ግጥም
4.27K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
ቤተሰብ ዛሬ የፍቅር ግጥም ይለቀቅ?
👉20 ❤️ reaction be fast
27👍10
#ምሪኝ_ወደ_ጣትሽ

የቱ ጋር ነው ጣትሽ ምሬኝ ለቀለበት
በዋዛ አይገኝም ለፍተሽ ውሰጂ ንብረት
የቀረኝን እድሜ ባንቺ ተደስቼ
ውርሱን ሳልናዘዝ በትንፋሽሽ ሞቼ
ልፋትሽ በከንቱ እንዳይቀር በሜዳ
ምሪኝ ወደ ጣትሽ በቃል ኪዳን እዳ
የቱ ጋር ነው ውዴ የቀለበት ጣትሽ
ላጥልቅልሽና ያለኝን ላውርስሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍32
#ጠባችን_ቀደመ

ፍቅራችን የውሸት ወረት ያሰከረው
በትናንሽ ሰበብ መውደቅ የሚያበዛው
ጠዋት ተማምለን ከሰአት ስናፈርስ
ምሽት አስጠንቁለን ማለዳ ማስቀደስ
ዛሬ ይታይልን እፍ እፍ ማለት አብሮ
ነገ ዓይን ለአፈር አፍለኛው ተጋግሮ
ፍቅራችን ተጥዶ በስሎ ሳይበላ
ጠባችን ቀደመ ተነስቶ ከሗላ
በወረት እስክስታ ለቀናት ደልቆ
ሀሜት ከተፍ ይላል ፍቅር ወዲያው አልቆ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6😭2👍1
#ተራ_በተራ_ነው

ሙታን ለመቀስቀስ ተስካር አትደግሱ
ይልቅስ ተግታችሁ ለቆመው አልቅሱ
ዓለምን ሰልችተው ለሄዱት በግዜ
ማዘን አቁማችሁ ለቅሶና ትካዜ
ለቆሙት አልቅሱ ደረትም ደልቁ
መከራው መኖር ነው እየተጨነቁ
ሞትማ ጥሪ ነው በተራ የሚደርስ
መኖር ነው አሁን ላይ ከልብ የሚያስለቅስ
ይተኙ ተዋቸው ሙታን እፎይ ብለው
የዚህች ዓለም ጉዞ ተራ በተራ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
9❤‍🔥6
#ከንፈር_መች_ሆነና

ልሳምህ አትበይኝ ልብሽ ክህደት አዝሎ
በቂም አቆማዳ በደል አንጠልጥሎ!!!
ወዳጅ መስሎ ቀርቦ ስሞ ያስረከበው
ከተመረጡት ውስጥ ይሁዳ እኮ ሰው ነው
ለወዳጅ ምሽጉ ልብ እንጂ መኖሪያው
ከንፈር መች ሆነና ለሰው መታመኛው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍92
በዛሬ መስታወት ትላንትን አቅርቤ
አየሁት በፎቶ ትዝታን ደርቤ!!!
የአሁኑ ላይ ቆሜ በሗሊት ጎዳና
ያለፈው ናፈቀኝ ይሻል ነበር እና
ቢሆንም ተመስገን የዛሬው ባይደላ
እድሜ መስታወት ነው ያሳያል የሗላ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍4
ግጥም pinned Deleted message
#እኛ!!!

በጥባጩ በዛና ጠላው ደፈረሰ
ጠርቶ ሳይጠጣ በከንቱ ፈሰሰ
በመናናቅ ዜማ ሙዚቃው ተሰርቶ
አድማጭ እያነሰ ተናጋሪ ሞልቶ
በባቢሎን ሚዛን ሀገር ተለክቶ
ጠጅ ሲሉን ውሃ ውሃ ሲሉን ጠላ
ጤፍ ሲሉን ዘንጋዳ ጮማን በማሽላ
ምድር ሲሉን ሰማይ ሰማይ ሲሉን መሬት
በተቃርኖ መስሚያ በግራው መግባባት
ጥሩ ሲሉን ድፍርስ አልጋ ሲሉን መሬት
በምላስ እስክስታ ተጓዥ ነን በስሜት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍92
ሲከፋው የሰው ልጅ ለምን ሞት ይመኛል?
ድንጋይ ተንከባሎ ደልዳላ ያገኛል
ዛሬ ይሁን ያልኩት ከመሆን ቢጠፋ
ቻል አድርገው ልቤ ተው አትቁረጥ ተስፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍6
#ጤናችንን_ነሳን

የተጣደው ሁሉ እያደረ ጥሬ
በስሎ ማይበላ ለምን ነው? ሀገሬ
ይበስላል ስንለው ከመጣዱ ጨሰ
ጣፍጦ ላይበላ ማገዶን ጨረሰ።
ጦምን ላለማደር ጥሬን እየበላን
ምግብነቱ ቀርቶ ጤናችንን ነሳን
ብስል ሲባል ጥሬ ጥሬ ሲባል አሮ
እንዴት ብሎ ይውረድ ጣፍጦ ከጉሮሮ።
እህሉ ሳይጠፋ ሞልቶ ከጎተራ
ባለሙያ ጠፍቶ አረረ በተራ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
4👍3
በስጋችን ድሎት ነፍስ ተበድላ
ከቆሻሻ ስፍራ በሃጢአት ተጥላ
መነሳት ተስኗት መቆም ከጌታ ፊት
ትርመጠመጣለች ተይዛ በዝሙት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6👍1🔥1
#የማይጠግብ_ዝቆ

ሆድ ከአገር ይሰፋል ይሉት ብሂል ዛሬ
ተረት ብቻ አይደለም እውነት ነው ሀገሬ
ከአንቺ የሚሰፋ ወርዱ ተንቦርቅቆ
ቢበላ ቢበላ የማይጠግብ ዝቆ
ብዙ ሆዳም አለሽ ከሀገር የሰፋ
በትውልድ እድሜ ላይ ቆሞ የሚያንቀላፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
7👍1
ተናገር ክራሬ የውስጤን በዜማ
ቃላት አይወጣኝም ከንግዲህ እኔማ
ሃዘን ደስታዬን ውስጤን በመረዳት
በቅኝት አስረዳ ወክለህ ንገራት!!!
በአንቺ ሆዬ ባቲ አንባሰል ትዝታ
ይገባታል እርሷ ክራሩ ሲመታ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
6
React እያረጋቹ እንጂ🙄

ሚያልፍልኝ ነዋ ሚመስላቹ 🤔🤔🤔
👍9🔥2
#በማይከፈት_ቤት!!!

ተሻለህ አትበሉኝ ዛሬም ብሶብኛል
ወይ አልሞት አልድንም ስቃይ ያኖረኛል
በሰቀቀን እንባ በሐዘን ዜማ ስልት
ግራ በተጋባ ትርጉም አልባ ቅኝት
ክራሬን ስገርፈው ብሶት እያዜመ
የአምናው በሽታየ ዘንድሮም ከረመ
ግርፉ ሲሰለቸኝ ብደረድረውም ቅኝቱን ቀይሬ
ከተለከፈበት የሗሊት አዙሪት ቆሞ ቀርቷል እግሬ
እንኳንስ መራመድ መንፏቀቅ ብርቁ ነው
በትዝታ አለንጋ በመለየት ጅራፍ የተገረፈ ሰው
ዳዴ ማለት አይችል ግፋ ቢል መንፏቀቅ
በታመነ ልቡ የናፍቆት ከበሮ ቀን በቀን መደለቅ
ክራሬን ስበሩት ድንገት ከተሻለኝ
ዋሽንቱን ሰንጥቁት ሳጣው  ከቀለለኝ
በገና ማሲንቆ አደራ እንዳተሰብሩ
ካምላክ እንድታረቅ ይልቅስ ደርድሩ
አምና ዝናብ ጥሎ እህል በቅሎ ነበር
የኔ ልብ ግን ዘርቶ ድርቅ ያጠቃው ፍቅር
ከውስጥ በተዘጋ በማይከፈት ቤት
ለብቻው ነው ዛሬም በስቃይ አዙሪት
ይኸ ሰው ምን ነካው ሲሉ እየሰማሁኝ
ከንፈር እያስመጠጥኩ በህይወት አለሁኝ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍82🔥2
ወዳጅ መስሎ ቀርቦ አቅፎ ስለሳመህ
ይሁዳን አትርሳው ስራው ትዝ ይበልህ
ስንቱ የዋህ ምስኬን በወዳጅ ጠላቱ
ተስሞ ተሽጧል ፈርሶ አይተናል ቤቱ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
14
#እንባችን_ባልበቃ

የከፋንን ትተን ለመኖር ስንስቅ
መስለን ደስተኛ በተስፋ ስንርቅ
የደላን መስሏቸው ይቀኑ ጀመረ
ችለነው ነው እንጂ ስንት ጉድ ነበረ
እናልቅስ ካልንማ በደረሰብን ልክ
በመከፋት ሚዛን ቢዘረዘር ታሪክ
እንባችን ባልበቃ ብሶት ማስተንፈሻ
እየሸሸግነው ነው በሳቃችን እርሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍72
እያረረ ውስጤ ጥርሴ ሲስቅ አይተሽ
ደልቶታል አትበይ እቴዋ ሞኝ ነሽ።
እየተመራሁ ነው በፈንድሻ ዘዴ
ጥርሴ የሚስቀው እያረረ ሆዴ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍4
#ዛሬም_ካንቺ_ጋር_ነኝ

በትዝታ ፈረስ የኋሊት ተጉዤ
ፍቅርሽን ላስታዉስ ከስሩ መዝዤ
ካፍንጫዬ ሲደርስ የ ፍቅርሽ ሽዉታ
ጆሮዬ ሲገባ ድምጽሽ በሹክሹክታ
ያ ዉብ ኣካላትሽ ከፊቴ ተስሎ
ምላሴ ሲፈታ አነ ጽጌ ብሎ
ኣሁን ግን
ሲወራ ሰማሁኝ የለቺም ተብሎ
አቺን የቀማኝን ባገኘው ምን አለ
እጠይቀው ነበር ምን አንዳስጨከነው
አይቻት ሳልጠግብ ቀስሜያት ሳልረካ የልቤን ላይ ፅጌ ከኔ የነጠለው
እሱ ባይነግረኝም ባይመልስልኝም
ዛሬም ካንቺ ጋር ነኝ ምን ጊዜም ኣልቀርም
ጨረቃን ከሰማይ እመለከትና
በ ጊዮርጊስ ፈረስ ሽቅብ ጋልብና
የዝናቡ ሃይል ዉርጩ ቢያይልብኝ
የሳጥናኤል ጭፍሮች መንገድ ላይ ቢይዙኝ
ከቶ እንዳታስቢ እንዳትጨነቂ
እመጣልሻለው የኔ ተናፋቂ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
👍9
በሰው ሀሳብ ቢሆን በምድራዊ ስሜት
መቼ እንኖር ነበር ዛሬንስ ለማየት
እግዚአብሔር ፈቅዶ እንጂ ሰጥቶን ትልቅ ዋጋ
በምቾት ያለነው እንደ ባለጸጋ!!!
ሳይኖረን ያኖረን እኛን ክርስቶስ ነው
እንደኛማ ቢሆን ህይወት አዙሪት ነው
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ      ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
8🙏2👎1