ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ህይወት_ፊልም_በሆነች

ሪሞት ቢኖረው ግዜ የእጅ ስራ
ማሳለፍ መመለስ በተራ በተራ
ደጉን ወደሗላ ክፉውን ወደፊት
መቆጣጠር ቢቻል ፊልም ሆና ህይወት ።
የትላንቱን ውብ ቀን ከዛሬ መልሶ
ደግ ደጉን ብቻ ለማየት ከልሶ
መርጦ የሚኖሯት በዘውግ የተቃኘች
ደራሲው የጻፉት ህይወት ፊልም በሆነች።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍6👏32🔥1
#በሰው_ልብ_ከተማ

ስቆ ማለፍ እንጅ ዘንድሮን ለከርሞ
በፈገግታ ዜማ ብሶትን አስታሞ
የሌለንን ትተን ባለን ካልተደሰትን
ጊዜውስ ሞክሯል አዙሮ ሊጥለን
የሳቃችን ሚዜ ሀዘናችን ሆኖ
በጥርሳችን ጋቢ ከውስጥ ተከድኖ
ሳቃችን ሙሽራ ሐዘናችን ሚዜ
አብረው እየበሉ ሳቅና ትካዜ
ጥርሳችን ቢስቅም ሐዘንን ሸሽጎ
ጥርስ እየደመቀ መከራን ሚዜ አርጎ
ደስታና ሐዘን አብረው እቁብ ጣሉ
በሰው ልብ ድንኳን ድግስ እየበሉ
በስቃይ ከተማ ድርሻቸውን ይዘው
የፈረቃ ስልጣን ስፍራቸውን ወስደው
ይፈራረቃሉ በሰው ልብ አዳራሽ
ችሎትን ዘርግተው በሌለበት ከሳሽ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
12👍8🔥1
#ላመኑት_ብቻ_ነው!

የመስቀሉ ትርጉም ቅኔ ነው ምስጢሩ
በዋዛ አይፈታም ማመን ካልጀመሩ
ላመኑት ብቻ ነው የመስቀሉ ድህነት
ለከዱት ቀልድ ነው ይፈልጋል እውነት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#እንኳን_አደረሳችሁ
16👍6😁2
መልክ ቁንጅናሽን ውበትሽን አይቼ
ከቆምኩበት ቀረሁ ግራ ተጋብቼ
ግራ እንደተጋባሁ መላው ቢጠፋኝ
ሰርቄያት ልጥፋ አልኩኝ ማንም ሳያየኝ
      ግና ምን ያደርጋል.....
ሰርቄሽ ብጠፋ ማንም ሳያየኝ
ፈረሰኛ አባትሽ ከፊት ቀደሙኝ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
😁10👏9👍4🏆2😱1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍4🙏3
እሺ ስላላሺኝ ፍቅሬን ተቀብለሽ
እኔም ወድሃለው ባትይኝ  መልሰሽ
አንቺ ባይኖረሽም እንደ እኔ ዓይነት ስሜት
ጨለማ ሳትሆኝ ብርሃን ነሽ ለእኔ ቤት

          #ለምን?

ብዙ ሳልደክምብሽ አንዲያው በባዶ ህልም
ተስፋ  በማደረግ ዉስጥ እራሴም ሳልደክም
ስለ አዳንሺኝ እኔን ከቶ ከአጉል ምኞት
ብርሃን ነሽ አንቺ ሻማየ እና ማዶት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ገጣሚ_ገላና ዳንዴና
👍9😁4👏21
ከነፋስ ለሚፈጥን ለተወርዋሪ እድሜ
ለምን ቂምን ላትርፍ ሰውን አስቀይሜ
ለተሰፈረ ቀን ለማይጨምር መኖር
በጥላቻ ስካር እኔ አላጣም ፍቅር።
        
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍156
#ያልጣዱት_አይበስልም

ፍቅር እንደ ዝናብ ከሰማይ አይወርድም
         ያበባ መደብ ነው
በሰው የሚታነፅ ፡ በሰው የሚወድም
ተዘርቶብን እንጅ ፡ ተሰብከን አንወድም።
"ወዳጄ ወዳጄ" የሚያቀነቅኑ
አገር ያቀኑ ለት መች ልብን አቀኑ
       ሳይወጡ ሳይወርዱ
ውብ ስራን ከውብ ቃል ፡ ሳያስተባብሩ
ከድሜ እና ከምቾት ቆርሰው ሳይገብሩ
         ፍቅር መች ይፈልቃል?
በስብከት በምልጃ በየዋህ ሰዎች ህልም
            ያልጣዱት አይበስልም
            ያልዘሩት አይበቅልም።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዪም
👍7👏43
እኔው ለኔ አልቅሼ እኔው ለኔ ስቄ
በውጣ ውረዱ ታሪኬን አድምቄ!!!
ዛሬን አይቻለሁ ትላንትን አልፌ
ጊዜን እየቆጠርኩ ቀናትን ገፍፌ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰64👍1
#ኑሪልኝ_እህቴ

ክፉ አይንካሽ ውዴ ኑሪልኝ በጤና
የደስታዬ ምስጢር የሂወቴ ፍና
ስከፋም ስደሰት ሁኝልኝ ከጎኔ
የሁልግዜ አጋሬ የመኖሬ ቅኔ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍74👏3
#ሙግት

ጊዜ ለሰው ህይወት
ዘበት አይታክተው
እኔም ምላሽ ባጣም
መጠየቄን አልተው።
ኩታ ገጠም ናቸው
አልፋና ኦሜጋ
እንዴት ቀን ይመሻል
በቅጡ ሳይነጋ?
ማን ዘረፈው ጠጉሬን?
ማን አሰረው እግሬን?
ጉልበቴን ምን በላው?
አቅሜን ማን ወረሰው?
ተወልዶ ሳይጨርስ
እንዴት ያረጃል ሰው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዪም
16👍9
#ያንተ_ዘር_የቱ_ነው?

ዘር ቁጠር ይለኛል ሰው መሆኑን ትቶ
ገላ አፈር መሆኑን መሞቱን ዘንግቶ
እስኪ በል ንገረኝ ያንተ ዘር የቱ ነው?!
ከተደረደሩት ብሔርህስ ማነው?!
አየህ ሰው ከንቱ ነው አይኖርም ዘላለም
ቋሚ ፈጣሪ እንጅ ቋሚ ብሔር የለም!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍15👏2
" #ከየትኛው_ላይ_ነን?!!!"

ወደፊት መጥተናል? ወይ ሗላ ቀርተናል?
ይኼ የእኔ ትውልድ ግራ ያጋባኛል፤
ድሮ ላይ ነው ስለው ዛሬ ላይ ነኝ ይላል፤
በዛሬ ስሰፍረው ትላንት ላይ ይገኛል ፤
የትኛው ዘመን ላይ ይሆን የቀረነው?
ከአለፈው ከሌለን አሁንን ካልያዝነው?
ከባቢሎን ህዝቦች የባሰ ተቃርኖ፤
እንዲህ የለያየን በሀሳብ በታትኖ፤
ከፊት ነን ከሗላ ወይስ በትላንቱ?
የእኔ ዘመን ትውልድ የቱ ነው እውነቱ?
ወይ በአለፈው አይኖር? ከዛሬም ተጣልቶ፤
ከሁለቱም ሳይሆን መሀል መንገድ ቀርቶ፤
ወዲህ ነው ስትለው ወዲያ ነው እያለ፤
ወዲያ ነው ስትለው ወዲህ ከዘለለ?
የእኔ ዘመን ትውልድ ከየትኛው ላይ ነው?
እንኳንስ ሊያስረዳ ለራሱም  ያልገባው፤
የትኛው ላይ ይሆን መንገዱ የጠፋው?
በሀሳብ ተቃርኖ መታረቅ ያቃተው?
ከትላንቱም የለ ከዛሬው የራቀ፤
እንኳንስ ከሌላ ከእራስ ያልታረቀ፤
ምን እንደሚፈልግ ማንስ ምን አወቀ?
ከባለፈው ሳይኖር በአሁን ያልደመቀ፤
ያልገባኝ ያልገባን አንድ ነገር አለ!
ከትላንት ከዛሬም ከየትም የሌለ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍124🔥4
#የኔነሽ

የምጠረጥረው ፥ የማልጠረጥረው
ቄሱ መነኮሱ ፥ ወታደር ደብተራው
           ያም የኔነሽ ሲላት፤
           ያም የኔነሽ ሲላት፤
  ለበለበኝ ፍቅር አቃጠለኝ ቅናት
ወይ ጠንካራ ክንዴ ፥ ጉልበቴ አያስቀራት!
   እንዴት የብቻዬ ፥ የግሌ ላድርጋት?
ሰው በጠራት ቁጥር ፥ ባልነቴ ሟሟ
የሰማኒያ ሚስቴ ፥ የኔነሽ ነው ስሟ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደራሲ ይስማዕክ ወርቁ
😁17👍84🔥2
" #ይገለባበጣል "

ጠላቴ አትደሰት ለእኔ ተራ መውደቅ
መነሳቴ አይቀርም ነግ ለኔ በል ይልቅ
ይገለባበጣል ጊዜ ቋሚ አይደለም
ሳይወድቅ የኖረ ሰው እስከዛሬ የለም
የወደቀው ቆሞ የቆመው ይወድቃል
ይልቅ መደጋገፍ ለሁሉም ይበጃል!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏11👍8
#ልቤ_ክፍት_ይሰንብት

ከራሚ ጠፋ እንጅ ከልባችን ጓዳ
ገብቶ ወጭስ አለ የማያድር እንግዳ
ሳይጠራ ገብቶ ሳይሸኝ ይሄዳል
በዚህ ዘመን ከልብ ማን ይሰነብታል
ገብተው እየወጡ የልቤ በር ሰፍቷል
እያደር ማገሩ የጠበቀው ላልቷል!
እኔን የናፈቀኝ ከራሚ ሰው ነበር
ቃሉ የሚፀና የሚያድር ለፍቅር
ገብታችሁ አትውጡ አይባል ሰው በግድ
ሳይጋበዝ መጥቶ ሳይሸኙት ለሚሄድ
ለካስ ይከብድ ነበር ከልብ ሰው ማልመድ
ከማይዘልቅ ተጓዥ ጋር ከንቱ ነው መዋደድ
ድግስ አትደግሱ አብዝታችሁ ለሰው
ቁርስ በልቶ ምሳ ውሎ ለማይደግመው
አይዘጋ በሩ ልቤስ ክፍት ይሰንብት
አንድ ቀን ከመጣ ከራሚ ሰው ድንገት
ይመላለሱበት አይዘጋም በሩ
ቢወጡም ቸኩለው ቢጓዙ ሳያድሩ
ድንገት እንዳያጣኝ ከራሚ ሲመጣ
ልቤ ክፍት ክረም ሁሉም ገብቶ ይውጣ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
9👍4😁2👏1
#ልብና_መስታወት

አንዳችም ሳይጨምር ፥ አንዳችም ሳይቀንስ፤
በተሰጠው መጠን ለሁሉም ሲመልስ፤
    ከትዝታ ገጹ ምንም ሳይጽፍበት፤
መስታወት ብቻ ነው ኑሮን ያወቀበት።
        ልብ ግን አቃተው!
በመጣው ሲደሰት በሄደው ሲከፋ፤
ውለታ ሲደምር ቅያሜ ሲያጠፋ፤
ከሚስጥር ሆድ እቃው ነገር ሲያመሰኳ፤
ቀለም አልባ ሆነ- ይቅርታችን መልኳ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በረከት በላይነህ
👍8
#ተራርቆ_ከእውነት

ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏84👍4
#እባካችሁ_ተውኝ!!!

እንኳን የሰው ሀጢአት ደርቤ ሊቀለኝ
የእራሴንም አልቻልኩ እያንገዳገደኝ
የእኔ ነውር በዝቶ ከብዶኝ እያያችሁ
የሌላውን ሸክም ደርብ ማለታችሁ
በየትኛው አቅሜ ችዬ ልሸከመው
ሁሉም የስራውን በግሉ ይቻለው
ሰው የእራሱን በደል እያለባበሰ
የሌላውን ሀጢአት ቆሞ እየቀደሰ
ሲበርደው ይኖራል ፀጋውን ተገፎ
በሰው ጉዳይ ገብቶ እያደር ወፍፎ
እባካችሁ ተውኝ የእኔም አቅቶኛል
ከአቅሜ በላይ በዝቶ ዘንድሮስ ከብዶኛል
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍15😭42👏1
#ባልተቋጨ_ፍቅር

ያልረሳውን እውነት የረሳ ለመምሰል
ስንቱ ይታገላል ትዝታን ለማቅለል
በልቡ ማህደር ፍቅርን ተሸክሞ
በውሸት ፈገግታ እራሱን አስታሞ
ዛሬን አስመስሎ ለትላንት የሚኖር
ብዙ አለ ታማሚ ባልተቋጨ ፍቅር
በልቡ እያነባ በጥርሱ እየሳቀ
ደስተኛ መስሎ ግን የተጨነቀ
ምዕራፍ ባጣ ታሪክ እልባት በሌለው
በትላንት ትዝታ ዛሬን የሚኖረው
በውሸት ፈገግታ የሚወዛወዘው
ስንት አለ ባለበት እሱን ቤት ይቁጠረው።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
6👍5🔥4👏2🥰1
#ተራ_ነሽ_ለልቤ

እንደ ዛሬው ሳትሆኝ ክፋት ሳትማሪ
አውቄያለሁ ብለሽ ዘርንም ሳትቆጥሪ
በንጹሕ ልቦናሽ ሰው በመሆን ቅኔ
እወድሽ ነበረ አልወደሽም እኔ።
ስልጣኔ መስሎሽ እርቃን እውቀት ይዘሽ
ልብሽ ሲደነድን ክብርሽም ሲሟሽሽ
ጠላሁሽ ከልቤ በርካሽ ጸባይሽ
ተራ ነሽ ለልቤ የልቤን ልንገርሽ
ያኔ! ግን በእውነቱ ልብሽ የከበረ
ሰው የማክበር ዜማሽ ሰውነት ነበረ
አንደበትሽ ማርማር ለእግዚአብሔር ያደረ
ያ " ሁሉ ቀረና ዘምኛለሁ ብለሽ ቅሉም ተሰበረ
አሁን አልወድሽም የለሽም ከሆዴ
ስልጣኔሽ ሁሉ የቂል ሆኗል ውዴ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍103🥰1