ግጥም
4.27K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ነገሽን_ስሪበት

ነገ ከሚረግፈው ከዛሬው ውበትሽ
ይዋል ተቀንሶ ለመቃብር ስምሽ
ተግባርሽ በበጎ ዘወትር እንዲጠራ
ውበትሽ ዛሬ ላይ የነገን ስም ይስራ
ተዋቢ ግድየለም መልክሽ ይመርበት
ከዛሬው ቀንሰሽ ነገሽን ስሪበት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👍2👏2🥰1
አጥርሽ ገረገራ ውሻሽ ተናካሽ
ተቋጥሬ ልግባ በመቀነትሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
5👍1
#ችክ_አትበልበት

ስትወደው ከጠላህ
ስትነግረዉ ካልሰማህ
ስትሰጠዉ ፊትህን
ከሰጠህ ጀርባዉን
ፍፁም ካልተረዳዉ አስተሳሰብህን
ችክ አትበልበት አትለማመጠው
ወዳጅ አይሆንህም በግድ ያስጠጋኸው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👏4👍3
ዛሬ ላይ ፈገግታ ወርቅ ሆኖ ቢወደድ
ዞረን እንስቃለን በመጣነው መንገድ ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6🥰1
#ንከስ_ንከስ_አለኝ

ለከንፈርሽ ዘወትር የሚወጣው ወጪ
ከሰርጉ በለጠ ምን ነበር ባትመጪ?
አልልም ደፍሬ እንኳንም የመጣሽ
ለእኔም ይደርሰኛል አጥብቄ ስስምሽ
ያወጣሁት ወጪ ትዝ ትዝ እያለኝ
ከመሳም ባሻገር ንከስ ንከስ አለኝ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍8
ስለ አብሮነታችሁ ምስጋናዬ ከልብ ነው
🤳 👌
SHARE COMMENT REACT
በማድረግ አበረታቱኝ ቶሎ ቶሎ ፖስት
አደርጋለሁ
#I_LOVE_YOU_ALL🫶
7
Channel photo updated
አሁን በዚህ ዘመን ቢመጣ አምላካችን
መልስ ይሆነን ይሆን የትኛው ስራችን?
የግፋችን ባህር ሞልቶ በደላችን
እንዲሁ እንደከፋን አትምጣ ጌታችን
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏7👎4
#ሰው_ፈልጉ

ለዕምነቱ ያደረ ቃሉን የማይበላ
ፊትን ተመልክቶ ሰው የማያዳላ
እውነት ተናጋሪ የሚኖር ለነፍሱ
ለሰው የሚራራ አብልጦ ከራሱ
ፊት ለፊት አድንቆ ዞሮ የማያማ
በተንኮል በሀሜት ልብ የማያደማ
ጥሩ ወዳጅ መስሎ እየሸነገለ
ወንድሙን ለነዋይ ዋሽቶ ያልገደለ
አደራ ጠባቂ ምሎ የማይከዳ
እስኪ ሰው ፈልጉ ከሁሉ የፀዳ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
8🔥3👌2
ስድብ እችላለሁ ለዱላም ግዴለኝ
እናቴን ከነካህ ሳልገድልህ ግደለኝ
           እናቴ ❤️
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
14
#ቀኑ_ይለወጣል

የትላንቱ ችግር ነገ ላይ ተረት ነው
ያሳለፍነው ስቃይ ወደ ፊት ክብር ነው
በዛሬ ውስጥ ሆኖ ፈተናው ቢከብድም
ይለወጣል ቀኑ ዛሬ ነገ አይደለም
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍1
Go to 800 ........🏃🏃‍♀🏃‍♂
👍5
ደመናው ሲዳምን ይወረዛል ገደል
ወተት ይሸፋታል እንኳን ሰው ሲበደል ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌2
❤️ #አፈቅርሻለሁ ❤️

አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈልጌው አይደለም አላበዛም ሰበብ
ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ርሃብ ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለማንም አልፈቅድም እንዲለዪሽ ከእኔ
ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እሰከማይሽ በዓይኔ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍5🥰41
የሆዳም ሰው ግብሩ
ሲተፋ ማደሩ!!!
አልጠግብ ባይ ከርሱ
ሁሉን ማግበስበሱ!!!
የሁሉን ሰው ድርሻ አለመጠን ጎርሶ
ህይወቱን ይገፋል ሆዱን ተንተርሶ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
8
ያ ዶሮዬ ጮኸ መንጋቱን ነገረኝ
በዛሬ ቀን ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
😁63🥰2😢1
#እግረ_መንገድ

አላዋቂ ተጓዥ
እግር አለኝ ብሎ
መንገዱን ሳያበጅ ለመሄድ ይነሳል
ወትሮስ መንገድ እንጅ እግር መች ያደርሳል
እግርማ ታዛዥ ነው ባዘዙት ይሄዳል
ምን እግር ቢኖረው
መንገድ የሌለው ሰው ወዴት ይራመዳል
በማያደርስ እግር ሲሄዱ ከማርጀት
አንዴ ቆም ብሎ መንገድ ነው ማበጀት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👏5
እግሬም አትቸኩል ልቤም ተረጋጋ
እንደመሸ አይቀርም ጠብቅ እስኪነጋ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7🥰3
#አድዋ

የጥቁር ህዝቦች ኩራት
የነፃነት ተምሳሌት
የማንነት ኩራታችን
የጀግንነት እርስታችን
አድዋ ነው መለያችን
    @gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
10👍2
ምሽቱ ፀጥ ሲል አረፍ ሲል ጎኔ
ድምፅሽ በሹክሹክታ ይመጣል ወደኔ
ለብቻዬ ስሆን ሲከፋኝ ታውቂያለሽ
ፍቅሬ በዚህ ሰዓት ታስፈልጊኛለሽ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9
#ሳቅሽ_ውርሴ

የማሽላን ፀባይ ወረስኩኝ ዘንድሮ
እያረሩ መሳቅ በውስጥ እንጉርጉሮ
ከላይ እስቃለሁ ከውስጥ እየነደድኩ
በፈንድሻ ዘዴ እኔስ ስንቱን አለፍኩ!!!
ተቃጥሎ መሳቅን አስተምረሽኛል
ማሽላ ወዳጄ ሳቅሽ ውርሴ ሆኗል
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍2👏1