ግጥም
4.25K subscribers
25 photos
1 video
8 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ባይልልን ነው እንጂ ባንታደለው
ለሰው ሰው ነበር የሚያስፈልገው
ገንዘብና ስልጣን ሰው ከሌለ ባዶ
ሁሉም ከፍቶ አደረ በቁሳቁስ አብዶ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍155
#የሁላችን_ጉድለት

እኛ እኮ ደግ ነን ለሰው እናዝናለን
ከቸገረው ጋራ ሰልፊ እንነሳለን
ቀኝ እጅ የሰጠውን ግራ እየመለሰ
እጸድቃለሁ ያለው ይበልጥ እረከሰ
ሰው ለሰው መድረሱ ግዴታ ነበረ
ግዜው አረጀና ዝና ሆኖ ቀረረ!!!
የሁላችን ጉድለት የዘመን ወለምታ
መታበያችን ነው የማይድን በሽታ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏102
መጣሁ ብላ መቅረት
ቀረሁ ብላ መምጣት
አስተምራው ልቤን
እወዛገባለሁ ተዘርፌ ቀልቤን።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍95
#ምኑንስ_ተኖረ

እንቅልፍ አልባ ሌሊት
ትርጉም የለሽ ህይወት
መግፋት ቢሰለቸኝ ዋ! አልኩ ለራሴ
ግራ ብትጋባ ብትጨነቅ ነፍሴ
ድሃ እንቅልፍ አግኝቶ ህልምን ካላለመ
ህይወት ትርጉም አጥታ ቀኑ ከጨለመ
ምኑንሰ ተኖረ ተመስገን ተብሎ
ነገን ለመናፈቅ የዛሬን አቅልሎ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍114
ለሌሎች በረሃን ሳትሰስት እውቀት ስጥ
በቅንነት እሳት ሻማ ሆነህ ቅለጥ።
ሞት የማይቀር እውነት መሆኑን ያወቀ
እርሱ ሻማን ሆኖ ትውልድ አደመቀ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍4
#በተራ_ይዞራል

እኔ ስከተልሽ አንች ግን ስትርቂ
በእኔ ስቃይ ደምቀሽ ዘወትር ስትስቂ
ተራሽ ደረሰና ተከታዬ አድርጎሽ
እንደዚህ ነው ፍቅር አዙሮ መለሰሽ
ሲፈለግ የኮራ ሲፈልግ ይገኛል
ፍቅር ወረት አያውቅ በተራ ይዞራል
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍131
ዓለም ይብላኝ ለአንቺ ለእኔስ ኮንትራት ነሽ
ጥየሽ እሄዳለሁ እስከነክፋትሽ
ሞት እስኪመጣ ነው በእኔ መቀለድሽ
ለየትኛው እድሜ የምለማመጥሽ!!!
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
2🔥2
#ሲሞቱ_ደራሽ

ሰውማ መች ጠፋ ሲሞቱ ቀባሪ
የሌለው ወዳጅ ነው ሲኖሩ አኗኗሪ
ከንፈርን በመምጠጥ አፈር የሚያለብስ
ሞልቷል የሞቱ እለት ሲሻው የሚያለቅስ
ሲቸገሩ ሳይደርስ ሲሞቱ ደራሽ
ቀባሪማ ሞልቷል አፈሩን መላሽ
ሲኖሩ እንጅ ከባድ የዚህች ዓለም ህይወት
ሞልቷል አጋፋሪ ተድላ እኮ ነው መሞት።
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍143
ቤተ ሰሪ በዝቶ ማገር ማገር ይላል፣
መገንባቱን እንጂ መኖሩን ማን ያውቃል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍92
#ጓደኛ

ከልብህ ውሰጥ ጠልቆ ስቃይ ካልተረዳ
የጓደኛ መብዛት  አንተን ምን ሊረዳ?
ከሚግተለተለው ከሺህ ሳቅ አድማቂ
ከልብ የሚረዳ አንድ ሰው ነው በቂ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍22
ችየበት ነው እንጂ ሀዘንን መደበቅ
በማሽላ ዘዴ እያረሩን መሳቅ
እንደኔ የከፋው ማን ይሆን ዘንድሮ
በጥርሱ የሚኖር ከልቡ ሃዘን ቀብሮ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍84
#አዎ_ፍቅር_የለም

በዝሙት ህሊና በክህደት እይታ
በእምነት አልባ ቅኔ በጥቅመኞች ኩታ
ከሆነ ልኬቱ የሚዛኑም ክብደት
በእርግጥ ፍቅር የለም ሲረክስ ሰውነት
ፍቅርን በፍቅር ለሚለካ ደግሞ
የእውነት ፍቅር አለ ደጋግሞ ደጋግሞ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍63🔥3
ጉልበትም ውበትም በግዜ ይረግፋል
መልካም ስራ ብቻ ዘመን ይሻገራል
የከንቱ ከንቱ ነው ቁመና ደም ግባት
በጎነት ይኖራል ሲመሰክር እውነት።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
3
#ተወደደ_ጆሮ

እኔው ለእኔ ብቻ ዝምታዬን ልስማ
መቼም ዘመኑ ነው ቢጮሁ አይሰማ
ተናግሬ ሰሚ አድማጭ በሌለበት
ዝምታ ወርቅ ነው እስኪነጋ እውነት
ላድምጠው እራሴን የብቻዬን ቅኔ
መልሱን እየመለስኩ እኔው ቆሜ ለኔ
ዝምታ አይሰማም አትበሉ ዘንድሮ
መናገር ከንቱ ነው ተወደደ ጆሮ
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
12👏1
ህሊናዬን ሼጬ በጮማ ከማድር
እፍኝ ቆሎ ስጡኝ ይበቃል ለመኖር
ሀሰትን ተናግሮ ከሚኖር አግስቶ
መኖር መታደል ነው እፍኝ ንፍሮ በልቶ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍12🔥1
#ነፍስ_ይማር

እውነት ታማ ነበር በወሸት ተጎድታ
መዳን ስላልቻለች ተቀበረች ሞታ
ነፍስ ይማር ይላታል የገደላት ሀሰት
ይኼኔ ነው እኮ ሁለት ግዜ መሞት
በዳይ አዛኝ መስሎ ገድሎ ካለቀሰ
በገደለው ቀብር እንባን ካፈሰሰ
በነፍስ ይማር ንፍሮ በደል ከተሻረ
ሁሉም በዳይ ቆሞ ሟችን ከቀበረ
የሞት ሞት ያኔ ነው የሟች ዳግም መሞት
በእውነት መቃብር ላይ ከነገሠች ሀሰት።
  @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍14❤‍🔥5🔥3
ቀን አይጥልም እያልኩ አልከራከርም
የዘንድሮ ዝናብ አያጉረመርምም
ድንገት እየጣለ ስንቱን አበስብሷል
መጠለያን አጥቶ የሚወድቀው በዝቷል።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍103
#እንደዚህ_ነው_ለካ!

የእራስ ምስል ገዝፎ ሌላን አኮስሶ
ሲወጠር ልባችን ትቢት እብሪት ለብሶ
በሌሎች ማንነት እራስን ፍለጋ
የእኛ ይመስለናል የሌሎቹ ዋጋ
ከተሰጠን ተመን ከተፈጥሮ ጸጋ
የእራስ ባልሆነ ዓለም ከፍታ ፍለጋ
መባዘን መኳተን በሌሎቹ ዱካ
ልካችን የጠፋን እንደዚህ ነው ለካ
ድመትን ነብር ነሽ ጀግና ነሽ እያሏት
ምስሏን አስረስተው የሌላትን ሰጧት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍73
መቼ አነሰን እና የሰው ሰራሽ ችግር
በተፈጥሮ አደጋ ቀጣኸን እግዚአብሔር?
አንተ እንኳን ተው ማረን እንደ ሰው አትክፋ
ገጠሩን አትቅጣው ከተሜው ባጠፋ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍9👏31
#አንድ_ነገር_አለ

አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ
የተጋረደብን በጫጫታ ኩታ
መረዳት ያልቻልነው የሰውነት ጥጉ
ከፍታው ዝቅታው ውርደቱ ማዕረጉ
በሀቅ ያልተቃኘ ያልገባን ግርታ
አንድ ነገር አለ ያልታየን እውነታ
ወደ ነፈሰበት የሚስብ አስልቶ
ከሰውኛ ስሌት የሚጥል ጎትቶ
መግነጢሳዊ ሀይል ለእኛ ያልታወቀን
በዘር ዛር አዙሪት የሚያንቀጠቅጠን
ያልታወቀን ህመም ያልታየን በሽታ
አንድ ነገር አለ ያልገባን እውነታ
የግርግር ዓለም ረባሽ ውካታ
የእራስ አቋም ነጥቆ በሰው የሚስመራ
ባልገባን በገባን ዘወትር የሚያስወራ
እወነትን አስትቶ ከሀቅ የሚያጣላ
በሆነ ባልሆነው ትውልድ የሚበላ
ለማወቅ ያልጣርነው ሊገባን ያልቻለ
ማየት ያልፈለግነው አንድ ነገር አለ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
3👏3❤‍🔥1
በበጋው ተገኝተሽ በክረምቱ መጥፋት
ምን አለ ብለሽ ነው ከዚህ በላይ ቅጣት
ያንችስ ክፋት በዛ የጭካኔሽ ጥልቀት
ፍች ይጠየቃል ወይ አሁን በዚህ ክረምት።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍8😁53