ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#አደን

አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሣደድኳት።
ኗሪ ሆንኩኝ እንደፍየል
በነብርና በቅጠል መሀል።

አቤት አለች ያልጠራኀት
የጠራኀት ድምፅም የላት።
ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ ምላት ከኔ ርቃ።

አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
እረፍት አጥቼ ስባክን
የዕድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍86
#ስውር_ኃይል

ውሎ-ገባው መንገድ ፥ ልስልሱ ጎዳና
ቀናት ሲፈጅብኝ ፥ አይቶ ታዘበና ፣
የት ይወለድ እንጃ ፥ ከየትኛው ነገድ
ስንቅ አትያዝ አለኝ፥ አስበህ ለመንገድ።

እውነትም .... እውነትም
......... . ሐሰት የለበትም።
በጊዜ ደረስኹኝ ፥ ዘንድሮ ከአምና
እረሃብና ጥም ፥ ጊዜ አይሰጡምና።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍10😱1
#ስሞታ_አቀርባለው

በሚያላዝን ቀኔ ገጠመኝ አላውቅም
ለከበደኝ ለአይኔ ሽሙጥ አያምረኝም
ዳገቱን ብቆፍር ጥቅም አገኝ ብዬ
ከዘብጥያ ባድር እንደ ጥሬ እንሻፎ
ባልተማማልኩበት ትቢያ ስር ተጥዬ
ሽቅብ ስመለከት ህማሞቼን ጥዬ

ረግፎ ለታየው ለዚህ ስጋ ለባሽ
ጽዋውን ለቃኘው ለታዛቢው ቢጤ
እንክርዳዱን ቀማሽ…………………..

በደሌን ይቅር በል አስበኝ እያልኩኝ
የልብ ሀዘኔታ ብሶት እያስቃኘው
የክስመቴን ክፋይ ህሊና ቢቀልበው
ክፋት ሲከረፋ እምባ ጣሬን ላየው
ስሞታ አቀርባለው………………።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ኢያሱ ከበደ
6👍3🔥2
#ናፍቆት

ስጋዬን ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት
ቆዳዬን ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት
እፎይ አስታገስኩት
ፀጥ ረጭ አረኩት።
የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ
ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ
ምንም አላረኩት
ምንም አላከኩት
ላልችል ችየ ቻልኩት።
አልፎክተው ነገር፣ ቆዳዬን መንቅሬ
አላኝከው ነገር፣ ስጋዬን ሰርስሬ
ይኸው እስከዛሬ፣
አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ(ህ) ፍቅሬ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኑረዲን ዒሣ
👍145👏2
#ነጠብጣብ_ሐሳቦች

ሰማይ ከሚመክን ፤ይጸንስ መከራ
ያርግፍ ! ያርግፍ! ያርግፍ ! መኣት እያፈራ
የ’ሣት ዛፍ ባለበት ፤ ሰደድ አያስፈራ

ከሐምሌት ጋር ሞቷል፤ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፤ አለመሆን የለም
ሸክም ጸጋ ሆኗል፤ ጸጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ፤ ትከሻህን አስፋ!

አንድ ሕልም እንደ ጠጅ፤ እየደጋገሙ
ንግር ፤ትንቢት ሳይሆን፤ ታሪክ እያልለሙ
ተኝቶ መነሣት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሣት
ነፍሴን እንቆቅልሽ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዮም
4👍2
#መራራ_ናፋቂ

ቃሉን ተሸክሞ አብዝቶ እየዞረ
አቅፎት እየዋለ ታቅፎ እያደረ
ሳያነበው ውሎ ሳያነበው ነጋ
ተሸክሞት ብቻ ለይታ እየተጋ
መኖር እንጂ ከባድ ለቃሉ ተገዝቶ
ለመሸከምማ ሁሉም ይዟል ገዝቶ
ቃል ይዞ መዞሩ ልብን ካልሰበረ
ጥላቻን በፍቅር ከቶ ካልቀየረ
ለጭነት ለጭነት አህያ ይችላል
የተሸከመውን ሳይበላው ይኖራል
ማርን ተሸክሞ ሳር ይግጣል ከምድር
እንዲህ ነው ዘንድሮ እንዴው የእኛ ነገር
ጣፋጭ ተሸክመን መራራ ናፋቂ
በመሸከም ብቻ የምንመስል አዋቂ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍125👎2👏2
" የማይነጋ ህልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ህይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም። "
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
19👍13👎1
#ባላላጠሽ

ፀጉርሽ ጠልፎ ጣለኝ
ወድቄም ተነሳው
ዐይንሽ ጠቅሶ ጣለኝ
ወድቄም ተነሳው
መነሳቴ እንዳለ በጠጠር ተበሳው።

እኔም በተራዬ
ካንቺው ተከትዬ
በፀጉሬ እንዳልጥልሽ ፀጉሬ አጭር ነው
በጥቅሻ እንዳልጥልሽ ጥቅሻውን አላቀው።

ታዲያ በምን አቅሜ እንዴትስ ልጣልሽ
አምላክ በጥበቡ እሱ እንደፈጠረሽ
ጉልበታም አድርጎ በኔ እንዳስጀገነሽ
አሞሽ ከምጨነቅ እጅጉን ተጎድተሽ
በጣሙን ሳይበዛ ትንሽ ከፍ አድርጎሽ
ከዛም ከከፍታው ጥሎ ባላላጠሽ።
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሄኖክ_ብርሃኑ
8😁8👍5
#ማነው_ገላ_ሻጩ?

እሷ
ሰማይ ተደፍቶባት
ከሰማዩ በታች
ምድር ከእግሯ ርቋት
መኖር አይሉት ኑሮ
ኑራ የምታኖር
ባዶ ባደረ ሆድ
ባዶ ላደረ ሆድ
አልቅሳ ምታጎርስ
በእንባዋ ጠብታ
እንባን የምታብስ

እሱ
እምነቱን ገዝቶ
ውስጡን አሸብቶ
በሰከንዶች ስሜት
በሰከንድ ተገዝቶ
በጭኗ  ያረፈ
ማእበሉን በእንባዋ
ተሻግሮ ያለፈ
ከሱ ጋ ተዋግቶ
በሱ የተሸነፈ
ታድያ ማነው ገላ ሻጩ?
እራሱን አጉድሎ ጎዶሎን የሞላ
ወይስ
በራሱ ስር ወድቆ በጭኗ ያሽላላ።
     @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ፀጋየ ግርማ(ሜሎስ)
15👍6
#ቅመሱኝ

የብቻዬ ነገር ፣ በሌለባት አለም
ሚስትህን ተኛናት..
.........…......ቢሉኝም አይደንቅም
እንደ ንብ ካ’በባ ፣ ጫፋጩን ቀፍፎ
ምላሱን ለዋጀ ፣ ከማር አጠንፍፎ
ዝክር ለለመነ…
እንደ ጠበል ጠዲቅ ፣ ይሰጠዋል ድፎ
ሳይላስ በምላስ ፥ ለአይን'ኳ ሚጥም
ዳቦ እስካለ ድረስ ፥ .......ያጌጠ በቅመም
ለጉድ እየፈላ...
ቅመሱኝ ቅመሱኝ፥የሚል ወጥ አይጠፋም
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሚኪ እንዳለ
👍9
#በግራሽ_እቀፊኝ

ውዴ ሆይ ነይልኝ እንኩዋን ደህና መጣሽ
በጣም በርዶኝ ነበር ካጠገቤ ሳጣሽ
በይ እቅፍ አድርጊኝ ግራ እጅሽን ዘርጊ
ባይሆን ቀኝ እጅሽን ትንሽ ወደዛ አርጊ
ኡፍፍ...
በቀኝ መታቀፍ
እንዴት ነው የሚቀፍ?
እባክሽን ውዴ.....ያልኩሽን ሰምተሻል?
ቀኝሽን አርቂው ግራሽ ነው የሚሻል
በቀኝ እጅሽማ
ለስንቱ ጎረምሳ ሰላምታ ሰጥተሻል
የሰው ከጃይ ሁሉ የዘየረሽ መስሎ
ሲያልፍ አይቸዋለሁ ከመዳፍሽ መሃል ምኞት ቀልቡን ጥሎ::
ምን ይህ ብቻ ውዴ?
ከታሪክ ገፅ ላይ ብታተኩሪ አንዴ
ስንት ገራሚ እውነት ታገኝ የለም እንዴ
የያኔው ባለቀን :ለምዶበት ማቀንቀን
በቀኝ እጄ ሳቅፍህ
መንገድህ ይቀናል እያለ ሲያሞቀኝ
ውሎ ሳያድር ነው በቀኝ ሽብር መላ በወጠምሻ ክንዱ ጎኔን ያደቀቀኝ
ይሄኛውስ ቢሆን በእሱ የተተካው
ላክምልህ በሚል ከንቱ ፖለቲካው
ለስንቴ መሰለሽ እየተደበቀ ቁስሌን የሚነካው
ታዲያ በዚህ ዘመን
እነዚህን ሁሉ የቀኝ አቀንቃኞች ከልቡ እያመነ
በተናገሩት ቃል እየተማመነ
ከቤቱ የወጣ ቀኝ አውለኝ እያለ
ከአውላላ ሜዳ ላይ ቀረ እንደዋለለ::
እናልሽ ፍቅሬ ሆይ ይሄ ተሞክሮ
ልቤ ውስጥ ተቁዋጥሮ
እንኩዋንስ በቀኝ እጅ ልቀፍህ ተብዬ
"ቀ" የሚባል ፊደል ሲያልፍ በጆሮዬ
ቀማኛ
ቀበኛ
ቀጣፊ
ቀሳፊ...
የሚል የ"ቀ" ውላጅ
የክፉ አሳብ ጉማጅ
ባሳቤ እየመጣ
ጤናና ሰላሜን ባንዴ ነው የማጣ::
ስለዚህ ህይወቴ ከገባሽ ጭንቀቴ
በግራሽ እቀፊኝ አድምጭኝ በሞቴ
በግራ ጡትሽ ስር ካለው ትንሽ ኮዳ
ልብ የሚሉት ጉዋዳ
እኔ ጠጋ ስልሽ ነፍሴ ከነፍስሽ ጋር
ሽርክና መፍጠርዋን በድንገት ሲረዳ
ምን ያህል ጋሎን ደም ባንዴ እንደሚቀዳ።
የፍቅሬ ማእበል የልብሽን ባህር ስንቴ እንደሚንጠው
ሽጉጥ ልበልና በደንብ ላዳምጠው
ከግራ አጥንቶችሽ እስኪ ልበል ልክክ
ለመቁጠር እንድችል የትርታሽን ልክ!!
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ጋሻው ለኔ
19👍10
#ፍርሃትና_ናፍቆት

"ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ
"የመቅሰፍት ጊዜ! የመከራ ዘመን!"
"የት ደርሷል?" ስላቸው ፣
"ቀርቧል!" ብቻ እያሉኝ ፣
"መች ይመጣል?" ም ስል ፣
"ደርሷል!" ብቻ እያሉኝ ፣
ይኸው አርባ አመቴ ፣ በፍርሃት አለሁኝ ፣
ወይ ዘመኑ መጥቶ ደቁሶ አልደቆሰኝ ፣
ፍርሃቱ፣ ፍርሃቱ፣ ፍርሃቱ ገደለኝ

"ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ ፣
"የሰላም የደስታ - የጥጋብ ዘመን!"
"የት ደርሷል?" ስላቸው ፣
"ተቃርቧል!" እያሉኝ ፣
"መች ይመጣል?" ም ስል ፣
"ተዳርሷል!" እያሉኝ ፣
ይኸው አርባ ዓመቴ፣ በናፍቆት አለሁኝ ፣
ወይ ዘመኑ መጥቶ በደስታ አላሻረኝ ፣
ናፍቆቱ፣ ናፍቆቱ፣ ናፍቆቱ ገደለኝ ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ
👍228👏1
#ቢጥፉት_ቢጥፉት

የተላበሱትን
ላይጥሉት አውልቀው
ቢጥፉት፣ቢጥፉት
መቀደዱን ዓይተው
      ዲሪቶን ቢደርቱት
ደጋግመው ቢጥፉት
አጋልጦ ይሰጣል
በአዲስ ካልቀየሩት
       እንደው ላይከርሙበት
      በመጣፌያ ጥፎ
     ገበና ላይሸፍን
      ሊሰጥ  አሳልፎ፡፡
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ግዛቸው ማሞ
5👎3👍1
#ነብስ_ይማር

አትጠብቁ ከቶ፣
ቀጠሮ አትያዙ ለዋይታ ለልቅሶ
ካፈር እስክገባ ጉዱጓዴ ተምሶ!

በፊቴ አፍስሱልኝ የወዳጅ እንባውን
ባንገቴ አጥልቁልኝ ጉንጉን አበባውን፣

ብርሃን ሲያኮበኩብ
ፅልመትም ሲያንዣብብ፣
ቀኔን ነጥቆኝ ሊሮጥ ሌቱ ሲንደረደር
ነብስ ይማር ነው እንጂ አትበሉኝ ደና 'ደር!
የ'ድሜ ሽኝት ሐውልት የለት ተለት ሞቴ
የመቃብር ላይ ፁፍ ጥቅስ ናት ህይወቴ!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍123🥰1
በጣም ትልቅ የተባለ የ website airdrop ልጠቁማችሁ

One FootBall Season 2 ላይ ነው  season 1 ተጠናቋል ነገር ግን አረፈደም አሁንም መስራት ትችላላችሁ

TGE Is Set To Be In Q1 2025.(የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ )

Backed By Adidas 🔥And Animoca🔥
raised 400+ million dollar🔥

✔️ምንም አይነት ወጭ ማውጣት አይጠበቅባችሁም

ለመጀመር
https://ofc.onefootball.com/s2?referral=a3evCNHQG7f9

➡️በመቀጠል Connect Wallet አድርጉ (metamask , phantom , trust wallet )

➡️ ያሉትን ሶስት ታስኮች አጠናቁ Balls ሰብስቡ

ትልቅ ፕሮጀክት ነው guys በደንብ ስሩ በእርግጠኝነት ጥሩ ታገኛላችሁ 🔥🔥
👍5
ሰማዩ መጅ
ምድሩ ወፍጮ
አተር ነፍሴ፣ እማህል ላይ ተንገርጭጮ
ቅጤ ቅርሴ ሲፈራርስ፣
"ኅጢያቴ ነው " ?፣ ልበል ላልቅስ?
"እቅዱ ነው"፣ ልበል ወይስ
እርዳኝ ብዬ ፀሎት ላድርስ?
በላይ በታች፣ መንትያ ጥርስ
አተር ነፍሴ፣ ሲፈራርስ
"አሜን" ልበል ወይ "አያድርስ"?
 @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ረድኤት አሰፋ
👍121
#ለምን_ሞተ_ቢሉ

ለምን ሞተ ቢሉ
ንገሩ ለሁሉ
ሳትደብቁ ከቶ፤
“ከዘመን ተኳርፎ
ከዘመን ተጣልቶ"፡፡
@gitm_post
  ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
 ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
🔥113👍3😴2
#ስደቢኝ_ግድየለም

ስደቢኝ ግድየለም አልቀየምሽም
ደደብ የማትረባ አህያ ነህ ቀሽም
ሲጠሉህ የማታውቅ እልም ያልክ ፋራ
ልክስክስም በይኝ አስቀያሚ ጭፍራ
ከፈለግሽ ደግሞ ደሀ ለቃቃሚ
ብትይኝ ግድየለም እባክሽን ስሚ

ከስድቦችሽ መሀል መልካሙን እያየሁ
ፋራ በመሆኔ እጅጉን እኮራለው
አህያ ላልሺኝ ደግሞ አንቺን ተሸክሜ
እስከዛሬ አለሁ ይሄውልሽ ህመሜ

ደሀ ነህ ብለሻል ደሀ ነኝ አውቃለው
ሀብታም ስላልሆንኩኝ አመሰግናለው
ምናልባት ግን ሆዴ.....
ገንዘብ ኖሮኝ እኔ በሀብቴ ብኮራ
ስድብሽን ሰምቼ እለይሽ ነ'በራ
ሁሉን ያጣ ሆኜ ብትይኝ ውዳቂ
እንደማልጠላሽ ግን አሁንም እወቂ፡፡
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ-መድህን
24👍8👏2
#የቀበሮ_ፀሎት

እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ
ታገል ሰይፉ
👍1610
ልብሽ ከወደደኝ በይኝ ወድካለሁ
ያው እድለኛ ነሽ መውደድ መታደል ነው።
                   
ካልወደድሺኝ ደሞ ውስጥሽ አያመንታ
ፍቅር በፍቅር እንጂ ሲሆን በይሉኝታ
ፍሬ መች ያፈራል የማታ የማታ።
                                          
ግን እየወደድሺኝ አትበይ አልወድክም
ስሜትን በማፈን ጎጆ ፀንቶ አያውቅም።
                                          
ሳትወጂኝም ደሞ አትበይ ወድካለሁ
ይህንም ታውቂያለሽ ...
ማስመሰል ካረጀ ጧሪ ዘመድ የለሁ።
                                         
እናም እኔ ዛሬ ላንቺው ሹክ የምልሽ
አልስማማ ብለው አፍሽና ልብሽ
ቡጢ ተጨባብጠው ከፀፀት ሳይጥሉሽ
ጎጆሽ እንዲቃና ፍቅር ተረብርቦ
ጥሪና አስማሚያቸው .....
ልብሽን ካራምባ አፍሽን ከቆቦ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሄኖክ ብርሀኑ
👍21
#የመጀመሪያ_ቀን

አየችው ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆው ተጋጨ
አየችው ተያዩ
አያት ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው
አየችው ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ
ታፋቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ገብረ ክርስቶስ ደስታ
👍152