#ቀረሽ_እንደዋዛ
እንደ ፡ ድመቶቹ...
የትም ፡ እንደሚያድሩት
እንደ ፡ ስልክ ፡ እንጨቶች፣
እንደ ፡ ዛፍ ፡ ሀረጎች
እንደ ፡ ቤት ፡ ክዳኖቸ
ብርድ ፡ አቆራመደኝ ~ ስጠብቅ ፡ ስጠብቅ
ትመጫለሽ ፡ ብዬ...
ሳይ ፡ ማዶ ፡ ሳይ ፡ ማዶ ፣
የልጅነት ፡ ዐይኔ ፡ ሟሟ ፡ እንደ ፡ በረዶ፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ደቂቃ ፡ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ባዝን ፡ ባንጎራጉር፣
ትወጫለሽ ፡ ብዬ ፡ በበራፍሽ ፡ ብዞር፣
ብርድ ፡ አቆራመደኝ፣
የመንገድ ፡ መብራቶች ፡ አይተው ፡ አፌዙብኝ፣
ውርጩ ፡ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ፡ ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን ፡ አውቀዋል ፡ ያውቃሉ፣
መስኮቶች ፡ ጨልመው፣
ቤቶች ፡ ተቆልፈው...
ከተማው ፡ ሲተኛ ፡ አይተዋል ያያሉ፣
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገጣሚገብረክርስቶስ ደስታ
እንደ ፡ ድመቶቹ...
የትም ፡ እንደሚያድሩት
እንደ ፡ ስልክ ፡ እንጨቶች፣
እንደ ፡ ዛፍ ፡ ሀረጎች
እንደ ፡ ቤት ፡ ክዳኖቸ
ብርድ ፡ አቆራመደኝ ~ ስጠብቅ ፡ ስጠብቅ
ትመጫለሽ ፡ ብዬ...
ሳይ ፡ ማዶ ፡ ሳይ ፡ ማዶ ፣
የልጅነት ፡ ዐይኔ ፡ ሟሟ ፡ እንደ ፡ በረዶ፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ደቂቃ ፡ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ባዝን ፡ ባንጎራጉር፣
ትወጫለሽ ፡ ብዬ ፡ በበራፍሽ ፡ ብዞር፣
ብርድ ፡ አቆራመደኝ፣
የመንገድ ፡ መብራቶች ፡ አይተው ፡ አፌዙብኝ፣
ውርጩ ፡ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ፡ ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን ፡ አውቀዋል ፡ ያውቃሉ፣
መስኮቶች ፡ ጨልመው፣
ቤቶች ፡ ተቆልፈው...
ከተማው ፡ ሲተኛ ፡ አይተዋል ያያሉ፣
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገጣሚ
👏8❤6👍4🔥1
#አንችን_አይጠጋ
ያንጎራጎርሽልኝ በመረዋ ድምጽሽ
ሲያውደኝ የነበር ያ ሽቶ ጠረንሽ
ትራስ የነበሩኝ መክዳ ጡቶችሽ
እማኝ እንዲሆኑኝ ላድርጋቸው ነቃሽ
በዕውነት ላፈቀሩት መሆን መስዋዕት
የቆዬ ነውና ከአያት ቅድመ አያት
በወረት መደሰት እስኪያልፍ ወረት
ምኞትሽ መሆኑን አሁን አወቅሁት
ሕይወቴን አጋልጠሽ ለሕመም ለአደጋ
ፍቅሬን ቸል ብለሽ ከሔድሽ እሌላጋ
የኔውስ የኔነው ምንም አያሰጋ
ብቻ የኔ ሐዘን አንችን አይጠጋ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
ያንጎራጎርሽልኝ በመረዋ ድምጽሽ
ሲያውደኝ የነበር ያ ሽቶ ጠረንሽ
ትራስ የነበሩኝ መክዳ ጡቶችሽ
እማኝ እንዲሆኑኝ ላድርጋቸው ነቃሽ
በዕውነት ላፈቀሩት መሆን መስዋዕት
የቆዬ ነውና ከአያት ቅድመ አያት
በወረት መደሰት እስኪያልፍ ወረት
ምኞትሽ መሆኑን አሁን አወቅሁት
ሕይወቴን አጋልጠሽ ለሕመም ለአደጋ
ፍቅሬን ቸል ብለሽ ከሔድሽ እሌላጋ
የኔውስ የኔነው ምንም አያሰጋ
ብቻ የኔ ሐዘን አንችን አይጠጋ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
👍8
#ይመሻል_ይነጋል!!!
የከፋው ሰው እንጂ ህግን ያጓደለ፣
ከእግዚአብሔር እርቆ አድሮ የቀለለ፣
ግዜማ ቁጥር ነው ይመሻል ይነጋል፣
የተፈጥሮ ህጉን ጠብቆ ይጓዛል።
ጥፋቱ የሰው ነው ህግ የተላለፈ፣
በደልን በጉያው ደጋግሞ ያቀፈ።
ግዜ ነው አትበሉ ግዜ ምን አጠፋ?
ሰው እኮ ነው ዛሬም በቢጤው የከፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
የከፋው ሰው እንጂ ህግን ያጓደለ፣
ከእግዚአብሔር እርቆ አድሮ የቀለለ፣
ግዜማ ቁጥር ነው ይመሻል ይነጋል፣
የተፈጥሮ ህጉን ጠብቆ ይጓዛል።
ጥፋቱ የሰው ነው ህግ የተላለፈ፣
በደልን በጉያው ደጋግሞ ያቀፈ።
ግዜ ነው አትበሉ ግዜ ምን አጠፋ?
ሰው እኮ ነው ዛሬም በቢጤው የከፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍12❤5❤🔥1🔥1
#ሀገርህ_ናት_በቃ
ይቺው ናት ኢትዮጵያ
ሀገርህ ናት በቃ!
በዚች ንፍቀ ክበብ፤
አይምሽ እንጅ መሽቶ ፥ ማታው ከጠረቃ፤
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ ፥ ብቻዋን የተኛች
ከዓለም ተደብቃ!
አኪሯ ቀዝቅዞ ፥ "ያንቀላፋች ውበት"
ያንተው የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ ፥ ወይ አብረሃት ንቃ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ መኮንን
ይቺው ናት ኢትዮጵያ
ሀገርህ ናት በቃ!
በዚች ንፍቀ ክበብ፤
አይምሽ እንጅ መሽቶ ፥ ማታው ከጠረቃ፤
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ ፥ ብቻዋን የተኛች
ከዓለም ተደብቃ!
አኪሯ ቀዝቅዞ ፥ "ያንቀላፋች ውበት"
ያንተው የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ ፥ ወይ አብረሃት ንቃ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ መኮንን
👍18
#መንፈሴን_አመመኝ!!
ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
❤17👍7👏2😢2
#ትዝታ
ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
🥰8👍4👏4❤3
#ተራርቆ_ከእውነት
ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍17❤2😭2🔥1
#ፋኖስ_እና_ብርጭቆ
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ
እንዲህ ሲል ተጣላ - ከብርጭቆ ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሀን የምሰጥ
ጨለማን አጥፉቼ የምገላልጥ
አንተ ግን ተፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበኸኝ እንዲያው ተገትረህ።
አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ
ብርሀኔ እርቆ ደምቆ እንዳያበራ
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንክ ስራየን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሀኔ ይስፋ።
''እውነትማ ለንተ ከሆንኩኝ እንቅፋት፣ ልሂድልህ ብሎ ቢለቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰው የንፋስ ሽውታ
መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፉታ።
አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ፣
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሳ
ሰውም እንዲሁ ነው ያመጣል አበሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ
እንዲህ ሲል ተጣላ - ከብርጭቆ ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሀን የምሰጥ
ጨለማን አጥፉቼ የምገላልጥ
አንተ ግን ተፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበኸኝ እንዲያው ተገትረህ።
አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ
ብርሀኔ እርቆ ደምቆ እንዳያበራ
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንክ ስራየን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሀኔ ይስፋ።
''እውነትማ ለንተ ከሆንኩኝ እንቅፋት፣ ልሂድልህ ብሎ ቢለቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰው የንፋስ ሽውታ
መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፉታ።
አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ፣
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሳ
ሰውም እንዲሁ ነው ያመጣል አበሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
❤13👍6👎1
ሳቅ እንኳን ባትፈቅዱ ማልቀስ አትከልክሉ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰18👏6👍3
#ኮረዳ
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
❤13👍7👏4
#የምጡ_ጅማሬ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍20❤5🥰5🔥3👏3
ዓለም ቅንዝረኛ ብዙ ባል አግብታ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
🥰11👍7🏆1
#ችግር
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍13
#የተቃርኖ_ሕግ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍9
#ፍቅር_ወረተኛ
ፍቅር እንደሞት ጥላ በድን አደረገኝ
አጥንቴን ሰበረው ከቶ አዝለፈለፈኝ
ፍቅር በአበባው መዓዛው ጣፈጠኝ
አሁን ግን ጠውልጎ ሽታው አሰለቸኝ
የፍቅር ክፋቱ ትዝታ ነው ሲሉ
አላመንኩም ነበር ውሸት በመምሰሉ
አሁን ግን አወቅሁት ይሰማኛል ቁስሉ
የነደፈኝ መርዙ የወጋኝ ሾተሉ
ይህ ጣፋጭ እንደማር መራር እንደኮሶ
ልፍስፍስ እንደጥጥ ጥብቅ ከምሰሶ
ዛሬ ህይወት አለው ነገ ይቀራል ፈርሶ
ፍቅርን አትመኑት ቢታይ ድርብ ለብሶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ፍቅር እንደሞት ጥላ በድን አደረገኝ
አጥንቴን ሰበረው ከቶ አዝለፈለፈኝ
ፍቅር በአበባው መዓዛው ጣፈጠኝ
አሁን ግን ጠውልጎ ሽታው አሰለቸኝ
የፍቅር ክፋቱ ትዝታ ነው ሲሉ
አላመንኩም ነበር ውሸት በመምሰሉ
አሁን ግን አወቅሁት ይሰማኛል ቁስሉ
የነደፈኝ መርዙ የወጋኝ ሾተሉ
ይህ ጣፋጭ እንደማር መራር እንደኮሶ
ልፍስፍስ እንደጥጥ ጥብቅ ከምሰሶ
ዛሬ ህይወት አለው ነገ ይቀራል ፈርሶ
ፍቅርን አትመኑት ቢታይ ድርብ ለብሶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍17🔥2❤1🥰1
#ፍቅርን_ባይተካም
ይታሰር ቀለበት ቃልን ያስታውሳል
ፍቅርን ባይተካም አጥፊን ይታዘባል
ፍቅርን ጠፍሮ አስሮ ባይጠብቅም
የጎደለን እምነት ሰፍሮ ባይመልስም
ይታሰር ቀለበት አጥፊን ያሳቅቃል
በወለቀ ቁጥር ህሊናን ይከሳል
ሐይል ባይኖረውም ክህደትን ለማስቆም
አንደበት አውጥቶ ለፍርድ ባያቀርብም
ቃል እያስታወሰ አጥፊን እንዲቀጣ
ከቦርሳና ከኪስ ሲገባ ሲወጣ
ህሊናን አድምቶ በደልን ይናገር
ይደረግ ቀለበት ከጣት ላይ ይታሰር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ይታሰር ቀለበት ቃልን ያስታውሳል
ፍቅርን ባይተካም አጥፊን ይታዘባል
ፍቅርን ጠፍሮ አስሮ ባይጠብቅም
የጎደለን እምነት ሰፍሮ ባይመልስም
ይታሰር ቀለበት አጥፊን ያሳቅቃል
በወለቀ ቁጥር ህሊናን ይከሳል
ሐይል ባይኖረውም ክህደትን ለማስቆም
አንደበት አውጥቶ ለፍርድ ባያቀርብም
ቃል እያስታወሰ አጥፊን እንዲቀጣ
ከቦርሳና ከኪስ ሲገባ ሲወጣ
ህሊናን አድምቶ በደልን ይናገር
ይደረግ ቀለበት ከጣት ላይ ይታሰር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
❤13👏2
#ገንዘብ
ድሀ ከሀብታም ሰው የሚለይበት
በገንዘብ መሆኑ እውነት ነው ውሸት?
እውነት ይሆን ውሸት እንደዚህ መባሉ
ገንዘብ ከመሰብሰብ መበተን መቅለሉ
እውነት ይሆን ውሸት ደሀው ሰው ሲራብ
የሀብታም ፍላጎት መቆጠብ ከምግብ
እውነት ይሆን ውሸት ዕዳ ከሌለበት
ድሀ ሰው ካብታሙ እኩል የሆነበት
እንዲያው በደፈናው የሆነውን ሆኖ
ምነው ገንዘብ ቢኖር ከሁሉም ተዋስኖ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ድሀ ከሀብታም ሰው የሚለይበት
በገንዘብ መሆኑ እውነት ነው ውሸት?
እውነት ይሆን ውሸት እንደዚህ መባሉ
ገንዘብ ከመሰብሰብ መበተን መቅለሉ
እውነት ይሆን ውሸት ደሀው ሰው ሲራብ
የሀብታም ፍላጎት መቆጠብ ከምግብ
እውነት ይሆን ውሸት ዕዳ ከሌለበት
ድሀ ሰው ካብታሙ እኩል የሆነበት
እንዲያው በደፈናው የሆነውን ሆኖ
ምነው ገንዘብ ቢኖር ከሁሉም ተዋስኖ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍11❤1
#የሌቦች_እቁብ!!
ሌቦች ተሰባስበው እቁብ መሰረቱ
ሰብሳቢ ለመምረጥ እጅግ ተሟገቱ
ማንስ ማንን ይመን የመንታፊ መንጋ
አንድ ታማኝ ጠፍቶ አስመሳይ ቢንጋጋ
ውሸታም በጋራ እድር ቢመሰርት
መኖሩም ውሸት ነው መሞቱም የሐሰት
ሀይማኖት ቢበዛ በስም ተለያይቶ
አማኝ ሳይኖርበት የስም አሜን በዝቶ
በምላስ ማሞገስ በልብ ግን መርከስ
በማስመሰል ዜማ የውሸት መደገስ
ባልዘነበ ዝናብ በዘር ጎርፍ መበስበስ
በግም ፖለቲካ ቅዱሱ ሰው ሲረክስ
እንዴት ኢትዮጵያችን እንደጥንቱ ትንገስ
ቆመን እያወደስን የነበረው ሲፈርስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ሌቦች ተሰባስበው እቁብ መሰረቱ
ሰብሳቢ ለመምረጥ እጅግ ተሟገቱ
ማንስ ማንን ይመን የመንታፊ መንጋ
አንድ ታማኝ ጠፍቶ አስመሳይ ቢንጋጋ
ውሸታም በጋራ እድር ቢመሰርት
መኖሩም ውሸት ነው መሞቱም የሐሰት
ሀይማኖት ቢበዛ በስም ተለያይቶ
አማኝ ሳይኖርበት የስም አሜን በዝቶ
በምላስ ማሞገስ በልብ ግን መርከስ
በማስመሰል ዜማ የውሸት መደገስ
ባልዘነበ ዝናብ በዘር ጎርፍ መበስበስ
በግም ፖለቲካ ቅዱሱ ሰው ሲረክስ
እንዴት ኢትዮጵያችን እንደጥንቱ ትንገስ
ቆመን እያወደስን የነበረው ሲፈርስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤10👏9👍6🫡2
#ናፍቆት
መለሎ ቁመናሽ ቀጭን ወገብሽ
ኮራ ያለ ዳሌሽ ጉች ጉች ጡትሽ
ኧረ እንዴት ከረሙ አንችስ ደህና ነሽ?
እኔ በበኩሌ በጣም ደህና ነኝ
ግን ለደብዳቤዬ መልስ ሳላገኝ
ባነቺ ናፍቆት ብቻ ሞቼ እንዳትቀብሩኝ
ቢሮዬ ስገባ ስብሰባ ስቀመጥ
አሳቤ ኮብሎ ወዳንቺ ዘንድ ሲሮጥ
ሥጋቴ በዛና ጀመርኩኝ መደንገጥ
በሰው በደብዳቤ የላክሁት መልዕክት
ደርሶሽ ነው ዝም ያልሽው ወይስ ረሱት
እኔ እምሰቃየው በዝናሽ መጥፋት
ከፋም ተናግሬሽ በነገር መሐል
አስቀይሜሽ ከሆንኩ ፈጽሜ በደል
ባይሆን ለይቅርታሽ ካሳውን ልክፈል
ይቅር ግድ የለኝም ያለፈውስ ይለፍ
በሽታ እንዳይዘኝ አብጄም እንዳልከንፍ
ለዚች ለደብዳቤ ቶሎ መልስሽ ይጻፍ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
መለሎ ቁመናሽ ቀጭን ወገብሽ
ኮራ ያለ ዳሌሽ ጉች ጉች ጡትሽ
ኧረ እንዴት ከረሙ አንችስ ደህና ነሽ?
እኔ በበኩሌ በጣም ደህና ነኝ
ግን ለደብዳቤዬ መልስ ሳላገኝ
ባነቺ ናፍቆት ብቻ ሞቼ እንዳትቀብሩኝ
ቢሮዬ ስገባ ስብሰባ ስቀመጥ
አሳቤ ኮብሎ ወዳንቺ ዘንድ ሲሮጥ
ሥጋቴ በዛና ጀመርኩኝ መደንገጥ
በሰው በደብዳቤ የላክሁት መልዕክት
ደርሶሽ ነው ዝም ያልሽው ወይስ ረሱት
እኔ እምሰቃየው በዝናሽ መጥፋት
ከፋም ተናግሬሽ በነገር መሐል
አስቀይሜሽ ከሆንኩ ፈጽሜ በደል
ባይሆን ለይቅርታሽ ካሳውን ልክፈል
ይቅር ግድ የለኝም ያለፈውስ ይለፍ
በሽታ እንዳይዘኝ አብጄም እንዳልከንፍ
ለዚች ለደብዳቤ ቶሎ መልስሽ ይጻፍ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍15❤1👏1
#ከዛሬ_ላይ_ጣለን
በሰቀቀን ዜማ በብሶት ተሰልቶ ፣
የእድሜ ቁጥር ገደብ ሳንኖረው ሞልቶ ፣
የኖርን የመሰለን እድሜያችን የራቀ፣
በጭንቀት ተባዝቶ ሳይኖር አለቀ!!!
በስጋም አልደላን በነፍስም አልታደልን፤
የህይወት አዙሪት ከዛሬ ላይ ጣለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
በሰቀቀን ዜማ በብሶት ተሰልቶ ፣
የእድሜ ቁጥር ገደብ ሳንኖረው ሞልቶ ፣
የኖርን የመሰለን እድሜያችን የራቀ፣
በጭንቀት ተባዝቶ ሳይኖር አለቀ!!!
በስጋም አልደላን በነፍስም አልታደልን፤
የህይወት አዙሪት ከዛሬ ላይ ጣለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍21🥰1
#ወድቄ_ተሰበርኩ
አተኩሮ ሲያየኝ ቀዝቃዛ መሰልኩት
አፈፍ ቢያረገኝ እጁን ቀዘቀዝኩት
ሽንጤን ጨበጥ አርጎ አንገቴን አቅንቶ
ዓይን ዓይኔን እያዬ አፍ ከንፈሬን ከፍቶ
ሳም-ላስ ቢያደርገኝ ዕውነት ቀዝቃዛ ነኝ
የሱ ከንፈር መሞቅ እኔን ግን ገረመኝ
ከዚህማ ወዲያ ምኑ ይጠየቃል
ቃናዬ ተስማምቶት ምራቄን ይውጣል
ደጋግሞ ሲስመኝ ሲመጠኝ ሲልሰኝ
ሰውነቴ ሲቀል አቅም ሳጣ ተሰማኝ
ፍላጎት ምኞቱ ሞልቶለት ሲረካ
ገልበጥ ቀና አድርጎ ገላዬን ሲነካ
ድንገት ሳያስበው ገፍተር ሲያደርገኝ
ወድቄ ተሰበርኩ የመጠጥ ጠርሙስ ነኝ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
አተኩሮ ሲያየኝ ቀዝቃዛ መሰልኩት
አፈፍ ቢያረገኝ እጁን ቀዘቀዝኩት
ሽንጤን ጨበጥ አርጎ አንገቴን አቅንቶ
ዓይን ዓይኔን እያዬ አፍ ከንፈሬን ከፍቶ
ሳም-ላስ ቢያደርገኝ ዕውነት ቀዝቃዛ ነኝ
የሱ ከንፈር መሞቅ እኔን ግን ገረመኝ
ከዚህማ ወዲያ ምኑ ይጠየቃል
ቃናዬ ተስማምቶት ምራቄን ይውጣል
ደጋግሞ ሲስመኝ ሲመጠኝ ሲልሰኝ
ሰውነቴ ሲቀል አቅም ሳጣ ተሰማኝ
ፍላጎት ምኞቱ ሞልቶለት ሲረካ
ገልበጥ ቀና አድርጎ ገላዬን ሲነካ
ድንገት ሳያስበው ገፍተር ሲያደርገኝ
ወድቄ ተሰበርኩ የመጠጥ ጠርሙስ ነኝ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍13👎3👏2❤1