ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ተራርቆ_ከእውነት

ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏84👍4
#እባካችሁ_ተውኝ!!!

እንኳን የሰው ሀጢአት ደርቤ ሊቀለኝ
የእራሴንም አልቻልኩ እያንገዳገደኝ
የእኔ ነውር በዝቶ ከብዶኝ እያያችሁ
የሌላውን ሸክም ደርብ ማለታችሁ
በየትኛው አቅሜ ችዬ ልሸከመው
ሁሉም የስራውን በግሉ ይቻለው
ሰው የእራሱን በደል እያለባበሰ
የሌላውን ሀጢአት ቆሞ እየቀደሰ
ሲበርደው ይኖራል ፀጋውን ተገፎ
በሰው ጉዳይ ገብቶ እያደር ወፍፎ
እባካችሁ ተውኝ የእኔም አቅቶኛል
ከአቅሜ በላይ በዝቶ ዘንድሮስ ከብዶኛል
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍15😭42👏1
#ባልተቋጨ_ፍቅር

ያልረሳውን እውነት የረሳ ለመምሰል
ስንቱ ይታገላል ትዝታን ለማቅለል
በልቡ ማህደር ፍቅርን ተሸክሞ
በውሸት ፈገግታ እራሱን አስታሞ
ዛሬን አስመስሎ ለትላንት የሚኖር
ብዙ አለ ታማሚ ባልተቋጨ ፍቅር
በልቡ እያነባ በጥርሱ እየሳቀ
ደስተኛ መስሎ ግን የተጨነቀ
ምዕራፍ ባጣ ታሪክ እልባት በሌለው
በትላንት ትዝታ ዛሬን የሚኖረው
በውሸት ፈገግታ የሚወዛወዘው
ስንት አለ ባለበት እሱን ቤት ይቁጠረው።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
6👍5🔥4👏2🥰1
#ተራ_ነሽ_ለልቤ

እንደ ዛሬው ሳትሆኝ ክፋት ሳትማሪ
አውቄያለሁ ብለሽ ዘርንም ሳትቆጥሪ
በንጹሕ ልቦናሽ ሰው በመሆን ቅኔ
እወድሽ ነበረ አልወደሽም እኔ።
ስልጣኔ መስሎሽ እርቃን እውቀት ይዘሽ
ልብሽ ሲደነድን ክብርሽም ሲሟሽሽ
ጠላሁሽ ከልቤ በርካሽ ጸባይሽ
ተራ ነሽ ለልቤ የልቤን ልንገርሽ
ያኔ! ግን በእውነቱ ልብሽ የከበረ
ሰው የማክበር ዜማሽ ሰውነት ነበረ
አንደበትሽ ማርማር ለእግዚአብሔር ያደረ
ያ " ሁሉ ቀረና ዘምኛለሁ ብለሽ ቅሉም ተሰበረ
አሁን አልወድሽም የለሽም ከሆዴ
ስልጣኔሽ ሁሉ የቂል ሆኗል ውዴ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍103🥰1
#ፖለቲካ_አልባ_ስንኝ

ዳሌሽ ያንቺ ነው? ንገሪኝ በሞቴ
ሰው ሰራሽ ከሆነ እንዳትገቢ ቤቴ
ከደረትሽ ገዝፈው የተወደሩቱ
ከጦር በላይ ሾለው የተቀሰሩቱ
ሁለቱ መንትዮች እውነት ያንቺ ናቸው?
ንገሪኝ ሳትፈሪ ዘመኑ ፎርጅድ ነው።
ከዐይኖችሽ ሽፋሽፍት የተንጨባረሩት
ከከንፈርሽ ዳርዳር ደምቀው የሚታዩት
ጸጉርሽን አስንቀው የሚንዘናፈሉት
ውዴ የማናቸው? እውነቱን እናውራ
ከተፈጥሮ በላይ ምን አለ ሚያኮራ?
አትመሪ አልልም መድመቅሽን አልጠላም
የማን እንደሆኑ ማወቅ ግን አይከፋም።
ተፈጥሮን አስንቀው ባንቺ የነገሡ
ማንነት ያስናቁ ማን ናቸው? እነርሱ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏12👍32❤‍🔥1👎1🥰1
#ጀሮ_ባጣ_ሀገር

አድማጭ በሌለበት በነጠፈ ጀሮ
በስንኝ ቋጠሮ የሚያሰሙ እሮሮ
ዜማው ቢሽሞነሞን ቃላቱ ተመርጦ
ክራሩ ቢሰደር በዋሽንት አጊጦ
አድማጭ በሌለበት ብሶት ቢደረደር
ጀሮ ዋጋ ላይሰጥ ምላስ ቢቀባጥር
ቅኔ ምን ሊፈይድ ዜማስ ምን አባቱ!!!
ሰሚ በሌለው ቤት መባከን ነው ከንቱ
ከበሮ ቢደለቅ መሰንቆ ቢያነባ ዋሽንት እህ እህ ቢል
የስንኝ ቋጠሮ ከዜማው ቃል ቢጥል
ሁሉም ተዋህደው ተስማምተው ቢገጥሙ
ጀሮ ባጣ ሀገር ትርፉ ነው ድካሙ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍93🥰2
#በእንባ_የራሰ_ፍትፍት

ቀበሌ ሂድና ፥ ድህነት አስመስክር
ይላል አሉ ሃብታም ፥ መፅውቶ ሲሰክር

እማኝ ጥራ ይላል ፤ ቀበሌ በተራው
እማኙ ሲመጣ ፤ ይንዛዛል ወረፋው

           አሹቅ ከጨበጠ...
ከነዳይ መዳፋ ላይ ፥ ሹም እየዘገነ
"ድሃ!" መባል እንኳን ፥ ገንዘብ ላለው ሆነ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በርናባስ ከበደ
👍12👏6
#ዝኑፋ_ወቀሳ

        ይለኛል ታዛቢ...
"በእኛ ተረማምዶ - ስኬቱን ሸመተ፤
ሲመቸው ፣ ሲደላው - ትቶን ሰነበተ!"
         ይለኛል ታዛቢ...
"አቅፈን አሳድገን - ከሰው መሐል ለየን፤
አለፈለትና - ዞር ብሎም አያዬን!"
         እኔ ግን እላለሁ...
       "ስህተት የለብኝም፤
ያለፍኩበት ሁሉ አላሻገረኝም፤
የረገጥኩት ሁሉ አልተሸከመኝም!"
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በረከት በላይነህ
10👍2👏1
#ውሻሽን_እሰሪው

አንችን ስመለከት እንቅፋት መትቶኛል
መምጫሽን ስጠብቅ ፀሐይ አጥቁሮኛል
ባጥር ላይሽ ብዬም ውሻችሁ ነክሶኛል
          ያውም ክፉ ውሻ...
መምጫው ሳይታወቅ አድብቶ ሚያጠቃ
ገዳይ መሬት ጥሎ የሚለውስ ጭቃ
እችን ስንጥር እግሬን ከአፉ አስገብቶ
አንከባሎኝ ሄዷል እመሬት ጎትቶ
      ውሻሽን እሰሪው...
ይህን ሀይለኝነት ከማንስ ተማረ አሳዳጊው አንቺ
አትንኩኝ የምትይ አመል የነፈገሽ ለሰው ማትመቺ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
      አቤል ሽመልስ
10👍2
#ለሰውነቱ_ክብር

ሰው ኑሮን ለመኖር ሌት ተቀን መዋተት
መውጣት መውረድና እድሜ ሙሉ መልፋት
ፍዳ ነው ፍዳ ነው የሰው ልጆች ሕይወት
       ሲያገኙ መደሰት ሲያጡ መሸማቀቅ
       ተለምዶ መሆኑ በገሀድ ሲታወቅ
       ታድያ ዘመናይ ሰው ለምን ይንደላቀቅ?
ይኸን ውጣ ውረድ የኑሮ ሚዛን
ማሰብ መመራመር መረዳት ሐቁን
ማስተካከል ያሻል በማመጣጠን
       ይኸ የዓለም ጣጣ እንዲስተካከል
       ምሁር መኃይሙ ሳይነጣጠል
       ለሰውነቱ ክብር ሊሰጥ ይገባል
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ደራሲ ታደለ ብጡል
👍4
#በሰው_ልብ_ከተማ

ስቆ ማለፍ እንጅ ዘንድሮን ለከርሞ
በፈገግታ ዜማ ብሶትን አስታሞ
የሌለንን ትተን ባለን ካልተደሰትን
ጊዜውስ ሞክሯል አዙሮ ሊጥለን
የሳቃችን ሚዜ ሀዘናችን ሆኖ
በጥርሳችን ጋቢ ከውስጥ ተከድኖ
ሳቃችን ሙሽራ ሐዘናችን ሚዜ
አብረው እየበሉ ሳቅና ትካዜ
ጥርሳችን ቢስቅም ሐዘንን ሸሽጎ
ጥርስ እየደመቀ መከራን ሚዜ አርጎ
ደስታና ሐዘን አብረው እቁብ ጣሉ
በሰው ልብ ድንኳን ድግስ እየበሉ
በስቃይ ከተማ ድርሻቸውን ይዘው
የፈረቃ ስልጣን ስፍራቸውን ወስደው
ይፈራረቃሉ በሰው ልብ አዳራሽ
ችሎትን ዘርግተው በሌለበት ከሳሽ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍13👏91
#በምናልባት_ኑሮ

  አይቦዝን አንቀልባው
   አይሞላም ጉድጓዱ
ሺሆች ሞተው ቢያድሩ
    ሺሆች ተወለዱ
    ይመሻል ይነጋል
    ያው እንደልማዱ፤

መሬት ባህር ሆኖ ፥ ድሃን ሰለቀጠው
ትልልቁ ቪላ ፥ ትንሹን ቤት ዋጠው
በመስታወት ጫካ ፥ በጡብ በብረት ደን
አየሁ ባደባባይ ፥ ሰው በሰው ሲታደን፤

   ማን በገላገለኝ ፥ የጄን ሰዓት ሰብሮ
   በምናልባት አገር ፥ በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጅ ፥ ማን ያቅዳል ደፍሮ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
10👍4🔥4🥰1
#ታማሁኝ_በፍቅር

የዘንድሮማ ሰው ማውራት ያውቅበታል
ልቡን ወስደዋለች ብሎ ያዋሽካል
    ሐሜተኞች አሙኝ ደካማ ነው ብለው
    መልካም ልጅ ባፈቅር ድካሜ እምን ላይ ነው
ኃጢአት አደለም ወይ ወንጀል ማፍቀር
እስቲ ተውኝ ሰዎች በሰላም ልኑር
     ለኑሮ መዋተት መውጣትና መውረድ
     መቺ አነሰኝና በፍቅር ልዋረድ
ይኸ ሀሜታቸው እንዳይሆን እውነት
ተይ አታንገላችኝ በፍቅርሽ አልሙት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ደሪሲ ታደለ ብጡል
👍11
#አንቺ_ምን_አለብሽ

ባልጠበቀ ስንኝ በላላ ቋጠሮ
ውበትሽን ለመግለጽ ስጭር እንደ ዶሮ
ቤት መታ ቤት ደፋ እያልኩኝ ለእራሴ
ስደክም ስባክን ስትጨነቅ ነፍሴ
አንቺ ምን አለብሽ ተኝተሽ አልሚ
ክረምቱን በሙቀት ሳይበርድሽ ክረሚ
ብዙ አድናቂ ያለሽ ሲጭር የሚያነጋ
ውበትሽን አወዳሽ የገጣሚ መንጋ
ቃላትን አዋቅሮ ይጭራል ይጽፋል
ውበትሽን ለመግለጽ ስንኝ ይቋጥራል
አንቺ ተኝተሻል አይገድሽ አይሞቅሽ
ይብላኝ ለማይተኛው ቆሞ ለሚያልምሽ
በክረምቱ ቆፈን ብርድ እያነዘረው
ሲያስብሽ አዳሪው እልፍ አላፍ ጫሪ ነው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍13👏2
#ነጠብጣብ_ሀሳቦች

ሰማይ ከሚመክን ይፀንስ መከራ
ያርግፍ" ያርግፍ" ያርግፍ" መዓት እያፈራ
የሣት ዛፍ ባለበት ሰደድ ላያስፈራ።
ከሐምሌት ጋር ሞቷል ፣ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፣ አለመሆን የለም፤
ሸክም ፀጋ ሆኗል ፀጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ ትከሻህን አስፋ።
አንድ ህልም እንደ ጠጅ፣ እየደጋገሙ
ንግር፣ ትንቢት ሳይሆን ታሪክ እያለሙ
ተኝቶ መነሳት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሳት
ነፍሴን እንቆቅልሽ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም
👍6🔥1
#ዋ!

ዓይኔ ወደደሽ ስልሽ
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ
ስለት
ምኞትሽ ሰመረ አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው እንደዘበት።
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ ዓይን ዛሬም አይሻለው።
ደሞ እንደዚህ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሻለሁ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ በረከት በላይነህ
13👍6🤯1
አንድ ⭐️ እንኳን የሚሰጠኝ ሰው ጠፋ ቆይ ማልቀስ ይሻላል?
🥰20
#መራራቅ

ቅዠታም አዳሩን
ጨፍጋጋ ውሎዉን
ዝብርቅርቅ ተስፋውን
ደረቅ ትዝታውን...
በይሉኝታ ኮፈን እየጠቀለለ
ከጥርሱ ሲጥለው
ተቀባይ ይሻማል ሳቅ እየመሰለው።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ በረከት በላይነህ
👍9🥰6👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ምሥጢር

ምሥጢር ነው ያልከውን ለሌላ ሰው መንገር
መሆኑን ተረዳ በገዛጅ መታሰር
         ግን ምሥጢር ለባዕድ እስካልተነገረ
          ምሥጢርህ ምሥጢር ነው ባንተው ከታሠረ
ምሥጢርህን ሌላ ሰው ካየና ከሰማው
ያባከንከው ምሥጢር ላንተ ዘብጥያህ ነው
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ደሪሲ ታደለ ብጡል
👍9😁1
ተቃቅፈን ስንሄድ ለሚያገላግሉ
ጉንጭሽን ስስምሽ ነከሳት ለሚሉ
ከፍቅራችን ይልቅ ጸብ ለናፈቃቸው
ከራስሽ ተጣልተሽ...
የወሬ ማድመቂያ ሰበብ አትሁኛቸው
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ አቤል ሽመልስ
👏10👍43🔥2