#ዛሬም_በመጠበቅ
ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍2❤1
#ልጅነት_ቅርስ_ነው
የትላንቱ ውበት ያ መልካም ልጅነት
ተንኮል ያልበረዘው የልብ ቅንነት
ናፈቀኝ ዛሬ ላይ ክፋት ሲበረክት
ምነው ዞሮ ባየው ያ ደግ ልጅነት
ተመልሶ አይመጣም ቢመጣማ ዞሮ
መፈንደቅ መደሰት ከእኩያ ጋር አብሮ
ክፋት ምቀኝነት ተንኮል የማያውቀው
ከሁሉም የነጻ ልጅነት ቅርስ ነው!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
የትላንቱ ውበት ያ መልካም ልጅነት
ተንኮል ያልበረዘው የልብ ቅንነት
ናፈቀኝ ዛሬ ላይ ክፋት ሲበረክት
ምነው ዞሮ ባየው ያ ደግ ልጅነት
ተመልሶ አይመጣም ቢመጣማ ዞሮ
መፈንደቅ መደሰት ከእኩያ ጋር አብሮ
ክፋት ምቀኝነት ተንኮል የማያውቀው
ከሁሉም የነጻ ልጅነት ቅርስ ነው!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
👍5❤3
🥰9👎1
ፀሐይ ብትጠልቅም ጨረቃዋን ጠብቅ
ጨረቃ ብጠፋም ከዋክብትን አድንቅ
ገንዘብ ቢቸግርህ መኖርህን ውደድ
በየምክንያቱ ማመስገንን ልመድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ጨረቃ ብጠፋም ከዋክብትን አድንቅ
ገንዘብ ቢቸግርህ መኖርህን ውደድ
በየምክንያቱ ማመስገንን ልመድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍9👏2
#አልገባሽምና
በእኔ ሀዘን ሳቂ
ሳለቅስ ድመቂ
ምን በወጣሽ አንቺ ከቶ አትጨነቂ
ተራው እስኪደርስሽ ደምቀሽ ተፍለቅለቂ
አንቺም በሰው ፍቅር ተማርከሽ ስቶድቂ
ያኔ ነው ፈተናሽ ያኔ ነው ከልቤ ፈጥነሽ የምትርቂ።
በእኔ የሳቅሽው ሳቅ ተሰፍሮ በጥርስሽ
ይደርስሻል ዞሮ አፍቅረሽ ሲጠሉሽ።
ለዛሬው ግን ሳቂ አይክፋሽ የኔ ማር
አልገባሽምና ሲፈቀሩ መክበር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በእኔ ሀዘን ሳቂ
ሳለቅስ ድመቂ
ምን በወጣሽ አንቺ ከቶ አትጨነቂ
ተራው እስኪደርስሽ ደምቀሽ ተፍለቅለቂ
አንቺም በሰው ፍቅር ተማርከሽ ስቶድቂ
ያኔ ነው ፈተናሽ ያኔ ነው ከልቤ ፈጥነሽ የምትርቂ።
በእኔ የሳቅሽው ሳቅ ተሰፍሮ በጥርስሽ
ይደርስሻል ዞሮ አፍቅረሽ ሲጠሉሽ።
ለዛሬው ግን ሳቂ አይክፋሽ የኔ ማር
አልገባሽምና ሲፈቀሩ መክበር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤8
ከጎረቤትህ ቤት ሞት መጥቶ ሲጣራ
በቀጣይ አንተ ነህ በመኖር አትኩራ
አለሁ አለሁ አትበል በስጋ ምቾትህ
ነገ ባለተራ አንተም ተከታይ ነህ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በቀጣይ አንተ ነህ በመኖር አትኩራ
አለሁ አለሁ አትበል በስጋ ምቾትህ
ነገ ባለተራ አንተም ተከታይ ነህ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍11
#ውስጤ_የሚፈራው
በምናብ ተጉዤ ከጥበብ ውቂያኖስ
የጨለፍኩት ታሪክ ሲነቀፍ ሲወደስ
እኔን ያሳዘነኝ የምናቤ ፍጡር በሞት የምቀጣው
"ያን" ገፀባህርይ ምስኪኑን ሳስብ ነው።
ውስጤ የሚፈራው የሚንቀጠቀጠው
እጄ ብዕር መያዝ ግራ የሚጋባው
ስቃይ መከራውን ሞትን ስፈርድ ነው
በራብ በውሃ ጥም በብርድ ስጠብሰው
ለሌሎች ደስታ እርሱን ሳንገላታው
ወይም ሴት ከሆነች የፈጠርኳት ፍጡር
በብዙ መከራ ስትዳክር ስታዛክር
ያኔ ልቤ ያዝናል ጥበብን ይረግማል
እጅግ ተጸጽቶ ብዕሩን ይጥላል።
ግን ደግሞ ግድ ነው በፍጡር መጨከን
አምላክም ይገድላል በምድር ቀሪ የለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
በምናብ ተጉዤ ከጥበብ ውቂያኖስ
የጨለፍኩት ታሪክ ሲነቀፍ ሲወደስ
እኔን ያሳዘነኝ የምናቤ ፍጡር በሞት የምቀጣው
"ያን" ገፀባህርይ ምስኪኑን ሳስብ ነው።
ውስጤ የሚፈራው የሚንቀጠቀጠው
እጄ ብዕር መያዝ ግራ የሚጋባው
ስቃይ መከራውን ሞትን ስፈርድ ነው
በራብ በውሃ ጥም በብርድ ስጠብሰው
ለሌሎች ደስታ እርሱን ሳንገላታው
ወይም ሴት ከሆነች የፈጠርኳት ፍጡር
በብዙ መከራ ስትዳክር ስታዛክር
ያኔ ልቤ ያዝናል ጥበብን ይረግማል
እጅግ ተጸጽቶ ብዕሩን ይጥላል።
ግን ደግሞ ግድ ነው በፍጡር መጨከን
አምላክም ይገድላል በምድር ቀሪ የለም።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
❤6
ሀብታም ከሹመኛ ውስኪ እያወረዱ
የድሀውን ሽሮ በግፍ ተራመዱ።
አብዛኛው ተርቦ ጥቂቱ እያገሳ
ከላይ ያለው ጠግቦ መሶቡ ተነሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የድሀውን ሽሮ በግፍ ተራመዱ።
አብዛኛው ተርቦ ጥቂቱ እያገሳ
ከላይ ያለው ጠግቦ መሶቡ ተነሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤3
#ወድቀው_ሳይነሱ
በጥጥሽ ባዘቶ በእንዝርትሽ ቀሰም
በፈትልሽ ሸማ ጨርቅ በጥለትሽ ቀለም
በሙያሽ ተማርከው
በውበትሽ ዝለው
የተንበረከኩት ወድቀው ሳይነሱ
ሌሎች ተራ ያዙ ከደጅሽ ደረሱ
ውበትሽ መብረቁ እያጉረመረመ
ስንቱ ከታዛሽ ስር ተረስቶ ከረመ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
በጥጥሽ ባዘቶ በእንዝርትሽ ቀሰም
በፈትልሽ ሸማ ጨርቅ በጥለትሽ ቀለም
በሙያሽ ተማርከው
በውበትሽ ዝለው
የተንበረከኩት ወድቀው ሳይነሱ
ሌሎች ተራ ያዙ ከደጅሽ ደረሱ
ውበትሽ መብረቁ እያጉረመረመ
ስንቱ ከታዛሽ ስር ተረስቶ ከረመ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
❤4
😁4❤2
#ዘላለም_የሚኖር
ከእናት ገጽታ ላይ ከዓይናቸው መስተዋት
ደምቆ የተጻፈ ይነበባል እውነት
ማስተዋል ለቻለ ማየት ለታደለ
በህይወት ጀርባ ላይ ጥበብን ላዘለ
የእናት ገጽታ ነው የእውነት መዳረሻ
ዘላለም የሚኖር የፍቅር መናገሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
ከእናት ገጽታ ላይ ከዓይናቸው መስተዋት
ደምቆ የተጻፈ ይነበባል እውነት
ማስተዋል ለቻለ ማየት ለታደለ
በህይወት ጀርባ ላይ ጥበብን ላዘለ
የእናት ገጽታ ነው የእውነት መዳረሻ
ዘላለም የሚኖር የፍቅር መናገሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
❤6👍2
#የአገሬ_ሰው_ደጉ
የአገሬ ሰው ደጉ ለሞተ ያለቅሳል
በተቃራኒ ግን የቆመን ይገድላል
በህመም ለሞተ በተፈጥሮ ህጉ
እግዜርን ይወቅሳል የአገሬ ሰው ደጉ
በተቃራኒው ግን ገድሎ ይፎክራል
እግዜር ለገደለው አምርሮ ያነባል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
የአገሬ ሰው ደጉ ለሞተ ያለቅሳል
በተቃራኒ ግን የቆመን ይገድላል
በህመም ለሞተ በተፈጥሮ ህጉ
እግዜርን ይወቅሳል የአገሬ ሰው ደጉ
በተቃራኒው ግን ገድሎ ይፎክራል
እግዜር ለገደለው አምርሮ ያነባል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
👍7
#እናትነት_ብቻ!!!
ዘመን ሲለዋወጥ የነበረው ሲቀር
እናትነት ብቻ ህያው ነው እያደር
ሁሉን ወረት በልቶት በሂደት ሲለወጥ
የዓለም አኖኖር ስልት ቀን በቀን ሲናወጥ
ባለበት የጸናው ከወረት የራቀ
ዘላለም የሚኖር ሁሌ እየደመቀ
እናትነት ብቻ ዘመን ያልበረዘው
በነበር የጸና ትውልድ ያልቀየረው
ከጥንት እስከዛሬ አለ ዋጋ ከፍሎ
የእናትነት ሚዛን ዘወትር ፍቅር አዝሎ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ዘመን ሲለዋወጥ የነበረው ሲቀር
እናትነት ብቻ ህያው ነው እያደር
ሁሉን ወረት በልቶት በሂደት ሲለወጥ
የዓለም አኖኖር ስልት ቀን በቀን ሲናወጥ
ባለበት የጸናው ከወረት የራቀ
ዘላለም የሚኖር ሁሌ እየደመቀ
እናትነት ብቻ ዘመን ያልበረዘው
በነበር የጸና ትውልድ ያልቀየረው
ከጥንት እስከዛሬ አለ ዋጋ ከፍሎ
የእናትነት ሚዛን ዘወትር ፍቅር አዝሎ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
👍8❤5
እውነት አፍ ቢኖራት ነገር ተለውጦ
ስንቱ እርቃን በቀረ ማንነት ተጋልጦ
እውነተኛ መሳይ አስማሳይ በሙሉ
አንደበት ቢኖራት እውነት ነበር ቃሉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ስንቱ እርቃን በቀረ ማንነት ተጋልጦ
እውነተኛ መሳይ አስማሳይ በሙሉ
አንደበት ቢኖራት እውነት ነበር ቃሉ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
🥰2👍1
#የማንችለው_በዛ
በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
ጥርስ ከላይ ከላይ በማስመሰል ስቆ
ልብ እህ እህ ይላል በስቃይ ዋይታ
ለማለፍ ሲያጣጥር ሁሉን በዝምታ።
የደረሰበትን በጥርስ ሳቅ ከልሎ
ውስጥ እረመጥ ፈጀው የማይቻል ችሎ።
ላያስችል አይሰጥም ይባል ነበር ድሮ
የማንችለው በዛ እንጃልኝ ዘንድሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
ጥርስ ከላይ ከላይ በማስመሰል ስቆ
ልብ እህ እህ ይላል በስቃይ ዋይታ
ለማለፍ ሲያጣጥር ሁሉን በዝምታ።
የደረሰበትን በጥርስ ሳቅ ከልሎ
ውስጥ እረመጥ ፈጀው የማይቻል ችሎ።
ላያስችል አይሰጥም ይባል ነበር ድሮ
የማንችለው በዛ እንጃልኝ ዘንድሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
❤7
አንተ ስትሰጠን የንስሐን ዘመን
አይተህ እንዳላየ ቀን በቀን ስትምረን
እኛ ግን አዋልነው ለክፋት ለበቀል
እድሜ ብቻ ቆጥረን ተመርቀን ተንኮል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አይተህ እንዳላየ ቀን በቀን ስትምረን
እኛ ግን አዋልነው ለክፋት ለበቀል
እድሜ ብቻ ቆጥረን ተመርቀን ተንኮል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍10
#ምሪኝ_ወደ_ጣትሽ
የቱ ጋር ነው ጣትሽ ምሬኝ ለቀለበት
በዋዛ አይገኝም ለፍተሽ ውሰጂ ንብረት
የቀረኝን እድሜ ባንቺ ተደስቼ
ውርሱን ሳልናዘዝ በትንፋሽሽ ሞቼ
ልፋትሽ በከንቱ እንዳይቀር በሜዳ
ምሪኝ ወደ ጣትሽ በቃል ኪዳን እዳ
የቱ ጋር ነው ውዴ የቀለበት ጣትሽ
ላጥልቅልሽና ያለኝን ላውርስሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የቱ ጋር ነው ጣትሽ ምሬኝ ለቀለበት
በዋዛ አይገኝም ለፍተሽ ውሰጂ ንብረት
የቀረኝን እድሜ ባንቺ ተደስቼ
ውርሱን ሳልናዘዝ በትንፋሽሽ ሞቼ
ልፋትሽ በከንቱ እንዳይቀር በሜዳ
ምሪኝ ወደ ጣትሽ በቃል ኪዳን እዳ
የቱ ጋር ነው ውዴ የቀለበት ጣትሽ
ላጥልቅልሽና ያለኝን ላውርስሽ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍3❤2
#ጠባችን_ቀደመ
ፍቅራችን የውሸት ወረት ያሰከረው
በትናንሽ ሰበብ መውደቅ የሚያበዛው
ጠዋት ተማምለን ከሰአት ስናፈርስ
ምሽት አስጠንቁለን ማለዳ ማስቀደስ
ዛሬ ይታይልን እፍ እፍ ማለት አብሮ
ነገ ዓይን ለአፈር አፍለኛው ተጋግሮ
ፍቅራችን ተጥዶ በስሎ ሳይበላ
ጠባችን ቀደመ ተነስቶ ከሗላ
በወረት እስክስታ ለቀናት ደልቆ
ሀሜት ከተፍ ይላል ፍቅር ወዲያው አልቆ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ፍቅራችን የውሸት ወረት ያሰከረው
በትናንሽ ሰበብ መውደቅ የሚያበዛው
ጠዋት ተማምለን ከሰአት ስናፈርስ
ምሽት አስጠንቁለን ማለዳ ማስቀደስ
ዛሬ ይታይልን እፍ እፍ ማለት አብሮ
ነገ ዓይን ለአፈር አፍለኛው ተጋግሮ
ፍቅራችን ተጥዶ በስሎ ሳይበላ
ጠባችን ቀደመ ተነስቶ ከሗላ
በወረት እስክስታ ለቀናት ደልቆ
ሀሜት ከተፍ ይላል ፍቅር ወዲያው አልቆ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤6😭2👍1
#ተራ_በተራ_ነው
ሙታን ለመቀስቀስ ተስካር አትደግሱ
ይልቅስ ተግታችሁ ለቆመው አልቅሱ
ዓለምን ሰልችተው ለሄዱት በግዜ
ማዘን አቁማችሁ ለቅሶና ትካዜ
ለቆሙት አልቅሱ ደረትም ደልቁ
መከራው መኖር ነው እየተጨነቁ
ሞትማ ጥሪ ነው በተራ የሚደርስ
መኖር ነው አሁን ላይ ከልብ የሚያስለቅስ
ይተኙ ተዋቸው ሙታን እፎይ ብለው
የዚህች ዓለም ጉዞ ተራ በተራ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
ሙታን ለመቀስቀስ ተስካር አትደግሱ
ይልቅስ ተግታችሁ ለቆመው አልቅሱ
ዓለምን ሰልችተው ለሄዱት በግዜ
ማዘን አቁማችሁ ለቅሶና ትካዜ
ለቆሙት አልቅሱ ደረትም ደልቁ
መከራው መኖር ነው እየተጨነቁ
ሞትማ ጥሪ ነው በተራ የሚደርስ
መኖር ነው አሁን ላይ ከልብ የሚያስለቅስ
ይተኙ ተዋቸው ሙታን እፎይ ብለው
የዚህች ዓለም ጉዞ ተራ በተራ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
❤9❤🔥6