ግጥም
5.71K subscribers
23 photos
1 video
6 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
የማለዳ ወፌ የምሽት ጀንበሬ፣
ዜማሽ መፅናኛየ መሄድሽ ችግሬ።
ዉቧ ጨረቃየ የምሽት ድባቤ፣
የህይወት ስኬቴ ምግባረ ሐሳቤ፣
መሆንሽን እያወቅሽ የልቤ ከተማ፣
የከናፍሬ ጣዓም ያ'ንደበቴ ዜማ፣
ለምን ረሳሽኝ በጥልቅ ባህር ቆሜ?
ፍቅርሽን እያለምኩ በፍቅር ዓለሜ።

ዜማሽን ሳልሰማ እነቃ ይመስል፣
እዉላለሁ አድራለሁ አ'ንችን ሳንሰላስል።
እድሜየ ባክኖ ዘመኔ ጨቅይቶ፣
ትዝታሽ ብቻዉን ከእኔ ጋር ቆይቶ።
ቆይቶ...ቆይቶ...ቆይቶ...ቆይቶ፣
ድንገት አስነቅቶ...
''አይዞህ አትተክዝ በፍቅር ጠብቃት፣
ባ'ካል ብትለያት በመንፈስ አትራቃት፣
አንተ እንደምትወዳት እሷም ፍቅር አላት''፣
እያለ ያፅናናኛል በፅኑ ዉብ ቃላት።

እኔ የምለዉ ግን እኔ አንችን ወድጄ፣
ጨርቄን ማቄን ጥየ እርቃን ተሰድጄ፣
በፍቅርሽ በርሬ በፍቅርሽ አብጄ፣
ድንገት ከተፍ ብትይ በጨቀየ ደጄ፣
ምን ይሰማሽ ይሆን እብደቴን እያየሽ፣
ምን ይሰማኝ ይሆን ካ'ጠገቤ ቆመሽ፣
መቸም ታዉቂዋለሽ አይጠፋሽም ፍቅሬ፣
የኔ ጥልቅ ሱሴ አንች ነሽ ችግሬ።

ከማንም ከምንም የበለጥሽ ሱሴ፣
ፍቅሬ አንች ብቻ ነሽ የህይወት ፋኖሴ።
እናም ስትሄጅ ሞቼ ስትመጭ እድናለው፣
ትንሳኤና ሞቴ መምጣት መሄድሽ ነዉ።
እየሄድሽ ገለሽኝ ስትመጭ እድናለው፣
ትንሳኤና ሞቴ መምጣት መሄድሽ ነው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
❤17🥰1
#በቃ_ትመጫለሽ!

የወሰደሽ መንገድ ፣ ያራቀሽ ጎዳና፤
ቢያገናኘን እያልኩ ፣ መልሶ እንደገና፤
አሻግሬ እያየሁ ፣ በተስፋ መስታወት፤
ዛሬ ነገ መጣች ፣ በማይቀንስ ጉጉት፤
እጠብቅሻለሁ ፣ በማይወዥብ ጊዜ፤
በማይሰለች ትግስት ፣ በፍቅር ትካዜ፤
አርቆ ወሳጁን ፣ አቅርቦ መላሹን፤
ጎዳናን አምኜ ፣ እልፍ አንቀሳቃሹን፤
ለቃሌ ታምኜ ፣ ፍቅርሽን ስናፍቅ፤
ዓመታት አለፉ ፣ መንገዱን ስጠብቅ፤
ግን አይሰለችኝም ፣ ጎዳናው ወዶኛል፤
ዛሬ ነገን ወልዶ ፣ ተስፋን ያሳየኛል!!!
በቃ ትመጫለሽ ! እጠብቅሻለሁ፤
ወሳጁ መልሶሽ ፣ በአካል አይሻለሁ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤30🥰3👍2
#ፍቅር_ማለት

ከእውቀት-ባሻገር
ከዝና-ባሻገር
ከሀብት-ባሻገር
ከውበት- ባሻገር
ባለው ስብዕና ከተማረካችሁ
ሰው መሆኑ ብቻ እውነት ከገባችሁ
አ ቤ ት !! ታድላችሁ
በቃ!!
ፍቅር ማለት ይህ ነው
እውቀት- ዝና- ውበት- ገንዘብ የማይገዛው
ፍቅር ማለት ይህ ነው

እውቀትም ይጠፋል
ዝናም ሀብትም ያልፋል
ውበትም ይረግፋል
ሰው መሆኑ ብቻ ስብዕናው ብቻ
ከሱ ጋር ይዘልቃል

ፍቅር ማለት ይህ ነው
እውቀት ዝና ውበት ገንዘብ የማይገዛው

እንዲሁ መዋደድ
መጓዝ ባንድ መንገድ
እራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠት
ስለሌላው መኖር ! ስለሌላው መሞት!
ይህ ነው ፍቅር ማለት
......ይህ
...........ነው
................ፍቅር
.......................ማለት...
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳሚ
❤24👎2👍1
#እኔ_ሞኙ_ልጅሽ!!

አንችን ገላጭ ቅኔ አንች ገላጭ ዜማ
የውበትሽን ጥግ የክብርሽን ግርማ
ብሞክር ባስሞክር በስንኝ ቋጠሮ
ቤት ባልመታ ግጥም በቃል እጉርጉሮ
በሀገር መስዬ ላወድስሽ ብጥር
አልገልጽልህ አለኝ እኔስ ያንችን ፍቅር
አናት ከማለት ውጭ ሌላው ቀለለብኝ
ብጽፈው ባጽፈው ሚዛኑ አነሰብኝ!
የፍቅርሽን ልኬት የደግነት ጥልቀት
የትኛው ቃል ይሆን ገላጭ እናትነት
ቃል አዋቂ ፈለኩ የተማረ አብዝቶ
ከውስጡ የሚፈስ ዜማ ቅኔ ሞልቶ
ግን አላረካኝም ውበቱ አነሰብኝ
ለደግነትሽን ክብር በቂ ቃል አጣሁኝ
ያወቁ የበቁ ሽህ አመት ቢመክሩ
ቋንቋ ላይ ተራቀው አብዝተው ቢማሩ
እናት ነው ውብ ቃሉ  ረቂቅ ቀመሩ
ሌላ ስም የላትም አትመራመሩ!
አልኳቸው እናቴ እኔ ሞኙ ልጅሽ
ቢሳነኝ በቅኔ በዜማ ልገልጽሽ
ሌላ ቃል ፈልጌ አስፈልጌ ባጣ
ከደጋ እስከቆላ ወርጄ ስወጣ
ከፊደላት ድምር እናት የሚል መጣ
እየደጋገመ እርሱው ከአፌ ይውጣ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤15
#የሰው_ልጅ_ፈተና

እልፍ ባላ ቢቆም ፣ ሕይወትን ሊያቀና ፤
እኩል ሚዛን ሆኖ ፣ በአንድ ላይ ቢፀና ፤
ሃሳቡ ቢሟላ ፣  ብሎ ደፋ ቀና ፤
አያልቅም ተዝቆ ፣ የሰው ልጅ ፈተና ።
ቢወጣ ቢወረድ ፣ ከ,እስከ የሌለው ፤
ፍላጎቱ ብዙ ፣ ሲያድጉ አብሮ የሚያድገው ፤
ሃጢአትና ፅድቁን ፣ ሁሉን የሚያሰኘው ፤
ቀን በቀን መዋተት፣እንዲያው በከንቱ ነው ፤
ቢሆንማ ኖሮ  ፣ ሰው እንደማያስበው  ፤
የትናንቱ ፅልመት ፣ ነግቶ ባላየነው ።
ይመስለዋል እንጅ ፣ ሁሉ የሚሞላ ፤
የሰው ልጅ ፣ ሞኝ ነው ዝንጉና ተላላ ፤
ወይ አለማወቁ
እንደሚፈራረቅ ፣ ችግርና ተድላ ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     ✍️ ሐና አምታታው
👌10❤6🔥1
#ከህይወት_በስተቀር...

ያ ሁሉ መቦረቅ
ያ ሁሉ መፈንደቅ
ወዙ ሳይቀየር ፥ የልጅነት መልኩ፣
ይመተራል ለካ
ገደብ አለው ለካ ፥ የነፃነት ልኩ።

ያ ሁሉ መተከዝ
ያ ሁሉ መደንዘዝ

ውሉ እየጠፋ
ህመም እያካፋ

በጉንጬ ደረት ላይ ፥ እንባዬ ሲለማ፣
ለአንዲት ዕድሜ ዘመን ፥ ለህይወት ዜማ፣

እንኳን ሰው ቀርቶ ፥ ገላዬ ሲለወጥ፣
አንድ መሸሸጊያ  ፥ በስቃይ ሲናወፅ፤

ማንም አልነገረኝ
ፍርቅርቅ ቅኝቱ ፥ ፍቅረ ምንዛሬ፣
የትላንቷን ፀሐይ ፥ ላትመስል ዛሬ፤

ሳይገባኝ
ሁሉ-እየወቃኝ
ህይወት-እያነቃኝ

ማንም ስለማንም ፥ ፀንቶ ለማይፀና፣
ስንት ሴል ይሞታል
ስንት ሴል ይበቅላል ፥ በመኖር ቀጠና።

ማንም አልነገረኝ
ከህይወት በስተቀር ፥ ከእዚህ በፊት ቀድሞ፣
ለቀርፋፋ ተጓዥ
ስክነት እንደሌላት
ግብሯ የተቃርኖ ፥ መደለቋን ላተው የመሞት ኣታሞ።

ቢሆንም ፣ ቢያይልም፣
ህይወት ፊት ባትሰጥም፤

ማንም ላያበድር ፥ ከዕለት ቀፈፋ፤
በእዚህ ጥድፊያ መኃል
ያጣሁትም ሁሉ ፥ እንኳን ሁሉም ከፋ።

ኩሸት ይሆናል
ከራስ መፋታት ፥ ብዬ ብፅናና፣
እንዴት አጣለሁ ፥ የፍቅርን ቃና?

ምንስ
አረፍኩት ፥ ከቶ መች ረጋው፣
ለይቶ ማየት
አንቺ እና ፍቅር ፥ ትርፍና ዋጋው?

አቸኳኮሌ
አጠዳደፌ
ቅዱን ለመስፋት ፥ ብቀመጥ ደጄ፣
አንቺን እያጣሁ
እንዴት ልልበሰው ፥ ፍቅርን ቀድጄ።

ካጣሁት ሁሉ ፥ ሁሉን ከነሳኝ፣
አንቺን አጊንቼ ፥ ፍቅር ግን ጠፋኝ።

ከእንግዲህ ምን አለኝ ፥ ሀዘነ ዝማሜ
ከእውነቴ ተጋጨሁ ፥ ከህይወት ፊቷ ቆሜ።

ማንም አልነገረኝ
ከህይወት በስተቀር ፥ ፊት ለፊቴ ቆሞ፣
ሰው እንዴት ይኖራል
እንዴት ይራመዳል ፥ ሰው በሰው ላይ ዘሞ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍ ፍቃዱ-አሥራት
❤9👍1👎1
#ይባላል_አላውቅም!

"እሱ ለታመመ ለሞተም ግድ የለው"
እንጃ ያንን ልቡን ምን እንደገደለው::

ይባላል? አላውቅም!
"አንተ በበኩልህ ትወደኝ ነበረ"
ያ ሁሉ፣ ያ ሁሉ ምን አድርጌህ ቀረ?

ለ'ለምን' ትተኸኝ ለ'ለምን' ለእሾኹ
'ላጋም እስር ቁስል፤ ቄስ ላይፈታው ሼኹ
ተገራህ አካልህ?፤ ተረገጠህ መሬት?
  ኮሶ ንክ አዳሬን ለውሰኸው ሬት::

ምን ባይታይህ ነው፤
ተስፋ ያስደገፍኩት እግሬ እየታከተ፣
እቆማለሁ ማለት ጣይ እየመከተ፣
ልቤን ለመውደድህ ላተርፍ ስፍገመገም፣
ቁስሎቼን በዋዛ በእጆቼ ስታከም፣
መስቀሌን በአንጀቴ፣ በሆዴ ስሸከም::

እንጂ ሂድ፣ እንጂ ሂድ፤
አስደንቆም አያውቅ የነበረ ባይኖር
እስተጊዜው እንጂ፤
የሰማዪም ባላ መታጠፉ ላይቀር
ቃል ባልደፋሁ ነበር፤
ኮከቤ ያልከውን እግርህ ብትከተል
የልቤን ጫፍ ብትለቅ፤
ባትተረትራት ነፍሴን እንደ ዳንቴል::

እንደ ጋመ ወስፌ፣ እንዳፋጩት ስለት
ጎን ይበጣጥሳል ምን ባደረግኩ ማለት።
ንገረኝ!
ንፋስ ልም አካሌን እየነቀነቀው፣ እያዘናፈለኝ
ብቆም ለመልስህ ነው፤ የቀረ ምን አለኝ?!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍ ማህደር ወሰኑ
❤7💔1
#ይብላኝ_የደገስሽው

‎ከእንግዲህ ትቻለኹ!
‎ቃል መፍተል ማማጡን
‎ትነግሪኝ እንደሆን
‎በይ ንገሪኝ ቁርጡን
‎ነጋ መሸ እያልኹኝ ፡ ወደያለፍሽበት
‎እንደማፈራረቅ ፡ በእኩል ባንድ ቅጽበት
‎ዘመን እና እድሜ ፡ ልደት እና ሽበት
‎
‎በሰፊው ጎዳና
‎በቀናው ጎዳና
‎ሂድ ብትይ መጥቼ
‎ሄጄ ብትይኝ ና
‎
‎ለግዑዝ መልሼ ሕያው ላናገረኝ
‎ቀኝ እና ግራዬ
‎ፊት እና ኃላዬ  ፡ ካደነደነጋገረኝ
‎"አንድ ቃል ፡ አንድ አፍታ
‎"ወድሻለሁ" ማለት እንዲሕ ካስቸገረኝ
‎
‎አልችልም ከእንግዲህ ቃል መፍተል ማማጡን
‎ትነግሪኝ እንደሆን በይ ንገሪኝ ቁርጡን
‎
‎ያው ሞቴም እንደሆን ፡ 
‎ለሥቃይ በተስፋ ፡ ከምታዘገይኝ
‎ከምንም ከፍጥረት ፡ ከምታታግይኝ
‎ይብላኝ የደገስሽው ፡ "አልወድሕም" በይኝ!!!
‎        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
❤8🔥8
#አቃተን_ሰውነት

ጥላቻና ክፋት አብሮን እየኖረ፣
ፍቅርም እንደ ሰው ድንበር ተሻገረ!
አምላክ ልብን ስጠን ከፍቅር መታረቂያ፣
በሰውነት ገዝፈን ጥላቻን መቅበሪያ ።
እድሜያችን አጭር ነው የማለዳ ጤዛ፣
ምነው? ለመታረቅ ሰበባችን በዛ?
ለፍቅር ከሆነ የሁላችን እምነት፣
እንዴትስ ቸገረን አቃተን ሰውነት ?
ምላሳችን ሰላም ልባችን ጥላቻ ፣
አምላክ ይላክልን ማስተዋልን ብቻ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤11🔥5👍1
#ትቀሪያለሽ_ብዬ

ግድየለሽምና  ፥ ከልብ ላፈቀረሽ
ሶስቴ ተቀጣጥረን፥ አራት ጊዜ ቀረሽ::
ዛሬም እንደ ወትሮው፥ትቀርያለሽ ብየ
እድል የላከውን፥ እጣ የሚመስል፤ እጦት ተቀብየ፥
አበባ ሳልቀጥፍ
አልጋ ሳላነጥፍ
ሙታንታየን ሳልጥፍ
በትራስጌየ ላይ ፎቶሽን ሳለጥፍ ፥
ትቀርያለሽ ብየ፥
በመስታውቴ ፊት
ከልብ አስቀይሜ
አንድ እፍኝ ነጭ ሽንኩርት
እንደ ተልባ ቅሜ
አየሩን መርዤ፥ ህዋሴን አክሜ፤
ትቀርያለሽ ብየ፥
ጥፍሬን ሳልከረክም
በመቀስ ሳልንደው፥ የጉያየን ሸክም
ትቀርያለሽ ብየ
ጀንበርን ቀድሜ፤ ቤቴ ተከትቼ
ግቤን ያለ ረዳት፥ በጊዜ መትቼ
የከሸፈ ትውልድ አንሶላ ላይ ትቼ
ልተኛ ስዘጋጅ፥ እፎይ ብየ አርፌ
ከወደ በራፌ
“ ውዴ! ደርሻለሁ፥ የሚል ድምጽሽ መጣ”
ከመግባትሽ በፊት፥ እኔ በየት ልውጣ?
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም
❤25😁13👍1
#አበጀው_በያቸው

አንቺ አትሳቀቂ ሀቁን ንገሪያቸው
እውነት ነወይ? ሲሉሽ እውነት ነው በያቸው
በአንቺ ፍቅር ያጣሁ ማግኘት ያልታደልኩኝ
ትህምርቴን አቁሜ እብድት ያጠናሁኝ
ውበትና ፍቅር አቅሌን አስጥለውኝ
እብደት በሚል ማዕረግ ሰውነት ያጣሁኝ
እኔ ያንቺ  ምርኮ የፍቅርሽ ቁስለኛ
እብድ ነኝ ለሰዎች ያልሆንኩ ወረተኛ
እናም ሲጠይቁሽ ሳትሸማቀቂ
በአንቺ መወፈፌን ለሁሉ አሳውቂ
ልብሴን አሶልቆ በሰፊ ጎዳና
የሚያንከራትቱኝ ያው ፍቅርሽ ነውና
ለሚጠይቁሽም እንዲህ ንገሪያቸው
የአበደው በእኔ ነው አበጀው በያቸው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤16
#በተረት_ላሰላስል

መሬትና ጥንቸል ማኅበር ገቡና
ጽዋ ተጣጡና፤ . . .
ያው እንደዚያው ማለት
ያጋጣሚ አይደለም፤
የተፈጥሮ ባህል፣ የታሪክ ዘይቤ፣ አለው አንድ ቋንቋ፣ አለው አንድ መላ
--- አንተና ልደትህን፣ አንተና ሀገርህን -
በማይረግብ ገመድ፣ ባንድ ላይ የቋጨ፣ ከዐፀደ ዘመን፣ ከቦታ ከለላ
በደም ቃልኪዳኑ ባንድ ያስተሣሠረ፣ በማይታዩ እጆች፣ ባልተሰማ መሀላ፡፡
እና፣
መሬትና ጥንቸል ማኅበር ገቡና
ጽዋ ተጣጡና፤ . . .
መሬት የፈንታዋን ስትከፍል በጽሞና፤ . . .
ያው እንደዚያው ማለት
የሀገርን ህይወት - የብዙኀን ሕይወት - ወዝ ደምና ቅስሙ
ብርታቱ ድካሙ - ተስፋውና ሕልሙ
ከእንቡጥ ወደ አበባ - ከአበባ እስከፍሬ - ለምልመህ ለማየት
በክንዶችህ ብርታት - በአእምሮህ ንቃት -
በኅሊናህ ጥራት - ፀንተህ ለመመልከት
ዘንሟል በዘመናት - ወርዷል እንደዠማ - ፈሷል እንደዥረት፡፡
እና፣
መሬትና ጥንቸል ማኅበር ገቡና፣ ጽዋ ተጣጡና፤
መሬት የፈንታዋን ስትከፍል በጽሞና
እብስ አለች ጥንቸል፣ መክፈል ጠላችና፤ . . .
ያው እንደዚያው ማለት
በስንት ትላንት ነውና ፣ ዘንቦ ወይ ፀህይቶ
በቁር ተኮራምቶ፣ በዋዕይ ገርጥቶ
የበቀለ ዛሬ፣
ትውልድም ነውና ፣ ያያት የቅድመ አያት
የእንዝላት የእንጅላት
የመሠረት ፍሬ፣
በሺ እግሮች ተራምዶ፣ ዛሬን የደረሰ፣ ለእሱ እሱነቱ
በወቅቱ ለወቅቱ
ይኖር ወይ ደካማ፣ የትውልድ እንክርዳድ
አደገኛ አዝመራ፣ ከዚህ ከወጣቱ?
ማነው ይህ መጢቃ፣ የፀደይ ቀን ዘመድ
ወጪቱን እሚሰብር፣ ዕዳውን እሚክድ
ከወገኑ እማይቆም፣ ከወገኑ እማይነድ?
የጫጨ መንፈሱ ፣ የሸፈተ ሀሣቡ የከነፈ ልቡ
ራሱ መነሻው፣ ደሞ ራሱ ግቡ?
እና! . . . .
መሬትና ጥንቸል ማኅበር ገቡና፣ ጽዋ ተጣጡና፤
መሬት የፈንታዋን ስትከፍል በጽሞና
እብስ አለች ጥንቸል፣ መክፈል ጠላችና፤ . . .
ግና ምን ይሆናል?
ብትሮጠው ብትሮጠው፣ ጋራውን ተሻግራ፣ ሜዳውን አቋርጣ
አልቻለችም ከቶ፣ ከዕዳዋ ልትድን ፣
ከመሬት አምልጣ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደበበ ሰይፉ
👍3
#ሰው_ወዳጁን_ሲያጣ

የሚያወጣው ቃል ከአንደበቱ ፤
የውስጡ እረመጥ እሳቱ ፤
ሰው አያስጠጋም እንፏሎቱ ።
የእልህ ነዲድ አካሉን ፣
ገሞራ ሆኖ ሲያነደው ፤
አጥንቶች ነበልባል ሆነው ፤
ህዋሳት በረመጥ ፍመው፤
የዓይኖቹ ስር በዕንባ ቀልተዉ፤
ብቻውን የሚያወራው ፤
ሰው ወዳጁን ሲያጣ ነው ።
ውስጡ አርግዞ እምቅ ቃላት ፤
ተሸክሞ ለዘመናት፤
ሲያስመርጠው ብቸኝነት ፤
ሰዎች በሙሉ ሲፈርዱበት፤
ከንቱ ፍጥረት ብለው ሲያሙት ።
በስጋ ልብስ ተጠቆልሎ ፤
እልፍ ጊዜ ብሶት አዝሎ፤
ተድላ ያለው ለሰው መስሎ፤
ልቡ በሃዘን ተቀጣጥሎ ፤
መኖርን ገፋ ዝም ብሎ ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
  ✍️ ሐና አምታታው
❤8
#ማንስ_ዋስትና_አለው?!!

ለማያውቀው ነገ ፣ ሞትን ተንተርሶ፤
ዋስትና ሳይኖረው ፣ ሰው ከሰው ተናክሶ፤
የሌሊቱን ማለፍ ፣ ሳያውቅ መንጋቱን፤
ዛሬ ይቀምራል ፣ የነገ ክፋቱን።
ለማያውቀው ነገ ፣ ዛሬን እየከፋ፤
ማደሩን ሳይዘው ፣ እየተገፋፋ
የጨለመው አልፎ ፣ ለማየት ማለዳ፤
ማንስ ዋስትና አለው? አንዱ አንዱን ሊጎዳ?
የእኛ ባልሆነ ቀን ፣ በማናውቀው ሌሊት፤
እንዴት ከፍቶ ይለፍ? ጤዛ እኮ ናት ህይወት ።
የቀኑ ሳያንሰው ፣ ሰው ሰውን ለመጣል፤
ሌሊት እንቅልፍ አጥቶ ፣ ለተንኮል ይተጋል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤11👏4👍1