ግጥም
4.27K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ሳቅሽ_ውርሴ

የማሽላን ፀባይ ወረስኩኝ ዘንድሮ
እያረሩ መሳቅ በውስጥ እንጉርጉሮ
ከላይ እስቃለሁ ከውስጥ እየነደድኩ
በፈንድሻ ዘዴ እኔስ ስንቱን አለፍኩ!!!
ተቃጥሎ መሳቅን አስተምረሽኛል
ማሽላ ወዳጄ ሳቅሽ ውርሴ ሆኗል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍2👏1
ህልም አየሁ አትበሉ ቅዠት ነው ዘንድሮ
መች ያስተኛልና የእኛ ዘመን ኑሮ።
ለማለም የሚሆን እንቅልፍ ሳይኖራችሁ
ህልም ፍቱ አትበሉ ይልቅ ልምከራችሁ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍9
#የድሃ_እንባ_ይፍሰስ

ጨቋኝ ተሸኝቶ ጨቋኝ ከተተካ
አልበላም አልጠጣም በግፍ የተቦካ
የሚል ሰው ከጠፋ እውነተኛ ዳኛ
እስከመቼ ድረስ አንግሠን ቀማኛ
የሰማዩ ንጉሥ በምድር ካልተፈራ
የድሃ እንባ ይፍሰስ አምላኩን ይጣራ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🔥6🤔1
በትዝታ መርከብ በናፍቆት ጎዳና
ልጓዝ ወደ እናቴ መውደዴ ናትና
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🥰9👍2
#ዓለምህን_ስራ

ገለል በል ለብቻህ እራቅ ከሰው መንጋ
የእራስ ዓለም ፍጠር ሰላምን ፍለጋ
ሰዎች በበዙበት ፍቅር ከነጠፈ
አንዱ ላንዱ ድካም ቆሞ ካልደገፈ
ተገለል ከመንጋው ዓለምህን ስራ
በጫጫታ መኻል ላይሰሙህ አታውራ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍12🔥2👏1
የብዙ ቀን እንባ የብዙ ህዝብ ለቅሶ
የተሰማ ለታ ከአምላክ ዙፋን ደርሶ
ተበዳይ ሲጽናና በዳይ ወየውለት
በሰፈረው ቁና እጥፍ ሲሆንለት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍9🥰31
ግዜ ዳኛ ሆኖ ችሎቱን ቢመራ
ዛሬ መጥሪያ አውጥቶ ትላንትን በጠራ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍54🤔1
#ውድ_ነው_ሴትነት

የሰው ልጅ መዳኛ ገነት መመለሻ
ለአዳም እንባ ፍሰት የፀሎት መካሻ
ክብር ያለው ምስጢር የተሰጠ ገዝፎ
የፍዳን ደብዳቤ ጨለማውን ገፎ
ውድ ነው ሴትነት እህቴ አታርክሽው
ይልቅ ጸጋነቱን በክብር ልበሽው!!!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
11👌4👍1
ይሄ ጥቁር ሰማይ በኮኮብ አጊጧል
አትጨነቅ ልቤ ያለዉ ተቀማጧል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌2
#ዝቅታ_መረጠ

ለከርሱ እያደረ ለሆዱ እያደላ
ለኩርማን እንጀራ አንጀት ለማይሞላ
ስንቱ ብኩርናውን በዳቦ እየሸጠ
እውነትን በሀሰት ቀን በቀን ለወጠ
ከአንጀት ጠብ ላይል ጠግቦ ላያገሳ
የሰው ልጅ ለሆዱ ከክብሩ ተነሳ!!!
በውሸት በሀሰት እየመሰከረ
ህሊናውን ሸጦ ለከርሱ እያደረ
ከተሰጠው ክብር ዝቅታ መረጠ
በማይጠቅም ዳቦ ብኩርናውን ሸጠ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍10
ሰው ከግዜ ከፍቶ ሲጥል እያያችሁ
ግዜው ነው ግዜው ነው ለምን ትላላችሁ
አሁን ከሰው በላይ ክፉ የት አለና
ይከሰሳል ግዜ ዛሬም እንደገና!!!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍10👏3🥰1
#ለጸሎት_አቁመኝ

ያንተ ችሎ ማለፍ የፍቅርህ ዝምታ
ሀጢአቴን ከልሎኝ ወድቂያለሁ ጌታ
ገስጸህ ቀስቅሰኝ ለጸሎት አቁመኝ
ታውቀዋለህ ውስጤን እኔ ደካማ ነኝ
የትግስትህ ፍቅር በዝቶብኝ ውልታ
በአለም ተጠልፌ ተሰናከልኩ ጌታ
ሀጢአት እንዳልሰራ እንደ ጻድቅ ሰው
ትግሰትህ በዝቶብኝ አንተን እረሳው
በል ቀስቅሰኝና ላመስግንህ ቆሜ
ጨለማው ውጦኛል በበደል ታምሜ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍8💯2🥰1
የእውነት መኖር እንጂ የሁላችን ችግር
የእውነት መሞትማ ተገደንም አይቀር
ኑሯችን የውሸት
ሞታችን ግን የእውነት
የእድሜ ዳገት አልቆ የመኖር ህግ ሲመሽ
ሁሉም የማይቀር ነው ሽህ ግዜ እውነት ቢሸሽ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏5👌2👍1
#ወድቆ_ይሰበራል

የሌለን ስንፈልግ ያለንን እያጣን
የሩቁን ፍለጋ የቅርቡን እየጣልን
ብንጠጣ አንረካ ብንበላ አንጠረቃ
የአዞ አመልን የያዝን ፈላጊ ነን በቃ
የተሰጠን ትልቅ የፈለግነው ትንሽ
ማመስገን የራቅን በምሬት ሁሌ አልቃሽ
የቆጡን ለማውረድ እጅ ስንዘረጋ
ወድቆ ይሰበራል ያለው ትልቅ ዋጋ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍4👏31
ቢከፋን ባይከፋን ግዜ መች ይቆማል
እድሜ እየቆጠረ ቀን በቀን ይተካል
ይብላን እንጂ ለእኛ ፍቅርን ለጣልነው
ለአምላክ ይታዘዛል ግዜማ ታማኝ ነው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍11👌2👏1
በሰላም ያሳደርከኝ በሰላም አውለኝ
ክፉ የሚያስቡብኝኝ ደግ ደግ አሳስብልኝ
ከተናግሮ አናጋሪ ከስቆ ቀባሪ
ከጉልበተኛ አባራሪ ከሀሰት መስካሪ
ከወዳጅ ጠላት ከሀጢአት ሹመት
አንተ ጠብቀኝ አንተ ጠብቀን
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🙏16🔥3
ቤተሰብ እንዴት ናችሁ?
ተከታታይ ትረካ ይጀመር?

👍 Yes

👎 No
👍33👎9
#ናፈቅሽኝ

ከፍቶሻል መሰለኝ እኔን ሀዘን ዋጠኝ
አልቅሰሻል መሰል ዓይኔን ቆጠቆጠኝ
ሆድ ባሰሽ መሰለኝ ሆዴ ተላወሰ
ትዝ አልኩሽ መሰለኝ ትዝታሽ ፈሰሰ
ካልጠፋው አካሌ ልቤጋ ከበደኝ
ዓይን፣ጥርስ አካልሽ ጨዋታሽ ናፈቀኝ
አቦ ናፍቀሽኛል ብዙ አታስለፍልፊኝ
መምጣት ባትችይ እንኳን ባሳብሽ እቀፊኝ
          ያንችን ልክ የያዘው
የልቤ ላይ ጥጉ ብርድ አንዘፍዝፎታል
አለሁልህ በይው ያ ድምፅሽ ናፍቆታል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍9🥰3😢3
ግጥም
ቤተሰብ እንዴት ናችሁ? ተከታታይ ትረካ ይጀመር? 👍 Yes 👎 No
በ Like ብዛት ይለቀቅ ወይስ ቀን በቀን?

❤️ Like

🔥 Day to Day
🔥82👍1🥰1
ናፍቆት አቃጠለኝ
      ልክ እንደ ውሃ ጥም
                 የሚጠጣ ቢሆን
                        ባደረኩት ግጥም💋
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👍1
የድሀ ፍቅር

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ

ክፍል 1

ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግኩበት ስም የለውም ማለቴ አዲስ አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ ነው አባቴን
አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም አንድ ወንድም አለኝ ናቲ ይባላል ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት አልፈልግም ትላለች እናቴ ያገኘችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ መልስ ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር ትፈልጋለች በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች የ10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው ከትምህርት ቤት እንደተመለስኩ የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ ግዴታዬ ስለሆነ በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት
አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን ሜላት የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር ክንፍ ብለናል የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት በደረጃና በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን አላማና ፍላጎት
ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን ሁለት ወር ክረምት ሜላት ከቤት ብዙም መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም ብቻ ተመስገን ነው ።
ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዩ ልብስም እቃም ታመጣለች የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት ግን አልፈለኩም እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር ዝም የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት መጣ.......
ይቀጥላል.....

@gitm_post

Like እና Share
13🔥2👍1