ግጥም
4.25K subscribers
26 photos
1 video
9 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#በይቅርታ_ጋሻ

ከበደሉህ በላይ በዳይ ልብ ከኖረህ
አንተስ ከበዳዮች በምን ትለያለህ?
የተሻለ በዳይ ካልተባልክ በስተቀር
ቂምን በቂም አጥቦ አይገኝም ፍቅር
የክርስቶስ ጀግና መሆንን የሚሻ
ጠላቱን ይማርከው በይቅርታ ጋሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6👍3💯2
ብስልና ጥሬ ሆኖብኝ ነገሩ
ጥሬው እስኪበስል ብስሉ ማረሩ
ግራ ተጋብቼ ጠፍቶኝ ቁም ነገሩ
ሳልበላው ታማሁኝ ላይቀር ጾም ማደሩ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
14
የድሀ ፍቅር

ክፍል 12

በጣም ደነገጥኩ ደግሜ ስደውል ስልካቸውን አያነሱም ግራ ገባኝ በሜላት ስልክ ትንሽ ታገሰኝ እደውላለሁ የሚል ሜሴጅ ደረሰኝ ትንሽ ተረጋጋሁ ከትንሽ ቆይታ በሀኋላ ሜላት ደወለች በፍጥነት አነሳሁት ምንድነው ምን ተፈጠረ ሜላቴ አልኳት ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አለችኝ እና ለምን ይሄን ያክል ጊዜ ደጋግማችሁ ደወላችሁ አልኳት የኔ ውድ እንዳትደነግጥ በጥሞና አዳምጠኝ አለችኝ እሽ አልኳት ግን ምንድነው አልኳት ልቤ ፍራት ፍራት እያለው ካልተረጋጋህ ልነግርህ አልችልም አለችኝ እሽ !እሽ ! ንገሪኝ አልኳት ለመረጋጋት እየሞከርኩ እየውልህ የኔ ፍቅር ዛሬ ትንሽ ችግር ተፈጥሯል አንተ ትምህርት ልትጨርስ አንድ ወር ነው የቀረህ አይደል? እኛ ደግሞ ይቺን አንድ ወር በዘዴ ማለፍ ይኖርብናል አለችኝ ምንድነው ግራ ገባኝ እኮ ንገሪኝ አልኳት ውስጤ ግን ይበልጥ ፍርሀት ውስጥ ገብቷል ምን መሰለህ የኔ ውድ ማታ እንደነገርኩህ አባቴ ሌላ ቦታ ለስራ ሊሄድ ነበር ነገር ግን ጠዋት ትንሽ ችግር ተፈጥሮ እኔ ከቤት ወጥቻለው አለችኝ ደነገጥኩ ለምን እንዴት ብዬ ጥያቄየን አፋጠንኩት ተረጋጋ አባቴ ውሳኔየን ሲጠይቀኝ የማላውቀውን የማልወደውን ሰው ማግባት እንደማልችልና እንደማልፈልግ ስነግረው ከቤት አባረረኝ አሁን እናንተ ቤት ነኝ አለችኝ ብደነግጥም ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌው ወይኔ በጌታ እሽ በቃ እሱው ጋ ሁኚ ግን ተጠንቀቁ አልኳት ችግር የለውም እኔ ግን የደወልኩት ዋነኛው ምክንያት ይሄ አይደለም አባቴ ምናልባት የት ዮኒቨርሲቲ እንደደረሰህና ያለህበትን ካወቀ ችግር እንዳያደርስብ እንድትጠነቀቅ ልነግርህ ነው ምክንያቱም በጣም ሲዝት ነበር አለችኝ አይ ችግር የለውም እዚህ ምንም አይፈጠርም አታስቢ አልኳት አባቷ እኔን ምንም ማድርግ አይችሉም የፈራሁት ለወንድሜና ለእናቴ ነው ምንም እንዲሆኑብኝ አልፈልግም ሜላቴንም ማጣት አልፈልግም እሷ ሀብታም እኔ ድሀ ሆኜ ያለን ፍቅር እሷም እንደእኔ ድሀ ስትሆን ይዘልቅ ይሆን አላውቅም ብቻ ግን አሁን ላይ አፈቅራታለሁ ሁሉም ምንም አይሁኑብኝ የሚገርመው እኔ ሳላውቅ ሜላቴ ብር በእኔ አካወንት ማስገባቷን ስትነግረኝ ደነገጥኩ ብዙ ብር ነው ስፈልግ ስፈልግ ትልክልኛለህ ይቀመጥ ለጊዜው ትንሽ ብር እጄ ላይ አለ አለችኝ እሽ አልኳት ሜላት እኛ ቤት መኖር ከጀመረች ሳምንት ሆኗቷል እኔም ፈተና ስለደረሰብኝ በጥናት ተወጥሪያለው በቃ ብቻ ስለ ወደፊቱም አስባለው አንዳንዴ የነገን አምላክ ያውቃል ብዬ እተወዋለው ሜላት እኔ ጋ መምጣት ፈልጋ ነበር እኔ ግን የፈተና ሰአት ስለደረስ አትምጪ አልኳት ምክንያቱም እሷን ትቼ ማጥናት አልችልም ግዴታ አብሪያት መዝናናት ይኖርብኛል እሷም ስለተረዳችኝ ምንም አላለችኝም እሽ ብላ ቀረች ሜላት ስራ አቁማለች ምንም አትሰራም እኛ ድሮ ከምንኖርበት ቤት ለቀው ሌላ ቦታ ተከራይተው ነው የሚኖሩም ምክንያቱም ወንድሟ ቤታችንን ያውቀው ስለነበር እንዳያገኛት በማሰብ ነበር የሜላት እናት ለሜላት እባቷ ሳያውቅ ብርም አንዳንድ ነገር ያደርጉላታልእባቷ ግን ደውለው አያውቁም የት እንደምትኖርም ለማጣራት አልፈለጉም ብር ስትጨርስ ተመልሳ ትመጣለች ብለው አስበዋል እሷ ግን ወደ ቤት አልተመለሰችም ነበር ማታ ሳጠና አምሽቼ ጠዋት ተነስቼ ሻወር ወስጄ ወደ ላይብረሪ ሄድኩኝ ትንሽ አጠናሁና ተመልሼ ወደ ዶርም ገባሁ ሜላቴ ደወለች በጣም እያለቀሰች ነው እባቷ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሎ ተነግሯት ወደ ሆስፖታል እየሄደች መሆኑን ነገረችኝ ደነገጥኩ ምንም አባቷ ሊለያዬን ቢፈልጉም ምንም እንዲሆኑ ግን አልፈልግም ነበር በቃ አይዞሽ ተረጋግተሽ ሂጂ አልኳት በቃ ደረስኩ ብላኝ ስልኩ ተዘጋ እኔም ቆሜ ቀረሁ .....

ይቀጥላል............

@gitm_post

LIKE & SHARE
8👍5🥰1
#ዓለም_ወዬው_ላንቺ!!!

የትኛው ምግባሬ በየቱስ ስራዬ
መልስ ይዤ እቀርባለሁ ሲመጣ ጌታዬ
እብሪተኛው ልቤ ትቢት የወጠረው
ከጌታ ፊት ሸሽቶ ከአምላክ የሸፈተው
ተግሳጽን የናቀች ቅልብልብ ምላሴ
ስቃይ ሃጢአት ጠርታ ተረፈች ለነፍሴ
ዓለም ወዬው ላንቺ ለሚመጣው ቁጣ
ማን ይሆን ዋስትናሽ ክርስቶስ ሲመጣ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍96💯3
የድሀ ፍቅር

ክፍል 13

ሜላቴ ደወለችልኝ በጣም እያለቀሰች ነበር በጣም ስለደነገጥሁ ምን እንደተፈጠረ ጠየቅኋት እሷም አባቷ የመኪና አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል ተጠርታ እየሄደች እንደሆነ ነገረችኝ በቃ አይዞሽ ሁሉም ለበጎ ነው አባትሽ ምንም አይሆኑም ተረጋጊ አልኳት እሽ በቃ ሆስፒታል ደርሻለው በኃላ እናወራለን ብላኝ ስልኩን ዘጋችው ደነገጥኩ አምላኬ ምን ይፈጠር ይሆን አባቷ ምንም እንዲሆኑ አልፈልግም ሜላቴ ትጎዳብኛለች በቃ ጌታዬ አደራህን ብዬ ወደ ዶርሜ ገባሁ ዶርሜ ውስጥ ቁጭ ብዬ ስልኬን መጠባበቅ ጀመርኩ እስካሁን አልደውለችም ግራ ገባኝ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም ማንም ጋ መደወል አልቻልኩ እናቴ ጋ ለመደወል አስቤ እሷን ማስጨነቅ ስለመሰለኝ ተውኩት ደብተሬን ማገላበጥ ጀመርኩ ማጥናት ባልችልም ከደብተሬ ጋ ግን ተፋጠጥን ሜላቴ አልደወለችም በጣም ሲብስብኝ ምን ተፈጠረ የኔ ፍቅር ብዬ ሜሴጅ ላኩላት ደህና ነው ትንሽ ቆይቼ እደውልልሀለው እሽ አለችኝ ትንሽ ተረጋጋሁ ወደ ጥናቴ ተመለስኩ ሰአቱ እየመሽ ስለነበር ከዶርም አልወጣሁም ወዲያው እናቴ ደወለችልኝ ሰላም አለችኝ ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቅኋት ምንም አልተፈጠረም ሜላት ደውላ ደውዬ እንድነግርህ ነግራኝ ነው አባቷ ደህና ናቸው ምንም አልሆኑም ዛሬ ሆስፒታል ስለሚያድሩ እሷም እዛው ነው የምታድረው ለመደወል ስላልተመቸኝ ነው ብላሀለች አለችኝ እሽ አልኳት የአባቷ ደህና መሆን አስደስተኝ ጠዋት ተነስቼ ወደ ክላስ ከመግባቴ በፊት ለሜላት ሜሴጅ ፃፍኩላት አባትሽ ተሻላቸው? አንቺስ እንዴት ነሽ የኔ ፍቅር? አልኳት አላየችውም መሰል መልስም አልተላከልኝም ወደ ክላስ ገባሁ ከትምህርት መልስ ላይብረሪ ገብቼ አጥንቼ ስወጣ ሜላት ደወለችልኝ ይቅርታ የኔ ውድ ለመደወል ስላልተመቸኝ ነው ምናልባት ሳወራ ስምተው ስልኬን ፈትሽው ቁጥርህን እንዳይወስዱ በማሰብ ነው ይቅርታ አለችኝ እረ ችግር የለውም አባትሽ ግን እንዴት ናቸው አልኳት ተሽሎታል ወደ ቤት ልንወስደው ነው እኔም ወደ ቤት እመለሳለሁ እስከሚሻለው ድረስ አለችኝ የሜላት ወደ ቤት መመለስ ቢያስደስተኝም ላግባት ያለው ልጅ መምጫው ስለደረስ ግን አሳስቦኛል ብቻ ምንም ማለት ስላልፈለግሁ እሽ በቃ ሂጂ አባትሽን እግዚአብሔር ጨርሶ ይማራቸው ብያት ስልኩ ተዘጋ ፈተና ለመፈተን ሳምንት ስለቀረን በጣም በጥናት ተወጥሪያለው ወደ ጥናቴ ተመልሼ ሳጠና አመሸሁ ሜላት አንድ ታላቅ እህት አለቻት አላገባችም ማግባት አትፈልግም የመጀመርያ ፍቅረኛዋ በመኪና አደጋ ስለሞተባት ብዙ ተሰቃይታለች ሌላ ወንድ አልፈልግም እሱም ቀርቷል እንኳን ሌላው የሚል አመለካከት አላት ሜላት እቤቷ ተመልሳለች አባቷም ደህና ናቸው ከቤት ልጁን አባረረ ላለመባል እንጂ ተመልሳ ወደ ቤት እንድትገባ አይፈልጉም ነበር ሜላት ስልክ ደወለችልኝ እቤት እንደሆነችና ነገ ማታ እንግዳ እቤት ይመጣል ስለተባልኩ ብር ያስፈልገኛል ላክልኝ አለችሽ እሽ ብዬ የራሷን ብር አውጥቼ የምትፈልገውን ያክል ላክሁላት እንግዳው ማን እንደሆነ አላወቅሁም ግን ሲያወሩ የሰማሁት የአባቴ የስራ ባልደረቦች እንደሆኑ ነው አለችኝ ችግር የለውም ብቻ እራስሽን ጠብቂ አልኳትና ስልኬን ዘግቼ ወደ ጥናት ተመለስኩኝ እኔ ከተመረቅሁ በኋላ ቶሎ ስራ ይዤ ሜላቴን ማስደሰት እናቴን ማስደስት ነው የምፈልገው ለዛም ነው የምችለውን ያክል የማደርገው ሜላቴ ቀኑን ሙሉ አልደወለችም እንግዳ አለ ስላለች ልረብሻት ስላልፈለግሁ ዝም ብዬ አመሽሁ ሜላቴ ደወለችልኝ የሚገርም ነገር ልንገርህ አለችኝ በደስታ እየተፍለቀለቀች ምን ተገኝቶ ነው ንገሪኝ እስኪ የኔፍቅር አልኳት ሜላቴ ፍፁም ደስተኛ ነበረች.....

ይቀጥላል ......

@gitm_post

LIKE & SHARE
👍75
ታዋቂው ተግተልታይ መንገድ እየዘጋ
አዋቂው ተኝቶ ህይወት ተዘነጋ።
ቀስቀስ ቀስቅስ አርጉት ነቅቶ ያስተምረን
የአለማወቅ ጎርፉ ጨርሶ ሳይወስደን።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
💯3🙈1
የድሀ ፍቅር

ክፍል 14

ሜላት ደወለችልኝ በጣም ደስተኛ ነበረች ደስተኛ ስለሆነች በጣም ደስ አለኝ ግን ምን እንዳስደሰታት አላውቅም የኔ ፍቅር ምን ተገኘ ዛሬ ደስተኛ ሆነሽልኛል አልኳት የኔ ውድ ዛሬ አዲስ አበባ ብትሆን አለህበት ድረስ እመጣ ነበር አለችኝ በደንብ አሳቀችኝ የኔ ፍቅር እውነት ደስታሽ እኔንም አስደሰተኝ የኔ ፍቅር አለችኝ ሜላት በሚያምር ድምጿ ወዬ የኔ ውድ አልኳት በምን ደስ እንዳለኝ ታውቃለህ ንገሪኛ ካልነገርሽኝ በምን አውቃለው አልኳት ሊያገባኝ የሚፈልገው ልጅ መጣ አለችኝ ቆሌዬ ግፍፍ አለ ተርበተበትኩ ሜላቴን ይሄንን ያክል ያስደስታል ብዬ አስቤ አላውቅም ግን ደስታዋ አስደነገጠኝ ምን ማለት ነው የእሱ መምጣት ነው እንደዚህ ያስደሰተሽ? አልኳት ከትትትትትትት😄 ብላ ሳቀችብኝ ይበልጥ ተናደድኩ እሽ ጠዋት እደውልልሻለው አልኳት ቆይ ቆይ እንዳትዘጋው አለችኝ የሜላት በልጁ መምጣት እንደዚህ መደሰት በጣም አበሳጭቶኛል ለዛም ነበር ደህና እደሪ ብዬ ስልኩን ልዘጋባት የነበረው መናደዴ ስለገባት ልንገርህ ምን መሰለህ ልጁ ስለመጣ አይደለም የተደሰትኩት እሱ እኔን ሳይሆን ታላቅ እህቴን ማግባት እንደሚፈልግ ስለተናገረ ነው አለችኝ ቆሌዬ ግፍፍ አለ ምን አልኳት አዎ እህቴን እንዳያት እሷን ነው ያጫችሁልኝ ብሎ ሲጠይቅ አባቴም አዎ አለ ከዛ እኔ ከጨዋታው ውጪ ሆንኩልህ ማለት ነው አለችኝ እየተፍለቀለቀች ኦ አምላኬ ብዬ ደስ አለኝ ሜላቴ እኔ ማመን አልችልም አልኳት እመን በቃ ከዚህ በኋላ ማንም በመሀከላችን አይገባም አለችኝ አብረን ደስ አለን ፈተናዬን ጨረሼ እስከማገኛት ድረስ ጓጉቻለው ፈተና ለመፈተን ለ3 ቀን ያክል ሲቀረኝ ሙሉ በሙሉ ትኩረቴ ጥናቴ ላይ ሆኖል ሜላትን በቀን አንድ ጊዜ ነው የማገኛት የሳምንት ፈተናዬን እንደምንም ተወጣሁ በጣም ይከብድ ነበር ግን በቃ ሰራሁት ውጤት እስከሚመጣ ድረስ ቤተሰብ ጋ ሂድኩኝ ሜላቴ መኪናዋን ይዛ መጥታ ወሰደችኝ ፍፁም ሰላም ተሰማኝ እናቴ ያላትን ብር አሰባስባ ለእኔ የምርቃት ዝግጅት ለማዘጋጅት ደፋ ቀና ማለት ጀመረች እኔ ግን ምንም ድግስ አልፈልግም ብላት ልትሰማኝ ፈቃደኛ አይደለችም ጊዜው ደርሶ የምርቃት ቀን ደርሶ እኔም ሜላቴም እናቴም ታናሽ ወንድሜን ይዘን ወደ ዮኒቨርሲቲ ሄድን የሚገርመው ከዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች የበለጠውን ውጤት ያመጣሁት እኔ ነበርኩ የማዕረግ ተመራቂ ሆኜ ተመረቅሁኝ እናቴን አሰደስትኩ ሜላቴን አስደሰትኩ በቃ እኔም የልፋቴን ውጤት ሳይ ደስ አለኝ ሁሉንም አስደስቼ ድህነቴ ሳያግደኝ የምፈልግበት ደረጃ ላይ ደረስኩኝ በዮኒቨርሲቲያችን ከተማሩና ከፍተኛ ውጤት ካመጠት ተማሪዎች ውስጥ ተመርጠን የውጪ የትምህርት እድል እንደመጣልን ተነገረኝ ለሜላት ይሄ ዜና ባያስደስታትም ለኔ ግን ጥሩ እድል ነበር እኔና ሜላት ፍቅራችን በጣም ደስ የሚል ነው ለደቂቃ እንኳን ተጣልተን አናውቅም ይህ የትምህርት እድል ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ግን በወጣሁ በገባሁ ቁጥር ስልክ ባወራን ቁጥር መጨቃጨቅ ጀምረናል ነገሩ በጣም እያሳሰበኝ ነው.....

የመጨረሻው ክፍል ነገ ከ 30 React በኋላ ይቀርባል

@gitm_post
👍22🥰5🔥41
የድሀ ፍቅር

ክፍል15

የመጨረሻው ክፍል

አሪፍ ውጤት ስለነበረ ያመጣሁት ከዮኒቨርሲቲያችን ውስጥ እኔና ሌላ ሁለት ልጆች ለትምህርት እድል ወደ ውጪ ለመሄድ ተመረጥን ነገር ግን ሜላት ደስተኛ እንደማትሆን ሳስብ ግራ ገባኝ ከተመረቅሁ በኃላ እኔና ሜላት እንደድሮው አይደለንም በቃ አብዛኛን ጊዜ እኛ ቤት ስለምትውል በቃ ፀባይዋ ተቀያይሯል የት ወጣህ የት ገባህ ማለትም ጀምራለች እኔ በፍፁም ሜላቴን ማስከፋት አልፈልግም ምክንያቱም ሜላት ሁሉ ነገሬ ናት ፍቅር ሀ ብዬ የጀመርኩባት ብቻ ሳትሆን ዛሬ ላይ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፆ ያበረከተችም ጨምር ናት በቃ የምትለኝን ከማድረግ ውጪ ምንም ነገር አላገርግም በፍፁም ከፍቷት ማየት አልፈልግም ሜላት አንዳንዴ በነገር ወጋ ታደርገኛለች እዚህ አድርሼህ ትለኛለች ግን እኔ ምንም መናገር አልፈልግም ብትልም እውነቷን ነው በሷ ሀይል ነው እዚህ የደረስኩት ግን አንዳንዴ ይሄንን ሳስብ የትምህርት እድሉን መጠቀም እንዳለብኝ ይሰማኛል ምክንያቱም ነገ አብረን መኖር ስንጀምር ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ የኔ የሆነ ነገር ሳይኖረኝ አብረን መኖር እንደማንችል ይሰማኛል ሜላት አብረን እንድንኖር ትፈልጋለች በተለይ ታላቅ እህቷ በሚያምር ሰርግ ካገባች በኋላ የማግባት ትዳር የመመስረት ፍላጎቷ ጨምሯል እኔ ደግሞ ይሄንን የማድረግ አቅሙ የለኝም ሜላቴ ሁሌም በስልክም ሆነ በአካል ወሬዋ ትዳር አብሮ መኖር ከዛም ባለፈ ስለ ገንዘብ ሆኗል የእሷ ገንዘብ እንደሚያኖረን ትነግረኛለች ግን ይሄ ለእኔ አላስደሰተኝም እስካሁን ያደረገችልኝ ይበቃል ከዚህ በኋላ እኔ የምትፈልገውን ላደርግላት ነው የምፈልገው ስለዚህ የሷ ሀሳብ አልተስማማኝም ሁሌም በህይወቴ የሚፈጠሩትን ነገሮች ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት ለእናቴ አሳውቃታለው በቃ እሷ አድርግ ያለችኝን አደርጋለው እሷ አይሆንም ካለች እተወዋለሁ በቃ አሁንም እናቴን ማማከርና ውሳኔዋን ማወቅ እፈልጋለው እሷ ያለችው ይሆናል ማታ ላይ በረንዳ ቁጭ ብለን እያወራን እያለ ለእናቴ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት ምንም አላስቀረሁም ውሳኔሽን እፍልጋለው ምን ልወስን ግራ ገባኝ አልኳት እናቴ በጣም ስለምታስብልኝ ትክክለኛውን ውሳኔ ነው
የምትነግረኝ ልጄ እዚህ ደረጃ ለመድረስህ የሜላት አስተዋፆ በጣም ትልቅ ነው እሷን በፍፁም እንዳታስከፋት የትምህርት እድልህንም እንዳታጣ ይሄ ላንተ በጣም ጥሩ እድል ነው ለወደፊት ህይወትህ ይጠቅምሀል እኔ የምልህ ከሜላት ጋ ተነጋግራችሁ ውሳኔ ወስኑ ነው አስፋላጊ ከሆነ ነገ ማታ ጥራትና እንመካከር ይሄ ይሻላል ነው የምልህ አለችኝ እሽ እማ አልኳት እናቴ ያለችኝ ነገር ትንሽ ቀለል እንዲለኝ አደረገኝ በማግስቱ ጠዋት ተነስቼ ሜላቴ ጋ ደውዬ ማታ ላገኛት እንደምፈልግና እቤት እንድትመጣ ነገርኳት እሽ አለችኝ ሜላት ጥሩ ስሜት የላትም ብቻ ግን እሽ ስላለች ደስ ብሎኛል ሜላቴ መጥታ ምን እንደምንባባል እያሰብኩ ዋልኩ መምሸቱ አይቀር ሜላትም መጣች እኔም እናቴም ሜላቴም ቁጭ ብለን መነጋገር ጀመርን እናቴ ለሜላት ሁሉንም ነገር ነገረቻት በቃ በመነጋገር የድሮ ፍቅራችሁን አድሱ እኔ እንደድሮው እንድትሆኑ ነው የምፈልገው አለችኝ ተነጋግረን አንድ ውሳኔ ላይ ደረስን እኔም የትምህርት እድሌን እንዳያመልጠኝ መሄድና መማር እንዳለብኝ እኔና ሜላትም ቀለበት ማድረግ እንዳለብን ተወሰነ በሀገር ባህላችን እኔና እናቴ ለሜላት ቤተሰቦች ሽማግሌ ላክን ቤተስቦቿ ትንሽ ቢግደረደሩም እሽ እሉ እኔና ሜላት ቀለበት አሰርን እኔም ወደ አወስትራሊያ ለትምህርት ሄድኩ ፍቅራችን እንደድሮው ሆነ እኔ ያለ ሜላት ሜላት ያለ እኔ ማንንም አንፈልግም ፍቅራችን ችግር ቢበዛውም ችግሩን ተቋቁመን አለፍን::

ተፈፀመ

ውድ አንባቢያን አስተያየትዎን ይስጡን 🙏

@gitm_post
👍20
#ይልቅስ_ልብን_ላክ

ልባችን ሳይማር የፍቅር አቡጊዳ
እንዲሁ  እንደ ዘቀጥን ሰው ሳይሰናዳ
አትምጣ ጌታ ሆይ በጎችን ፍለጋ
ትከፍላለህና ዛሬም ሌላ ዋጋ።
ይልቅስ ልብን ላክ ለልብ አልባው ትውልድ
ከመምጣትህ በፊት እርስ በእርስ ይዋደድ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
15👍4
⁉️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በግዜ ህግጋት በቀመር ሲሰላ
ህይወት ፈረቃ ናት ከፊትና ሗላ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍121
#ምን_አለበት?

ኮንትራት ለሆነ ለዚች ዓለም ኑሮ
ዘመን ላይሻገር ዕድሜ ተበድሮ
ሁልጊዜ እንደሮጠ በሕይወት ጎዳና
በከንቱ ሲባዝን ብሎ ጎንበስ ቀና
ጭቅጭቅ ቅራኔ ሰንቆ ጥላቻ
መዋደድን ጠልቶ ሲኖር ለየብቻ
ላያስከፍል ዋጋ ቅንነት ደግነት
ሰው በክፋት መንገድ ባይሄድ ምን አለበት?
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏124👍2
#በላቡ_ጠብታ

የከበረ ካለ በላብ በጥረቱ
በተሰጠው ጸጋ እዲሁም በእውቀቱ
የእግዚአብሔርን ገንዘብ ደፍሮ ያላነሳ
ከድሃ ጉሮሮ ነጥቆ ያላገሳ
በላብ በጉልበቱ ለፍቶ የከበረ
ለእውነተኛ ድካም ለቃሉ ያደረ
እስኪ ሰው ፈልጉ ጀግና ባለጸጋ
በቅጡ የሚሰጥ የእግዚአብሔርን ዋጋ
ከእናቶች መቀነት ነጥቆ የማይበላ
በተሰጠው ወንበር ከቶ ማያዳላ
በህጻናት ጉልበት በአባቶች ሳይነግድ
በእውነተኛ ድካም ሀብቱን የሚያሳድግ
በላብ በጉልበቱ በጥረቱ ደክሞ
ሀገሩን ሳይቀማ ለማደጓ ቆሞ
በላቡ ጠብታ ለክብር የበቃ
ለስራ ለትጋት ገስግሶ የነቃ
እርሱ ነው ሰው ማለት ትልቅ ባለዋጋ
ሲጠሩት ደስ የሚል የእውነት ባለጸጋ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰7👍6👌1💯1
እንኳን እዩኝ እዩኝ ትቢት ተደማምሮ
መኖር ከባድ ሆኗል አንገትንም ሰብሮ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍12💯53
#ማዘንስ_ለከዳ!

ወዳጅ ሸርተት ሲል ጊዜ ሲያዳልጠው
ሰው ከመሆን ወርዶ ገንዘብ ሲለውጠው
አትከፋ ከቶ ወቀሳ አታብዛበት
ጉዳቱ ለእርሱ ነው ከጠላ ሰውነት
በገንዘብ መዝኖ ውብን ጓደኝነት
ሲያረክሰው በንዋይ ያንተን ታማኝነት
ማዘን ለከዳ ነው ለተከዳ አይደለም
ለቃል ያልታመነ ሰላም አያገኝም
ወርቅን አበድረህ መዳብ ቢመልሱ
ይብሳል ፀፀቱ አይተኙም እነርሱ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍6
ምን አንሰማው  አለን እኛማ ዘንድሮ
መቼም ሞልቶ ማይፈስ ውቂያኖስ ነው ጀሮ ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍2👏1
#ናፈቅሽኝ

ከፍቶሻል መሰለኝ እኔን ሀዘን ዋጠኝ
አልቅሰሻል መሰል ዓይኔን ቆጠቆጠኝ
ሆድ ባሰሽ መሰለኝ ሆዴ ተላወሰ
ትዝ አልኩሽ መሰለኝ ትዝታሽ ፈሰሰ
ካልጠፋው አካሌ ልቤጋ ከበደኝ
ዓይን፣ጥርስ አካልሽ ጨዋታሽ ናፈቀኝ
አቦ ናፍቀሽኛል ብዙ አታስለፍልፊኝ
መምጣት ባትችይ እንኳን ባሳብሽ እቀፊኝ
          ያንችን ልክ የያዘው....
የልቤ ላይ ጥጉ ብርድ አንዘፍዝፎታል
አለሁልህ በይው ያ ድምፅሽ ናፍቆታል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍169🥰2🔥1
አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ
ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ
ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም
ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም
ቅዝምዝሙ ይለፍ ጎንበስ ልበልና
ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰9👍2
ተከታታይ ትረካ በ Facebook page ተጀምሯል Follow እያደረጋችሁ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61557221074498
👍1
#እንዲህ_ብለሽ_ጻፊ

በፍቅሬ ተይዞ ስሜን እየጠራ
በየጎዳናው ላይ ብቻውን ሲያወራ
ወፍፎ እየሳቀ አጥቶኝ ሲንከራተት
ለእኔ ፍርቅር ታምኖ ሲሸለመው እብደት
እኔ እስቅ ነበረ በድል ኩራት ጥርሴ
ለእርሱ ጥልቅ ፍቅር ማዘን ትታ ነፍሴ
በሞቀው ከተማ በትርምስ ቀለም
ወድቆ በእኔ ውበት ሲስቅበት ዓለም
አብሬ ስቂያለሁ መውደቁ አስደስቶኝ
ስሜን እየጠራ ሁሌም ሲከተለኝ!!!
ግና ግፌ በዝቶ ሞልቶ ፈሰሳና
እጣውን ቀመስኩኝ በእኔ ደረሰና
እኔም በተራዬ በሌላ ሰው ፍቅር
ወፍፌ እዞራለሁ በወሰድኩት ብድር
እርሱ ዛሬ የለም ለእውነት ኖሮ ሞቷል
ህመም ስቃዩን ግን ለራሴ ውርስ ሆኗል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍13🤗1