ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
9 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ምን_አለበት?

ኮንትራት ለሆነ ለዚች ዓለም ኑሮ
ዘመን ላይሻገር ዕድሜ ተበድሮ
ሁልጊዜ እንደሮጠ በሕይወት ጎዳና
በከንቱ ሲባዝን ብሎ ጎንበስ ቀና
ጭቅጭቅ ቅራኔ ሰንቆ ጥላቻ
መዋደድን ጠልቶ ሲኖር ለየብቻ
ላያስከፍል ዋጋ ቅንነት ደግነት
ሰው በክፋት መንገድ ባይሄድ ምን አለበት?
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏124👍2
#በላቡ_ጠብታ

የከበረ ካለ በላብ በጥረቱ
በተሰጠው ጸጋ እዲሁም በእውቀቱ
የእግዚአብሔርን ገንዘብ ደፍሮ ያላነሳ
ከድሃ ጉሮሮ ነጥቆ ያላገሳ
በላብ በጉልበቱ ለፍቶ የከበረ
ለእውነተኛ ድካም ለቃሉ ያደረ
እስኪ ሰው ፈልጉ ጀግና ባለጸጋ
በቅጡ የሚሰጥ የእግዚአብሔርን ዋጋ
ከእናቶች መቀነት ነጥቆ የማይበላ
በተሰጠው ወንበር ከቶ ማያዳላ
በህጻናት ጉልበት በአባቶች ሳይነግድ
በእውነተኛ ድካም ሀብቱን የሚያሳድግ
በላብ በጉልበቱ በጥረቱ ደክሞ
ሀገሩን ሳይቀማ ለማደጓ ቆሞ
በላቡ ጠብታ ለክብር የበቃ
ለስራ ለትጋት ገስግሶ የነቃ
እርሱ ነው ሰው ማለት ትልቅ ባለዋጋ
ሲጠሩት ደስ የሚል የእውነት ባለጸጋ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰7👍6👌1💯1
እንኳን እዩኝ እዩኝ ትቢት ተደማምሮ
መኖር ከባድ ሆኗል አንገትንም ሰብሮ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍12💯53
#ማዘንስ_ለከዳ!

ወዳጅ ሸርተት ሲል ጊዜ ሲያዳልጠው
ሰው ከመሆን ወርዶ ገንዘብ ሲለውጠው
አትከፋ ከቶ ወቀሳ አታብዛበት
ጉዳቱ ለእርሱ ነው ከጠላ ሰውነት
በገንዘብ መዝኖ ውብን ጓደኝነት
ሲያረክሰው በንዋይ ያንተን ታማኝነት
ማዘን ለከዳ ነው ለተከዳ አይደለም
ለቃል ያልታመነ ሰላም አያገኝም
ወርቅን አበድረህ መዳብ ቢመልሱ
ይብሳል ፀፀቱ አይተኙም እነርሱ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍6
ምን አንሰማው  አለን እኛማ ዘንድሮ
መቼም ሞልቶ ማይፈስ ውቂያኖስ ነው ጀሮ ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍2👏1
#ናፈቅሽኝ

ከፍቶሻል መሰለኝ እኔን ሀዘን ዋጠኝ
አልቅሰሻል መሰል ዓይኔን ቆጠቆጠኝ
ሆድ ባሰሽ መሰለኝ ሆዴ ተላወሰ
ትዝ አልኩሽ መሰለኝ ትዝታሽ ፈሰሰ
ካልጠፋው አካሌ ልቤጋ ከበደኝ
ዓይን፣ጥርስ አካልሽ ጨዋታሽ ናፈቀኝ
አቦ ናፍቀሽኛል ብዙ አታስለፍልፊኝ
መምጣት ባትችይ እንኳን ባሳብሽ እቀፊኝ
          ያንችን ልክ የያዘው....
የልቤ ላይ ጥጉ ብርድ አንዘፍዝፎታል
አለሁልህ በይው ያ ድምፅሽ ናፍቆታል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍169🥰2🔥1
አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ
ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ
ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም
ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም
ቅዝምዝሙ ይለፍ ጎንበስ ልበልና
ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰9👍2
ተከታታይ ትረካ በ Facebook page ተጀምሯል Follow እያደረጋችሁ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61557221074498
👍1
#እንዲህ_ብለሽ_ጻፊ

በፍቅሬ ተይዞ ስሜን እየጠራ
በየጎዳናው ላይ ብቻውን ሲያወራ
ወፍፎ እየሳቀ አጥቶኝ ሲንከራተት
ለእኔ ፍርቅር ታምኖ ሲሸለመው እብደት
እኔ እስቅ ነበረ በድል ኩራት ጥርሴ
ለእርሱ ጥልቅ ፍቅር ማዘን ትታ ነፍሴ
በሞቀው ከተማ በትርምስ ቀለም
ወድቆ በእኔ ውበት ሲስቅበት ዓለም
አብሬ ስቂያለሁ መውደቁ አስደስቶኝ
ስሜን እየጠራ ሁሌም ሲከተለኝ!!!
ግና ግፌ በዝቶ ሞልቶ ፈሰሳና
እጣውን ቀመስኩኝ በእኔ ደረሰና
እኔም በተራዬ በሌላ ሰው ፍቅር
ወፍፌ እዞራለሁ በወሰድኩት ብድር
እርሱ ዛሬ የለም ለእውነት ኖሮ ሞቷል
ህመም ስቃዩን ግን ለራሴ ውርስ ሆኗል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍13🤗1
#ናፍቀሽኛል_ብዬ

ናፍቀሽኛል ብዬ ለመጮህ አልወጣ
ሰውም ቢያፌዝ እንጅ አንችን ይዞ አይመጣ
ናፍቀሽኛል ብዬ እኔም ግጥም አልፅፍ
ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ
ናፍቀሽኛል ብዬ ከአንቺ ዘንድ አልደርስም
ከፊትሽ የመቆም ድፍረቱም የለኝም
ናፍቀሽኛል ብዬ እምባም አይወርደኝም
ያንችን ሲያስነባ አይቷል ዓይኔም እሽ አይለኝም
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍143💔1
ክርስቶስ ቢመጣ በይፋ ለመፍረድ ፤
ዘሩን ይጠይቃል የእኔ ዘመን ትውልድ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍17😢6
#ግዜ

ጌዜ ዳኛ ሆኖ በሁሉም ይፈርዳል
የሄደው ይመጣል የመጣው ይሄዳል
ያበደው ይድናል ጤነኛውም ያብዳል
ግዜ እንደፔንዱለም በሁሉም ይዞራል
አንድ የሚቀር የለም ሁሉም ይቀየራል
ቀባሪም በተራው ሞቶ ይቀበራል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌8👍5
Forwarded from PHOTO STYLE (《Madonna》)
🔤🔤🔤 🔤🔠🔠🔠🔠🔠🔠

@photo_style_shop
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍4
እወድሽ ነበረ አልወድሽም ተውኩት
ልብሽ ወደ ሌላ ሲንሻፈፍ አየሁት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
13👍1👎1
የእኔ ፍላጎቴ ምኞቴ ባይሞላ
ጌታ አትዘገይም ተነስተህ ከሗላ
የረፈደ መስሎኝ ባንተ ሳጉረመርም
ለካስ ለበጎ ነው ያሳጣኸኝ የለም።
ያለግዜው አትሮጥ በግዜውም አትቀር
አንተ ያልከው ይሁን ታማኝ ነህ እግዚአብሔር
  #ተመስገን_ጌታዬ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰162👍1
#ለቅሶ_ቤት_ሄድኩና

እንባዬ ደርቆብኝ ለማልቀስ ስቸገር
በድንገት ትዝ አለኝ ያደረግሽኝ ነገር
ትውስ ያለኝ ጊዜ የሰራሽኝ ስራ
ሚፈሰው እንባዬ እንደምን ያባራ
አልቅሼ አላቀስኩኝ ሳላዝን በሟቹ
ድሮም ያንች ፍቅር ለሀዘን ነው ምቹ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍20😁6
ሁሉንም አየሁት
ሁሉንም ጀመርኩት
ሁሉንም ሰማሁት
መጨረሻም ተውኩት
  የልብ የሚሞላም...
ሆኖ አላገኘሁት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏121👌1
#መታረቅ_ከራስ_ነው

በጠለቀ ስሜት ውስጥን በሚጠይቅ
የህይወትን ግጭት ከራስ በሚያስታርቅ
ማሰብ ማሰላሰል እራስን መጠየቅ
በውስጣዊ ውበት ከራስ ጋር መታረቅ
ከአለፈው ልምድ ወስዶ ዛሬ ላይ አስቦ
የነገን ህልም ስሌት በተስፋ ደርቦ
ለተሰጠው እድሜ ምስጋና እየቸሩ
መታረቅ ከራስ ነው መብሰል እያደሩ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌6🔥5👍1🥰1
ሽሽት ሽሽት አለኝ
ግን ወዴት ይሸሻል
ህይወት ያው ህይወት ነው
     ይነጋል ይመሻል
ሰውም እንደዘበት ይቀርባል ይርቃል
እኮ ወዴት ልሽሽ ውስጤ ይጨነቃል
አንድ ፈጣሪ ግን መድረሻዬን ያውቃል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
20👍4🎉2
#ሰውና_ዘመን

ሰው ዘመንን ሲከስ
እድሜም ሲገሰግስ
ከላይ ያለው ሲስቅ
የስሩ ሲጨነቅ
ሰውና ዘመንን ሲጠፋ አስታራቂ
አዋቂነት ጠፍቶ ሲበዛ ታዋቂ ፤
በእንዲህ አይነት ህይወት እድሜ እየለመኑ
አሁን ምን ይባላል ? ማለት ነው ዘመኑ?
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍11🫡3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍5🥰2