#ምሥጢር
ምሥጢር ነው ያልከውን ለሌላ ሰው መንገር
መሆኑን ተረዳ በገዛጅ መታሰር
ግን ምሥጢር ለባዕድ እስካልተነገረ
ምሥጢርህ ምሥጢር ነው ባንተው ከታሠረ
ምሥጢርህን ሌላ ሰው ካየና ከሰማው
ያባከንከው ምሥጢር ላንተ ዘብጥያህ ነው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደሪሲ ታደለ ብጡል
ምሥጢር ነው ያልከውን ለሌላ ሰው መንገር
መሆኑን ተረዳ በገዛጅ መታሰር
ግን ምሥጢር ለባዕድ እስካልተነገረ
ምሥጢርህ ምሥጢር ነው ባንተው ከታሠረ
ምሥጢርህን ሌላ ሰው ካየና ከሰማው
ያባከንከው ምሥጢር ላንተ ዘብጥያህ ነው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደሪሲ ታደለ ብጡል
👍9😁1
ተቃቅፈን ስንሄድ ለሚያገላግሉ
ጉንጭሽን ስስምሽ ነከሳት ለሚሉ
ከፍቅራችን ይልቅ ጸብ ለናፈቃቸው
ከራስሽ ተጣልተሽ...
የወሬ ማድመቂያ ሰበብ አትሁኛቸው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገጣሚአቤል ሽመልስ
ጉንጭሽን ስስምሽ ነከሳት ለሚሉ
ከፍቅራችን ይልቅ ጸብ ለናፈቃቸው
ከራስሽ ተጣልተሽ...
የወሬ ማድመቂያ ሰበብ አትሁኛቸው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገጣሚ
👏10👍4❤3🔥2
#አልቻልኩም
(አብሮ መሰደድ)
የልቤ ሰመመን የፍቅሬ ትዝታ
የዓይኖቼ ብሌን የሕይወቴ አለኝታ
አኔን ከጠላሽኝ ከናቅሽ ፍቅሬን
ከመሔዴ በፊት ስሚማ እሮሮዬን
ልዝብ አንደበትሽ ታጋሽ ተፈጥሮሽ
አስተዋይ አእምሮሽ ንጹሕ ልቦናሽ
ተባብሮ ከዓይኖችሽ ከውበትሽ ጋር
ልቤን ማርኮ ወስዶ አሰረው በፍቅር
ኮኮብ ዓይኖችሽን ጉብል ጉንጮችሽን
የቀጭኔ ጭራ መሳይ ጸጉሮችሽን
ለጋ ከንፈርሽን ወለላ እንደማር
ንብረቴ ለማድረግ ምኞቴ ነበር
አይቻልም ካልሽኝ ማቀፍ ሽንጥሽን
እኔ አልፈቅድም ካልሽኝ መሳም ከንፈርሽን
ፍቅሬን መግለጥ ካልቻልኩ የልቤን መንገር
በሰላም እናብቃው መጣላት ይቅር
እንሰነባበት ነውና መጓዜ
ጻፊልኝ ቢቻልሽ ትዝ ባልኩሽ ጊዜ
ስለተለበለብኩ በፍቅርሽ ንዳድ
አልቻልኩም ለመኖር አብሮ መሰደድ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
(አብሮ መሰደድ)
የልቤ ሰመመን የፍቅሬ ትዝታ
የዓይኖቼ ብሌን የሕይወቴ አለኝታ
አኔን ከጠላሽኝ ከናቅሽ ፍቅሬን
ከመሔዴ በፊት ስሚማ እሮሮዬን
ልዝብ አንደበትሽ ታጋሽ ተፈጥሮሽ
አስተዋይ አእምሮሽ ንጹሕ ልቦናሽ
ተባብሮ ከዓይኖችሽ ከውበትሽ ጋር
ልቤን ማርኮ ወስዶ አሰረው በፍቅር
ኮኮብ ዓይኖችሽን ጉብል ጉንጮችሽን
የቀጭኔ ጭራ መሳይ ጸጉሮችሽን
ለጋ ከንፈርሽን ወለላ እንደማር
ንብረቴ ለማድረግ ምኞቴ ነበር
አይቻልም ካልሽኝ ማቀፍ ሽንጥሽን
እኔ አልፈቅድም ካልሽኝ መሳም ከንፈርሽን
ፍቅሬን መግለጥ ካልቻልኩ የልቤን መንገር
በሰላም እናብቃው መጣላት ይቅር
እንሰነባበት ነውና መጓዜ
ጻፊልኝ ቢቻልሽ ትዝ ባልኩሽ ጊዜ
ስለተለበለብኩ በፍቅርሽ ንዳድ
አልቻልኩም ለመኖር አብሮ መሰደድ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
👍14
#ዝምታም_ይጮኻል
የምላስ ጋጋታ ጀሮን ባይጋርደው
ይደመጥ ነበረ ዝምታም ቃል አለው
በህሊና ከሳሽ በልብ ዳኝነት
የዝምታ ችሎት የተሰየመ እለት
ሁሉም ተናጋሪ ጸጥ! ቢል ላንድ አፍታ
እመኑኝ ይጮሃል ድምጽ አለው ዝምታ
የተፈጥሮ ችሎት በልብ ሚዛን ቢረግጥ
ዓለም ለሴኮንዶች መናገርን ቢል ጸጥ
ያኔ ይደመጣል ቃል አለው ዝምታ
ገለል ሲልለት የምላስ ውካታ
ጆሮ ባይጋረድ በቃላት ጋጋታ
መጮኽ በጀመረ የስንቱ ዝምታ
የሰው ልጅ ቢኖረው ስድስተኛ ህዋስ
ይሰማው ነበረ ዝምታችን ሲፈስ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
የምላስ ጋጋታ ጀሮን ባይጋርደው
ይደመጥ ነበረ ዝምታም ቃል አለው
በህሊና ከሳሽ በልብ ዳኝነት
የዝምታ ችሎት የተሰየመ እለት
ሁሉም ተናጋሪ ጸጥ! ቢል ላንድ አፍታ
እመኑኝ ይጮሃል ድምጽ አለው ዝምታ
የተፈጥሮ ችሎት በልብ ሚዛን ቢረግጥ
ዓለም ለሴኮንዶች መናገርን ቢል ጸጥ
ያኔ ይደመጣል ቃል አለው ዝምታ
ገለል ሲልለት የምላስ ውካታ
ጆሮ ባይጋረድ በቃላት ጋጋታ
መጮኽ በጀመረ የስንቱ ዝምታ
የሰው ልጅ ቢኖረው ስድስተኛ ህዋስ
ይሰማው ነበረ ዝምታችን ሲፈስ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍9👏6❤4🥰2
#መዋሸክ
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ብልሹ
መዋሸት ብቻ ነው ትልቁም ትንሹ
ባገራችን ባህል በአገራችን ልምድ
አስነዋሪ ነበር መዋሸክ መልመድ
ግን የዘመኑ ሰው ልማድ ያደረገው
ትንሹም ትልቁም ሰውን ማማትን ነው
ለዚች ላጭር ዕድሜ መቶ ለማትሞላ
እንዴት ሰው ይኖራል ሰውን እያጣላ?
የመዋሽክና የሐሜት ዘይቤ
አያስፈልገኝም ይራቅ ካጠገቤ
ብሎ የሚል ወጣት ወይም አረጋዊ
ምነዋ በኖረ በሐቅ ኢትዮጵያዊ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ብልሹ
መዋሸት ብቻ ነው ትልቁም ትንሹ
ባገራችን ባህል በአገራችን ልምድ
አስነዋሪ ነበር መዋሸክ መልመድ
ግን የዘመኑ ሰው ልማድ ያደረገው
ትንሹም ትልቁም ሰውን ማማትን ነው
ለዚች ላጭር ዕድሜ መቶ ለማትሞላ
እንዴት ሰው ይኖራል ሰውን እያጣላ?
የመዋሽክና የሐሜት ዘይቤ
አያስፈልገኝም ይራቅ ካጠገቤ
ብሎ የሚል ወጣት ወይም አረጋዊ
ምነዋ በኖረ በሐቅ ኢትዮጵያዊ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
👏6👍4❤3🙏3
#ቅደሙኝ_አልኳቸው
ብዙ ሰው በዋይታ
ጥቂቱ በእልልታ
ዓለምን ተጋርተው
ሳቅና እንባን አዝለው
እየተገፋፉ መንገዱ ጠቧቸው
ሁሉንም በግዜ ሞቱ ሲጠራቸው
ተከትለን ሲሉኝ ቅደሙኝ አልኳቸው
እኔ ከሞት ተራ የምቀር መስሏቸው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ብዙ ሰው በዋይታ
ጥቂቱ በእልልታ
ዓለምን ተጋርተው
ሳቅና እንባን አዝለው
እየተገፋፉ መንገዱ ጠቧቸው
ሁሉንም በግዜ ሞቱ ሲጠራቸው
ተከትለን ሲሉኝ ቅደሙኝ አልኳቸው
እኔ ከሞት ተራ የምቀር መስሏቸው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
🔥13👍6😁4❤2
#እድሜ_ለሷ
አየሁ ራቁቷን
ውበቷን
እሳቷን
ልቤ በጣም ፈራ ድፍረቴ መከነ
ከጭኖቼ መሐል ድንኳን ተደኮነ
ና ትላለች ባይኗ
ሚሳኤል ጡቶቿን ተፊቴ ደግና
ፈራሁ ጠፋኝ አቅም
ከራዲዮኔ ውጭ ጡት ጠምዝዤ አላውቅም።
ከምኔው አቀፍኳት ከንፈሬስ እራሰ
ቋሚው ብቻ ቀርቶ ድንኳኔ ፈረሰ
ከምኔው እሳቷን አቀፍኩት እስክነድ
እንዴት በዚህ ፍጥነት ተሰራሁ እንደወንድ
በውበቷ ገዳም ገባሁኝ ምናኔ
አጎንባሹ ቀናሁ ለቀሪ ዘመኔ
ፍቅሯን በገሞራ ለውሳ ቀይጣ
ወንድ አርጋ ሸኘችኝ ሰራችኝ አቅልጣ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አየሁ ራቁቷን
ውበቷን
እሳቷን
ልቤ በጣም ፈራ ድፍረቴ መከነ
ከጭኖቼ መሐል ድንኳን ተደኮነ
ና ትላለች ባይኗ
ሚሳኤል ጡቶቿን ተፊቴ ደግና
ፈራሁ ጠፋኝ አቅም
ከራዲዮኔ ውጭ ጡት ጠምዝዤ አላውቅም።
ከምኔው አቀፍኳት ከንፈሬስ እራሰ
ቋሚው ብቻ ቀርቶ ድንኳኔ ፈረሰ
ከምኔው እሳቷን አቀፍኩት እስክነድ
እንዴት በዚህ ፍጥነት ተሰራሁ እንደወንድ
በውበቷ ገዳም ገባሁኝ ምናኔ
አጎንባሹ ቀናሁ ለቀሪ ዘመኔ
ፍቅሯን በገሞራ ለውሳ ቀይጣ
ወንድ አርጋ ሸኘችኝ ሰራችኝ አቅልጣ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤16👎3🔥3❤🔥2👍1
#ቀረሽ_እንደዋዛ
እንደ ፡ ድመቶቹ...
የትም ፡ እንደሚያድሩት
እንደ ፡ ስልክ ፡ እንጨቶች፣
እንደ ፡ ዛፍ ፡ ሀረጎች
እንደ ፡ ቤት ፡ ክዳኖቸ
ብርድ ፡ አቆራመደኝ ~ ስጠብቅ ፡ ስጠብቅ
ትመጫለሽ ፡ ብዬ...
ሳይ ፡ ማዶ ፡ ሳይ ፡ ማዶ ፣
የልጅነት ፡ ዐይኔ ፡ ሟሟ ፡ እንደ ፡ በረዶ፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ደቂቃ ፡ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ባዝን ፡ ባንጎራጉር፣
ትወጫለሽ ፡ ብዬ ፡ በበራፍሽ ፡ ብዞር፣
ብርድ ፡ አቆራመደኝ፣
የመንገድ ፡ መብራቶች ፡ አይተው ፡ አፌዙብኝ፣
ውርጩ ፡ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ፡ ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን ፡ አውቀዋል ፡ ያውቃሉ፣
መስኮቶች ፡ ጨልመው፣
ቤቶች ፡ ተቆልፈው...
ከተማው ፡ ሲተኛ ፡ አይተዋል ያያሉ፣
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገጣሚገብረክርስቶስ ደስታ
እንደ ፡ ድመቶቹ...
የትም ፡ እንደሚያድሩት
እንደ ፡ ስልክ ፡ እንጨቶች፣
እንደ ፡ ዛፍ ፡ ሀረጎች
እንደ ፡ ቤት ፡ ክዳኖቸ
ብርድ ፡ አቆራመደኝ ~ ስጠብቅ ፡ ስጠብቅ
ትመጫለሽ ፡ ብዬ...
ሳይ ፡ ማዶ ፡ ሳይ ፡ ማዶ ፣
የልጅነት ፡ ዐይኔ ፡ ሟሟ ፡ እንደ ፡ በረዶ፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ደቂቃ ፡ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ባዝን ፡ ባንጎራጉር፣
ትወጫለሽ ፡ ብዬ ፡ በበራፍሽ ፡ ብዞር፣
ብርድ ፡ አቆራመደኝ፣
የመንገድ ፡ መብራቶች ፡ አይተው ፡ አፌዙብኝ፣
ውርጩ ፡ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ፡ ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን ፡ አውቀዋል ፡ ያውቃሉ፣
መስኮቶች ፡ ጨልመው፣
ቤቶች ፡ ተቆልፈው...
ከተማው ፡ ሲተኛ ፡ አይተዋል ያያሉ፣
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገጣሚ
👏8❤6👍4🔥1
#አንችን_አይጠጋ
ያንጎራጎርሽልኝ በመረዋ ድምጽሽ
ሲያውደኝ የነበር ያ ሽቶ ጠረንሽ
ትራስ የነበሩኝ መክዳ ጡቶችሽ
እማኝ እንዲሆኑኝ ላድርጋቸው ነቃሽ
በዕውነት ላፈቀሩት መሆን መስዋዕት
የቆዬ ነውና ከአያት ቅድመ አያት
በወረት መደሰት እስኪያልፍ ወረት
ምኞትሽ መሆኑን አሁን አወቅሁት
ሕይወቴን አጋልጠሽ ለሕመም ለአደጋ
ፍቅሬን ቸል ብለሽ ከሔድሽ እሌላጋ
የኔውስ የኔነው ምንም አያሰጋ
ብቻ የኔ ሐዘን አንችን አይጠጋ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
ያንጎራጎርሽልኝ በመረዋ ድምጽሽ
ሲያውደኝ የነበር ያ ሽቶ ጠረንሽ
ትራስ የነበሩኝ መክዳ ጡቶችሽ
እማኝ እንዲሆኑኝ ላድርጋቸው ነቃሽ
በዕውነት ላፈቀሩት መሆን መስዋዕት
የቆዬ ነውና ከአያት ቅድመ አያት
በወረት መደሰት እስኪያልፍ ወረት
ምኞትሽ መሆኑን አሁን አወቅሁት
ሕይወቴን አጋልጠሽ ለሕመም ለአደጋ
ፍቅሬን ቸል ብለሽ ከሔድሽ እሌላጋ
የኔውስ የኔነው ምንም አያሰጋ
ብቻ የኔ ሐዘን አንችን አይጠጋ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
👍8
#ይመሻል_ይነጋል!!!
የከፋው ሰው እንጂ ህግን ያጓደለ፣
ከእግዚአብሔር እርቆ አድሮ የቀለለ፣
ግዜማ ቁጥር ነው ይመሻል ይነጋል፣
የተፈጥሮ ህጉን ጠብቆ ይጓዛል።
ጥፋቱ የሰው ነው ህግ የተላለፈ፣
በደልን በጉያው ደጋግሞ ያቀፈ።
ግዜ ነው አትበሉ ግዜ ምን አጠፋ?
ሰው እኮ ነው ዛሬም በቢጤው የከፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
የከፋው ሰው እንጂ ህግን ያጓደለ፣
ከእግዚአብሔር እርቆ አድሮ የቀለለ፣
ግዜማ ቁጥር ነው ይመሻል ይነጋል፣
የተፈጥሮ ህጉን ጠብቆ ይጓዛል።
ጥፋቱ የሰው ነው ህግ የተላለፈ፣
በደልን በጉያው ደጋግሞ ያቀፈ።
ግዜ ነው አትበሉ ግዜ ምን አጠፋ?
ሰው እኮ ነው ዛሬም በቢጤው የከፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍12❤5❤🔥1🔥1
#ሀገርህ_ናት_በቃ
ይቺው ናት ኢትዮጵያ
ሀገርህ ናት በቃ!
በዚች ንፍቀ ክበብ፤
አይምሽ እንጅ መሽቶ ፥ ማታው ከጠረቃ፤
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ ፥ ብቻዋን የተኛች
ከዓለም ተደብቃ!
አኪሯ ቀዝቅዞ ፥ "ያንቀላፋች ውበት"
ያንተው የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ ፥ ወይ አብረሃት ንቃ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ መኮንን
ይቺው ናት ኢትዮጵያ
ሀገርህ ናት በቃ!
በዚች ንፍቀ ክበብ፤
አይምሽ እንጅ መሽቶ ፥ ማታው ከጠረቃ፤
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ ፥ ብቻዋን የተኛች
ከዓለም ተደብቃ!
አኪሯ ቀዝቅዞ ፥ "ያንቀላፋች ውበት"
ያንተው የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ ፥ ወይ አብረሃት ንቃ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ መኮንን
👍18
#መንፈሴን_አመመኝ!!
ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
❤17👍7👏2😢2
#ትዝታ
ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
🥰8👍4👏4❤3
#ተራርቆ_ከእውነት
ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍17❤2😭2🔥1
#ፋኖስ_እና_ብርጭቆ
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ
እንዲህ ሲል ተጣላ - ከብርጭቆ ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሀን የምሰጥ
ጨለማን አጥፉቼ የምገላልጥ
አንተ ግን ተፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበኸኝ እንዲያው ተገትረህ።
አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ
ብርሀኔ እርቆ ደምቆ እንዳያበራ
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንክ ስራየን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሀኔ ይስፋ።
''እውነትማ ለንተ ከሆንኩኝ እንቅፋት፣ ልሂድልህ ብሎ ቢለቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰው የንፋስ ሽውታ
መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፉታ።
አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ፣
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሳ
ሰውም እንዲሁ ነው ያመጣል አበሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ
እንዲህ ሲል ተጣላ - ከብርጭቆ ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሀን የምሰጥ
ጨለማን አጥፉቼ የምገላልጥ
አንተ ግን ተፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበኸኝ እንዲያው ተገትረህ።
አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ
ብርሀኔ እርቆ ደምቆ እንዳያበራ
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንክ ስራየን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሀኔ ይስፋ።
''እውነትማ ለንተ ከሆንኩኝ እንቅፋት፣ ልሂድልህ ብሎ ቢለቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰው የንፋስ ሽውታ
መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፉታ።
አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ፣
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሳ
ሰውም እንዲሁ ነው ያመጣል አበሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
❤13👍6👎1
ሳቅ እንኳን ባትፈቅዱ ማልቀስ አትከልክሉ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰18👏6👍3
#ኮረዳ
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
❤13👍7👏4
#የምጡ_ጅማሬ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍20❤5🥰5🔥3👏3
ዓለም ቅንዝረኛ ብዙ ባል አግብታ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
🥰11👍7🏆1
#ችግር
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
👍13
#የተቃርኖ_ሕግ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_
👍9