ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ወረት በበዛባት በግርግር ዓለም፣
የእኔ የምትለው ቋሚ ወዳጅ የለም፣
ለቁርስ አብሮህ ሆኖ ለምሳ ክዶሀል፣
ግዜ ለሰጠው ሰው ለእራት ይሸጥሀል።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
10👍7
#ለቀልድ_እንዳይመስለሽ

ፍቅሬን ተረጅልኝ የመውደዴን ነገር
ማሰብ አቀቶኛል  እኔ ካንቺ  በቀር
የማፍቀረን ነገር መውደዴን  ስንገረሽ
የምሬን ነው ውዴ ለቀልድ እንዳይመስለሽ

አብሮ ለመታየት ለሳቅ እና ፌሽታ
ለጊዜያዊ  ስሜት ለደቂቃ ደስታ
ነበርን ለማለት እንዲህ ነው እንደዛ  
ዝም ብዬ ምተወሽ  በዋዛ ፈዛዛ
የማፍቀሬን ነገር መውደዴን  ስንገረሽ
የምሬን ነው ውዴ ለቀልድ እንዳይመስለሽ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ገጣሚ_ገላና ዳንዴና
👍11🔥53
ገፍቶኛል ጅረትሽ ከቀዬ አስወጥቶ
በርሽ ተዘጋብኝ በኔ ላይ አየለ ጉልበትሽ በርትቶ
ልበላ ስጠጋ ከሰፊው ማዕድሽ
ልጠጣ ልጎነጭ ከዛ ከማር ጠጅሽ
ልብስሽን ጠይቄሽ ልዋብ ላጌጥበት
ለካ ክደሽኛል የኔውን ልጅነት
አፈር ይብላኝ በቃ ልፍሰስ እንደ ውሀ
ባንቺ ከተካድኩኝ ከፊትሽ ልሂደው ያቃጥለኝ በረሀ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ባንቺአለም ሽፈራው
👍5
ምንም ቢደብቁት ምንም  ቢሸፍኑት
ቆሻሻ  ከምረው   ጭራሽ  ቢሰውሩት
ጭሱ አመለከተ መገኛውን ቦታ
መስቀል  ተገኝልን የእኛ መከታ

አይሁድ ቢደብቁት የመስቀሉን ስፍራ
እሌኒ አገኘችው ደመራ ደምራ

ዛሬስ በኛ ዘመን

ስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ?
ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ?
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ገጣሚ_ገላና ዳንዴና
9👍3👏2
#ትላንትን_ቀመስኩት

በትዝታ ሪሞት ግዜውን መልሼ
ደግ ደጉን አየሁ ክፉውን ቀንሼ
የፊቱ ቢያስፈራኝ የሗሊት መለስኩት
ደጉን ግዜ ስቤ በዛሬው ቀየርኩት!
አሁን ያለው ግዜ ቢመረኝ እንደ እሬት
ህይወት ለማጣፈጥ ትላንትን ቀመስኩት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍74👏3
ስቀርብሽ መራቅሽ
ስርቅሽ መቅረብሽ
ስወድሽ መጥላትሽ
ስጠላሽ  መውደድሽ
ሳትረጂኝ  ቀርተሽ ሳልረዳሽ እኔ
ጥፋቶችን  ሁሉ  አታሳቢ በኔ

ያንቺም ችገር  የኔም ችግር ያንቺ
መፍትሄን እናፍልቅ ሆነን እኔና አንቺ

            #እንጂ

የኔ  ነው ያንተ ነው መባባል ከመጣ
ትዳርም  ችግር ነው  አለው  ብዙ  ጣጣ

         #እናም

ስቀርብሽ ቅረቢኝ
ስወድሽ  ውደጂኝ
ስረዳሽ  ተረጂኝ
ሳፈቀረሽ  አፍቅሪኝ
ተዋደን  እንኑር  ተሳስበን በጋራ
አንድ  አካል እንሁን እንደ እግዚአብሔር ስራ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ገጣሚ_ገላና ዳንዴና
👍175👏3
#ህይወት_ፊልም_በሆነች

ሪሞት ቢኖረው ግዜ የእጅ ስራ
ማሳለፍ መመለስ በተራ በተራ
ደጉን ወደሗላ ክፉውን ወደፊት
መቆጣጠር ቢቻል ፊልም ሆና ህይወት ።
የትላንቱን ውብ ቀን ከዛሬ መልሶ
ደግ ደጉን ብቻ ለማየት ከልሶ
መርጦ የሚኖሯት በዘውግ የተቃኘች
ደራሲው የጻፉት ህይወት ፊልም በሆነች።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍6👏32🔥1
#በሰው_ልብ_ከተማ

ስቆ ማለፍ እንጅ ዘንድሮን ለከርሞ
በፈገግታ ዜማ ብሶትን አስታሞ
የሌለንን ትተን ባለን ካልተደሰትን
ጊዜውስ ሞክሯል አዙሮ ሊጥለን
የሳቃችን ሚዜ ሀዘናችን ሆኖ
በጥርሳችን ጋቢ ከውስጥ ተከድኖ
ሳቃችን ሙሽራ ሐዘናችን ሚዜ
አብረው እየበሉ ሳቅና ትካዜ
ጥርሳችን ቢስቅም ሐዘንን ሸሽጎ
ጥርስ እየደመቀ መከራን ሚዜ አርጎ
ደስታና ሐዘን አብረው እቁብ ጣሉ
በሰው ልብ ድንኳን ድግስ እየበሉ
በስቃይ ከተማ ድርሻቸውን ይዘው
የፈረቃ ስልጣን ስፍራቸውን ወስደው
ይፈራረቃሉ በሰው ልብ አዳራሽ
ችሎትን ዘርግተው በሌለበት ከሳሽ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
12👍8🔥1
#ላመኑት_ብቻ_ነው!

የመስቀሉ ትርጉም ቅኔ ነው ምስጢሩ
በዋዛ አይፈታም ማመን ካልጀመሩ
ላመኑት ብቻ ነው የመስቀሉ ድህነት
ለከዱት ቀልድ ነው ይፈልጋል እውነት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ

#እንኳን_አደረሳችሁ
16👍6😁2
መልክ ቁንጅናሽን ውበትሽን አይቼ
ከቆምኩበት ቀረሁ ግራ ተጋብቼ
ግራ እንደተጋባሁ መላው ቢጠፋኝ
ሰርቄያት ልጥፋ አልኩኝ ማንም ሳያየኝ
      ግና ምን ያደርጋል.....
ሰርቄሽ ብጠፋ ማንም ሳያየኝ
ፈረሰኛ አባትሽ ከፊት ቀደሙኝ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
😁10👏9👍4🏆2😱1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍4🙏3
እሺ ስላላሺኝ ፍቅሬን ተቀብለሽ
እኔም ወድሃለው ባትይኝ  መልሰሽ
አንቺ ባይኖረሽም እንደ እኔ ዓይነት ስሜት
ጨለማ ሳትሆኝ ብርሃን ነሽ ለእኔ ቤት

          #ለምን?

ብዙ ሳልደክምብሽ አንዲያው በባዶ ህልም
ተስፋ  በማደረግ ዉስጥ እራሴም ሳልደክም
ስለ አዳንሺኝ እኔን ከቶ ከአጉል ምኞት
ብርሃን ነሽ አንቺ ሻማየ እና ማዶት
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍️ገጣሚ_ገላና ዳንዴና
👍9😁4👏21
ከነፋስ ለሚፈጥን ለተወርዋሪ እድሜ
ለምን ቂምን ላትርፍ ሰውን አስቀይሜ
ለተሰፈረ ቀን ለማይጨምር መኖር
በጥላቻ ስካር እኔ አላጣም ፍቅር።
        
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍156
#ያልጣዱት_አይበስልም

ፍቅር እንደ ዝናብ ከሰማይ አይወርድም
         ያበባ መደብ ነው
በሰው የሚታነፅ ፡ በሰው የሚወድም
ተዘርቶብን እንጅ ፡ ተሰብከን አንወድም።
"ወዳጄ ወዳጄ" የሚያቀነቅኑ
አገር ያቀኑ ለት መች ልብን አቀኑ
       ሳይወጡ ሳይወርዱ
ውብ ስራን ከውብ ቃል ፡ ሳያስተባብሩ
ከድሜ እና ከምቾት ቆርሰው ሳይገብሩ
         ፍቅር መች ይፈልቃል?
በስብከት በምልጃ በየዋህ ሰዎች ህልም
            ያልጣዱት አይበስልም
            ያልዘሩት አይበቅልም።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዪም
👍7👏43
እኔው ለኔ አልቅሼ እኔው ለኔ ስቄ
በውጣ ውረዱ ታሪኬን አድምቄ!!!
ዛሬን አይቻለሁ ትላንትን አልፌ
ጊዜን እየቆጠርኩ ቀናትን ገፍፌ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰64👍1
#ኑሪልኝ_እህቴ

ክፉ አይንካሽ ውዴ ኑሪልኝ በጤና
የደስታዬ ምስጢር የሂወቴ ፍና
ስከፋም ስደሰት ሁኝልኝ ከጎኔ
የሁልግዜ አጋሬ የመኖሬ ቅኔ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍74👏3
#ሙግት

ጊዜ ለሰው ህይወት
ዘበት አይታክተው
እኔም ምላሽ ባጣም
መጠየቄን አልተው።
ኩታ ገጠም ናቸው
አልፋና ኦሜጋ
እንዴት ቀን ይመሻል
በቅጡ ሳይነጋ?
ማን ዘረፈው ጠጉሬን?
ማን አሰረው እግሬን?
ጉልበቴን ምን በላው?
አቅሜን ማን ወረሰው?
ተወልዶ ሳይጨርስ
እንዴት ያረጃል ሰው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዪም
16👍9
#ያንተ_ዘር_የቱ_ነው?

ዘር ቁጠር ይለኛል ሰው መሆኑን ትቶ
ገላ አፈር መሆኑን መሞቱን ዘንግቶ
እስኪ በል ንገረኝ ያንተ ዘር የቱ ነው?!
ከተደረደሩት ብሔርህስ ማነው?!
አየህ ሰው ከንቱ ነው አይኖርም ዘላለም
ቋሚ ፈጣሪ እንጅ ቋሚ ብሔር የለም!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍15👏2
" #ከየትኛው_ላይ_ነን?!!!"

ወደፊት መጥተናል? ወይ ሗላ ቀርተናል?
ይኼ የእኔ ትውልድ ግራ ያጋባኛል፤
ድሮ ላይ ነው ስለው ዛሬ ላይ ነኝ ይላል፤
በዛሬ ስሰፍረው ትላንት ላይ ይገኛል ፤
የትኛው ዘመን ላይ ይሆን የቀረነው?
ከአለፈው ከሌለን አሁንን ካልያዝነው?
ከባቢሎን ህዝቦች የባሰ ተቃርኖ፤
እንዲህ የለያየን በሀሳብ በታትኖ፤
ከፊት ነን ከሗላ ወይስ በትላንቱ?
የእኔ ዘመን ትውልድ የቱ ነው እውነቱ?
ወይ በአለፈው አይኖር? ከዛሬም ተጣልቶ፤
ከሁለቱም ሳይሆን መሀል መንገድ ቀርቶ፤
ወዲህ ነው ስትለው ወዲያ ነው እያለ፤
ወዲያ ነው ስትለው ወዲህ ከዘለለ?
የእኔ ዘመን ትውልድ ከየትኛው ላይ ነው?
እንኳንስ ሊያስረዳ ለራሱም  ያልገባው፤
የትኛው ላይ ይሆን መንገዱ የጠፋው?
በሀሳብ ተቃርኖ መታረቅ ያቃተው?
ከትላንቱም የለ ከዛሬው የራቀ፤
እንኳንስ ከሌላ ከእራስ ያልታረቀ፤
ምን እንደሚፈልግ ማንስ ምን አወቀ?
ከባለፈው ሳይኖር በአሁን ያልደመቀ፤
ያልገባኝ ያልገባን አንድ ነገር አለ!
ከትላንት ከዛሬም ከየትም የሌለ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍124🔥4
#የኔነሽ

የምጠረጥረው ፥ የማልጠረጥረው
ቄሱ መነኮሱ ፥ ወታደር ደብተራው
           ያም የኔነሽ ሲላት፤
           ያም የኔነሽ ሲላት፤
  ለበለበኝ ፍቅር አቃጠለኝ ቅናት
ወይ ጠንካራ ክንዴ ፥ ጉልበቴ አያስቀራት!
   እንዴት የብቻዬ ፥ የግሌ ላድርጋት?
ሰው በጠራት ቁጥር ፥ ባልነቴ ሟሟ
የሰማኒያ ሚስቴ ፥ የኔነሽ ነው ስሟ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ደራሲ ይስማዕክ ወርቁ
😁17👍84🔥2
" #ይገለባበጣል "

ጠላቴ አትደሰት ለእኔ ተራ መውደቅ
መነሳቴ አይቀርም ነግ ለኔ በል ይልቅ
ይገለባበጣል ጊዜ ቋሚ አይደለም
ሳይወድቅ የኖረ ሰው እስከዛሬ የለም
የወደቀው ቆሞ የቆመው ይወድቃል
ይልቅ መደጋገፍ ለሁሉም ይበጃል!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏11👍8