትሮስ ስድብ እንጂ
ሠላምታ መች አለ።

ዘማኒው ሰው ግን ጥል በእጅጉ የሻተው
እንካ ሠላንቲያን ፈጥሮ ሲፈላለጥ ኖረው።

ታዲያን ከዚህ በላይ ምን ነገር ይጥማል
በሠላም ሸፍኖ ለጠብ አሸጋግሮ ሺ-ፀብን
ይፈጥራል።

ታዲያን ከዚህ በላይ ምን ነገር ይጥማል
አሁንም መልሶ እንካ ሠላም ብሎ እርድናን ይተክላል።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መልአኩ ስብሐት ባይህ
👍31
#አታልቅስ_አትበሉኝ

አትሳቅስ በሉኝ
ግዴለም ከልክሉኝ፤
የፊቴን ፀዳል
አጠልሹት በከሰል፤ የግንባሬን ቆዳ
ስፉት በመደዳ፤
ጨጓራ አስመስሉት።
ግዴለም።
አትጫወት በሉኝ
ዘፈኔን ንጥቁኝ ግዴለም።
ብቻ ፤
አታልቅስ አትበሉኝ
አትጩህ አትበሉኝ ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍81👏1😁1
የውበትሽ ቅኔ ቢቋጠር ቢፈታ
ማረፊያው መርገፍ ነው የማታ የማታ
የዛሬው አጃቢ ተከታይ ከሗላሽ
መቼ ይፈልጋል ለማየት ከፊትሽ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍102👎2🥰2
#ፍርሀት_አዶከብሬ

ፍርሀት አዶከብሬ
አያ አይምሬ
የቁም መቃብሬ
የቅዠት ሀገሬ፡፡
ከስጋ ከነብሴ ከደሜ ቆንጥሬ     
     ከአጥንቴ ሰንጥሬ
ምስህን ሰጥቼህ ላመልህ ገብሬ
ያው ነህ አንተ ግና
ልጓምህ አይላላ፡፡
ትጋልበኛለህ በእሾህ በቆንጥር ላይ
ጨለማ እንደግራር በቅሎበት በሚታይ
አንዲት ዘሀ - ጮራ
     በማትደፍርበት
እውነት - ፍቅር - ውበት
      በተቀበሩበት፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍74🤔1
አህያ ሁን አለኝ : አህያ ሆንኩለት
አሰሱን ገሰሱን : እንድሸከምለት
መጋዣ ሁን ብሎ : ፈረሱ አደረገኝ
በየዳገቱ ላይ : ወስዶ እሚጋልበኝ
እንጃ ግን ሰሞኑን : በግ ነህ ተብያለሁ
ሊያርደኝ ነው መሰለኝ : አሁን ፈርቻለሁ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     
   ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
😁32👍54