ሳቅ እንኳን ባትፈቅዱ ማልቀስ አትከልክሉ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰18👏6👍3
#ኮረዳ
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
❤13👍7👏4
#የምጡ_ጅማሬ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍20❤5🥰5🔥3👏3
ዓለም ቅንዝረኛ ብዙ ባል አግብታ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
🥰11👍7🏆1
#ችግር
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍13
#የተቃርኖ_ሕግ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍9
#ፍቅር_ወረተኛ
ፍቅር እንደሞት ጥላ በድን አደረገኝ
አጥንቴን ሰበረው ከቶ አዝለፈለፈኝ
ፍቅር በአበባው መዓዛው ጣፈጠኝ
አሁን ግን ጠውልጎ ሽታው አሰለቸኝ
የፍቅር ክፋቱ ትዝታ ነው ሲሉ
አላመንኩም ነበር ውሸት በመምሰሉ
አሁን ግን አወቅሁት ይሰማኛል ቁስሉ
የነደፈኝ መርዙ የወጋኝ ሾተሉ
ይህ ጣፋጭ እንደማር መራር እንደኮሶ
ልፍስፍስ እንደጥጥ ጥብቅ ከምሰሶ
ዛሬ ህይወት አለው ነገ ይቀራል ፈርሶ
ፍቅርን አትመኑት ቢታይ ድርብ ለብሶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ፍቅር እንደሞት ጥላ በድን አደረገኝ
አጥንቴን ሰበረው ከቶ አዝለፈለፈኝ
ፍቅር በአበባው መዓዛው ጣፈጠኝ
አሁን ግን ጠውልጎ ሽታው አሰለቸኝ
የፍቅር ክፋቱ ትዝታ ነው ሲሉ
አላመንኩም ነበር ውሸት በመምሰሉ
አሁን ግን አወቅሁት ይሰማኛል ቁስሉ
የነደፈኝ መርዙ የወጋኝ ሾተሉ
ይህ ጣፋጭ እንደማር መራር እንደኮሶ
ልፍስፍስ እንደጥጥ ጥብቅ ከምሰሶ
ዛሬ ህይወት አለው ነገ ይቀራል ፈርሶ
ፍቅርን አትመኑት ቢታይ ድርብ ለብሶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍17🔥2❤1🥰1
#ፍቅርን_ባይተካም
ይታሰር ቀለበት ቃልን ያስታውሳል
ፍቅርን ባይተካም አጥፊን ይታዘባል
ፍቅርን ጠፍሮ አስሮ ባይጠብቅም
የጎደለን እምነት ሰፍሮ ባይመልስም
ይታሰር ቀለበት አጥፊን ያሳቅቃል
በወለቀ ቁጥር ህሊናን ይከሳል
ሐይል ባይኖረውም ክህደትን ለማስቆም
አንደበት አውጥቶ ለፍርድ ባያቀርብም
ቃል እያስታወሰ አጥፊን እንዲቀጣ
ከቦርሳና ከኪስ ሲገባ ሲወጣ
ህሊናን አድምቶ በደልን ይናገር
ይደረግ ቀለበት ከጣት ላይ ይታሰር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ይታሰር ቀለበት ቃልን ያስታውሳል
ፍቅርን ባይተካም አጥፊን ይታዘባል
ፍቅርን ጠፍሮ አስሮ ባይጠብቅም
የጎደለን እምነት ሰፍሮ ባይመልስም
ይታሰር ቀለበት አጥፊን ያሳቅቃል
በወለቀ ቁጥር ህሊናን ይከሳል
ሐይል ባይኖረውም ክህደትን ለማስቆም
አንደበት አውጥቶ ለፍርድ ባያቀርብም
ቃል እያስታወሰ አጥፊን እንዲቀጣ
ከቦርሳና ከኪስ ሲገባ ሲወጣ
ህሊናን አድምቶ በደልን ይናገር
ይደረግ ቀለበት ከጣት ላይ ይታሰር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
❤13👏2
#ገንዘብ
ድሀ ከሀብታም ሰው የሚለይበት
በገንዘብ መሆኑ እውነት ነው ውሸት?
እውነት ይሆን ውሸት እንደዚህ መባሉ
ገንዘብ ከመሰብሰብ መበተን መቅለሉ
እውነት ይሆን ውሸት ደሀው ሰው ሲራብ
የሀብታም ፍላጎት መቆጠብ ከምግብ
እውነት ይሆን ውሸት ዕዳ ከሌለበት
ድሀ ሰው ካብታሙ እኩል የሆነበት
እንዲያው በደፈናው የሆነውን ሆኖ
ምነው ገንዘብ ቢኖር ከሁሉም ተዋስኖ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ድሀ ከሀብታም ሰው የሚለይበት
በገንዘብ መሆኑ እውነት ነው ውሸት?
እውነት ይሆን ውሸት እንደዚህ መባሉ
ገንዘብ ከመሰብሰብ መበተን መቅለሉ
እውነት ይሆን ውሸት ደሀው ሰው ሲራብ
የሀብታም ፍላጎት መቆጠብ ከምግብ
እውነት ይሆን ውሸት ዕዳ ከሌለበት
ድሀ ሰው ካብታሙ እኩል የሆነበት
እንዲያው በደፈናው የሆነውን ሆኖ
ምነው ገንዘብ ቢኖር ከሁሉም ተዋስኖ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍11❤1
#የሌቦች_እቁብ!!
ሌቦች ተሰባስበው እቁብ መሰረቱ
ሰብሳቢ ለመምረጥ እጅግ ተሟገቱ
ማንስ ማንን ይመን የመንታፊ መንጋ
አንድ ታማኝ ጠፍቶ አስመሳይ ቢንጋጋ
ውሸታም በጋራ እድር ቢመሰርት
መኖሩም ውሸት ነው መሞቱም የሐሰት
ሀይማኖት ቢበዛ በስም ተለያይቶ
አማኝ ሳይኖርበት የስም አሜን በዝቶ
በምላስ ማሞገስ በልብ ግን መርከስ
በማስመሰል ዜማ የውሸት መደገስ
ባልዘነበ ዝናብ በዘር ጎርፍ መበስበስ
በግም ፖለቲካ ቅዱሱ ሰው ሲረክስ
እንዴት ኢትዮጵያችን እንደጥንቱ ትንገስ
ቆመን እያወደስን የነበረው ሲፈርስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ሌቦች ተሰባስበው እቁብ መሰረቱ
ሰብሳቢ ለመምረጥ እጅግ ተሟገቱ
ማንስ ማንን ይመን የመንታፊ መንጋ
አንድ ታማኝ ጠፍቶ አስመሳይ ቢንጋጋ
ውሸታም በጋራ እድር ቢመሰርት
መኖሩም ውሸት ነው መሞቱም የሐሰት
ሀይማኖት ቢበዛ በስም ተለያይቶ
አማኝ ሳይኖርበት የስም አሜን በዝቶ
በምላስ ማሞገስ በልብ ግን መርከስ
በማስመሰል ዜማ የውሸት መደገስ
ባልዘነበ ዝናብ በዘር ጎርፍ መበስበስ
በግም ፖለቲካ ቅዱሱ ሰው ሲረክስ
እንዴት ኢትዮጵያችን እንደጥንቱ ትንገስ
ቆመን እያወደስን የነበረው ሲፈርስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤10👏9👍6🫡2
#ናፍቆት
መለሎ ቁመናሽ ቀጭን ወገብሽ
ኮራ ያለ ዳሌሽ ጉች ጉች ጡትሽ
ኧረ እንዴት ከረሙ አንችስ ደህና ነሽ?
እኔ በበኩሌ በጣም ደህና ነኝ
ግን ለደብዳቤዬ መልስ ሳላገኝ
ባነቺ ናፍቆት ብቻ ሞቼ እንዳትቀብሩኝ
ቢሮዬ ስገባ ስብሰባ ስቀመጥ
አሳቤ ኮብሎ ወዳንቺ ዘንድ ሲሮጥ
ሥጋቴ በዛና ጀመርኩኝ መደንገጥ
በሰው በደብዳቤ የላክሁት መልዕክት
ደርሶሽ ነው ዝም ያልሽው ወይስ ረሱት
እኔ እምሰቃየው በዝናሽ መጥፋት
ከፋም ተናግሬሽ በነገር መሐል
አስቀይሜሽ ከሆንኩ ፈጽሜ በደል
ባይሆን ለይቅርታሽ ካሳውን ልክፈል
ይቅር ግድ የለኝም ያለፈውስ ይለፍ
በሽታ እንዳይዘኝ አብጄም እንዳልከንፍ
ለዚች ለደብዳቤ ቶሎ መልስሽ ይጻፍ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
መለሎ ቁመናሽ ቀጭን ወገብሽ
ኮራ ያለ ዳሌሽ ጉች ጉች ጡትሽ
ኧረ እንዴት ከረሙ አንችስ ደህና ነሽ?
እኔ በበኩሌ በጣም ደህና ነኝ
ግን ለደብዳቤዬ መልስ ሳላገኝ
ባነቺ ናፍቆት ብቻ ሞቼ እንዳትቀብሩኝ
ቢሮዬ ስገባ ስብሰባ ስቀመጥ
አሳቤ ኮብሎ ወዳንቺ ዘንድ ሲሮጥ
ሥጋቴ በዛና ጀመርኩኝ መደንገጥ
በሰው በደብዳቤ የላክሁት መልዕክት
ደርሶሽ ነው ዝም ያልሽው ወይስ ረሱት
እኔ እምሰቃየው በዝናሽ መጥፋት
ከፋም ተናግሬሽ በነገር መሐል
አስቀይሜሽ ከሆንኩ ፈጽሜ በደል
ባይሆን ለይቅርታሽ ካሳውን ልክፈል
ይቅር ግድ የለኝም ያለፈውስ ይለፍ
በሽታ እንዳይዘኝ አብጄም እንዳልከንፍ
ለዚች ለደብዳቤ ቶሎ መልስሽ ይጻፍ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍14❤1👏1
#ከዛሬ_ላይ_ጣለን
በሰቀቀን ዜማ በብሶት ተሰልቶ ፣
የእድሜ ቁጥር ገደብ ሳንኖረው ሞልቶ ፣
የኖርን የመሰለን እድሜያችን የራቀ፣
በጭንቀት ተባዝቶ ሳይኖር አለቀ!!!
በስጋም አልደላን በነፍስም አልታደልን፤
የህይወት አዙሪት ከዛሬ ላይ ጣለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
በሰቀቀን ዜማ በብሶት ተሰልቶ ፣
የእድሜ ቁጥር ገደብ ሳንኖረው ሞልቶ ፣
የኖርን የመሰለን እድሜያችን የራቀ፣
በጭንቀት ተባዝቶ ሳይኖር አለቀ!!!
በስጋም አልደላን በነፍስም አልታደልን፤
የህይወት አዙሪት ከዛሬ ላይ ጣለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍21🥰1
#ወድቄ_ተሰበርኩ
አተኩሮ ሲያየኝ ቀዝቃዛ መሰልኩት
አፈፍ ቢያረገኝ እጁን ቀዘቀዝኩት
ሽንጤን ጨበጥ አርጎ አንገቴን አቅንቶ
ዓይን ዓይኔን እያዬ አፍ ከንፈሬን ከፍቶ
ሳም-ላስ ቢያደርገኝ ዕውነት ቀዝቃዛ ነኝ
የሱ ከንፈር መሞቅ እኔን ግን ገረመኝ
ከዚህማ ወዲያ ምኑ ይጠየቃል
ቃናዬ ተስማምቶት ምራቄን ይውጣል
ደጋግሞ ሲስመኝ ሲመጠኝ ሲልሰኝ
ሰውነቴ ሲቀል አቅም ሳጣ ተሰማኝ
ፍላጎት ምኞቱ ሞልቶለት ሲረካ
ገልበጥ ቀና አድርጎ ገላዬን ሲነካ
ድንገት ሳያስበው ገፍተር ሲያደርገኝ
ወድቄ ተሰበርኩ የመጠጥ ጠርሙስ ነኝ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
አተኩሮ ሲያየኝ ቀዝቃዛ መሰልኩት
አፈፍ ቢያረገኝ እጁን ቀዘቀዝኩት
ሽንጤን ጨበጥ አርጎ አንገቴን አቅንቶ
ዓይን ዓይኔን እያዬ አፍ ከንፈሬን ከፍቶ
ሳም-ላስ ቢያደርገኝ ዕውነት ቀዝቃዛ ነኝ
የሱ ከንፈር መሞቅ እኔን ግን ገረመኝ
ከዚህማ ወዲያ ምኑ ይጠየቃል
ቃናዬ ተስማምቶት ምራቄን ይውጣል
ደጋግሞ ሲስመኝ ሲመጠኝ ሲልሰኝ
ሰውነቴ ሲቀል አቅም ሳጣ ተሰማኝ
ፍላጎት ምኞቱ ሞልቶለት ሲረካ
ገልበጥ ቀና አድርጎ ገላዬን ሲነካ
ድንገት ሳያስበው ገፍተር ሲያደርገኝ
ወድቄ ተሰበርኩ የመጠጥ ጠርሙስ ነኝ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍13👎3👏2❤1
#ከራስህ_ተስማማ
ስትናገር ፎካሪ
ዝም ስትል ፈሪ
ዓለም ስም አታጣ
ለአንተ ስታወጣ
ክፉም ጥሩም ስራ
ዝም በልም አውራ
ስም ትሰጥሃለች
እንዲህ ነው እያለች
አንተ እርሷን አተስማ
ከእራስህ ተስማማ
ዛሬ ከላይ ሰቅላ ነገ ለምታወርድ
ከሰውነት ክብርህ አንተ ብቻ አትውረድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ስትናገር ፎካሪ
ዝም ስትል ፈሪ
ዓለም ስም አታጣ
ለአንተ ስታወጣ
ክፉም ጥሩም ስራ
ዝም በልም አውራ
ስም ትሰጥሃለች
እንዲህ ነው እያለች
አንተ እርሷን አተስማ
ከእራስህ ተስማማ
ዛሬ ከላይ ሰቅላ ነገ ለምታወርድ
ከሰውነት ክብርህ አንተ ብቻ አትውረድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👏20👍5❤2🔥2
#ሐዘኔ_ከበደ
አፈር ፈጭተን ስናድግ እዚያ እኛ መንደር
ገደብ ባልነበረው ተሳስረን በፍቅር
እጅ ለጅ ተያይዘን ስንሸረሸር
ምን ብለሽኝ ነበር? ምን ብዬሽ ነበር?
በዛፎች ከለላ አዝግመን ስንሔድ
የአበቦች ሽታ መዓዛው ሲያውድ
እንኳን ጠላትና ሲቀና ዘመድ
ተጋብተን ለመኖር ወልደን ለመክበድ
ምኞት ሕልማችንን ያኔ ያቀድነውን
ልንፈጽም ካልቻልን ቃል የገባነውን
ዛሬ ቀዝቀዝ ካለ ያ ሁሉ ፍቅራችን
በጣም ያሳዝናል ሰዎች መሆናችን
በወፎች ጫጫታ ልቤ ተመስጦ
ያንችም ልብ እንደኔ ኔው በሃሳብ ተውጦ
በፍቅር ትኩሳት አካላችን ቀልጦ
ጉድ እንዳልተባለ ሚሥጥሩ ተገልጦ
የጋለው ፍቀራችን ዛሬ ከበረደ
ደንዳናው ልባችን ለመናድ ከራደ
ፍቅርን ያመነ ሰው መሆኑን ያበደ
በእውን ተረዳሁት ሐዘኔ ከበደ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
አፈር ፈጭተን ስናድግ እዚያ እኛ መንደር
ገደብ ባልነበረው ተሳስረን በፍቅር
እጅ ለጅ ተያይዘን ስንሸረሸር
ምን ብለሽኝ ነበር? ምን ብዬሽ ነበር?
በዛፎች ከለላ አዝግመን ስንሔድ
የአበቦች ሽታ መዓዛው ሲያውድ
እንኳን ጠላትና ሲቀና ዘመድ
ተጋብተን ለመኖር ወልደን ለመክበድ
ምኞት ሕልማችንን ያኔ ያቀድነውን
ልንፈጽም ካልቻልን ቃል የገባነውን
ዛሬ ቀዝቀዝ ካለ ያ ሁሉ ፍቅራችን
በጣም ያሳዝናል ሰዎች መሆናችን
በወፎች ጫጫታ ልቤ ተመስጦ
ያንችም ልብ እንደኔ ኔው በሃሳብ ተውጦ
በፍቅር ትኩሳት አካላችን ቀልጦ
ጉድ እንዳልተባለ ሚሥጥሩ ተገልጦ
የጋለው ፍቀራችን ዛሬ ከበረደ
ደንዳናው ልባችን ለመናድ ከራደ
ፍቅርን ያመነ ሰው መሆኑን ያበደ
በእውን ተረዳሁት ሐዘኔ ከበደ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
👍9❤1🔥1👏1
#አንድ_ነገር_አለ!
አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ
የተጋረደብን በጫጫታ ኩታ
መረዳት ያልቻልነው የሰውነት ጥጉ
ከፍታው ዝቅታው ውርደቱ ማዕረጉ
በሀቅ ያልተቃኘ ያልገባን ግርታ
አንድ ነገር አለ ያልታየን እውነታ
ወደ ነፈሰበት የሚስብ አስልቶ
ከሰውኛ ስሌት የሚጥል ጎትቶ
መግነጢሳዊ ሀይል ለእኛ ያልታወቀን
በዘር ዛር አዙሪት የሚያንቀጠቅጠን
ያልታወቀን ህመም ያልታየን በሽታ
አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ
የግርግር ዓለም ረባሽ ውካታ
የእራስ አቋም ነጥቆ በሰው የሚያስመራ
ባልገባን በገባን ዘወትር የሚያስወራ
እወነትን አስትቶ ከሀቅ የሚያጣላ
በሆነ ባልሆነው ትውልድ የሚበላ
ለማወቅ ያልጣርነው ሊገባን ያልቻለ
ማየት ያልፈለግነው አንድ ነገር አለ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ
የተጋረደብን በጫጫታ ኩታ
መረዳት ያልቻልነው የሰውነት ጥጉ
ከፍታው ዝቅታው ውርደቱ ማዕረጉ
በሀቅ ያልተቃኘ ያልገባን ግርታ
አንድ ነገር አለ ያልታየን እውነታ
ወደ ነፈሰበት የሚስብ አስልቶ
ከሰውኛ ስሌት የሚጥል ጎትቶ
መግነጢሳዊ ሀይል ለእኛ ያልታወቀን
በዘር ዛር አዙሪት የሚያንቀጠቅጠን
ያልታወቀን ህመም ያልታየን በሽታ
አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ
የግርግር ዓለም ረባሽ ውካታ
የእራስ አቋም ነጥቆ በሰው የሚያስመራ
ባልገባን በገባን ዘወትር የሚያስወራ
እወነትን አስትቶ ከሀቅ የሚያጣላ
በሆነ ባልሆነው ትውልድ የሚበላ
ለማወቅ ያልጣርነው ሊገባን ያልቻለ
ማየት ያልፈለግነው አንድ ነገር አለ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍12❤2👏1
#ኑዛዜ
ቀበሮ ነኝ እኔ ዘመድ አልጠጋ
አንደበቴ እሾህ ነው ሁሉን የሚወጋ
አውሬ ነኝ ተኩላ ነኝ ነገር አነፍናፊ
ስድ ነኝ ጠበኛ አጉል ተናዳፊ
ይሉኝታ የሌለኝ ሁሉን ነገር አጥፊ
ዋሾ ነኝ ቀጠፊ እንዲሁም ሴሰኛ
እርጉም ነኝ ክፉ ነኝ አጉል ቀናተኛ
አፈጀሁ አረጀሁ በመሆን ምቀኛ
ነብር ነኝ ጭራቅ ነኝ የሰው ደም የምመጥ
አታልላለሁኝ ወዳጅ ዘመድ ሳልመርጥ
አምናለሁ በሰይጣን ከመላዕክት ይበልጥ
እሰው ቤት እየዞርኩ ቅራሪ ሳጣራ
ካንዱ ተቀብዪ ለሌላው ሳወራ
ጨረስኩት ዕድሜዬን ቁምነገር ሳልሠራ
ክፋቴ ብዙ ነው አላውቅም ቁጥሩን
በግምት ይበልጣል ከአንድ ሚሊዮን
የኔ መጨረሻ ኧረ ምን ይሆን?
ደከመኝ ታከተኝ መሆን ማን ዘራሽ
እንዳልሰርቅ እንዳልገል ደግሞም አንዳልዋሽ
አጣሁኝ መድኃኒት ኧረ የት ልሽሽ?
መልሱን የምታውቁ እኔን ያልሆናችሁ
ከእውነተኛው መንገድ ከቶ ያልራቃችሁ
አካፍሉኝ ምስጢሩን ለነፍስ ብላችሁ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ቀበሮ ነኝ እኔ ዘመድ አልጠጋ
አንደበቴ እሾህ ነው ሁሉን የሚወጋ
አውሬ ነኝ ተኩላ ነኝ ነገር አነፍናፊ
ስድ ነኝ ጠበኛ አጉል ተናዳፊ
ይሉኝታ የሌለኝ ሁሉን ነገር አጥፊ
ዋሾ ነኝ ቀጠፊ እንዲሁም ሴሰኛ
እርጉም ነኝ ክፉ ነኝ አጉል ቀናተኛ
አፈጀሁ አረጀሁ በመሆን ምቀኛ
ነብር ነኝ ጭራቅ ነኝ የሰው ደም የምመጥ
አታልላለሁኝ ወዳጅ ዘመድ ሳልመርጥ
አምናለሁ በሰይጣን ከመላዕክት ይበልጥ
እሰው ቤት እየዞርኩ ቅራሪ ሳጣራ
ካንዱ ተቀብዪ ለሌላው ሳወራ
ጨረስኩት ዕድሜዬን ቁምነገር ሳልሠራ
ክፋቴ ብዙ ነው አላውቅም ቁጥሩን
በግምት ይበልጣል ከአንድ ሚሊዮን
የኔ መጨረሻ ኧረ ምን ይሆን?
ደከመኝ ታከተኝ መሆን ማን ዘራሽ
እንዳልሰርቅ እንዳልገል ደግሞም አንዳልዋሽ
አጣሁኝ መድኃኒት ኧረ የት ልሽሽ?
መልሱን የምታውቁ እኔን ያልሆናችሁ
ከእውነተኛው መንገድ ከቶ ያልራቃችሁ
አካፍሉኝ ምስጢሩን ለነፍስ ብላችሁ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍9👏3
#አዎ_ፍቅር_የለም
በዝሙት ህሊና በክህደት እይታ
በእምነት አልባ ቅኔ በጥቅመኞች ኩታ
ከሆነ ልኬቱ የሚዛኑም ክብደት
በእርግጥ ፍቅር የለም ሲረክስ ሰውነት
ፍቅርን በፍቅር ለሚለካ ደግሞ
የእውነት ፍቅር አለ ደጋግሞ ደጋግሞ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
በዝሙት ህሊና በክህደት እይታ
በእምነት አልባ ቅኔ በጥቅመኞች ኩታ
ከሆነ ልኬቱ የሚዛኑም ክብደት
በእርግጥ ፍቅር የለም ሲረክስ ሰውነት
ፍቅርን በፍቅር ለሚለካ ደግሞ
የእውነት ፍቅር አለ ደጋግሞ ደጋግሞ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍11❤3
#ስልክ_ተደወለ
ስልክ ተደወለ
መላልሶ አቃጨለ
እኔ አነሳዋለሁ ብላ ሮጠች ሒሩት
እጮኛዋ መስሏት ይህች የኔ እኅት
ስልኩ ጭርር ብሎ ሲደውል ቆየና
እቴ ስታነሳው ዝም አለ እንደገና
ከዚያ እቴ አለች ማንን ፈላጊ ነው
ፍቀረኛዬ ይሆን አሁን የደወለው?
ብላ ብትጠይቅ ወንድሜ እንዲህ አለ
የለም የኔ ፍቅር ነች የኔዋ አምሳለ!
እማማም በተራ እነሱ አይደሉም
አለች ማኅበረተኞቼ ሳይሆኑ አይቀሩም
አባቴም በፊናው የኔ ጓደኞች
ናቸው የደወሉት ምን ሆነሻል አንች?
ብለው በጭቅጭቅ አፍ ላፍ ሲካፈቱ
ለኔ ነው ለኔ ነው ብለው ሲሟገቱ
ያ! ያቃጨለው ስልክ መልሶ ጭጭ እስኪል
ከጎረቤት ሔጄ የነበርኩ ስደውል
በጠቡ መሐከል በጣልቃ ገብቼ
እኔ ነኝ የደወልኩ አልኩኝ ዘመዶቼ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ስልክ ተደወለ
መላልሶ አቃጨለ
እኔ አነሳዋለሁ ብላ ሮጠች ሒሩት
እጮኛዋ መስሏት ይህች የኔ እኅት
ስልኩ ጭርር ብሎ ሲደውል ቆየና
እቴ ስታነሳው ዝም አለ እንደገና
ከዚያ እቴ አለች ማንን ፈላጊ ነው
ፍቀረኛዬ ይሆን አሁን የደወለው?
ብላ ብትጠይቅ ወንድሜ እንዲህ አለ
የለም የኔ ፍቅር ነች የኔዋ አምሳለ!
እማማም በተራ እነሱ አይደሉም
አለች ማኅበረተኞቼ ሳይሆኑ አይቀሩም
አባቴም በፊናው የኔ ጓደኞች
ናቸው የደወሉት ምን ሆነሻል አንች?
ብለው በጭቅጭቅ አፍ ላፍ ሲካፈቱ
ለኔ ነው ለኔ ነው ብለው ሲሟገቱ
ያ! ያቃጨለው ስልክ መልሶ ጭጭ እስኪል
ከጎረቤት ሔጄ የነበርኩ ስደውል
በጠቡ መሐከል በጣልቃ ገብቼ
እኔ ነኝ የደወልኩ አልኩኝ ዘመዶቼ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
😁22👍7❤1
#ሰው_ሊሆነኝ
የብቼኝነቴ ማስታገሻ
የመከፋቴ ቅኔ መርሻ
ትዝታሽ ነው ቅርብ ወዳጄ
የማይጠፋው ዘወትር ደጄ
ሊጠይቀኝ
ሊያስታውሰኝ
የማይሰለች ተመላላሽ አስታዋሼ
ሰውን ሳጣ ሰው ሊሆነኝ ቅኔ ሞክሼ
የሚተጋ የማይረሳኝ ነግቶ ሲመሽ
አለኝ ክብር አለኝ ሞገስ ለትዝታሽ።
ወረት አያውቅ ማግኘት ማጣት
የሚጋራኝ ተካፋዬ የእኔን እውነት
ትዝታ ነው ዘር የሌለው
የእርሱ መስፈርት ሰው መሆን ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
የብቼኝነቴ ማስታገሻ
የመከፋቴ ቅኔ መርሻ
ትዝታሽ ነው ቅርብ ወዳጄ
የማይጠፋው ዘወትር ደጄ
ሊጠይቀኝ
ሊያስታውሰኝ
የማይሰለች ተመላላሽ አስታዋሼ
ሰውን ሳጣ ሰው ሊሆነኝ ቅኔ ሞክሼ
የሚተጋ የማይረሳኝ ነግቶ ሲመሽ
አለኝ ክብር አለኝ ሞገስ ለትዝታሽ።
ወረት አያውቅ ማግኘት ማጣት
የሚጋራኝ ተካፋዬ የእኔን እውነት
ትዝታ ነው ዘር የሌለው
የእርሱ መስፈርት ሰው መሆን ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏11👍6
#የቆሰለው_ልቤ
የቆሰለው ልቤ እያለኝ አልችል
ዓይኖቼ እንባ ሲያዝሉ እኔ ስታገል
በፍጹም ጭካኔ ፍቅሬን ስለጣልሽ
ተመቸሽ ወይ አሁን ደስ አለሽ ደላሻ
በረዶ እንኳን ሳይጥል ውርጩ ሳይወረዛ
ቁሩ ሳይጠነክር ምድር ሳይሞላው ጤዛ
ስምሽን ስሰማ ሳስብ ፍቅርሽን
እንዘፈዘፋለሁ በብርድ በሐዘን
ሃሳብ ተለዋውጠን ምስጢር ተወያይተን
በክፉ በደግ ቀን እንደዚያ ተስማምተን
አሁን ብንለያይ እንባ ብንራጭ
ማነው ደስ የሚለው፣ ማነው የሚቆጭ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
የቆሰለው ልቤ እያለኝ አልችል
ዓይኖቼ እንባ ሲያዝሉ እኔ ስታገል
በፍጹም ጭካኔ ፍቅሬን ስለጣልሽ
ተመቸሽ ወይ አሁን ደስ አለሽ ደላሻ
በረዶ እንኳን ሳይጥል ውርጩ ሳይወረዛ
ቁሩ ሳይጠነክር ምድር ሳይሞላው ጤዛ
ስምሽን ስሰማ ሳስብ ፍቅርሽን
እንዘፈዘፋለሁ በብርድ በሐዘን
ሃሳብ ተለዋውጠን ምስጢር ተወያይተን
በክፉ በደግ ቀን እንደዚያ ተስማምተን
አሁን ብንለያይ እንባ ብንራጭ
ማነው ደስ የሚለው፣ ማነው የሚቆጭ?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
👍7👏3