#ማነው_ስልጡን_ታዲያ?
ቀሚስ ገዛሽ አሉ በውድ ሸምተሽ፣
ለምን አለበስሽም? እንደናትሽ ፈትለሽ?
ጭኗ እዝርት አያውቀው ይልሻል ሀገሩ፣
ስለምን አቃተሽ? ከእናት ስር መማሩ?
አለላ ቢሰጡሽ ሰበዝ ገዝተው ዛሬ፣
መስፋቱ ተስኖሽ ትሪ ሞላ ሀገሬ።
አገልግል መሶቡ የእናትሽ ፈጠራ፣
ተዘነጋሽ እንዴ? እንቅጩን እናውራ?
ስንደዶ ተገዝቶ ቢሏት ስፊ ሰፌድ፣
ተጠቀመችበት እሳቱን ለማንደድ።
አንች የከተሜ ልጅ ልውሰድሽ ወይ ገጠር፣
እራስ ፈትሎ መልበስ ከናፈቀሽ ማማር!
ሗላ ቀር ይሏታል ባለሀገሯን ጉብል፣
ከፊት ግን ቀድማለች ተውባ በባህል፣
አንች ገዝተሽ ልበሽ ሰልጥኝ በመግዛት፣
የገጠሯ እህቴን በሙያ ላትቀድሚያት፣
ፈትላ ትለብሳለች ሰፍታ ትበላለች፣
ከተሜዋ እፈሪ ቀድማሽ ሰልጥናለች።
ውብ ኢትዮጵያዊት በኩታ ደምቃለች፣
የእናቷን ጥበብ ውርስ ጠብቃ ዘልቃለች!!!
ያንች ማወቅ ከንቱ ሸምቶ መልበስ ነው፣
እስኪ እንጠያየቅ ማነው የሰለጠነው?!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ቀሚስ ገዛሽ አሉ በውድ ሸምተሽ፣
ለምን አለበስሽም? እንደናትሽ ፈትለሽ?
ጭኗ እዝርት አያውቀው ይልሻል ሀገሩ፣
ስለምን አቃተሽ? ከእናት ስር መማሩ?
አለላ ቢሰጡሽ ሰበዝ ገዝተው ዛሬ፣
መስፋቱ ተስኖሽ ትሪ ሞላ ሀገሬ።
አገልግል መሶቡ የእናትሽ ፈጠራ፣
ተዘነጋሽ እንዴ? እንቅጩን እናውራ?
ስንደዶ ተገዝቶ ቢሏት ስፊ ሰፌድ፣
ተጠቀመችበት እሳቱን ለማንደድ።
አንች የከተሜ ልጅ ልውሰድሽ ወይ ገጠር፣
እራስ ፈትሎ መልበስ ከናፈቀሽ ማማር!
ሗላ ቀር ይሏታል ባለሀገሯን ጉብል፣
ከፊት ግን ቀድማለች ተውባ በባህል፣
አንች ገዝተሽ ልበሽ ሰልጥኝ በመግዛት፣
የገጠሯ እህቴን በሙያ ላትቀድሚያት፣
ፈትላ ትለብሳለች ሰፍታ ትበላለች፣
ከተሜዋ እፈሪ ቀድማሽ ሰልጥናለች።
ውብ ኢትዮጵያዊት በኩታ ደምቃለች፣
የእናቷን ጥበብ ውርስ ጠብቃ ዘልቃለች!!!
ያንች ማወቅ ከንቱ ሸምቶ መልበስ ነው፣
እስኪ እንጠያየቅ ማነው የሰለጠነው?!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤14🤷♀5👍1
#ሰው_ነው_የረቀቀ
ሰው ነው የረቀቀ
ከሜርኩሪ ቬነስ፥ ከጨረቃ ከማርስ
ከፕሉቶ ኔፕቱን፥ ኡራኑስ የላቀ
ከጁፒተር ሳተርን፥ ከጣይ የደመቀ
ባካባቢው ሁሉ እያሸበረቀ፥
ሰው አደገ አወቀ፥
መሬት እንቁላሉን ሰበረ መጠቀ፤
ሰው ዓለምን አዬ....
በጨለማው ቦታ ዶቃ አንፀባራቂ
ውብ ሰማያዊ ኩዋስ፥ ሮዝ አብረቅራቂ።
በተጣራው አየር በነጣው ደመና
ባረንጉዋዴው ባህር ውሃ ተሸፍና ፥
ውብ ሉል ኮከብ ዓለም፥ የጠፈር ላይ ጤዛ፥ የሰው ልጆች እናት፥ የሰው ልጆች ቤዛ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ሰው ነው የረቀቀ
ከሜርኩሪ ቬነስ፥ ከጨረቃ ከማርስ
ከፕሉቶ ኔፕቱን፥ ኡራኑስ የላቀ
ከጁፒተር ሳተርን፥ ከጣይ የደመቀ
ባካባቢው ሁሉ እያሸበረቀ፥
ሰው አደገ አወቀ፥
መሬት እንቁላሉን ሰበረ መጠቀ፤
ሰው ዓለምን አዬ....
በጨለማው ቦታ ዶቃ አንፀባራቂ
ውብ ሰማያዊ ኩዋስ፥ ሮዝ አብረቅራቂ።
በተጣራው አየር በነጣው ደመና
ባረንጉዋዴው ባህር ውሃ ተሸፍና ፥
ውብ ሉል ኮከብ ዓለም፥ የጠፈር ላይ ጤዛ፥ የሰው ልጆች እናት፥ የሰው ልጆች ቤዛ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
👍14
#ቀልባቸው_ተወስዶ
ሞልተሽ በጎዳናው መልተሽ በመንገዱ
ሌሎች ትኩረት ሰጥተው እንዴት ይራመዱ
ቀልባቸው ተወስዶ በውበትሽ ፈዘው
ሁሉም አድናቂሽ ነው ያንቺ ነው ጎዳናው
ስንቱ ተላተመ ስንቱ ሰው ሰመጠ
አረማመድሽ ላይ ትኩረት እየሰጠ
አፍዝ አደንግዝ ነው መልክሽ አስገራሚ
ኬሬ ዳሽ ነው ጆሮሽ ማንንም አትሰሚ
ተመላለሽበት ጎዳናው የግልሽ
ግድ አይሰጥሽ ከቶ ማንም ቢከተልሽ
ጥላሽን ዘርግተሽ ከቤትሽ ውጪና
ሁሉም እግሩ ይጋጭ ልማዱ ነውና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ሞልተሽ በጎዳናው መልተሽ በመንገዱ
ሌሎች ትኩረት ሰጥተው እንዴት ይራመዱ
ቀልባቸው ተወስዶ በውበትሽ ፈዘው
ሁሉም አድናቂሽ ነው ያንቺ ነው ጎዳናው
ስንቱ ተላተመ ስንቱ ሰው ሰመጠ
አረማመድሽ ላይ ትኩረት እየሰጠ
አፍዝ አደንግዝ ነው መልክሽ አስገራሚ
ኬሬ ዳሽ ነው ጆሮሽ ማንንም አትሰሚ
ተመላለሽበት ጎዳናው የግልሽ
ግድ አይሰጥሽ ከቶ ማንም ቢከተልሽ
ጥላሽን ዘርግተሽ ከቤትሽ ውጪና
ሁሉም እግሩ ይጋጭ ልማዱ ነውና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤14👏6🥰3👍2
#ዛሬ_ወዴት_አለ?
ቅኝ አገር መሻማት ዛሬ ወዴት አለ?
የመርከብ ወንበዶች ጊዜዓቸው የታለ?
እንደዱሮ አይሆንም
ታሪኩ ቢወራ ሃተታው ቢለቀም
እንደጥንቱ አይሆንም።
መሰሉም ቢመጣ ጥቂት ተለውጦ
«ታሪክ ተደገመ!»
ይባላል ሲጠፋ ጊዜ እየታመመ።
በራሱ ከረጢት ገብቶ ተጠቅልሎ
ለብቻው ሲደበቅ ሸሽቶ ተገልሎ
ሁሉም ይለወጣል ጊዜ እየቆጠረ
አንዳንዴም ይረሳል እየተሰወረ።
ጨረቃ እንደክብሪት ፀሃይ እንደሻማ
በርተው ይጠፋሉ
ተቃጥለው ያልቃሉ።
ሰማይ ተቀዳዶ እንዳሮጌ ሸማ
ከዋክብት አንድ ባንድ ወድቀው ተንጠባጥበው
የባህርይ ፍጥረቶች እንዳልነበር ሆነው
ሲመጣ ጊዜያቸው
ያልፋሉ ጨልመው።
የማይቀር ምን አለ?
የማይቀር ምን አለ?
ሞትም ሙት ይሆናል የሚሞት ሲጠፋ
ጊዜም እየገፋ
የሚገፋው ሲያጣ ይሆናል የጠፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረ ክርስቶስ ደስታ።
ቅኝ አገር መሻማት ዛሬ ወዴት አለ?
የመርከብ ወንበዶች ጊዜዓቸው የታለ?
እንደዱሮ አይሆንም
ታሪኩ ቢወራ ሃተታው ቢለቀም
እንደጥንቱ አይሆንም።
መሰሉም ቢመጣ ጥቂት ተለውጦ
«ታሪክ ተደገመ!»
ይባላል ሲጠፋ ጊዜ እየታመመ።
በራሱ ከረጢት ገብቶ ተጠቅልሎ
ለብቻው ሲደበቅ ሸሽቶ ተገልሎ
ሁሉም ይለወጣል ጊዜ እየቆጠረ
አንዳንዴም ይረሳል እየተሰወረ።
ጨረቃ እንደክብሪት ፀሃይ እንደሻማ
በርተው ይጠፋሉ
ተቃጥለው ያልቃሉ።
ሰማይ ተቀዳዶ እንዳሮጌ ሸማ
ከዋክብት አንድ ባንድ ወድቀው ተንጠባጥበው
የባህርይ ፍጥረቶች እንዳልነበር ሆነው
ሲመጣ ጊዜያቸው
ያልፋሉ ጨልመው።
የማይቀር ምን አለ?
የማይቀር ምን አለ?
ሞትም ሙት ይሆናል የሚሞት ሲጠፋ
ጊዜም እየገፋ
የሚገፋው ሲያጣ ይሆናል የጠፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረ ክርስቶስ ደስታ።
❤10
#አባ_ጨጓሬ_ነው
በእኔና አንቺ ፍቅር በእኔና አንች አብሮነት
ተፈጥሮም ያዜማል እንኳንስ አንደበት
አበቦች ፈንድቀው ንቦች ማር ቢሰሩ
ዜመኜች በዋሽንት ምን ቢያንጎራጉሩ
በእኔና አንቺ ፍቅር ሀሳብ መነሻ ነው
የደራሲው ብዕር ቅኔን የሚቀኘው
ፀሀይ ከጨረቃ የሚፈራረቁ
በተራ በተራ ዘወትር የሚደምቁ
ሳጋንን አይደለም እመኝኝ ለኛ ነው
ህይወት ያለ ፍቅር ከቶ ጣዕምም የለው
ሁሉም የተሰራው እጅግ ውብ የሆነው
ፍቅርን ለማጀብ ለእኛ ደስታ ነው!!!
ስነግርሽ እመኝኝ ውዴ አለጥርጥር
አባ ጨጓሬ ነው ዓለም ያለፍቅር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
በእኔና አንቺ ፍቅር በእኔና አንች አብሮነት
ተፈጥሮም ያዜማል እንኳንስ አንደበት
አበቦች ፈንድቀው ንቦች ማር ቢሰሩ
ዜመኜች በዋሽንት ምን ቢያንጎራጉሩ
በእኔና አንቺ ፍቅር ሀሳብ መነሻ ነው
የደራሲው ብዕር ቅኔን የሚቀኘው
ፀሀይ ከጨረቃ የሚፈራረቁ
በተራ በተራ ዘወትር የሚደምቁ
ሳጋንን አይደለም እመኝኝ ለኛ ነው
ህይወት ያለ ፍቅር ከቶ ጣዕምም የለው
ሁሉም የተሰራው እጅግ ውብ የሆነው
ፍቅርን ለማጀብ ለእኛ ደስታ ነው!!!
ስነግርሽ እመኝኝ ውዴ አለጥርጥር
አባ ጨጓሬ ነው ዓለም ያለፍቅር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤5🤷♀3🔥3🎃1
#ተይ_ይግባሽ_ተመለሽ
ነፍሴ እስከሚወጣ ~ እኔ እየወደድኩሽ ፤
በቃኝ ህይወት ብሎ ~ ካመረረ ልብሽ ፤
ለመሄድ ወስኖ ~ ከቆረጠ አንጀትሽ ፤
የኔ ልብ ቆስሎ ~ ሆዴ ካዘነብሽ ፤
እመኝኝ የኔ ዉድ ~ አይቀናም መንገድሽ ።
የተዳፈነ እሳት ~ ፍቅር እኮ ህመም ነው ፤
ቆስቋሹን ሳይፈልግ ~ ድንገት ነው ሚነደዉ፤
ለተፈቃሪ እንጂ ~ ላፍቃሪ ከባድ ነው ።
ያሳለፍነው ጊዜ ~ ያሁሉ ትዝታ ፤
ላያልቅ ተነግሮ ~ በቀለም ጠብታ ፤
ሊያለያየን ከቶ ~ እንደምን በረታ ።
አስታወስሽ የኔ አለም !
ያኔ ስንገናኝ ~ እድሜያችን ነዉ ለጋ ፤
የወደፊቱን ህልም ~ህይወት ስናወጋ ፤
በፍፁም ሳንተኛ ~ እነዴት እንደነጋ ።
ይቅር ታዉቂ እንደሆን ~ ልማፀንሽ በእንባ ፤
አሉባልታ ወሬ ~ ላይጠቅመን ላይረባ ፤
ክፉንና ደጉን ~ ችለን እንግባባ ።
የማይዘልቅ ፍቅር ~ አጉል አስለምደሽ ፤
ይኸው አቅሌን ጥየ ~ ተንከራተትኩልሽ ፤
ልቤንም ወስደሽዉ ~ ሌላ እንዳላይ አርገሽ፤
እንደዘጋሽዉ ነው ~ እንኪ ግቢ ከፍተሽ ።
የዚህ ሁሉ ሮሮ ~ ምክንያቴ አንቺ ነሽ ፤
እንዲህ ስለምንሽ ~ ተይ ይግባሽ ተመለሽ ።
እኔም ሳልጀማምር ~ አንቺም ሳትጀምሪ ፤
ሳይርቅ እንታረቅ ~ እንሁን አስተማሪ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ሐና
ነፍሴ እስከሚወጣ ~ እኔ እየወደድኩሽ ፤
በቃኝ ህይወት ብሎ ~ ካመረረ ልብሽ ፤
ለመሄድ ወስኖ ~ ከቆረጠ አንጀትሽ ፤
የኔ ልብ ቆስሎ ~ ሆዴ ካዘነብሽ ፤
እመኝኝ የኔ ዉድ ~ አይቀናም መንገድሽ ።
የተዳፈነ እሳት ~ ፍቅር እኮ ህመም ነው ፤
ቆስቋሹን ሳይፈልግ ~ ድንገት ነው ሚነደዉ፤
ለተፈቃሪ እንጂ ~ ላፍቃሪ ከባድ ነው ።
ያሳለፍነው ጊዜ ~ ያሁሉ ትዝታ ፤
ላያልቅ ተነግሮ ~ በቀለም ጠብታ ፤
ሊያለያየን ከቶ ~ እንደምን በረታ ።
አስታወስሽ የኔ አለም !
ያኔ ስንገናኝ ~ እድሜያችን ነዉ ለጋ ፤
የወደፊቱን ህልም ~ህይወት ስናወጋ ፤
በፍፁም ሳንተኛ ~ እነዴት እንደነጋ ።
ይቅር ታዉቂ እንደሆን ~ ልማፀንሽ በእንባ ፤
አሉባልታ ወሬ ~ ላይጠቅመን ላይረባ ፤
ክፉንና ደጉን ~ ችለን እንግባባ ።
የማይዘልቅ ፍቅር ~ አጉል አስለምደሽ ፤
ይኸው አቅሌን ጥየ ~ ተንከራተትኩልሽ ፤
ልቤንም ወስደሽዉ ~ ሌላ እንዳላይ አርገሽ፤
እንደዘጋሽዉ ነው ~ እንኪ ግቢ ከፍተሽ ።
የዚህ ሁሉ ሮሮ ~ ምክንያቴ አንቺ ነሽ ፤
እንዲህ ስለምንሽ ~ ተይ ይግባሽ ተመለሽ ።
እኔም ሳልጀማምር ~ አንቺም ሳትጀምሪ ፤
ሳይርቅ እንታረቅ ~ እንሁን አስተማሪ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ሐና
❤8😢4
#ባይጨንቀው_አይደለም
ካብ ጸንቶ የቆመው በመደጋገፍ ነው
አንዱ ደንጋይ አንዱን ስለወደደው ነው
አንዱ ከተነካ ሁሉም ስለሚፈርስ
ከስር ያለው ድንጋይ ችሎ በመታገስ
ሌላውን ከላዩ ያነገሰው አዝሎ
መሰረት የሆነው ከስር ተንከባሎ
ከላይ የተጫነው ባለብዙ መንጋ
እሱ ከተነካ ቢያውቅ እንደሚንጋጋ
ችሎ ማደር መርጦ ለሌሎች እርጋታ
ሸክሙ እየከበደው ቢመርጥም ዝምታ
ባይጨንቀው አይደለም ከስር ተቀምጦ
በጋራ መኖርን ቢያስቀድም ነው መርጦ
አንተ ከላይ ሆነህ የስሩን ብትረግጥም
ያለመሰረትህ አንድ ቀን አታድርም!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
ካብ ጸንቶ የቆመው በመደጋገፍ ነው
አንዱ ደንጋይ አንዱን ስለወደደው ነው
አንዱ ከተነካ ሁሉም ስለሚፈርስ
ከስር ያለው ድንጋይ ችሎ በመታገስ
ሌላውን ከላዩ ያነገሰው አዝሎ
መሰረት የሆነው ከስር ተንከባሎ
ከላይ የተጫነው ባለብዙ መንጋ
እሱ ከተነካ ቢያውቅ እንደሚንጋጋ
ችሎ ማደር መርጦ ለሌሎች እርጋታ
ሸክሙ እየከበደው ቢመርጥም ዝምታ
ባይጨንቀው አይደለም ከስር ተቀምጦ
በጋራ መኖርን ቢያስቀድም ነው መርጦ
አንተ ከላይ ሆነህ የስሩን ብትረግጥም
ያለመሰረትህ አንድ ቀን አታድርም!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
❤15👍7👏3
#ደኀና_ነው_ማለት_ነው
የፊቱን ውሃ ልክ ፂሙን አፈራርሶት፣
ጠይም ወዙ ነጥፎ፣ መልኩን ዳዋ ውጦት፣
ፀጉሩን አጎፍሮ፣ ከንፈሩን አጥቁሮ፣
ስስ ጭስ ተከልሎ፣ ብርጭቆ ስር አድሮ፣
የማይነቅዝ እህህ ለቀለቡ ሰፍሮ፣
ቤቱን ይቆልፋል::
ሰንብቶ ይወጣል
እግሩ ጥሎት ሲሄድ እየተከተለ፣
አካላቱን አዝሎ ዝግ፣ ቀስ እያለ፣
ይራመዳል አሉ በአበቦች መሐል
አብረን በተከልነው
ደኀና ነው ማለት ነው::
ትዝታ እየሳመ፣ ትላንትናን አቅፎ፣
ጨለማ ደርቦ፣ ደጃፉን ቆልፎ፣
ናፍቆት እየኳለ፣ ነፍሱን በሹል ሲነቅስ፣
ዘመን ሲሻገረው ሳይስቅ ሳያለቅስ፣
ይሉኛል አየነው
ደህና ነው ማለት ነው::
ማለዳ፣ ማለዳ ለአፉ ቡና አያስቀር፤
አከለበት እንጂ ለልቡ አዲስ ምሳር
አሁንም ያን ግጥም በቃሉ ይወጣል፣
አስር ሰዓት ሲሆን እደጅ ይቀመጣል፣
"በሚስጥር ቅበሪኝ" ቴፑን ያጫዉታል፣
ህልሙን ብቻ ትቷል!
ዛሬም ቡኒ ሹራብ ከጥቁር ሱሪ ጋር፤
ምን ገላው እንደኔ ቢከዳው ባያምር
ይለብሳል ይሉኛል ያኔ እንደምወደው
ደኀና ነው ማለት ነው::
ለራስ ለዘመዱ ያላነሰው ጉልበት
ልቡን በቀን በሌት ለማድቀቅ፣ ለማንከት
አጥቶት ለግዑዙ አውርዶ ለመስበር
ግድግዳው መሐል ላይ ከቆመ ምስሌ ጋር
ፊትለፊት አንጋጦ ይቆማል ውሎ አዳር
ናፈቀችኝ ይላል፣
ደኀና ነው ማለት ነው፤
ቃላት ይበቁታል::
ሴት ህፃን ልጅ አይቶ
ቶሎ አይሻገርም ሲወጣ ሲገባ
አይኑን ይጋርዳል
ህልሙን ገድሎ ሲቀብር ያልወጣለት እንባ
ሲነጋ ትኩስ ቁስል ለራሱ እየተካ፣
አቅሙን እዬፈጬ፣ ቅስሙን እየከካ፣
ነፍሱን እያረደ፤ ግን አለ እንደ ሰው፣
ሞት ልውስ ክህደት ፈትፍቼም ባጎርሰው፤
ደኀና ነው ማለት ነው::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ማህደር ወሰኑ
የፊቱን ውሃ ልክ ፂሙን አፈራርሶት፣
ጠይም ወዙ ነጥፎ፣ መልኩን ዳዋ ውጦት፣
ፀጉሩን አጎፍሮ፣ ከንፈሩን አጥቁሮ፣
ስስ ጭስ ተከልሎ፣ ብርጭቆ ስር አድሮ፣
የማይነቅዝ እህህ ለቀለቡ ሰፍሮ፣
ቤቱን ይቆልፋል::
ሰንብቶ ይወጣል
እግሩ ጥሎት ሲሄድ እየተከተለ፣
አካላቱን አዝሎ ዝግ፣ ቀስ እያለ፣
ይራመዳል አሉ በአበቦች መሐል
አብረን በተከልነው
ደኀና ነው ማለት ነው::
ትዝታ እየሳመ፣ ትላንትናን አቅፎ፣
ጨለማ ደርቦ፣ ደጃፉን ቆልፎ፣
ናፍቆት እየኳለ፣ ነፍሱን በሹል ሲነቅስ፣
ዘመን ሲሻገረው ሳይስቅ ሳያለቅስ፣
ይሉኛል አየነው
ደህና ነው ማለት ነው::
ማለዳ፣ ማለዳ ለአፉ ቡና አያስቀር፤
አከለበት እንጂ ለልቡ አዲስ ምሳር
አሁንም ያን ግጥም በቃሉ ይወጣል፣
አስር ሰዓት ሲሆን እደጅ ይቀመጣል፣
"በሚስጥር ቅበሪኝ" ቴፑን ያጫዉታል፣
ህልሙን ብቻ ትቷል!
ዛሬም ቡኒ ሹራብ ከጥቁር ሱሪ ጋር፤
ምን ገላው እንደኔ ቢከዳው ባያምር
ይለብሳል ይሉኛል ያኔ እንደምወደው
ደኀና ነው ማለት ነው::
ለራስ ለዘመዱ ያላነሰው ጉልበት
ልቡን በቀን በሌት ለማድቀቅ፣ ለማንከት
አጥቶት ለግዑዙ አውርዶ ለመስበር
ግድግዳው መሐል ላይ ከቆመ ምስሌ ጋር
ፊትለፊት አንጋጦ ይቆማል ውሎ አዳር
ናፈቀችኝ ይላል፣
ደኀና ነው ማለት ነው፤
ቃላት ይበቁታል::
ሴት ህፃን ልጅ አይቶ
ቶሎ አይሻገርም ሲወጣ ሲገባ
አይኑን ይጋርዳል
ህልሙን ገድሎ ሲቀብር ያልወጣለት እንባ
ሲነጋ ትኩስ ቁስል ለራሱ እየተካ፣
አቅሙን እዬፈጬ፣ ቅስሙን እየከካ፣
ነፍሱን እያረደ፤ ግን አለ እንደ ሰው፣
ሞት ልውስ ክህደት ፈትፍቼም ባጎርሰው፤
ደኀና ነው ማለት ነው::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ማህደር ወሰኑ
😢5❤2💯2
#የእኛ_ድንቁርና
አሁን በዚህ ዘመን አሁን በዚህ ግዜ፣
ዘር የመቁጠር ልክፍት የማበድ አባዜ፣
የዓለም ስልጣኔ ከሰማይ ላይ ደርሷል፣
የእኛ ድንቁርና እንደ አዲስ ታድሷል!
ሰው መሆን ተንቆ፣
ትልቅ ክብር ወድቆ፣
በዘር ብረት ምጣድ ሀገሩ ሲታመስ፣
የተማረው ሁሉ እያደር ሲረክስ፣
ምሁር ለምርምር ቆሞ ካላደረ፣
ግዜውን ካጠፋ ዘር እየቆጠረ፣
የትኛው ትውልድ ነው ሀገር የሚሰራ፣
ሁሉም ሰው ደንዝዟል በጅል ዘር ቆጠራ፣
ከዓለም ተነጥለን ወደ ሗላ ቀርተን፣
እስከመቼ ድረስ በዘር ተከፋፍለን?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
አሁን በዚህ ዘመን አሁን በዚህ ግዜ፣
ዘር የመቁጠር ልክፍት የማበድ አባዜ፣
የዓለም ስልጣኔ ከሰማይ ላይ ደርሷል፣
የእኛ ድንቁርና እንደ አዲስ ታድሷል!
ሰው መሆን ተንቆ፣
ትልቅ ክብር ወድቆ፣
በዘር ብረት ምጣድ ሀገሩ ሲታመስ፣
የተማረው ሁሉ እያደር ሲረክስ፣
ምሁር ለምርምር ቆሞ ካላደረ፣
ግዜውን ካጠፋ ዘር እየቆጠረ፣
የትኛው ትውልድ ነው ሀገር የሚሰራ፣
ሁሉም ሰው ደንዝዟል በጅል ዘር ቆጠራ፣
ከዓለም ተነጥለን ወደ ሗላ ቀርተን፣
እስከመቼ ድረስ በዘር ተከፋፍለን?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
👍15❤3👎1
በተሳልኹት (ሥ)ስለት
ምነው ዛሬ?
"ምኑ ማሬ?"
ሳቅሕ በዛ...
"ልትሄጅ አይደል እንደዋዛ?"
እና ያስቃል?
"እሱንማ ልብሽ ያውቃል"
ይሄ ማሳቁን?
"ከልቤ ሥር ያለው ሩቁን"
እንደምትወድደኝ ነበር 'ሚገባኝ
"ምኑ ሆነና እኔስ 'ሚያስነባኝ?"
ታዲያ እኮ ጥርስሕ.....
"ኦ! ልክ ነሽ አንቺ ፡ ለካ ይሄ ሳቅ ነው..
አታወሳስበው ኸረ ምንድነው?
"እኔም ያወቅኹት ፡ካንቺው እኩል ነው ።
እ?.."እናስይዝ ሰክረሃል!"
"ብዙ ገጽ ተቀድዷል ከሕይወቴ መሃል!"
ተው አትንካው ቁስሌን "
"አያመኝ ይመስል የኔ አልሽው ሥጋሽን?
እህ...
"ተይው.. ቦታዬ እንደጠፋኝ ፡ አታውቂም ዋጋሽን!"
እና ..ወዴት ትሔድ ?፡
"እዚሕ ጋር ይቆረጥ ይሄ ከንቱ ገመድ?"
ፍቅር ነበር ከንቱ?
"ከነዘር ማንዘሩ ከነምን ጅላቱ!!"
" ካልሽ እንግዲሕ......
ቻው! ቢያስደነግጥም!!"
"አንቺ ካደረግሽው ፡ በፍጹም አበልጥም!"
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ብጽዓት ስዩም
ምነው ዛሬ?
"ምኑ ማሬ?"
ሳቅሕ በዛ...
"ልትሄጅ አይደል እንደዋዛ?"
እና ያስቃል?
"እሱንማ ልብሽ ያውቃል"
ይሄ ማሳቁን?
"ከልቤ ሥር ያለው ሩቁን"
እንደምትወድደኝ ነበር 'ሚገባኝ
"ምኑ ሆነና እኔስ 'ሚያስነባኝ?"
ታዲያ እኮ ጥርስሕ.....
"ኦ! ልክ ነሽ አንቺ ፡ ለካ ይሄ ሳቅ ነው..
አታወሳስበው ኸረ ምንድነው?
"እኔም ያወቅኹት ፡ካንቺው እኩል ነው ።
እ?.."እናስይዝ ሰክረሃል!"
"ብዙ ገጽ ተቀድዷል ከሕይወቴ መሃል!"
ተው አትንካው ቁስሌን "
"አያመኝ ይመስል የኔ አልሽው ሥጋሽን?
እህ...
"ተይው.. ቦታዬ እንደጠፋኝ ፡ አታውቂም ዋጋሽን!"
እና ..ወዴት ትሔድ ?፡
"እዚሕ ጋር ይቆረጥ ይሄ ከንቱ ገመድ?"
ፍቅር ነበር ከንቱ?
"ከነዘር ማንዘሩ ከነምን ጅላቱ!!"
" ካልሽ እንግዲሕ......
ቻው! ቢያስደነግጥም!!"
"አንቺ ካደረግሽው ፡ በፍጹም አበልጥም!"
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ብጽዓት ስዩም
👏10❤2👍2💯1
“ለሱስ እንዳልሆነ የወደድኹሽ አንቺን "
ትፍረደኝ ሙዚቃ ፡ ይፍረደኝ ጥላሁን»
እንዳልልሽ ፈራኹ
እንዳልልሽ ኮራኹ
በነፋስ በወንዙ
በቅጠል ሽውታ
በጉዳን እርምጃ
የመሬት ንቅንቅታ
በአድባሩ በአውጋሩ
በመስኩ በጎራው
በዜማ በግጥሙ
በሐዘን በጭፈራው
አንቺን እያሰብኹኝ
አንቺን እየጠራኹ
ራሴን ሥለረሳኹ
ነፍሴን ስላሳሳኹ
ፍራሃት እና ኩራት እያደናገረኝ
ከቃላቴ መሃል ቃል እየቸገረኝ
እወሳሰባለኹ ፡ እጠማዘዛለኹ
እኔን እያሰስኹኝ ፡ ዓንቺን እይዛለኹ
ብቻ ሱስ አይደለም ፡ ይልቃል ከሱስም
ሕይወት ተኩል ሞላ ፡ የኖርኹት ባንቺ ሥም ።
ይኼንንም ቢሆን
እንዳልነግርሽ ፈራኹ
እንዳልነግርሽ ኮራኹ
አንቺን ሆኜ እንዳላልቅ
ነቁጥ እኔ ላስቀር...
ብትችይ አስተምሪኝ...
በመጠኑ ማፍቀር ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ካፒቴን ግራ
ትፍረደኝ ሙዚቃ ፡ ይፍረደኝ ጥላሁን»
እንዳልልሽ ፈራኹ
እንዳልልሽ ኮራኹ
በነፋስ በወንዙ
በቅጠል ሽውታ
በጉዳን እርምጃ
የመሬት ንቅንቅታ
በአድባሩ በአውጋሩ
በመስኩ በጎራው
በዜማ በግጥሙ
በሐዘን በጭፈራው
አንቺን እያሰብኹኝ
አንቺን እየጠራኹ
ራሴን ሥለረሳኹ
ነፍሴን ስላሳሳኹ
ፍራሃት እና ኩራት እያደናገረኝ
ከቃላቴ መሃል ቃል እየቸገረኝ
እወሳሰባለኹ ፡ እጠማዘዛለኹ
እኔን እያሰስኹኝ ፡ ዓንቺን እይዛለኹ
ብቻ ሱስ አይደለም ፡ ይልቃል ከሱስም
ሕይወት ተኩል ሞላ ፡ የኖርኹት ባንቺ ሥም ።
ይኼንንም ቢሆን
እንዳልነግርሽ ፈራኹ
እንዳልነግርሽ ኮራኹ
አንቺን ሆኜ እንዳላልቅ
ነቁጥ እኔ ላስቀር...
ብትችይ አስተምሪኝ...
በመጠኑ ማፍቀር ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ካፒቴን ግራ
🥰8❤7
#ከነገ_ትናንቶች!
እርግጥ ነው ቢያስፈራ ፤
የማያውቁት ቦታ ፤ የማይደርሱበት ቃል
ምን ቆርጠው ቢነሱ ፤ ሲጠጉት ይርቃል
ምን ተግተው ቢያልሙት ፤ ሳይነቁት ይጠልቃል
ብቻ ግን ብቻ ግን....
"ሞተው ሞትን ሲያጡት" ፤ከሁሉም ይጨንቃል..!!
ብቻ እዚሁ ከርሟል
ልቤ ላይሞት ታሟል
ላይሽር አገግሟል
እየቆሰልኹ ነው ፡ የማይደማ ቁስል
እያቀለምኹ ነው ፡ ሁሌ ግማሽ ምስል
አለማለቅማ ፡ሰው ሆኖ ወግ ነበር ፡
መንገድ ማጣትማ ፡ ላሳሽ ራቱ ነበር
ላይድኑ ላይሞቱ ፡ አሻል መሰባበር
የማንኳኳት ፍርጃ ፡ ያልተፈጠረ በር
ይኼን ይኼን ብቻ!
አሸክሞኝ በቃው
ሞቶ ቢሆን እንጂ..
ዝገት አቅፎ ሲኖር ፡
ወርቅ እቃው ውድ እቃው
አንድ የሞት ጭላንጭል ፡ ወይም የሕይወት በር
አሻግሮ መጠቆም ፡ ለእግዜ'ር ቀልድ አልነበር?
ግን እሱ ይኼን ብቻ!
አሸክሞኝ በቃው!
ዝገት አቅፎ ሲኖር
ወርቅ እቃው ውድ እቃው
ሸክላ ሆኖ ላይርስ
ላይሞት ሲፈራርስ
እፍፍ ያለበት ጭቃው
ዝም ብሎ እንዴት ያያል
መልክ ላይሰጣቸው?
እሳቱን ከነፋስ ለምን ይለያያል?!!
ብቻ እዚሁ ከርሟል
ልቤ ላይሞት ታሟል
ላይሽር አገግሟል ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
እርግጥ ነው ቢያስፈራ ፤
የማያውቁት ቦታ ፤ የማይደርሱበት ቃል
ምን ቆርጠው ቢነሱ ፤ ሲጠጉት ይርቃል
ምን ተግተው ቢያልሙት ፤ ሳይነቁት ይጠልቃል
ብቻ ግን ብቻ ግን....
"ሞተው ሞትን ሲያጡት" ፤ከሁሉም ይጨንቃል..!!
ብቻ እዚሁ ከርሟል
ልቤ ላይሞት ታሟል
ላይሽር አገግሟል
እየቆሰልኹ ነው ፡ የማይደማ ቁስል
እያቀለምኹ ነው ፡ ሁሌ ግማሽ ምስል
አለማለቅማ ፡ሰው ሆኖ ወግ ነበር ፡
መንገድ ማጣትማ ፡ ላሳሽ ራቱ ነበር
ላይድኑ ላይሞቱ ፡ አሻል መሰባበር
የማንኳኳት ፍርጃ ፡ ያልተፈጠረ በር
ይኼን ይኼን ብቻ!
አሸክሞኝ በቃው
ሞቶ ቢሆን እንጂ..
ዝገት አቅፎ ሲኖር ፡
ወርቅ እቃው ውድ እቃው
አንድ የሞት ጭላንጭል ፡ ወይም የሕይወት በር
አሻግሮ መጠቆም ፡ ለእግዜ'ር ቀልድ አልነበር?
ግን እሱ ይኼን ብቻ!
አሸክሞኝ በቃው!
ዝገት አቅፎ ሲኖር
ወርቅ እቃው ውድ እቃው
ሸክላ ሆኖ ላይርስ
ላይሞት ሲፈራርስ
እፍፍ ያለበት ጭቃው
ዝም ብሎ እንዴት ያያል
መልክ ላይሰጣቸው?
እሳቱን ከነፋስ ለምን ይለያያል?!!
ብቻ እዚሁ ከርሟል
ልቤ ላይሞት ታሟል
ላይሽር አገግሟል ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤9👏4
#አንገትህን_ስበር!!
አንተ ቤተ ሰሪ ፎቅ አብቃይ ባለ ብር
ድንጋይ በራስህ ላይ በጌጥ የምትከምር
ምቾቱ ውበቱ አቤት ገጹ ሲያምር
በግርማ የቆመ በኩራት በክብር
ግና ምን ያደረጋል እድሜህን አይጨመር
ከቶ ዝንፍ አይልም ከተሰጠህ ስፍር!!!
ቀድመህ ሳትገነባው የሰማዩን እልፍኝ
በምድሩ አትጨርሰው በማይጠቅም ቋጥኝ
ቤት መስራት ደስ ይላል ዘመኖ ለመኖር
ችግሩ ሞት አለ ለሁሉም የማይቀር!!!
አንተ ቤተ ሰሪ ህንጻህ አሸብርቋል
ከድሆች ከፍ ብሎ በጌጣጌጥ ደምቋል
ይሁን ይመርበት ሀብትህን ይመስክር
ከድሆች ቤት በላይ ደንጋዮችን ከምር
በሞት ግን እኩል ነህ አንገትህን ስበር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
አንተ ቤተ ሰሪ ፎቅ አብቃይ ባለ ብር
ድንጋይ በራስህ ላይ በጌጥ የምትከምር
ምቾቱ ውበቱ አቤት ገጹ ሲያምር
በግርማ የቆመ በኩራት በክብር
ግና ምን ያደረጋል እድሜህን አይጨመር
ከቶ ዝንፍ አይልም ከተሰጠህ ስፍር!!!
ቀድመህ ሳትገነባው የሰማዩን እልፍኝ
በምድሩ አትጨርሰው በማይጠቅም ቋጥኝ
ቤት መስራት ደስ ይላል ዘመኖ ለመኖር
ችግሩ ሞት አለ ለሁሉም የማይቀር!!!
አንተ ቤተ ሰሪ ህንጻህ አሸብርቋል
ከድሆች ከፍ ብሎ በጌጣጌጥ ደምቋል
ይሁን ይመርበት ሀብትህን ይመስክር
ከድሆች ቤት በላይ ደንጋዮችን ከምር
በሞት ግን እኩል ነህ አንገትህን ስበር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ
👍8❤3🔥1👏1
እኛ ነን ከልካላ
እኛ ነን ነጠላ
ፍቅሬ ፍቅርማ
ነው።
ነበረ።
ጥላ።
እኛ ነን ያጠፋን
ያላደግንበትን ምን ስንል ገነባን?
(እማናድርበት ቤት ምን ስንል አመሸን)
ለመሄድ ነው መምጣት
ለማጣት ነው ማግኘት
ለመልቀቅ ነው መያዝ
ለመድከም ነው መሮጥ
ለማቅለል ነው መድረስ
ለመሞት ነው መኖር
ይኼን ልቤ አውቋል
ፍቅርም እንደ መንገድ ለካ ሲኬድ ያልቃል…
እንደ ተረት ተረት ሲሄዱ ሲሄዱ
እንደ ህልም ሩጫ እንደመሳደዱ
ቢረዝም ምን ነበር የፍቅር መንገዱ፤
እጣን እየጤሰ
ፍቅራአዲስ ስትዘፍን
ዝም ተባብለን
ልባችን ሲዘፍን፤
ንፍቀ ክበብ ኾነን
ጨረቃ እና ሰማይ
ዓለም ቢያልፍ ምን ነበር
ዓይኔ ይኼን ሳያይ፤
ይኼን ማለት ሳልችል
ይኼን መኾን ሳላውቅ
ሳይተነተነኝ ፍቅር እንደሚያልቅ
ምፅዐት ሊመጣ ምንበረ ባይርቅ።
ላልነበርከኝ ጊዜ
ላልነበርኩህ ሰዐት፥ተመልሼ ሳዝን
ከትናንት ከዛሬ፥ነገን ስመታትር
ማለቅ እንዲቀድም አላወኩም ነበር።
ፍቅር ጨርቅ እንደኾን
ፍቅር ጥዑም ሰንደል
እሱ እንደሚፀና ልብ ሸርፎ እንደገል
መቼም አንማርም ሳንገባ ገደል
እንደ አገሬ ሰው እንዳልገላገል
ፍቅር መርጦ ሞተ።
መርጦ ግን አይገድል…።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳምራዊት ውለታው
እኛ ነን ነጠላ
ፍቅሬ ፍቅርማ
ነው።
ነበረ።
ጥላ።
እኛ ነን ያጠፋን
ያላደግንበትን ምን ስንል ገነባን?
(እማናድርበት ቤት ምን ስንል አመሸን)
ለመሄድ ነው መምጣት
ለማጣት ነው ማግኘት
ለመልቀቅ ነው መያዝ
ለመድከም ነው መሮጥ
ለማቅለል ነው መድረስ
ለመሞት ነው መኖር
ይኼን ልቤ አውቋል
ፍቅርም እንደ መንገድ ለካ ሲኬድ ያልቃል…
እንደ ተረት ተረት ሲሄዱ ሲሄዱ
እንደ ህልም ሩጫ እንደመሳደዱ
ቢረዝም ምን ነበር የፍቅር መንገዱ፤
እጣን እየጤሰ
ፍቅራአዲስ ስትዘፍን
ዝም ተባብለን
ልባችን ሲዘፍን፤
ንፍቀ ክበብ ኾነን
ጨረቃ እና ሰማይ
ዓለም ቢያልፍ ምን ነበር
ዓይኔ ይኼን ሳያይ፤
ይኼን ማለት ሳልችል
ይኼን መኾን ሳላውቅ
ሳይተነተነኝ ፍቅር እንደሚያልቅ
ምፅዐት ሊመጣ ምንበረ ባይርቅ።
ላልነበርከኝ ጊዜ
ላልነበርኩህ ሰዐት፥ተመልሼ ሳዝን
ከትናንት ከዛሬ፥ነገን ስመታትር
ማለቅ እንዲቀድም አላወኩም ነበር።
ፍቅር ጨርቅ እንደኾን
ፍቅር ጥዑም ሰንደል
እሱ እንደሚፀና ልብ ሸርፎ እንደገል
መቼም አንማርም ሳንገባ ገደል
እንደ አገሬ ሰው እንዳልገላገል
ፍቅር መርጦ ሞተ።
መርጦ ግን አይገድል…።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ሳምራዊት ውለታው
❤4💯4🤔1
የማለዳ ወፌ የምሽት ጀንበሬ፣
ዜማሽ መፅናኛየ መሄድሽ ችግሬ።
ዉቧ ጨረቃየ የምሽት ድባቤ፣
የህይወት ስኬቴ ምግባረ ሐሳቤ፣
መሆንሽን እያወቅሽ የልቤ ከተማ፣
የከናፍሬ ጣዓም ያ'ንደበቴ ዜማ፣
ለምን ረሳሽኝ በጥልቅ ባህር ቆሜ?
ፍቅርሽን እያለምኩ በፍቅር ዓለሜ።
ዜማሽን ሳልሰማ እነቃ ይመስል፣
እዉላለሁ አድራለሁ አ'ንችን ሳንሰላስል።
እድሜየ ባክኖ ዘመኔ ጨቅይቶ፣
ትዝታሽ ብቻዉን ከእኔ ጋር ቆይቶ።
ቆይቶ...ቆይቶ...ቆይቶ...ቆይቶ፣
ድንገት አስነቅቶ...
''አይዞህ አትተክዝ በፍቅር ጠብቃት፣
ባ'ካል ብትለያት በመንፈስ አትራቃት፣
አንተ እንደምትወዳት እሷም ፍቅር አላት''፣
እያለ ያፅናናኛል በፅኑ ዉብ ቃላት።
እኔ የምለዉ ግን እኔ አንችን ወድጄ፣
ጨርቄን ማቄን ጥየ እርቃን ተሰድጄ፣
በፍቅርሽ በርሬ በፍቅርሽ አብጄ፣
ድንገት ከተፍ ብትይ በጨቀየ ደጄ፣
ምን ይሰማሽ ይሆን እብደቴን እያየሽ፣
ምን ይሰማኝ ይሆን ካ'ጠገቤ ቆመሽ፣
መቸም ታዉቂዋለሽ አይጠፋሽም ፍቅሬ፣
የኔ ጥልቅ ሱሴ አንች ነሽ ችግሬ።
ከማንም ከምንም የበለጥሽ ሱሴ፣
ፍቅሬ አንች ብቻ ነሽ የህይወት ፋኖሴ።
እናም ስትሄጅ ሞቼ ስትመጭ እድናለው፣
ትንሳኤና ሞቴ መምጣት መሄድሽ ነዉ።
እየሄድሽ ገለሽኝ ስትመጭ እድናለው፣
ትንሳኤና ሞቴ መምጣት መሄድሽ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ዜማሽ መፅናኛየ መሄድሽ ችግሬ።
ዉቧ ጨረቃየ የምሽት ድባቤ፣
የህይወት ስኬቴ ምግባረ ሐሳቤ፣
መሆንሽን እያወቅሽ የልቤ ከተማ፣
የከናፍሬ ጣዓም ያ'ንደበቴ ዜማ፣
ለምን ረሳሽኝ በጥልቅ ባህር ቆሜ?
ፍቅርሽን እያለምኩ በፍቅር ዓለሜ።
ዜማሽን ሳልሰማ እነቃ ይመስል፣
እዉላለሁ አድራለሁ አ'ንችን ሳንሰላስል።
እድሜየ ባክኖ ዘመኔ ጨቅይቶ፣
ትዝታሽ ብቻዉን ከእኔ ጋር ቆይቶ።
ቆይቶ...ቆይቶ...ቆይቶ...ቆይቶ፣
ድንገት አስነቅቶ...
''አይዞህ አትተክዝ በፍቅር ጠብቃት፣
ባ'ካል ብትለያት በመንፈስ አትራቃት፣
አንተ እንደምትወዳት እሷም ፍቅር አላት''፣
እያለ ያፅናናኛል በፅኑ ዉብ ቃላት።
እኔ የምለዉ ግን እኔ አንችን ወድጄ፣
ጨርቄን ማቄን ጥየ እርቃን ተሰድጄ፣
በፍቅርሽ በርሬ በፍቅርሽ አብጄ፣
ድንገት ከተፍ ብትይ በጨቀየ ደጄ፣
ምን ይሰማሽ ይሆን እብደቴን እያየሽ፣
ምን ይሰማኝ ይሆን ካ'ጠገቤ ቆመሽ፣
መቸም ታዉቂዋለሽ አይጠፋሽም ፍቅሬ፣
የኔ ጥልቅ ሱሴ አንች ነሽ ችግሬ።
ከማንም ከምንም የበለጥሽ ሱሴ፣
ፍቅሬ አንች ብቻ ነሽ የህይወት ፋኖሴ።
እናም ስትሄጅ ሞቼ ስትመጭ እድናለው፣
ትንሳኤና ሞቴ መምጣት መሄድሽ ነዉ።
እየሄድሽ ገለሽኝ ስትመጭ እድናለው፣
ትንሳኤና ሞቴ መምጣት መሄድሽ ነው።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
❤7🥰1