ግጥም
4.25K subscribers
24 photos
1 video
7 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ህይወቴ

ፍቅሬ ፍቅሬ እያልኩ ልጥራሽ
የመኖሬ ትርጉም ህይወቴ ነሽ
የልቤ ትርታ የነፍሴ ዕፎይታ
የእኔነቴ ምስጢር የአምላኬ ስጦታ
እንዲህ እንዲያ እያልኩ ብጠራሽ
እንዴት ሆኖ እንዴትስ ይመጥንሽ
ፍቅሬ ፍቅሬ እያልኩ ልጥራሽ
ሆሄያት ቢደረደሩ ቃላቶች ቢጣመሩ
ከቶ እንዴት ይቻሉ እንዴትስ ይድፈሩ
ቃላቶች ያልቻሉ ሆሄያት ያልሰየሙሽ
ታዲያ ምን ነሽ አንቺ አንደበት ማይገልፅሽ
ደከምኩልሽ ሆዴ ቃላቶች አጣሁኝ
በቃ በቃ !! ህይወቴ ነሽ አልኩኝ
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍10🥰2
መልስና ጥያቄ ሳይተዋወቁ
ከኢትዮጵያ ጋራ እንደተራራቁ
በአሽሙር በብሽሽቅ ዓመታት አለቁ
ዜጎች መልስን አጥተው እየተጨነቁ
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏7👍5❤‍🔥1
#ፍቅር_ሲደናበር

ባለርስቱ አባትሽ አልይህ ይሉኛል
ቅምጥል እናትሽ በአሽሙር ይልጡኛል
ወንድምሽ በዛቻ መቆም ከልክሎኛል
ደግሞ ያንቺ ፍቅር ሁሉን ቻል ይለኛል።
ፍቅር ታውሮ እንጂ ከአንቺ ላይ የጣለኝ
ከቤተሰብሽ ጋር ወስዶ ያላተመኝ
ጥንትስ ድህነቴ መቼ ዘነጋሁት
እኔን ተወት አርገው ፍቅርን ይክሰሱት።
ፍቅር ሲደናበር በውበት ታውሮ
ከጌታ ልጅ ጣለኝ ሰውነት አክብሮ
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍134🔥3
#እንዴውም_አትምጭ

ትመጫለሽ ብዬ ቁማር አሲዣለሁ
እንዳትቀሪ ፍቅሬ እረታብሻለሁ
በፍቅርሽ ቀለበት ተወራርጃለሁ
የቀረሽ እንደሆን ቃል ኪዳን አጣለሁ
ባትቆይም አንዴ ነይ
ዓይኖችሽን እንዳይ
ትመጫለሽ ብዬ ልቤን አሲዣለሁ
ጨክነሽ ከቀረሽ እጎዳብሻለሁ
አትቀርም ብዬ ተወራርጃለሁ
የቀረሽ እንደሆን ልብ አልባ እሆናለሁ
እንዴውም አትምጭ ልሸነፍ ልበላ
ሰው ልቡን ከሰጠ ምን ሊቀረው ሌላ
የምወድሽ ቢሆን ለፍቅር የታመንኩኝ
በውርርድ ሰበብ ባንቺ ባልቆመርኩኝ
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤‍🔥9🥰3👍1👏1
እንደ ገደል ላይ ዛፍ ግራ ተጋብቼ
እወዛወዛለሁ አቋሜን አጥቼ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
❤‍🔥1😁1
ለማንኛውም የሄዱት ሄደዋል ሌላም የሚሄድ ካለ በሩ ክፍት ነው
ተመችቶናል ብላችሁ ላላችሁ ለእናንተ ግን የጎደለ ነገር ካለ እታዘዛለሁ ይመቻችሁ ❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍29🔥63
#በቃ_እወድሻለሁ

አውቃለሁ መውደዴን ልፋት ነው ብለሻል
ደግሞ አንች በተራሽ....
ምንም አልጠቅምህም መጥፎ ነኝ ብለሻል
የኔ ባትሆኝም ፍቅሬን ብትገፊውም
ደግሞ በተራዬ መጥፎ ነሽ አልልም
በቃ እወድሻለሁ ይሄንን አልክድም
አውቃለሁ ምክንያቱን ልብሽን የጎዳው ሌላ ሰው ቢሆንም
ሁሉም ወንድ አንድ አይነት መስሎ ቢታይሽም
ስህተቱ እስኪገባሽ እጠብቅሻለሁ
ዛሬም ነገም ሁሌም....
            ......በቃ እወድሻለሁ....
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
22👍5👏1
ከሁሉም የሚልቅ የሰው ትልቅ ሀብቱ
ገንዘብ የማይገዛው ዋና ጤንነቱ
ማመስገን ነው እንጂ ሲመሽም ሲነጋ
ጤንነት እኮ ነው ለሰው ትልቅ ዋጋ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🔥7👍62
ጨርቅ አልጣለም እንጂ እርስ በእርስ ተፋፍሮ
የአበደው ብዙ ነው ወፈፌው ዘንድሮ።
ጎዳናውን ሞልቶ የሚርመሰመሰው
በኑሮ ውድነት እየጨለለ ነው።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍11😁8👌1
#ሳይበስል_አረረ!

እድሜ ፋኖስ ሆኖ ምግባር ካላበራ
ቁጥር ብቻ መቁጠር ከቶ ምን ሊሰራ
የሰው ልጅ ሚዛኑ መለኪያ ስፍረቱ
ምግባሩ አይደለም ወይ ዛሬስ ሰውነቱ
በግልብ እውቀት ስካር እድሜ እየቆጠረ
በባዶነት እሳት ሳይበስል አረረ!!!
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
12
ጊዜው ነው አትበሉኝ ጊዜው ምን አጠፋ
እየተመለከትን ሰው በሰው ሲከፋ
ጊዜማ ቀመር ነው መቼ ይዛነፋል
ቀንና ለሊቱም በየዎቅቱ ያልፋል
ሁሉም ሰው አይከፋ ሁሉም ደግ አይደለም
ህጉን ጠባቂ ግን እንደጊዜ የለም።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👏16👍3👎1
#መለየት_ቤቴ_ነው

አንቺን ይድላሽ እንጂ ካለሽበት ቦታ
እኔስ እኖራለሁ በሩቅ ሰው ትዝታ
ምን ይሆናል ብለሽ እንዴው ለነገሩ
በቂ ነው ትዝታ ከክራሬ ጋራ ለመነጋገሩ
ናፍቆትሽ ዜማዬን ፍቅርሽ ስንኝ ፈጥሮ
በልቤ ውቂያኖስ በትዝታ ጀልባ ቅኝት ነው ዘንድሮ
ይብላኝ እንጂ ላንቺ ወጥተሽ ለምቶርጅው
እኔማ ለመድኩት መለየት ቤቴ ነው።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍103
በዓመት አንድ ግዜ አንቺን መዘክሩ
መች ይበቃሽና አይመጥንም ክብሩ
ቀን በቀን ደጋግሞ ካልተከበርሽ እማ
እናቴ አይገልጸውም ዓመት ጠብቆማ
የእናት ቀንን ቆጥሮ ማመስገን ባይከፋም
ለውለታሽ ምላሽ ፍጹም አይበቃሽም!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
15👍3👏3👌2🔥1
#እኔ_ነበርኩ_እጩ!

ያብዳል ያሉኝ ሁሉ ቀድመውኝ አበዱ
እኔ ሳልጀምረው ልብስ አውልቀው ሄዱ
በማጣት መስሏቸው እብደት በደረጃ
ማግኘትም ነው ለካስ የሰው ልጅ ማበጃ
እኔ ነበርኩ እጩ አብዶ ለመታየት
ቀድመውኝ አበዱ ጥለው ያን ሁሉ ሀብት
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍34👎1👏1
እራሱን አግዝፎ በሌለው ማንነት
ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ሲደነፋ ሀሰት
ቃላት ሳተነፍስ በዝምታ ጥልቀት
ያንን ሁሉ ጉራ ዘረረችው እውነት።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
👍94❤‍🔥2
#ምዕራፍ_ያጣ_ፍቅር

በጅምር የቀረ ያልተቋጨ ፍቅር
ሁሌም የሚታወስ ዘመን የሚሻገር
በስንቱ ጓዳ ውስጥ አለ ተሸሽጎ
ፍርድን ያላገኘ ያልታየ በሸንጎ
ደብቆት ነው እንጂ በልቡ ማህደር
የፈራው የሸሸው ለሰው ለመናገር
የታሪክ ክታቡ ዶሴው ቢበረበር
በእያንዳንዱ ህይወት ያልተቋጨ ፍቅር
ሳይፈልግ የተወው አለው ቢመረመር
በትዝታ ዜማ በእህ! እህ! እንጉርጉሮ
በብቻ ጓዳ ውስጥ በልብ ተቀብሮ
ምዕራፍ ያጣ ፍቅር በአጭሩ የቀረ
ብዙ ታሪክ አለ!!! ያልተመረመረ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
12🔥3👌3👍1
ትማራለች ብዬ ሙያ ከጎረቢት
አግብቻት ነበረ አድልቼ ለውበት
እንኳንስ ልትማር የምታውቀው ጠፋት
ሽንኩርት ግዛ አለችኝ ገንፎ ለማገንፋት።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🤣24😁121
#ነይ_አብረን_እንማ

ባህል እንዲቀጥል በትውልድ ከተማ
በፌስቡክ በቲክቶክ ነይ አብረን እንማ
የጥንቱ ዘምኖ ከጀበና እርቆ
ሀሜት ዲጂታል ነው ትውልዱ ተራቆ
በቀጥታ ግቢ ከሀሜት ከተማ
በተሻሻለው ህግ ነይ አብረን እንማ
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
😁11👍8🔥3
🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6👍1
ጌታ መምጫኽ ዘመን ከመድረሱ በፊት
ልቤን ልብ ስጠው መልሰው ከጥፋት
ጴጥሮስን ከክህደት የመለሰው ዶሮ
ለእኔም ላከውና ያንቃኝ ልቤን ሰብሮ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
🙏15👍81👏1
#አበጀው_በያቸው

አንቺ አትሳቀቂ ሀቁን ንገሪያቸው
እውነት ነወይ? ሲሉሽ እውነት ነው በያቸው
በአንቺ ፍቅር ያጣሁ ማግኘት ያልታደልኩኝ
ትህምርቴን አቁሜ እብድት ያጠናሁኝ
ውበትና ፍቅር አቅሌን አስጥለውኝ
እብደት በሚል ማዕረግ ሰውነት ያጣሁኝ
እኔ ያንቺ ምርኮ የፍቅርሽ ቁስለኛ
እብድ ነኝ ለሰዎች ያልሆንኩ ወረተኛ
እናም ሲጠይቁሽ ሳትሸማቀቂ
በአንቺ መወፈፌን ለሁሉ አሳውቂ
ልብሴን አሶልቆ በሰፊ ጎዳና
የሚያንከራትተኝ ያው ፍቅርሽ ነውና
ለሚጠይቁሽም እንዲህ ንገሪያቸው
የአበደው በእኔ ነው አበጀው በያቸው።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
9💔6👍4