ግጥም
4.25K subscribers
25 photos
1 video
8 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
እባክሽ አንች እርግብ ነይ ተላኪኝማ
ሚስጥሬን ደብቀሽ ሌላ ሰው ሳይሰማ
ባደግኩበት ምድር በተወለድኩበት
አኩኩሉ አባሮሽ በተጫወትንበት
ለነበሩ ልጆች እኔ ለማውቃቸው
ለሁሉም ንገሪ እንደምወዳቸው
አደራ የኔ ውድ መልዕክቴን ስጫቸው
እነዳንረሳሳ ደግመሽ ንገሪያቸው
ዛሬ እንጀራ ሆኖ ምንም ብንራራቅ
ብዙ ትዝታ አለን እርቆ የማይርቅ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏117👍4
ሞትን ድል አድርጎ ቃሉን አከበረ
የሰይጣንን ቅጥር በድል ሰባበረ
አዳም ነጻ ወጣ ባርነት ተሻረ
የሲኦል ከተማ በቃል ተሸበረ።

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🌷🔤🌹

@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏12👍42🥰1
#ነይ_አብረን_እንጠጣ!!

ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ጌሾ
ነይ እንጠጣ ውዴ ላለመባል ዋሾ
እውነቱን እውነቱን እንድንነጋገር
ደጋግመን እንጠጣ ነይ አብረን እንስከር
አንቺም የልብሽን እኔም የልቤን ምት
በጌሾ በብቅል በሰካራም ድፍረት
መደባበቅ ሳይኖር ከማስመሰል ወጥተን
ከጠጁ ከጠላው እንጠጣ ደጋግመን!!!
እውነት በመናገር ነፃነት እንውጣ
ማስመሰል ይገፈፍ ነይ አብረን እንጠጣ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
14👏3👍2
የዓለም ስልጣኔ ዘምኑ ሲስፋፋ
ለልብ ስብራት መድኃኒቱ ጠፋ!!!
ለተሰበረ ልብ ክህደት ላደቀቀው
ከፍቅር በስተቀር ከቶ ሀኪሙ ማነው?
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
5😍3👎1
#ብትኖሪ_ባትኖሪ!

ለእኔ ቦታ የለው መምጣትትሽ መቅረትሽ
ባለሽበት ሆነሽ ቀን በቀን ልውደድሽ
ማጣት አያርቀው ማግኘት አያቀርበው
የፍቅር መነሻው ሚዛኑ ልብ ነው❤️
እድሜ ቢገሰግስ በዓመታት ቢቆጠር
ዘላለማዊ ነው አያረጅም ፍቅር
ብትኖሪ ባትኖሪ ብትርቂ ብትቀርቢ
የእኔን ናፍቆ መኖር ቀን በቀን አስቢ
ጎዳናው እድሜያችን ትዝታን ጎትቶ
ያመጣው የለም ወይ ከትላንት አስማምቶ ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍18👏4
ተደግፌ ነበር የሰው አጥር ትላንት
ተሰብሮ ጥሎኛል ሁሉም ሆኖ ወረት
አይ አለማወቄ ከንቱ ነበርኩ እኔ
ፈጣሪ እያለልኝ ፍጡርን ማመኔ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍213
#አልፈርድብሽም

ጥሩ ህሊና አለሽ መልካም ነሽ ብልሽም
ቆሜ ስንከላወስ ያለሁ ቢመስልሽም
የምነግርሽ አለኝ ካንቺ ማልደብቅሽ
አይገባሽም እንጅ እኔን ስላይደለሽ
ጀግናም ሰው ይሞታል ሲሉ ስለሰማሽ
እናም የኔ ጀግና ይኸው ሰው ገለሻል
ሰው የራበው አንጀት የማይሞት መስሎሻል🔪!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍104💔3
እኔን ከፋኝ ብላ ዓለም ላትጨነቅ
መቆዘሜን ትቼ በመጠኑ ልሳቅ
እርሷ ምን ቸገራት በእኔ ሀዘን ትጨነቅ
ቢከፋም ቢለማም እኔው ለእኔ ልሳቅ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍165👏4
#ርዕሰ_ያጣ_ግጥም

እፉየ ገላ ነኝ ያንቺ መጫወቻ
በትንፋሽሽ ሙቀት በራሪ ለብቻ
እፍ! በይኝና ልብረር አንቺ ሳቂ
በደስታ ሰክረሽ ቀን በቀን ድመቂ
እፉየ ገላሽ ነኝ አባሪኝ በትንፋሽ
አየር ላይ ሰፍፌ አንቺን ቁልቁል ልይሽ።
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
👍9🥰62
#አንቺ_ብቻ

ወዳጄን አጣሁት በቸገረኝ ጊዜ
ዘመዴን አየሁት ሲከበኝ ትካዜ
          ጎረቤቴም ቀና
           ኑሬዬን ባቃና
ወገኔ ነው ያልኩት ሲክደኝ ታዘብኩት
አግኝቶ በማጣት ወድቆ በመነሳት
አየኹት ሁሉንም ለካ ሰው የለኝም
#አማ ካንች ሌላ ዘመድ አይገኝም
ልብሽ ያልተከፋ ፊትሽ ያልጠቆረ
በችግር በደስታ አብሮኝ የነበረ
በእውነተኛ ፍቅር ከጎኔ የቆምሽው
ያንችን ኑሮ ትተሽ ስለእኔ የኖርሽው
      #እማ_እወድሻለሁ
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
🥰15👍62👏2
#እናት

ጓደኛ ሲያፈቅር ኪስ ይመለከታል
የጎደለብህ ቀን ቤቱ ይከተታል
ሚስት ስታፈቅር ደምግባት ታያለች
የረገፈ ለታ ትታ ትሄዳለች
ዘመድም ሲያፈቅር ዝናን ተመልክቶ
ጀርባውን ይሰጣል ቀን ሲጥልህ አይቶ
እናት ስታፈቅር የላትም ዳርቻ
ነፍሷን ትሰጣለች እሷ ላንተ ብቻ
@gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
26🥰8👍4👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔥2
ምን አለህ አትበለኝ ያለኝ ብዙ ነው
ገንዘብ የማይገዛው ውዱ ጤና ነው።
ጤናዬን አግኝቼ ከኖርኩኝ በሰላም
ከዚህ የበለጠ የሰው ሀብታም የለም።
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍12
#በጣም_ታምሪ_ነበር

ሠው ሰራሹ መልክሽ አፍጥጦ ባይውጣ
በጅንስ ታፍኖ ዳሌሽ ባይቀጣ
ጡትሽ ቤቱ ቢኖር ልታይ ባያበዛ
ፀጉርሽ ያንቺው ቢሆን ከሱቅ ባይገዛ
ጊዜ ባይቀይርሽ በቃልሽ ብታድሪ
ህሊናሽ ቢገዛሽ በሥጋሽ ባትኮሪ
የሴትነት ክብሩ ቢገባሽ በልኩ
ሲጠሩሽ ባ'ሮጭ በርሽን ሲያኳኩ
አስተዋይ ብትሆኝ ምግባርሽ ቢከበር
ሔዋን ሙች ልንገርሽ በጣም ታምሪ ነበር።
🚀@gitm_post 🚀
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
23👍3
ሪሞት ቢኖረው ግዜ የእጅ ስራ
ማሳለፍ መመለስ በተራ በተራ
ደጉን ወደሗላ ክፉውን ወደፊት
መቆጣጠር ነበር ፊልም ብትሆን ህይወት ።
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
18
#ሁላችን_ከንቱ_ነን!

የልብ አማኝ ጠፍቶ የአፍ አማኝ ከበዛ
በእውነት አመንጭቶ ፍቅርን ካልገዛ
መማር ከየት ይምጣ ልብ ተቆልፎ
የሰው ልጅ ካልጣለ ማስመሰልን ገፎ
ባንደበቱ ጌታን በልቡ ገንዘብን
አፉ አሜን እያለ በውስጡ ተንኮልን
ምላስ አምላክ ጠርቶ
ልብን ገንዘብ ሞልቶ
የስም ፃድቅ ሰፍቶ
በነብይ ተሞልቶ
ምህረት ከየት ይምጣ
እንዴት ይብረድ ቁጣ!
ጠዋት ክርስቶስን
ከሰአት ሰይጣንን
በግፍ ተሸፍኖ ልባችን በቀልን
የተንኮል አሽክላ አስልተን እየጣልን
ማረን እንላለን እንዴትስ ይማረን
በሁለት ቢለዋ አስብተን እያረድን
ዳዊት ከደገመ ጠዋት ምላሳችን
ማታ ላይ ስድብን ለምዶ አንደበታችን
ሊምረን ቢመጣ ቁጣውን ሊያበርደው
ምላስ ብቻ ቀርቷል ለካስ ልብ ባዶ ነው
በሐይማኖት ጥላ ተሸሽገን ከርመን
እምነት ግን ሲጠየቅ ሁላችን ከንቱ ነን
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍142
ከመቃብር በላይ ዘላለም ለመኖር
በጎ ተግባር ከውን በሰብዐዊ ፍቅር
ስምህ እንዲነሳ መቃብርን ፈንቅሎ
በህይወት እያለህ መብላት ነው ተካፍሎ።
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5🙏5🫡1
#ልሂድልሽ_በቃ

እንድንኖር እንጅ በፍቅር በደስታ
አጭሯ ዕድሜያችን በተስፋ ተሞልታ
ባንች ተደስቼ በእኔ ተፍለቅልቀሽ
ዕንባሽን አብሼ ሀዘኔን አርቀሽ
            ግና……
አስተውሎ ኑሮ አልሆንልሽ ካለሽ
ነገ ከራቀብሽ ዛሬ ካታለለሽ
ልሂድልሽ በቃ አንችም ካሻሽ ድረሽ
ለማይፀና ፍቅር ተቃቅፈን እንዳይመሽ
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍14👏4👌3
አሞኛል አሞኛል መድኃኒቱን እንጃ
እፎይ!! አበዛለሁ ለስንዝር እርምጃ !!!
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14
....... #ፃፍኩልሽ 💌 .......

አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ
ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ
ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል
ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል
አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ
ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ
ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ
የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ
እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት
ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት
ዛሬ ግን.....
ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ
አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ
በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ
ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ
እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ
ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ
✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍12👏6🔥3
የጋበዝሽኝ ዘፈን በደብዳቤ ጠቅሰሽ
አደመጥኩት ያልኩሽ መልሼ ጽፌልሽ
ውዴ ውሸቴን ነው ቴፑ ተበላሽቷል
የመረጥሽው ዘፈን ተነክሶ ተበልቷል ።

✈️ @gitm_post ✈️
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌14😁7🥴3👍1