#ዛሬም_በመጠበቅ
ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
ዛሬም በመጠበቅ የተሻለን ዘመን
የለሁም አልልም ይኸው ዛሬም አለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
ዛሬም በመጠበቅ የተሻለን ዘመን
የለሁም አልልም ይኸው ዛሬም አለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
🥰10👏1
👍10
ፈገግ በል ጥርሴ
ተቆጠብ ምላሴ
ቅን አስቢ ነፍሴ
ጠላት ሆኜ እንዳልቀር እራሴው ለራሴ
ከአምላክ አታጣላኝ ሰከን በል ከርሴ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ተቆጠብ ምላሴ
ቅን አስቢ ነፍሴ
ጠላት ሆኜ እንዳልቀር እራሴው ለራሴ
ከአምላክ አታጣላኝ ሰከን በል ከርሴ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤10👍2
#ምንድን_ነው_ሰውነት?
የሰው ሚዛን ወርዶ
ቁስ አካል ተወዶ
ፍቅርም ተሰዶ
ጥላቻ ተለምዶ
አንድነት ተንዶ
ሰላም ጥሎን ሄዶ
ሰው እየተናቀ
ቁስ ከተደነቀ
ምንድን ነው ሰውነት? የክብር መስፈሪያው
ሁሉም ተነጣጥሎ ጥላቻ እየመራው !!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የሰው ሚዛን ወርዶ
ቁስ አካል ተወዶ
ፍቅርም ተሰዶ
ጥላቻ ተለምዶ
አንድነት ተንዶ
ሰላም ጥሎን ሄዶ
ሰው እየተናቀ
ቁስ ከተደነቀ
ምንድን ነው ሰውነት? የክብር መስፈሪያው
ሁሉም ተነጣጥሎ ጥላቻ እየመራው !!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🔥6👍1
ተመስገን ማለት ነው ዛሬ ያደረሰን
ስንቱን ክፉ ዓመታት ሰላም ያሻገረን
በማመስገን ትግስት ሆዳችን ባይሰፋ
ያሳለፍነው ፍዳ ከዚህም በከፋ!!!
ይመስገን ፈጣሪ ብዙ ዓመት አልፈናል
የጊዜውስ መክፋት ቀን በቀን ይጥላል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
ስንቱን ክፉ ዓመታት ሰላም ያሻገረን
በማመስገን ትግስት ሆዳችን ባይሰፋ
ያሳለፍነው ፍዳ ከዚህም በከፋ!!!
ይመስገን ፈጣሪ ብዙ ዓመት አልፈናል
የጊዜውስ መክፋት ቀን በቀን ይጥላል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
❤10👍1
እንቅልፍ ያጡ ዓይኖቼ ማረፍን የፈሩ
በሀሳብ ነበልባል በቅዠት ያደሩ
በመስታወት መስኮት ሳያቸው ሲነጋ
እጅግ አሳዘኑኝ ለከፈሉት ዋጋ!!!
እረፍት ነፍጊያቸው በሽህ ሀሳብ ስሌት
በማይጠቅም እህ በማይነጋው እውነት
አሳርን እያዩ ማረፍ ሲናፍቁ
ደፍርሰው ያዩኛል አድረው ሲጨነቁ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በሀሳብ ነበልባል በቅዠት ያደሩ
በመስታወት መስኮት ሳያቸው ሲነጋ
እጅግ አሳዘኑኝ ለከፈሉት ዋጋ!!!
እረፍት ነፍጊያቸው በሽህ ሀሳብ ስሌት
በማይጠቅም እህ በማይነጋው እውነት
አሳርን እያዩ ማረፍ ሲናፍቁ
ደፍርሰው ያዩኛል አድረው ሲጨነቁ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍5❤4
በአህያ ሞት አዝኖ ጅብ ለቅሶ ቢቀመጥ
ለማመቻቸት ነው ሲመሽ ለመለወጥ
በግ ጠፋብኝ አትበል ለቀበሮ መንጋ
ይልቅ ለአምላክ ንገር ወርዷል ለፍለጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ለማመቻቸት ነው ሲመሽ ለመለወጥ
በግ ጠፋብኝ አትበል ለቀበሮ መንጋ
ይልቅ ለአምላክ ንገር ወርዷል ለፍለጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍6🥰1
#ማንነት_ሲምታታ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍4❤3🥰3
#በጎች_ተጠንቀቁ
በቀበሮ መንጋ በግ እያስጠበቁ
ተበልተው ተበልተው በየተራ አለቁ
እረኛ ባሉት ነው ሁሉም የሚጠቁ
በቀበሮ ዘመን በጎች ተጠንቀቁ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በቀበሮ መንጋ በግ እያስጠበቁ
ተበልተው ተበልተው በየተራ አለቁ
እረኛ ባሉት ነው ሁሉም የሚጠቁ
በቀበሮ ዘመን በጎች ተጠንቀቁ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍7❤4
#የጌታ_ደብዳቤ
የድሮ ሰው ደጉ
በ…30…ዲናር
ጌታዉን ካስማማ
ምንኛ ይከፋል
ያሁኑ ሠዉማ
ስለዚህ አትምጣ
ለምፅዓት ቀኑ
ዲናር እንዳይመስልህ
ዶላር ነው ያሁኑ
ይቅር በለኝ አምላክ
አይሁንብኝ ድፍረት
እንዳስቀመጥከው ነው
"ሠው" የሚሉት ፍጥረት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
የድሮ ሰው ደጉ
በ…30…ዲናር
ጌታዉን ካስማማ
ምንኛ ይከፋል
ያሁኑ ሠዉማ
ስለዚህ አትምጣ
ለምፅዓት ቀኑ
ዲናር እንዳይመስልህ
ዶላር ነው ያሁኑ
ይቅር በለኝ አምላክ
አይሁንብኝ ድፍረት
እንዳስቀመጥከው ነው
"ሠው" የሚሉት ፍጥረት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
👏12❤3👍3
መኖር በሰው ፍቃድ ሆነና ዘንድሮ
ማስተዋል ተሳነን ልባችን ታውሮ።
ጌታ የሰጠውን ፍጡር ከነጠቀ
አትጠራጠሩ ይህ ዘመን አለቀ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ማስተዋል ተሳነን ልባችን ታውሮ።
ጌታ የሰጠውን ፍጡር ከነጠቀ
አትጠራጠሩ ይህ ዘመን አለቀ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤5👍1👏1
#ሁሉም_ጥቅም_አይቶ
ሰውንስ አየሁት በወረት ሲመታ
የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ
ሰው የተደገፉ በተራ ሲወድቁ
ወጀቡን አለፉት አንተን ያጠበቁ
ሁሉም ጥቅም አይቶ ሲወድ ሲጠላ
አንተ ግን ክርስቶስ ሁልጊዜም ነህ ጥላ
ስንቱን ቀርበን አየን ፈተናን ወደቀ
የድንግል ልጅ ብቻ ቃሉን የጠበቀ
ሲኖረን አብረውን ስናጣ የጣሉን
ወረት ሲያንጓልለው አይተነዋል ሰውን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሰውንስ አየሁት በወረት ሲመታ
የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ
ሰው የተደገፉ በተራ ሲወድቁ
ወጀቡን አለፉት አንተን ያጠበቁ
ሁሉም ጥቅም አይቶ ሲወድ ሲጠላ
አንተ ግን ክርስቶስ ሁልጊዜም ነህ ጥላ
ስንቱን ቀርበን አየን ፈተናን ወደቀ
የድንግል ልጅ ብቻ ቃሉን የጠበቀ
ሲኖረን አብረውን ስናጣ የጣሉን
ወረት ሲያንጓልለው አይተነዋል ሰውን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤4👍2🥰1
ተናገር ክራሬ የልቤን ዝምታ
ያለፈውን ህይወት መልስ በትዝታ
አንደበቴ አይችልም የውስጤን መናገር
እስኪ አንደበት ሁነኝ ስማኝ አንተ ክራር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ያለፈውን ህይወት መልስ በትዝታ
አንደበቴ አይችልም የውስጤን መናገር
እስኪ አንደበት ሁነኝ ስማኝ አንተ ክራር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍4❤1👎1
👍3❤2
#እንኳን_ነፍስ_ሊድን
ልብ ቂም አርግዞ ዝክርን ቢዘክሩ
ዳዊት ይዞ ውሎ ዳዊት ይዞ ቢያድሩ
ለጽድቅ ያልታደለ ጠማማ ልብ ይዞ
ማንስ ድኖ ያውቃል ጥላቻን አርግዞ
እህት ወንድም ጠልቶ አሜን አሜን ቢሉ
አምላክ አምላክ ብሎ ምን ቢሸነግሉ
ልብ እንጂ መዳኛው ከእግዜር አስታራቂ
ማስመሰል አይደለም በምላስ አዋቂ።
የሰው ሀቅን በልቶ አስራትን ቢያወጡ
ውስጥ እየሰሰተ ለድሃው ቢሰጡ
እንኳን ነፍስ ሊያድን አይበጅም ለስጋ
በፈሪሳውያን ስልት አይገኝም ጸጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ልብ ቂም አርግዞ ዝክርን ቢዘክሩ
ዳዊት ይዞ ውሎ ዳዊት ይዞ ቢያድሩ
ለጽድቅ ያልታደለ ጠማማ ልብ ይዞ
ማንስ ድኖ ያውቃል ጥላቻን አርግዞ
እህት ወንድም ጠልቶ አሜን አሜን ቢሉ
አምላክ አምላክ ብሎ ምን ቢሸነግሉ
ልብ እንጂ መዳኛው ከእግዜር አስታራቂ
ማስመሰል አይደለም በምላስ አዋቂ።
የሰው ሀቅን በልቶ አስራትን ቢያወጡ
ውስጥ እየሰሰተ ለድሃው ቢሰጡ
እንኳን ነፍስ ሊያድን አይበጅም ለስጋ
በፈሪሳውያን ስልት አይገኝም ጸጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤10👍3🔥2🥰1🤝1
ቤተሰብ እንዴት ናችሁ🙌
ሜምበር እየጨመረ አይደለም why?
የደበራችሁ ነገር መስተካከል አለበት የምትሉትን ንገሩኝ ታዛዥ ነኝ
ደግሞ ዝም ብላችሁ ማንበብ አይነፋም🤔
React እና share አድርጉ😍😍
ሜምበር እየጨመረ አይደለም why?
የደበራችሁ ነገር መስተካከል አለበት የምትሉትን ንገሩኝ ታዛዥ ነኝ
ደግሞ ዝም ብላችሁ ማንበብ አይነፋም🤔
React እና share አድርጉ😍😍
🔥8👍3
#ቅንና_ክፉ
የቅን ሰዎች ቅኔ የቅን ሰዎች ዜማ
ተካፍሎ መብላት ነው በፍቅር አውድማ
ሰምና ወርቅ ያለው የልባቸው ምስጢር
ቅኝቱ ቅርብ ነው ታማኝ ነው ለእግዚአብሔር
የክፉ ሰው ቅኔ የክፉ ሰው ዜማ
ቀምቶ መብላት ነው በጥላቻ አውድማ
ፍቅር ያልገባቸው ለሰይጣን ያደሩ
ሌላውን ጥለው ነው በሀብት የሚከብሩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የቅን ሰዎች ቅኔ የቅን ሰዎች ዜማ
ተካፍሎ መብላት ነው በፍቅር አውድማ
ሰምና ወርቅ ያለው የልባቸው ምስጢር
ቅኝቱ ቅርብ ነው ታማኝ ነው ለእግዚአብሔር
የክፉ ሰው ቅኔ የክፉ ሰው ዜማ
ቀምቶ መብላት ነው በጥላቻ አውድማ
ፍቅር ያልገባቸው ለሰይጣን ያደሩ
ሌላውን ጥለው ነው በሀብት የሚከብሩ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤5👍2👏1