ዛሬ ሳቅ ቢወደድ ቢጠፋ ደስታ
ፈገግ እንላለን በትላንት ትዝታ
መቆዘም ቢበዛ ሀዘን በዝቶ ዛሬ
በትላንት ጥሩ ቀን ፈገግ አልኩኝ ዞሬ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ፈገግ እንላለን በትላንት ትዝታ
መቆዘም ቢበዛ ሀዘን በዝቶ ዛሬ
በትላንት ጥሩ ቀን ፈገግ አልኩኝ ዞሬ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍7🔥1
ድሮም በጅብ ቆዳ የተሰራ ክራር
ቅኝቱ እንብላው ነው መች ያዜማል ፍቅር
ቢደረድሩትም ቢገርፉት አምርሮ
የጅብ ቆዳ ክራር ሆድ ነው ዞሮ ዞሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ቅኝቱ እንብላው ነው መች ያዜማል ፍቅር
ቢደረድሩትም ቢገርፉት አምርሮ
የጅብ ቆዳ ክራር ሆድ ነው ዞሮ ዞሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🔥6👍3
#በይቅርታ_ጋሻ
ከበደሉህ በላይ በዳይ ልብ ከኖረህ
አንተስ ከበዳዮች በምን ትለያለህ?
የተሻለ በዳይ ካልተባልክ በስተቀር
ቂምን በቂም አጥቦ አይገኝም ፍቅር
የክርስቶስ ጀግና መሆንን የሚሻ
ጠላቱን ይማርከው በይቅርታ ጋሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ከበደሉህ በላይ በዳይ ልብ ከኖረህ
አንተስ ከበዳዮች በምን ትለያለህ?
የተሻለ በዳይ ካልተባልክ በስተቀር
ቂምን በቂም አጥቦ አይገኝም ፍቅር
የክርስቶስ ጀግና መሆንን የሚሻ
ጠላቱን ይማርከው በይቅርታ ጋሻ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍12❤3
#ማር_ከመሆን_ማማ
ማሩን ሊሰሩብሽ ንቦች ሲሰናዱ
ውሎሽ ከዝንብ ሆኖ ተመልሰው ሄዱ
አበባ ነሽ ብለው ለክብርሽ ሲመጡ
ከቆሻሻ ስፍራ ተገኘሽ ከድጡ!!!
አይ አለመታደል የዘመን ዝቅታ
ማር ከመሆን ማማ መውረድ ከከፍታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ማሩን ሊሰሩብሽ ንቦች ሲሰናዱ
ውሎሽ ከዝንብ ሆኖ ተመልሰው ሄዱ
አበባ ነሽ ብለው ለክብርሽ ሲመጡ
ከቆሻሻ ስፍራ ተገኘሽ ከድጡ!!!
አይ አለመታደል የዘመን ዝቅታ
ማር ከመሆን ማማ መውረድ ከከፍታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍6❤3
❤5👏2
#ምላስ_ተትረፍርፎ
ሁሉን ስሙኝ ባዩ ብዙ ተናጋሪ
የባጡን የቆጡን ዘወትር ቀባጣሪ
ጀሮ አልባ ምላሳም ነገረ ፈጅ ሁላ
ስሙኝ ስሙኝ ባዩ ማድመጥን የጠላ
ተሽክማ ሀገር ምላስ ተትረፍርፎ
የቀለለ ምሁር ግርማውም ተገፎ
በየትኛው ልኬት በየትኛው ቀመር
የምንበለጽገው ተለክፈን በዘር ዛር
ሁላችን አዋቂ ግን ደግሞ ደንቆሮ
ምላስ ተትረፍርፎ ተወደደ ጀሮ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሁሉን ስሙኝ ባዩ ብዙ ተናጋሪ
የባጡን የቆጡን ዘወትር ቀባጣሪ
ጀሮ አልባ ምላሳም ነገረ ፈጅ ሁላ
ስሙኝ ስሙኝ ባዩ ማድመጥን የጠላ
ተሽክማ ሀገር ምላስ ተትረፍርፎ
የቀለለ ምሁር ግርማውም ተገፎ
በየትኛው ልኬት በየትኛው ቀመር
የምንበለጽገው ተለክፈን በዘር ዛር
ሁላችን አዋቂ ግን ደግሞ ደንቆሮ
ምላስ ተትረፍርፎ ተወደደ ጀሮ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍9😁1
ከሁሉም ከሁሉም በእውነት የሚዳኘን
ሞታችን ነው ታማኝ እኩል የሚያደርገን።
ሚዛኑ አያጋድል አይቀር በቀጠሮ
በዳይ ከተበዳይ ከአፈር ዞሮ ዞሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሞታችን ነው ታማኝ እኩል የሚያደርገን።
ሚዛኑ አያጋድል አይቀር በቀጠሮ
በዳይ ከተበዳይ ከአፈር ዞሮ ዞሮ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👏5❤3
#ከውሻ_ጋር_ዋልኩኝ
ይታመናል ቢሉኝ ከሰው በላይ ልቆ
የጌታውን ስሜት በደመንፈስ አውቆ
ከውሻ ጋር ዋልኩኝ ከሰው ተነጥዬ
በብቻዬ ዓለም ውስጥ በአጥር ተከልዬ
ግና ምን ያደርጋል ስረዳ በሗላ
ውሻም ላበላው ነው ጭራ የሚቆላ
ከመሰሉ ፍጡር ከሰው ሳይግባባ
ውሻን ቢያለምድ ልቤ ከቶ ምን ሊረባ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ይታመናል ቢሉኝ ከሰው በላይ ልቆ
የጌታውን ስሜት በደመንፈስ አውቆ
ከውሻ ጋር ዋልኩኝ ከሰው ተነጥዬ
በብቻዬ ዓለም ውስጥ በአጥር ተከልዬ
ግና ምን ያደርጋል ስረዳ በሗላ
ውሻም ላበላው ነው ጭራ የሚቆላ
ከመሰሉ ፍጡር ከሰው ሳይግባባ
ውሻን ቢያለምድ ልቤ ከቶ ምን ሊረባ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍4
#ለቅሶ_መች_ተሰምቶ
የውስጣችን ሀዘን በጥርስ ተጋርዶ
እያነበቡ እስክስታ ቀን በቀን ተለምዶ
ሙሾ በሙዚቃ በዜማ ተሟሽቶ
በስንኝ ቋጠሮ እህ እህ ተቃኝቶ
ለምዶ ትክሻችን ሀዘን ችሎ ማደር
ደስታ መስሎታል ሳቃችን ለሀገር!
ደልቷቸው ነው ይላል ጥርሳችንን አይቶ
የውስጥ መከፋት ለቅሶ መች ተሰምቶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የውስጣችን ሀዘን በጥርስ ተጋርዶ
እያነበቡ እስክስታ ቀን በቀን ተለምዶ
ሙሾ በሙዚቃ በዜማ ተሟሽቶ
በስንኝ ቋጠሮ እህ እህ ተቃኝቶ
ለምዶ ትክሻችን ሀዘን ችሎ ማደር
ደስታ መስሎታል ሳቃችን ለሀገር!
ደልቷቸው ነው ይላል ጥርሳችንን አይቶ
የውስጥ መከፋት ለቅሶ መች ተሰምቶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤6🔥1
አይነጋም አትበሉ ይነጋል በግዜው
ሁሌም በክርስቶስ ነገር ለበጎ ነው
በእርሱ የሚሆነው ለመልካም ነውና
ሲነጋም ሲመሽም መኖር በምስጋና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሁሌም በክርስቶስ ነገር ለበጎ ነው
በእርሱ የሚሆነው ለመልካም ነውና
ሲነጋም ሲመሽም መኖር በምስጋና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍6❤2👏1
/// " አምላክ ጥበበኛ " ///
የሚታደል ቢሆን እድሜ በስም ጥሪ
ሁሉም ድሃ ሞቶ ሀብታም ነበር ነዋሪ
ስልጣኑ ቢገባ በቀበሌው መሪ
ልክ እንደ ዳቧችን ቢሆን በስም ጥሪ
የድሃ እድሜ ሁሉ ለሀብታም ተሽጦ
ከምድሩ በጠፋ እስካሁን ተመርጦ
አምላክ ጥበበኛ ሰውን ጥንት ሲሰራው
እንኳን የእድሜን ገደብ በእራሱ አደረገው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የሚታደል ቢሆን እድሜ በስም ጥሪ
ሁሉም ድሃ ሞቶ ሀብታም ነበር ነዋሪ
ስልጣኑ ቢገባ በቀበሌው መሪ
ልክ እንደ ዳቧችን ቢሆን በስም ጥሪ
የድሃ እድሜ ሁሉ ለሀብታም ተሽጦ
ከምድሩ በጠፋ እስካሁን ተመርጦ
አምላክ ጥበበኛ ሰውን ጥንት ሲሰራው
እንኳን የእድሜን ገደብ በእራሱ አደረገው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍3
#ሁሉም_በጋራ_ነው
ቤተ ሰሪ በዝቶ ይላል ማገር ማገር
መቼ ሊኖርበት ጸንቶ ሳይቆም ሀገር
ይልቅስ ይቀድማል መሰረቱን ማጽናት
ሁሉም በጋራ ነው ለማአገሩ መትጋት ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ቤተ ሰሪ በዝቶ ይላል ማገር ማገር
መቼ ሊኖርበት ጸንቶ ሳይቆም ሀገር
ይልቅስ ይቀድማል መሰረቱን ማጽናት
ሁሉም በጋራ ነው ለማአገሩ መትጋት ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤4
#ካልመጣሽ_ላይነቃ
በመቅረትሽ ዜማ በናፍቆት ቆዝሜ
ደህና ነኝ እያልኩኝ በፍቅርሽ ታምሜ
እጠብቅሻለሁ ከትዝታሽ ማዶ
ልቤ ከልብሽ ጋር አንድ ላይ ተዛምዶ።
ልብ አልባ እኔነቴ በደመነፍስ ቀርቶ
በድንዛዜ ስልት ብቻውን ሸፍቶ
ከሰው በመነጠል የእራሱ ዓለም ሰርቶ
ካልመጣሽ ላይነቃ ለእራሱ ቃል ገብቶ
ዛሬም ይጠብቃል ተስፋን ባለመቁረጥ
ከአስቀመጥሽው ቦታ ታምኖ በመቀመጥ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
በመቅረትሽ ዜማ በናፍቆት ቆዝሜ
ደህና ነኝ እያልኩኝ በፍቅርሽ ታምሜ
እጠብቅሻለሁ ከትዝታሽ ማዶ
ልቤ ከልብሽ ጋር አንድ ላይ ተዛምዶ።
ልብ አልባ እኔነቴ በደመነፍስ ቀርቶ
በድንዛዜ ስልት ብቻውን ሸፍቶ
ከሰው በመነጠል የእራሱ ዓለም ሰርቶ
ካልመጣሽ ላይነቃ ለእራሱ ቃል ገብቶ
ዛሬም ይጠብቃል ተስፋን ባለመቁረጥ
ከአስቀመጥሽው ቦታ ታምኖ በመቀመጥ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤4👍2
#የጭዋ_ዝምታ
አድማጭ ከሌለበት ከብዙ ጫጫታ
እጅጉን ያስፈራል የአንድ ሰው ዝምታ
ቃላትን ሰድሮ ብዙ ከሚያወራ
በስሜት ጋጋታ ስሙ ከሚጠራ
የጨዋ ዝምታ ቅኔ አለው አብዝቶ
ይፈሳል ማስተዋል ከልቡ ውስጥ ሞልቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
አድማጭ ከሌለበት ከብዙ ጫጫታ
እጅጉን ያስፈራል የአንድ ሰው ዝምታ
ቃላትን ሰድሮ ብዙ ከሚያወራ
በስሜት ጋጋታ ስሙ ከሚጠራ
የጨዋ ዝምታ ቅኔ አለው አብዝቶ
ይፈሳል ማስተዋል ከልቡ ውስጥ ሞልቶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤5🔥2
በመረረ ሀዘን ልባችን ተሰብሮ
ኑ " ሳቁ ይሉናል የጉድ ነው ዘንድሮ
እንኳንስ ለመሳቅ ከትከት ለማለት
ፈገግታም ታምር ነው አሁን ባለው ስሜት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ኑ " ሳቁ ይሉናል የጉድ ነው ዘንድሮ
እንኳንስ ለመሳቅ ከትከት ለማለት
ፈገግታም ታምር ነው አሁን ባለው ስሜት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍5❤1
የጊዜውን ክፋት በጥርስ እየሸኙ
የህይወትን ዜማ በእውነት እየቃኙ
አንጀት እያረረ ይለፍ በፈገግታ
እስኪገለጥ ድረስ የፈጣሪ እውነታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
የህይወትን ዜማ በእውነት እየቃኙ
አንጀት እያረረ ይለፍ በፈገግታ
እስኪገለጥ ድረስ የፈጣሪ እውነታ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤9👍4