ግጥም
4.28K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
በመረረ ሀዘን ልባችን ተሰብሮ
ኑ " ሳቁ ይሉናል የጉድ ነው ዘንድሮ
እንኳንስ ለመሳቅ ከትከት ለማለት
ፈገግታም ታምር ነው አሁን ባለው ስሜት።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍51
የጊዜውን ክፋት በጥርስ እየሸኙ
የህይወትን ዜማ በእውነት እየቃኙ
አንጀት እያረረ ይለፍ በፈገግታ
እስኪገለጥ ድረስ የፈጣሪ እውነታ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
9👍4
react በማድረግ አብሮናታቹን አሳዩን
👍15
ግጥም
react በማድረግ አብሮናታቹን አሳዩን
አያስከፍልም እኮ🤔🤔
20 react ሲሞላ እፖስታለሁ
🔥13👍8🤝4
ኧረ የቋጠራችሁ ፍቱ🙊🙊
👍9😁1
  #ዛሬም_በመጠበቅ

ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
ዛሬም በመጠበቅ የተሻለን ዘመን
የለሁም አልልም ይኸው ዛሬም አለን።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
🥰10👏1
በቁጥብ ፈገግታ በችሎ ማለፍ ህግ
ነገን ተስፋ አድርገን እንላለን ፈገግ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍10
እስኪ ቀልድ የምትወዱ React አድርጉ
🥰14🔥1
ፈገግ በል ጥርሴ
ተቆጠብ ምላሴ
ቅን አስቢ ነፍሴ
ጠላት ሆኜ እንዳልቀር እራሴው ለራሴ
ከአምላክ አታጣላኝ ሰከን በል ከርሴ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
10👍2
#ምንድን_ነው_ሰውነት?

የሰው ሚዛን ወርዶ
ቁስ አካል ተወዶ
ፍቅርም ተሰዶ
ጥላቻ ተለምዶ
አንድነት ተንዶ
ሰላም ጥሎን ሄዶ
ሰው እየተናቀ
ቁስ ከተደነቀ
ምንድን ነው ሰውነት? የክብር መስፈሪያው
ሁሉም ተነጣጥሎ ጥላቻ እየመራው !!!
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
🔥6👍1
ተመስገን ማለት ነው ዛሬ ያደረሰን
ስንቱን ክፉ ዓመታት ሰላም ያሻገረን
በማመስገን ትግስት ሆዳችን ባይሰፋ
ያሳለፍነው ፍዳ ከዚህም በከፋ!!!
ይመስገን ፈጣሪ ብዙ ዓመት አልፈናል
የጊዜውስ መክፋት ቀን በቀን ይጥላል።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
10👍1
እንቅልፍ ያጡ ዓይኖቼ ማረፍን የፈሩ
በሀሳብ ነበልባል በቅዠት ያደሩ
በመስታወት መስኮት ሳያቸው ሲነጋ
እጅግ አሳዘኑኝ ለከፈሉት ዋጋ!!!
እረፍት ነፍጊያቸው በሽህ ሀሳብ ስሌት
በማይጠቅም እህ በማይነጋው እውነት
አሳርን እያዩ ማረፍ ሲናፍቁ
ደፍርሰው ያዩኛል አድረው ሲጨነቁ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍54
በአህያ ሞት አዝኖ ጅብ ለቅሶ ቢቀመጥ
ለማመቻቸት ነው ሲመሽ ለመለወጥ
በግ ጠፋብኝ አትበል ለቀበሮ መንጋ
ይልቅ ለአምላክ ንገር ወርዷል ለፍለጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍6🥰1
#ማንነት_ሲምታታ

የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍43🥰3
#በጎች_ተጠንቀቁ

በቀበሮ መንጋ በግ እያስጠበቁ
ተበልተው ተበልተው በየተራ አለቁ
እረኛ ባሉት ነው ሁሉም የሚጠቁ
በቀበሮ ዘመን በጎች ተጠንቀቁ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍74
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍1
#የጌታ_ደብዳቤ

የድሮ ሰው ደጉ
በ…30…ዲናር
ጌታዉን ካስማማ
ምንኛ ይከፋል
ያሁኑ ሠዉማ
ስለዚህ አትምጣ
ለምፅዓት ቀኑ
ዲናር እንዳይመስልህ
ዶላር ነው ያሁኑ
ይቅር በለኝ አምላክ
አይሁንብኝ ድፍረት
እንዳስቀመጥከው ነው
"ሠው" የሚሉት ፍጥረት
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
👏123👍3
መኖር በሰው ፍቃድ ሆነና ዘንድሮ
ማስተዋል ተሳነን ልባችን ታውሮ።
ጌታ የሰጠውን ፍጡር ከነጠቀ
አትጠራጠሩ ይህ ዘመን አለቀ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
5👍1👏1
#ሁሉም_ጥቅም_አይቶ

ሰውንስ አየሁት በወረት ሲመታ
የማትቀያየር አንተ ብቻ ጌታ
ሰው የተደገፉ በተራ ሲወድቁ
ወጀቡን አለፉት አንተን ያጠበቁ
ሁሉም ጥቅም አይቶ ሲወድ ሲጠላ
አንተ ግን ክርስቶስ ሁልጊዜም ነህ ጥላ
ስንቱን ቀርበን አየን ፈተናን ወደቀ
የድንግል ልጅ ብቻ ቃሉን የጠበቀ
ሲኖረን አብረውን ስናጣ የጣሉን
ወረት ሲያንጓልለው አይተነዋል ሰውን
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
4👍2🥰1
ተናገር ክራሬ የልቤን ዝምታ
ያለፈውን ህይወት መልስ በትዝታ
አንደበቴ አይችልም የውስጤን መናገር
እስኪ አንደበት ሁነኝ ስማኝ አንተ ክራር።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍41👎1
ብስልና ጥሪ አንድ ላይ ተጥዶ
ጥሬው እስኪበስል ይፈጃል ማገዶ።
@gitm_post
♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲            
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
👍32