ግጥም
4.27K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ህሊና ታውሮ ዐይን እያፈጠጠ
ሀሰት ቀና ስትል እውነት ግን ጎበጠ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7
#እየመጣዉ_ነበር

በቀጠሮ ሰአት ከነገርኩሽ ቦታ🕙
በርሬ እየመጣዉ እንዳትቆሚ ላፍታ🏃‍♂️
አበባ ባንድ እጄ ቀለበት በኪሴ🌹💍
ሽቅርቅር ብዬ ከእግር እስከ ራሴ🕺
እየመጣዉ ነበር እያልኩ ፈራ ተባ
ቀለበቱ ይቅደም ወይንስ የእጄ አበባ
እያልኩኝ ለራሴ ባሳብ ስብሰለሰል
ካንዱ ወዳንዱ ሳሎጣ ሳማሰል
ድንገት አረረና የሀሳቡ ፍሬ
ከቀልቤ እርቄበት እየመራኝ እግሬ
ካሳቤ ስወጣ ከተዘፈኩበት
መሀል አስፓልት ነዉ ለካ የቆምኩበት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
😱82👍2
ተወት በማድረግ ካልታለፈ ነገር
በሆነው ልክማ ማን ችሎ ሊናገር።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
4👏2
#የነጠፈ_ብዕር

ብዕር ወዙን አጥቶ ቀለሙ ነጠፈ
ጥበብ ማማጥ ትቶ በዘር ተለከፈ
ቅኔን አፍልቅ ቢሉት ደም እየሰበከ
ከመንደር ሳይወጣ ግፍ እየታከከ
ወረቀቱን ሁሉ በክሎ ጨረሰው
ባለቅኔ መጥቶ እንዳይጠቀመው
የነጠፈ ብዕር ድርቀት ያደረቀው
ቢጽፍ አያምርበት ጽፎ መደለዝ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍62
እኔስ ናፍቀሽኛል አልናፈቅኩሽም ወይ
መራራቁ ቀርቶ አንገናኝም ወይ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
11👍5
#ሰው_ከመሆን_አንሶ !!!

ጠዋት የገቡት ቃል ማታ እየፈረሰ
በወዳጁ ክህደት ስንቱ እያለቀሰ
መተማመን ጠፍቶ
መገፋፋት በዝቶ
ገንዘብ ጣኦት ሆኖ ልብን እየገዛ
ሰውነት ተናቀ እረክሶ እንደዋዛ ።
የእግዚአብሔርን ዋጋ ለቄሳር ለግሶ
የዘር ዛር ያነግሣል ሰው ከመሆን አንሶ ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌53
አመለጠኝ ያልኩት የማይበጀኝ ነበር
ለካስ ለዚህ ነበር ተው ያልከኝ እግዚአብሔር
አብዝቼ ፈልጌ ያጣሁት የራቀኝ
መጥፊያዬ ቢሆን ነው ጌታ የነፈገኝ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
11👍3💯2
#ነገሽን_ስሪበት

ነገ ከሚረግፈው ከዛሬው ውበትሽ
ይዋል ተቀንሶ ለመቃብር ስምሽ
ተግባርሽ በበጎ ዘወትር እንዲጠራ
ውበትሽ ዛሬ ላይ የነገን ስም ይስራ
ተዋቢ ግድየለም መልክሽ ይመርበት
ከዛሬው ቀንሰሽ ነገሽን ስሪበት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👍2👏2🥰1
አጥርሽ ገረገራ ውሻሽ ተናካሽ
ተቋጥሬ ልግባ በመቀነትሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
5👍1
#ችክ_አትበልበት

ስትወደው ከጠላህ
ስትነግረዉ ካልሰማህ
ስትሰጠዉ ፊትህን
ከሰጠህ ጀርባዉን
ፍፁም ካልተረዳዉ አስተሳሰብህን
ችክ አትበልበት አትለማመጠው
ወዳጅ አይሆንህም በግድ ያስጠጋኸው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👏4👍3
ዛሬ ላይ ፈገግታ ወርቅ ሆኖ ቢወደድ
ዞረን እንስቃለን በመጣነው መንገድ ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6🥰1
#ንከስ_ንከስ_አለኝ

ለከንፈርሽ ዘወትር የሚወጣው ወጪ
ከሰርጉ በለጠ ምን ነበር ባትመጪ?
አልልም ደፍሬ እንኳንም የመጣሽ
ለእኔም ይደርሰኛል አጥብቄ ስስምሽ
ያወጣሁት ወጪ ትዝ ትዝ እያለኝ
ከመሳም ባሻገር ንከስ ንከስ አለኝ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍8
ስለ አብሮነታችሁ ምስጋናዬ ከልብ ነው
🤳 👌
SHARE COMMENT REACT
በማድረግ አበረታቱኝ ቶሎ ቶሎ ፖስት
አደርጋለሁ
#I_LOVE_YOU_ALL🫶
7
Channel photo updated
አሁን በዚህ ዘመን ቢመጣ አምላካችን
መልስ ይሆነን ይሆን የትኛው ስራችን?
የግፋችን ባህር ሞልቶ በደላችን
እንዲሁ እንደከፋን አትምጣ ጌታችን
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👏7👎4
#ሰው_ፈልጉ

ለዕምነቱ ያደረ ቃሉን የማይበላ
ፊትን ተመልክቶ ሰው የማያዳላ
እውነት ተናጋሪ የሚኖር ለነፍሱ
ለሰው የሚራራ አብልጦ ከራሱ
ፊት ለፊት አድንቆ ዞሮ የማያማ
በተንኮል በሀሜት ልብ የማያደማ
ጥሩ ወዳጅ መስሎ እየሸነገለ
ወንድሙን ለነዋይ ዋሽቶ ያልገደለ
አደራ ጠባቂ ምሎ የማይከዳ
እስኪ ሰው ፈልጉ ከሁሉ የፀዳ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
8🔥3👌2
ስድብ እችላለሁ ለዱላም ግዴለኝ
እናቴን ከነካህ ሳልገድልህ ግደለኝ
           እናቴ ❤️
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
14
#ቀኑ_ይለወጣል

የትላንቱ ችግር ነገ ላይ ተረት ነው
ያሳለፍነው ስቃይ ወደ ፊት ክብር ነው
በዛሬ ውስጥ ሆኖ ፈተናው ቢከብድም
ይለወጣል ቀኑ ዛሬ ነገ አይደለም
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍1
Go to 800 ........🏃🏃‍♀🏃‍♂
👍5
ደመናው ሲዳምን ይወረዛል ገደል
ወተት ይሸፋታል እንኳን ሰው ሲበደል ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👌2
❤️ #አፈቅርሻለሁ ❤️

አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈልጌው አይደለም አላበዛም ሰበብ
ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ርሃብ ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለማንም አልፈቅድም እንዲለዪሽ ከእኔ
ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እሰከማይሽ በዓይኔ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍5🥰41