ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#እኔ_ያንተ_ምስኪን

ለኔ መምጣትህ ነው የሚታየኝ ዞሮ
መቅረትህ ቢበዛም ዓመታት ተቆጥሮ
ትመጣለህ እያልኩ መቅረትህ ሳይረታኝ
የሴትነት እድሜ መንጎድ ሳያሰጋኝ
በቃል ተጠፍሬ በፍቅርህ ውለታ
እጠብቅሀለሁ ጠዋት ሳልል ማታ
እንዲህ ነው ሳትለኝ ወጥተህ እንደ ዘበት
ቀናት በሳምንታት ሳምንታት በወራት ወራትም በዓመታት
በተፈጥሮ ህጉ ቦታ ሲቀይሩ
ዓለምን ደጋግመው በተራ ሲዞሩ
እኔ ያንተ ምስኪን ከአስቀመጥከኝ ቦታ
በመምጣትህ ናፍቆት አለሁ በትዝታ
መቅረትህ ቢበዛም በዓመታት ተቆጥሮ
ለእኔ መምጣትህ ነው የሚታየኝ ዞሮ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏6👍532
ከግርግር ዓለም ከብዙ ጫጫታ
ግርማ ሞገስ አለው ያስፈራል ዝምታ
ውል ከሌለው ጩኸት ከውሸት ፈግግታ
ልብን ይማርካል ይደምቃል ዝምታ!!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍8🥰2
#የስንቱ_ዝምታ

የምላስ ጋጋታ ጀሮን ባይጋርደው
ይደመጥ ነበረ ዝምታም ቃል አለው
በህሊና ከሳሽ በልብ ዳኝነት
የዝምታ ችሎት የተሰየመ እለት
ሁሉም ተናጋሪ ጸጥ! ቢል ላንድ አፍታ
እመኑኝ ይጮሃል ድምጽ አለው ዝምታ
የተፈጥሮ ችሎት በልብ ሚዛን ቢረግጥ
ዓለም ለሴኮንዶች መናገርን ቢል ጸጥ
ያኔ ይደመጣል ቃል አለው ዝምታ
ገለል ሲልለት የምላስ ውካታ
ጆሮ ባይጋረድ በቃላት ጋጋታ
መጮኽ በጀመረ የስንቱ ዝምታ
የሰው ልጅ ቢኖረው ስድስተኛ ህዋስ
ይሰማው ነበረ ዝምታችን ሲፈስ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍64👏2
በማሽቃበጥ ትሪ እንጀራ ብንበላ
ሰው ታዘበን እንጂ ሆዳችን መች ሞላ
የማስመሰል ጉርሻ እራብ ላያስታግስ
ስም ነው ያተረፍነው በስስት ስንጎርስ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍63
#በተስፋ_የማልባት

ወተቷን ባልቀምስም ባትደርስ ለችግሬ፤
ላም አለኝ ከሰማይ ገዛሁ ተበድሬ፤
ጥገት የሆነች ናት ወተቷን የማላይ፤
በተስፋ የማልባት እያየሁ ወደ ላይ፤
ምራቅ የምታሱጥ እርጎ ቅቤ የማትሰጥ፤
ከደመና እርቃ ከላይ የምትቀመጥ፤
ላም አለች በስሜ ከቶ ማትዳሰስ፤
ለረሀብ ለችግሬ ለዛሬ የማትደርስ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
12👍3👏3🥰2
ለብቸኝነቴ ትላንት ሰበብ ሆነው
እብድ ነው ይላሉ ዛሬ ከንፈር  መጠው
ልብሴን የወሰዱት እነርሱ ነበሩ
ጨርቅ ጣልክ ለማለት እንዴትስ ደፈሩ?!!
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍124
#ልቤን_መልስልኝ!

ቀንና ሌሊቱ ጊዜም ተሻጋሪ
ትዝታህ ብቻ ነው ከኔ ጎጆ ነዋሪ
ሀምሌና ነሐሴ ይጥላል አብዝቶ
ሰውም ድንገት ያልፋል ትዝታን ተክቶ
አንተስ ካለህበት እንዴት ነው ትዝታ
ከኔ ቤት በርትቷል ጠዋት ሆነ ማታ
ጊዜን እንደዘበት የሗሊት መልሶ
አንተን ያገዝፍሐል እኔን አኮስሶ
በልቼ እንዳልበላሁ
ጠጥቼ እንዳልጠጣሁ
ዛሬም በመራቅህ አለሁ እንደከሳሁ
አመታት አልፈውም አንተን አስባለሁ
ስራመድ ብቻዬን ስተክዝ ለራሴ
በትዝታ ማእበል ስትሰቃይ ነፍሴ
እስቲ ልጠይቅህ ስላንተ ሁኔታ
እኔ አልሰነብትም ሟች ነኝ በትዝታ
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🥰10👍5👏41🤔1
ለሆዱ ሲንጫጫ ኮሚቴ በሞላ
ወርቁን አመጣልሽ ያ ታምራት ቶላ
ሀገር ለማሳነስ ዘወትር ለሚተጉ
ሀገሩን ለሚወድ ወርቅ ነው ማዕረጉ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
30👍5👏5
#አፋልጉኝ?!

ጉድለቴን ሳይቆጥር ድክመቱን ሳልቆጥር፤
ጓደኛ የሚሆን በሰውነት ክብር፤
ሳጠፋ ሚየመክረኝ ሲያጠፋ የምመክረው፤
በጎን የማያማኝ ከጀርባ የማላማው፤
አፋልጉኝ ጓደኛ መስተዋት የሆነ፤
በግልጽ ንግግር አምኖ የዘመነ፤
ግዜ አይቶ የማይጥል ሀብት አይቶ ማይከዳ፤
ውስጡን የምረዳው ውስጤን የሚረዳ፤
አፋልጉኝ ጓደኛ ከወረት የራቀ፤
ሰው መሆን የገባው ሰውነት ያወቀ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍159
ነፍሴ ለስጋዬ ባክሽ አታሽቃብጪ
ነገ አፈር ነው እርሱ አንቺ ስትቀጪ
ይልቅ እንቢ በይው በጸሎት ይረታ
እዳው ላንቺ እንዳይተርፍ የማታ የማታ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
14👍10👏2
#ጠርጥሪ

አንበሳና ነብር በጋራ እየሳቁ
ውበትሽን አጉልተው እያደናነቁ
ወደ አንቺ ሲመጡ ባልነበር ፈገግታ
ባልተለመደ መልክ የወዳጅ ሰላምታ
ያኔ ያንቺ ነገር አክትሟል መኖርሽ
ተማክረዋልና ቀድሞውን ሊበሉሽ።
ስለዚህ ጠርጥሪ
በልማድሽ ፍሪ
ተፈጥሮ ነውና መቀየር ላትችይ
አደነቁኝ እያልሽ ፊን ፊን አትበይ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍129
ሀዘኔ ሀዘናቸው ሳቄ ነው ሳቃቸው
ለሚወዱኝ ሰዎች ጥርሴ ሸልማቸው
ለሚጠሉን ሰዎች ባይሰጥም ደስታ
ለሚወዱን ሁሉ ምግብ ነው ፈገግታ
ፈገግ በል ጥርሴ ለሌሎች ስጥ ቦታ
ውስጣዊ ሀዘኔን  በመታገል እርታ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
13👍3👎1
#እኛም_የእኛ_አይደለን!

እንኳንስ ሀገሩ እንኳንስ መሬቱ፤
እኛም የእኛ አይደለን ይኸ ነው አውነቱ።
ቀኑም ድንገት ከድቶ በሞት የሚተካ፤
ገንዘብና ስልጣን ህይወት ላያረካ፤
ለዚህች ከንቱ ምድር ለወረተኛ ዓለም፤
የእኛ ያልነው ሁሉ መቼም የእኛ አይደለም።
በድንገት ለምታልፍ ለኮንትራት ህይወት፤
አፈር ለሚበላው ለከንቱ ሰውነት!።
እንኳን ቁሳቁሱ ተራ ገንዘብ ቀርቶ፤
እኛም የእኛ አይደለን መኖር ነው ተስማምቶ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍144
ዛሬ በሰው ችግር በግፍ የምትስቁ
ቀን መጣሉ አይቀርም ይህነን እወቁ
ሞልቶልኛል ብሎ በጎደለው መሳቅ
አወይ ነገን መርሳት ወየው አለማወቅ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍11👏4
#ወፊቷን_በሆንኩኝ!!

በራሴ ችሎታ ቤቴን በሳር ሰሪ
ሳልዘራ ሳላጭድ ቀለቤን ሰፋሪ
በእግዚአብሔር ቸርነት ሳልጨነቅ ነዋሪ
ወፊቷን በሆንኩኝ በሰማይ በራሪ!!!
ዶላር ሰማይ ነክቶ ብር መሬት ወድቆ
እያሉ ከመኖር በሁሉም ተጨንቆ
ምነው ወፍ በሆንኩኝ ከዛፍ ዛፍ በራሪ
ቀለብ የማይጨንቀኝ ቤቴን ብቻ ሰሪ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍7🥰42👏1
#ተፈጥሮም_ያኮርፋል

በእኔና አንቺ ፍቅር ሲታጀብ የኖረው
ድንገት ብንቀርበት ጭር አለ ጎዳናው
አብረን ያረፍንበት ተቃቅፈን ያን ግዜ
ልማዱን ነፍገነው ውጦታል ትካዜ
የእኛ መኮራረፍ እንኳን ለኛ ቀርቶ
መርዶ ሆኖበታል ጎዳናው ተከፍቶ
በኔና አንቺ ኩርፊያ ተፈጥሮም ያኮርፋል
ከሰው በላይ አውቆን ከልቡ ለምዶናል።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍63
የዲጂታሉ ዓለም ልብን ተቆጣጥሮ
መነጋገር ቀረ ሰው ከሰው ጋራ አብሮ
ህሊናችን ዛሬ መርጦ ብቼኝነት
ማንም ከማን አይደል ቢኖርም አንድ ቤት።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍15
#ምኑንስ_ተኖረ

እንቅልፍ አልባ ሌሊት
ትርጉም የለሽ ህይወት
መግፋት ቢሰለቸኝ ዋ! አልኩ ለራሴ
ግራ ብትጋባ ብትጨነቅ ነፍሴ
ድሃ እንቅልፍ አግኝቶ ህልምን ካላለመ
ህይወት ትርጉም አጥታ ቀኑ ከጨለመ
ምኑንሰ ተኖረ ተመስገን ተብሎ
ነገን ለመናፈቅ የዛሬን አቅልሎ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
11👍2
ግዜ አንደበት ኖሮት ብሶቱን ቢናገር
ተበዳይ በሰው ልጅ እኔ ነኝ ይል ነበር
እራሳቸው ከፍተው ዘመን ለሚከሱ
ሰው ነው ተጠያቂ ነበር ግዜ መልሱ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3
#የጠላ_ስባቱ

አንቺው ጠላ ጠምቀሽ አስክረሽ አስክረሽ
ትዳር ስጠይቅሽ ሰካራም አልወድም ለምን ትይኛለሽ?
የቀመምሽው አንቺ በብቅል በጌሾ
ሰካራም አይደለም ለካ አንቺ ነሽ ዋሾ
እርሱማ ይጠጣል የልቡን ሊናገር
ሰካራም ከሌለ መች ታምራለች ሀገር
ማስከር አይደለም ወይ የጠላ ስባቱ
አጠማመቅሽ ነው ያሶደደሽ እቱ።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍218