ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#እንዲያው_ዝም

ወድሻለሁ ማለት አይጠቅም አይበቃ፤
ፍቅሬ ነሽ ማለትም አይጠቅም አይበቃ !
ነፍሴ ነሽ ማለትም ልቤን አያርሰው 
የፍቅራችን' ነገር ዝም ነው ዝም ነው ።

ምን ላርገው መውደዴን ለመግለጽ በሙሉ?
ልሳምሽ ልቀፍሽ ፤ ላልቅስ ወይ ላመሉ ?

እግርሽን' ልሳም ወይ ፤ ልስገድልሽ ወይ?
ዓዋጅ ልናገረው ፡ በያደባባይ?
ወረቀት ልጻፍ' ወይ ፤ ልላክ' ወይ' ደብዳቤ ፡ እያንዳንዱን ቃላት ወልጄ ከልቤ!
ገንዘቤን ልስጥሽ ወይ ላይቆጨኝ መክሰሬ?
ልታረድ ልሰዋ ለፍቅርሽ ለፍቅሬ?

ይህ ሁሉ ከንቱ ነው
የልብ' አያደርስም።
በቃል' ወይ' በሥራ ፍቅር አይገለጽም።
ይሻላል መሰለኝ እንዲያው ዝም እንዲያው ዝም፤
እንዲያው በደፈና እንደ ሃይማኖት
ፍቅሬን ማወቅሽን ማመን መረዳት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መንግስቱ ለማ
👍8👏1
#የት_ነበሩ?!!

ይታየናል ባዮች ሳይበቁ የበቁ
መከራ ሲመጣ እንዴት አላወቁ?
የዘመን ነብያት ትንቢት ተናጋሪ
የቤት የመኪናው ሲደርሳቸው ጥሪ
ምነው ሰው ማለቁን ያልነገሩን ቀድመው?
በለመዱት ድፍረት አምላክን አናግረው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏13👍6
#ሐዘንሽ_አመመኝ

ውል አልነበረንም የፍቅር ቀጠሮ
ቃልም አላኖርንም በወግ ተቀምሮ፤
እኔ አንቺን እንዳላይ
አንቺ እኔን እንዳታይ አምባችን ተቃጽሮ
ዕጣችን ተካሮ፤
ቀለምሽ ከዐይኔ አሻራሽ ከጣቴ ባይጠፋ ተማትሮ
(እትብት እምብርት ሁኖ እንዲኖር ደድሮ)
ይኸው አካሄደን በድንገት ዘንድሮ።
የገጽሽ ብርሃን ቢጠይም ፀዳሉ
ድምፅሽ ቢቀጥንብኝ ቢሠልብኝ ቃሉ
ወዘናሽ ቢማስን ዛሬ ያለውሉ
በእጆችሽ ጨበጠኝ ሐዘንሽ ሥዕሉ
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጀንበር ነሽ አበባ ሕይወት ተስፋ ዘቦ
ፋሲካ ዕንቁጣጣሽ ማኅሌተ ገንቦ
ብዬ ያወደስኩበት ታዘበኝ ዘመኔ የትላንታት ቀኔ
ዛሬ ሊጮህብኝ ቅኔ እንዳይደል እውኔ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
የገደል ማሚቶን ታዘብኳት ተኝታ
በጩኽትሽ ማየል አኩርፋና ታክታ
ላንቃዋ ይታየኛል ደም ለብሶ ደም ጐርሶ
ቃልሽ ያለፈበት በጭንቅ ተለውሶ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
ጽጌሬዳይቱ ንቦችሽ አለቁ ሰዎችሽ ደቀቁ
ጨፌ ላይ ተኝተው ባድማ ላይ ነቁ፤
ዐዋይን ሰማኋት ስታለቅስ በይፋ
ከጐጆሽ ስትወጣ ትቢያዋን አራግፋ፤
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
አላውቅልሽ ብዬ አታውቂልኝ ብዬ
እምነትሽን ጥዬ ፍቅርሽን ገድዬ
አኩርፌሽ ስቀመጥ ያው እንደ ባላንጣ
ይኸው ነጭ ማተብሽ ሊያስታርቀን መጣ፤
ሐዘን ነው ውበትሽ ውበት ነው ፍቅርሽ
ብርሃን – ጥለት አልቦ ከል ነጠላሽ
ዐይኔን የገለጠው ጥቁር ጨለማሽ፤…
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ፦ ደበበ ሰይፉ
👍11👏2
#ከአዳም_ያልመጣ

ለወንድና ለሴት ለአዳም ልጆች
ሔዋን በበኩሏ እናታቸው ነች
      ብለን ብንገምት ብንገመግም
      አዳምና ሔዋን በአገኙት መርገም
አዳም እርሻውን ሲያርስ ሔዋን ስትፈትል
ማን ነበረች ልዕልት ማን ነበረ ልዑል
      መኳንንት መሳፍንት ከየት ተፈጠሩ
      ከአዳም ያልመጣ ግንዱስ የትነው ዘሩ?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ደራሲ ታደለ ብጡል
👍13
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጎጅሽን_በማፍቀር

ልብ ሳትመዝኝ በምላስ እያመንሽ
ከሰው ተራ ወጣሽ ስታምኝ ሲከዱሽ
ወደንሻል ሲሉሽ በምላስ ጋጋታ
ቆመሽ ማገናዘብ አቅቶሽ ለአንድ አፍታ
በስሜት ገስግሰሽ በህልም ዓለም ስካር
አፍቃሪሽን ጎድተሽ ጎጅሽን በማፍቀር
በከንቱ ባከነ ምድራዊ ውበትሽ
ልብ ቀርቶ ምላስ እሺ በማለትሽ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍17👏52
#የተካደ_ትውልድ

የተካደ ትውልድ
አይዞህ ባይ የሌለው፣
ታዳጊ የሌለው፡
ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው፡
ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤

የተካደ ትውልድ

አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ
ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ
እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት
አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤
ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍት የተቀማ
አልጋው ያጋም እሾህ፥ ምኝታው የሳማ፤

የተካደ ትውልድ

ሞቶ እንኳን ሬሳው፥ አይላላለት ቀንበር
በዘብ እጅ ተገድሎ ፥ በሹም የሚቀበር
ከጡት አስጥል በላይ፥ ኑሮ የመረረው
እንዳይሄድ ጎዳናው ፥ የተደናገረው
ድል ያልሰመረለት ፥ትግል ሳይቸግረው።

የተካደ ትውልድ
በስጋ በነፍሱ
በቀልቡ በገላው
ከቶ ምንድን ይሆን?
ምንድን ይሆን መላው?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ_ስዩም
👍135👏2
#ሳይፀልዩ_ማደር

የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋዋ ፀለየች አውጣኝ አውጣኝ አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ
አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ ሚዳቋዋን አይቶ
ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ

የሁለቱም  አምላክ  የሁላችን ሰሪ
ፀሎታቸውን ሠማቸው ፈጣሪ

አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት
እሩጠሽ አምልጪ ከበረታ ጠላት
ነብሩንም አለው እሩጥ ተከተላት ምግብ አርገክ ብላት
ሚዳቆዋም ስትሮጥ ከነብሩ ለማምለጥ
ነብሩም ሢከተላት ሆዱን ሊሞላባት

ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተሥፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛ ከርከሮ

ከንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር

አውጣኝ ያለው ወቶ አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው ከርከሮ ተበላ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   በረከት በላይነህ
👍338
#ያገረሸ_ፍቅር

የሰማይ አሞራ
ላዋይህ ችግሬን
ብረር ሂድ ንገራት
ከትልቁ ዛፍ ሥር
ድሮ በልጅነት
ከተጨዋትንበት
ከትልቁ ዛፍ ሥር አታጣትም ፍቅሬን
ብረር ሂድ ንገራት ንገር መናፈቄን፡፡
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገብረ ክርስቶስ ደስታ
6
#መርፌና_ቀዳዳ_ነጠላ

አንድ ቀን ስላየች ተቀዶ ነጠላ፣
የተለያየውን ልገጣጥመው ብላ፣
መርፌ ቀረብ አለች ምላሷን አሹላ፡፡
ነጠላ ግን አለ በየዋህነቱ፤
“የብረት ልጅ መርፌ አዬ ሹል አፊቱ
ከማሰብሽ በፊት እኔ እንዳልጎዳ
መድፈን ነበረብሽ የራስሽን ቀዳዳ፡፡”
እንዲህም መለሰች መርፌ ለነጠላ፤
“ወንድሜ ነጠላ ሞኝ ነህ ተላላ
ባይታይህ እንጂ እውነተኛው ፍርድ
አንተን ለመጥቀም ነው የእኔ መቀደድ፡፡”
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
        አቤ ጉበኛ
👍15👏61
#አደን

አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሣደድኳት።
ኗሪ ሆንኩኝ እንደፍየል
በነብርና በቅጠል መሀል።

አቤት አለች ያልጠራኀት
የጠራኀት ድምፅም የላት።
ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ ምላት ከኔ ርቃ።

አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
እረፍት አጥቼ ስባክን
የዕድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደበበ ሰይፉ
👍86
#ስውር_ኃይል

ውሎ-ገባው መንገድ ፥ ልስልሱ ጎዳና
ቀናት ሲፈጅብኝ ፥ አይቶ ታዘበና ፣
የት ይወለድ እንጃ ፥ ከየትኛው ነገድ
ስንቅ አትያዝ አለኝ፥ አስበህ ለመንገድ።

እውነትም .... እውነትም
......... . ሐሰት የለበትም።
በጊዜ ደረስኹኝ ፥ ዘንድሮ ከአምና
እረሃብና ጥም ፥ ጊዜ አይሰጡምና።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍10😱1
#ስሞታ_አቀርባለው

በሚያላዝን ቀኔ ገጠመኝ አላውቅም
ለከበደኝ ለአይኔ ሽሙጥ አያምረኝም
ዳገቱን ብቆፍር ጥቅም አገኝ ብዬ
ከዘብጥያ ባድር እንደ ጥሬ እንሻፎ
ባልተማማልኩበት ትቢያ ስር ተጥዬ
ሽቅብ ስመለከት ህማሞቼን ጥዬ

ረግፎ ለታየው ለዚህ ስጋ ለባሽ
ጽዋውን ለቃኘው ለታዛቢው ቢጤ
እንክርዳዱን ቀማሽ…………………..

በደሌን ይቅር በል አስበኝ እያልኩኝ
የልብ ሀዘኔታ ብሶት እያስቃኘው
የክስመቴን ክፋይ ህሊና ቢቀልበው
ክፋት ሲከረፋ እምባ ጣሬን ላየው
ስሞታ አቀርባለው………………።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ኢያሱ ከበደ
6👍3🔥2
#ናፍቆት

ስጋዬን ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት
ቆዳዬን ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት
እፎይ አስታገስኩት
ፀጥ ረጭ አረኩት።
የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ
ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ
ምንም አላረኩት
ምንም አላከኩት
ላልችል ችየ ቻልኩት።
አልፎክተው ነገር፣ ቆዳዬን መንቅሬ
አላኝከው ነገር፣ ስጋዬን ሰርስሬ
ይኸው እስከዛሬ፣
አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ(ህ) ፍቅሬ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኑረዲን ዒሣ
👍145👏2
#ነጠብጣብ_ሐሳቦች

ሰማይ ከሚመክን ፤ይጸንስ መከራ
ያርግፍ ! ያርግፍ! ያርግፍ ! መኣት እያፈራ
የ’ሣት ዛፍ ባለበት ፤ ሰደድ አያስፈራ

ከሐምሌት ጋር ሞቷል፤ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፤ አለመሆን የለም
ሸክም ጸጋ ሆኗል፤ ጸጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ፤ ትከሻህን አስፋ!

አንድ ሕልም እንደ ጠጅ፤ እየደጋገሙ
ንግር ፤ትንቢት ሳይሆን፤ ታሪክ እያልለሙ
ተኝቶ መነሣት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሣት
ነፍሴን እንቆቅልሽ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዮም
4👍2
#መራራ_ናፋቂ

ቃሉን ተሸክሞ አብዝቶ እየዞረ
አቅፎት እየዋለ ታቅፎ እያደረ
ሳያነበው ውሎ ሳያነበው ነጋ
ተሸክሞት ብቻ ለይታ እየተጋ
መኖር እንጂ ከባድ ለቃሉ ተገዝቶ
ለመሸከምማ ሁሉም ይዟል ገዝቶ
ቃል ይዞ መዞሩ ልብን ካልሰበረ
ጥላቻን በፍቅር ከቶ ካልቀየረ
ለጭነት ለጭነት አህያ ይችላል
የተሸከመውን ሳይበላው ይኖራል
ማርን ተሸክሞ ሳር ይግጣል ከምድር
እንዲህ ነው ዘንድሮ እንዴው የእኛ ነገር
ጣፋጭ ተሸክመን መራራ ናፋቂ
በመሸከም ብቻ የምንመስል አዋቂ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ስንታየሁ ሀብታሙ
👍125👎2👏2
" የማይነጋ ህልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ህይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም። "
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
19👍13👎1
#ባላላጠሽ

ፀጉርሽ ጠልፎ ጣለኝ
ወድቄም ተነሳው
ዐይንሽ ጠቅሶ ጣለኝ
ወድቄም ተነሳው
መነሳቴ እንዳለ በጠጠር ተበሳው።

እኔም በተራዬ
ካንቺው ተከትዬ
በፀጉሬ እንዳልጥልሽ ፀጉሬ አጭር ነው
በጥቅሻ እንዳልጥልሽ ጥቅሻውን አላቀው።

ታዲያ በምን አቅሜ እንዴትስ ልጣልሽ
አምላክ በጥበቡ እሱ እንደፈጠረሽ
ጉልበታም አድርጎ በኔ እንዳስጀገነሽ
አሞሽ ከምጨነቅ እጅጉን ተጎድተሽ
በጣሙን ሳይበዛ ትንሽ ከፍ አድርጎሽ
ከዛም ከከፍታው ጥሎ ባላላጠሽ።
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሄኖክ_ብርሃኑ
8😁8👍5
#ማነው_ገላ_ሻጩ?

እሷ
ሰማይ ተደፍቶባት
ከሰማዩ በታች
ምድር ከእግሯ ርቋት
መኖር አይሉት ኑሮ
ኑራ የምታኖር
ባዶ ባደረ ሆድ
ባዶ ላደረ ሆድ
አልቅሳ ምታጎርስ
በእንባዋ ጠብታ
እንባን የምታብስ

እሱ
እምነቱን ገዝቶ
ውስጡን አሸብቶ
በሰከንዶች ስሜት
በሰከንድ ተገዝቶ
በጭኗ  ያረፈ
ማእበሉን በእንባዋ
ተሻግሮ ያለፈ
ከሱ ጋ ተዋግቶ
በሱ የተሸነፈ
ታድያ ማነው ገላ ሻጩ?
እራሱን አጉድሎ ጎዶሎን የሞላ
ወይስ
በራሱ ስር ወድቆ በጭኗ ያሽላላ።
     @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ፀጋየ ግርማ(ሜሎስ)
15👍6
#ቅመሱኝ

የብቻዬ ነገር ፣ በሌለባት አለም
ሚስትህን ተኛናት..
.........…......ቢሉኝም አይደንቅም
እንደ ንብ ካ’በባ ፣ ጫፋጩን ቀፍፎ
ምላሱን ለዋጀ ፣ ከማር አጠንፍፎ
ዝክር ለለመነ…
እንደ ጠበል ጠዲቅ ፣ ይሰጠዋል ድፎ
ሳይላስ በምላስ ፥ ለአይን'ኳ ሚጥም
ዳቦ እስካለ ድረስ ፥ .......ያጌጠ በቅመም
ለጉድ እየፈላ...
ቅመሱኝ ቅመሱኝ፥የሚል ወጥ አይጠፋም
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሚኪ እንዳለ
👍9
#በግራሽ_እቀፊኝ

ውዴ ሆይ ነይልኝ እንኩዋን ደህና መጣሽ
በጣም በርዶኝ ነበር ካጠገቤ ሳጣሽ
በይ እቅፍ አድርጊኝ ግራ እጅሽን ዘርጊ
ባይሆን ቀኝ እጅሽን ትንሽ ወደዛ አርጊ
ኡፍፍ...
በቀኝ መታቀፍ
እንዴት ነው የሚቀፍ?
እባክሽን ውዴ.....ያልኩሽን ሰምተሻል?
ቀኝሽን አርቂው ግራሽ ነው የሚሻል
በቀኝ እጅሽማ
ለስንቱ ጎረምሳ ሰላምታ ሰጥተሻል
የሰው ከጃይ ሁሉ የዘየረሽ መስሎ
ሲያልፍ አይቸዋለሁ ከመዳፍሽ መሃል ምኞት ቀልቡን ጥሎ::
ምን ይህ ብቻ ውዴ?
ከታሪክ ገፅ ላይ ብታተኩሪ አንዴ
ስንት ገራሚ እውነት ታገኝ የለም እንዴ
የያኔው ባለቀን :ለምዶበት ማቀንቀን
በቀኝ እጄ ሳቅፍህ
መንገድህ ይቀናል እያለ ሲያሞቀኝ
ውሎ ሳያድር ነው በቀኝ ሽብር መላ በወጠምሻ ክንዱ ጎኔን ያደቀቀኝ
ይሄኛውስ ቢሆን በእሱ የተተካው
ላክምልህ በሚል ከንቱ ፖለቲካው
ለስንቴ መሰለሽ እየተደበቀ ቁስሌን የሚነካው
ታዲያ በዚህ ዘመን
እነዚህን ሁሉ የቀኝ አቀንቃኞች ከልቡ እያመነ
በተናገሩት ቃል እየተማመነ
ከቤቱ የወጣ ቀኝ አውለኝ እያለ
ከአውላላ ሜዳ ላይ ቀረ እንደዋለለ::
እናልሽ ፍቅሬ ሆይ ይሄ ተሞክሮ
ልቤ ውስጥ ተቁዋጥሮ
እንኩዋንስ በቀኝ እጅ ልቀፍህ ተብዬ
"ቀ" የሚባል ፊደል ሲያልፍ በጆሮዬ
ቀማኛ
ቀበኛ
ቀጣፊ
ቀሳፊ...
የሚል የ"ቀ" ውላጅ
የክፉ አሳብ ጉማጅ
ባሳቤ እየመጣ
ጤናና ሰላሜን ባንዴ ነው የማጣ::
ስለዚህ ህይወቴ ከገባሽ ጭንቀቴ
በግራሽ እቀፊኝ አድምጭኝ በሞቴ
በግራ ጡትሽ ስር ካለው ትንሽ ኮዳ
ልብ የሚሉት ጉዋዳ
እኔ ጠጋ ስልሽ ነፍሴ ከነፍስሽ ጋር
ሽርክና መፍጠርዋን በድንገት ሲረዳ
ምን ያህል ጋሎን ደም ባንዴ እንደሚቀዳ።
የፍቅሬ ማእበል የልብሽን ባህር ስንቴ እንደሚንጠው
ሽጉጥ ልበልና በደንብ ላዳምጠው
ከግራ አጥንቶችሽ እስኪ ልበል ልክክ
ለመቁጠር እንድችል የትርታሽን ልክ!!
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ጋሻው ለኔ
19👍10