ግጥም
4.25K subscribers
27 photos
1 video
11 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ታማሁኝ_በፍቅር

የዘንድሮማ ሰው ማውራት ያውቅበታል
ልቡን ወስደዋለች ብሎ ያዋሽካል
    ሐሜተኞች አሙኝ ደካማ ነው ብለው
    መልካም ልጅ ባፈቅር ድካሜ እምን ላይ ነው
ኃጢአት አደለም ወይ ወንጀል ማፍቀር
እስቲ ተውኝ ሰዎች በሰላም ልኑር
     ለኑሮ መዋተት መውጣትና መውረድ
     መቺ አነሰኝና በፍቅር ልዋረድ
ይኸ ሀሜታቸው እንዳይሆን እውነት
ተይ አታንገላችኝ በፍቅርሽ አልሙት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ደሪሲ ታደለ ብጡል
👍11
#አንቺ_ምን_አለብሽ

ባልጠበቀ ስንኝ በላላ ቋጠሮ
ውበትሽን ለመግለጽ ስጭር እንደ ዶሮ
ቤት መታ ቤት ደፋ እያልኩኝ ለእራሴ
ስደክም ስባክን ስትጨነቅ ነፍሴ
አንቺ ምን አለብሽ ተኝተሽ አልሚ
ክረምቱን በሙቀት ሳይበርድሽ ክረሚ
ብዙ አድናቂ ያለሽ ሲጭር የሚያነጋ
ውበትሽን አወዳሽ የገጣሚ መንጋ
ቃላትን አዋቅሮ ይጭራል ይጽፋል
ውበትሽን ለመግለጽ ስንኝ ይቋጥራል
አንቺ ተኝተሻል አይገድሽ አይሞቅሽ
ይብላኝ ለማይተኛው ቆሞ ለሚያልምሽ
በክረምቱ ቆፈን ብርድ እያነዘረው
ሲያስብሽ አዳሪው እልፍ አላፍ ጫሪ ነው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍13👏2
#ነጠብጣብ_ሀሳቦች

ሰማይ ከሚመክን ይፀንስ መከራ
ያርግፍ" ያርግፍ" ያርግፍ" መዓት እያፈራ
የሣት ዛፍ ባለበት ሰደድ ላያስፈራ።
ከሐምሌት ጋር ሞቷል ፣ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፣ አለመሆን የለም፤
ሸክም ፀጋ ሆኗል ፀጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ ትከሻህን አስፋ።
አንድ ህልም እንደ ጠጅ፣ እየደጋገሙ
ንግር፣ ትንቢት ሳይሆን ታሪክ እያለሙ
ተኝቶ መነሳት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሳት
ነፍሴን እንቆቅልሽ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም
👍6🔥1
#ዋ!

ዓይኔ ወደደሽ ስልሽ
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ
ስለት
ምኞትሽ ሰመረ አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው እንደዘበት።
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ ዓይን ዛሬም አይሻለው።
ደሞ እንደዚህ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሻለሁ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ በረከት በላይነህ
13👍6🤯1
አንድ ⭐️ እንኳን የሚሰጠኝ ሰው ጠፋ ቆይ ማልቀስ ይሻላል?
🥰20
#መራራቅ

ቅዠታም አዳሩን
ጨፍጋጋ ውሎዉን
ዝብርቅርቅ ተስፋውን
ደረቅ ትዝታውን...
በይሉኝታ ኮፈን እየጠቀለለ
ከጥርሱ ሲጥለው
ተቀባይ ይሻማል ሳቅ እየመሰለው።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ በረከት በላይነህ
👍9🥰6👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ምሥጢር

ምሥጢር ነው ያልከውን ለሌላ ሰው መንገር
መሆኑን ተረዳ በገዛጅ መታሰር
         ግን ምሥጢር ለባዕድ እስካልተነገረ
          ምሥጢርህ ምሥጢር ነው ባንተው ከታሠረ
ምሥጢርህን ሌላ ሰው ካየና ከሰማው
ያባከንከው ምሥጢር ላንተ ዘብጥያህ ነው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ደሪሲ ታደለ ብጡል
👍9😁1
ተቃቅፈን ስንሄድ ለሚያገላግሉ
ጉንጭሽን ስስምሽ ነከሳት ለሚሉ
ከፍቅራችን ይልቅ ጸብ ለናፈቃቸው
ከራስሽ ተጣልተሽ...
የወሬ ማድመቂያ ሰበብ አትሁኛቸው
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ አቤል ሽመልስ
👏10👍43🔥2
#አልቻልኩም
(አብሮ መሰደድ)

የልቤ ሰመመን የፍቅሬ ትዝታ
የዓይኖቼ ብሌን የሕይወቴ አለኝታ
      አኔን ከጠላሽኝ ከናቅሽ ፍቅሬን
     ከመሔዴ በፊት ስሚማ እሮሮዬን
ልዝብ አንደበትሽ ታጋሽ ተፈጥሮሽ
አስተዋይ አእምሮሽ ንጹሕ ልቦናሽ
      ተባብሮ ከዓይኖችሽ ከውበትሽ ጋር
      ልቤን ማርኮ ወስዶ አሰረው በፍቅር
ኮኮብ ዓይኖችሽን ጉብል ጉንጮችሽን
የቀጭኔ ጭራ መሳይ ጸጉሮችሽን
       ለጋ ከንፈርሽን ወለላ እንደማር
       ንብረቴ ለማድረግ ምኞቴ ነበር
አይቻልም ካልሽኝ ማቀፍ ሽንጥሽን
እኔ አልፈቅድም ካልሽኝ መሳም ከንፈርሽን
       ፍቅሬን መግለጥ ካልቻልኩ የልቤን መንገር
       በሰላም እናብቃው መጣላት ይቅር
እንሰነባበት ነውና መጓዜ
ጻፊልኝ ቢቻልሽ ትዝ ባልኩሽ ጊዜ
       ስለተለበለብኩ በፍቅርሽ ንዳድ
       አልቻልኩም ለመኖር አብሮ መሰደድ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደራሲ ታደለ ብጡል
👍14
#ዝምታም_ይጮኻል

የምላስ ጋጋታ ጀሮን ባይጋርደው
ይደመጥ ነበረ ዝምታም ቃል አለው
በህሊና ከሳሽ በልብ ዳኝነት
የዝምታ ችሎት የተሰየመ እለት
ሁሉም ተናጋሪ ጸጥ! ቢል ላንድ አፍታ
እመኑኝ ይጮሃል ድምጽ አለው ዝምታ
የተፈጥሮ ችሎት በልብ ሚዛን ቢረግጥ
ዓለም ለሴኮንዶች መናገርን ቢል ጸጥ
ያኔ ይደመጣል ቃል አለው ዝምታ
ገለል ሲልለት የምላስ ውካታ
ጆሮ ባይጋረድ በቃላት ጋጋታ
መጮኽ በጀመረ የስንቱ ዝምታ
የሰው ልጅ ቢኖረው ስድስተኛ ህዋስ
ይሰማው ነበረ ዝምታችን ሲፈስ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍9👏64🥰2
#መዋሸክ

ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ብልሹ
መዋሸት ብቻ ነው ትልቁም ትንሹ
      ባገራችን ባህል በአገራችን ልምድ
      አስነዋሪ ነበር መዋሸክ መልመድ
ግን የዘመኑ ሰው ልማድ ያደረገው
ትንሹም ትልቁም ሰውን ማማትን ነው
      ለዚች ላጭር ዕድሜ መቶ ለማትሞላ
      እንዴት ሰው ይኖራል ሰውን እያጣላ?
የመዋሽክና የሐሜት ዘይቤ
አያስፈልገኝም ይራቅ ካጠገቤ
     ብሎ የሚል ወጣት ወይም አረጋዊ
     ምነዋ በኖረ በሐቅ ኢትዮጵያዊ
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደራሲ ታደለ ብጡል
👏6👍43🙏3
#ቅደሙኝ_አልኳቸው

ብዙ ሰው በዋይታ
ጥቂቱ በእልልታ
ዓለምን ተጋርተው
ሳቅና እንባን አዝለው
እየተገፋፉ መንገዱ ጠቧቸው
ሁሉንም በግዜ ሞቱ ሲጠራቸው
ተከትለን ሲሉኝ ቅደሙኝ አልኳቸው
እኔ ከሞት ተራ የምቀር መስሏቸው።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🔥13👍6😁42
#እድሜ_ለሷ

አየሁ ራቁቷን
ውበቷን
እሳቷን
ልቤ በጣም ፈራ ድፍረቴ መከነ
ከጭኖቼ መሐል ድንኳን ተደኮነ
ና ትላለች ባይኗ
ሚሳኤል ጡቶቿን ተፊቴ ደግና
ፈራሁ ጠፋኝ አቅም
ከራዲዮኔ ውጭ ጡት ጠምዝዤ አላውቅም።
ከምኔው አቀፍኳት ከንፈሬስ እራሰ
ቋሚው ብቻ ቀርቶ ድንኳኔ ፈረሰ
ከምኔው እሳቷን አቀፍኩት እስክነድ
እንዴት በዚህ ፍጥነት ተሰራሁ እንደወንድ
በውበቷ ገዳም ገባሁኝ ምናኔ
አጎንባሹ ቀናሁ ለቀሪ ዘመኔ
ፍቅሯን በገሞራ ለውሳ ቀይጣ
ወንድ አርጋ ሸኘችኝ ሰራችኝ አቅልጣ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
16👎3🔥3❤‍🔥2👍1
#ቀረሽ_እንደዋዛ

እንደ ፡ ድመቶቹ...
የትም ፡ እንደሚያድሩት
እንደ ፡ ስልክ ፡ እንጨቶች፣
እንደ ፡ ዛፍ ፡ ሀረጎች
እንደ ፡ ቤት ፡ ክዳኖቸ
ብርድ ፡ አቆራመደኝ ~ ስጠብቅ ፡ ስጠብቅ
ትመጫለሽ ፡ ብዬ...
ሳይ ፡ ማዶ ፡ ሳይ ፡ ማዶ ፣
የልጅነት ፡ ዐይኔ ፡ ሟሟ ፡ እንደ ፡ በረዶ፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ደቂቃ ፡ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ፡ ብዬ ፡ ባዝን ፡ ባንጎራጉር፣
ትወጫለሽ ፡ ብዬ ፡ በበራፍሽ ፡ ብዞር፣
ብርድ ፡ አቆራመደኝ፣
የመንገድ ፡ መብራቶች ፡ አይተው ፡ አፌዙብኝ፣
ውርጩ ፡ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ፡ ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን ፡ አውቀዋል ፡ ያውቃሉ፣
መስኮቶች ፡ ጨልመው፣
ቤቶች ፡ ተቆልፈው...
ከተማው ፡ ሲተኛ ፡ አይተዋል ያያሉ፣
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ
👏86👍4🔥1
#አንችን_አይጠጋ

ያንጎራጎርሽልኝ በመረዋ ድምጽሽ
ሲያውደኝ የነበር ያ ሽቶ ጠረንሽ
ትራስ የነበሩኝ መክዳ ጡቶችሽ
እማኝ እንዲሆኑኝ ላድርጋቸው ነቃሽ
          በዕውነት ላፈቀሩት መሆን መስዋዕት
          የቆዬ ነውና ከአያት ቅድመ አያት
          በወረት መደሰት እስኪያልፍ ወረት
          ምኞትሽ መሆኑን አሁን አወቅሁት
ሕይወቴን አጋልጠሽ ለሕመም ለአደጋ
ፍቅሬን ቸል ብለሽ ከሔድሽ እሌላጋ
የኔውስ የኔነው ምንም አያሰጋ
ብቻ የኔ ሐዘን አንችን አይጠጋ!
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደራሲ ታደለ ብጡል
👍8
#ይመሻል_ይነጋል!!!

የከፋው ሰው እንጂ ህግን ያጓደለ፣
ከእግዚአብሔር እርቆ አድሮ የቀለለ፣
ግዜማ ቁጥር ነው ይመሻል ይነጋል፣
የተፈጥሮ ህጉን ጠብቆ ይጓዛል።
ጥፋቱ የሰው ነው ህግ የተላለፈ፣
በደልን በጉያው ደጋግሞ ያቀፈ።
ግዜ ነው አትበሉ ግዜ ምን አጠፋ?
ሰው እኮ ነው ዛሬም በቢጤው የከፋ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍125❤‍🔥1🔥1
#ሀገርህ_ናት_በቃ

      ይቺው ናት ኢትዮጵያ
        ሀገርህ ናት በቃ!
       በዚች ንፍቀ ክበብ፤
አይምሽ እንጅ መሽቶ ፥ ማታው ከጠረቃ፤
  የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ ፥ ብቻዋን የተኛች
        ከዓለም ተደብቃ!
አኪሯ ቀዝቅዞ ፥ "ያንቀላፋች ውበት"
         ያንተው የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ ፥ ወይ አብረሃት ንቃ!!
             @gitm_post
         ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
        ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ነብዩ መኮንን
👍18
#መንፈሴን_አመመኝ!!

ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
17👍7👏2😢2
#ትዝታ

ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
      የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
      እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
      በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
      አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
        ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
        ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
        ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
        እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ደራሲ ታደለ ብጡል
🥰8👍4👏43
#ተራርቆ_ከእውነት

ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍172😭2🔥1